20/05/2022
እጅግ ውድ ነገር ያለ ቦታው ከዋለ ርካሽ ነው። አንተ በክርስቶስ ደም ከሰይጣን ሰፈር የተገዛህ ውድ ፍጥረት ነህ። ታዲያ እዚህ ምን ታደርጋለህ?
☞ መጠጥ በሚሸትበት ቦታ ፣
☞ ሃሽሽ በሚቦንበት ቦታ ፣
☞ ሲጋራ በሚጤስበት ቦታ ፣
☞ ጭፈራ ባለበት ርካሽ ቦታ ምን ታደርጋለህ? ምን ታደርጊያለሽ?
ምናልባት እንደዚህ ርካሽ በሆነ ስፍራ ከሆንክ ዋጋህን አላወከውም ማለት ነው። ምን ያህል ውድ እንደሆንክ፣ ምን ያህል የከበረ ዋጋ እንዳለህ አላስተዋልክም ማለት ነው።
ታዲያ ምን ትጠብቃለህ? ተነስ። ተነስና ሂድ። ያንተን ውድነት በሚያስመሰክርልህ ፣ እንደ ሰማይ ከዋክብት ወደሚያብረቀርቅህ ከፍ ወዳለ ክቡር ስፍራ ተጓዝ።
ያኔ
☞ ልብህ በደስታ ይረሰርሳል፣
☞ የልብህ ስብራት ይፈወሳል ፣
☞ የገረጣው ቆዳህም ይወዛል ፣
☞ የደረቀው ህይወትህ በፍቅሩ ውሃ ይረሰርሳል።
አንተም በውሃ ዳር ላይ እንደተተከለ ዛፍ ቅጠልህ አይረግፍም፣ እጥፍ ታፈራለህ፣ የምትሰራውም ሁሉ ይከናወናል ፣ ወደ እርሱ ለተጠጉት ሁሉ እንዲህ ይደረጋል።
“በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ቀንበርን ከአንገትህ እሰብራለሁ፥ እስራትህንም እበጥሳለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ለሌላ አትገዛም፤”
— ኤርምያስ 30፥8
ደግሞም “እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ አመልስላቸዋለሁ፥ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ።”
— ኢሳይያስ 65፥24
የታላቁ ተስፋን የተለያዩ አገልግሎቶች ለማግኘት ከታች ባሉ ሊንኮችን ነክተው ይቀላቀሉ። ላይክና ሼር ያድርጉ።
ዮቱብ
https://youtube.com/channel/UC2eRMsiKBDGz3HG3f_l_15A
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/gratehopetsa/
ዋትሳፕ
https://chat.whatsapp.com/Ifsxs0lLLur3NqUBAzHm4U
ቴሌግራም
ታላቁ ተስፋ
https://t.me/talakutalakutesfa
ቲክቶክ
tiktok.com/
ሰብስክራይብ እና ሼር ላይክ በማድረግ ደግፉን።
እናመሰግናለን
🥑🍐🍈🌰🍇🌶 ሰናይ ቀን! 🍈🍒🥜🥑🥝