ሰዋስወ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት Sewaswe Tsdk Sunday School

ሰዋስወ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት Sewaswe Tsdk Sunday School በ1979 በባሁንክ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርቲያን የተመ?

24/03/2023

የገጠሩ ውብ ባህላችን የኔታ ገብረ መድኅን በጥቂቱ እንደዘረዘሩት

አንድ ወጣት ለአቅመ አዳም ሲደርስ እናትና አባት “ልጃችን ደረሰ ምን እናድርግ” ብለው ያስባሉ፣ ይወያያሉ። “ማንን እንዳረው” ብለው መፈለግ ይጀምራሉ። ጠባዩአን፣ ትህትናዋን፣ መልካም ምግባሯን አይተው ይመርጣሉ።
ከወገን መርጠው ሽማግልና ይልካሉ። “እንግዳ ይመጣልና ከቤት ሰው አይጥፋ” የሚል መረጃ ለሴት ወገን ቤተሰቦች ይደርሳል።

👉🏽እናትና አባት የአብና የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ናቸው። የሚታጭለት የወልድ ምሳሌ ነው። የምትሆነውን ሴት መፈለግ ደግሞ “ዐየ፣ መረመረም፣ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም” እንዳለ መጽሐፍ። የምትታጨዋ የድንግል ምሳሌ ናት።

👉🏽የሚያጩት ሽማግሌዎች የቅዱስ ገብርኤል፣ “እንግዳ ይመጣልና ከቤት አትጥፉ” የሚለው መረጃ የነቢያት ትንቢት ምሳሌ ናቸው።

ሽማግሌዎች የሴት ቤት ደርሰው በውጭ ይቆማሉ። ግቡ ሲባሉ “አንገባም፣ መጀመሪያ ጉዳያችንን አድምጡን” ይላሉ። 👉🏽ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ደርሶ ያለ ሰላምታና ማብራሪያ “ትወልጃለሽ” እንዳላላት።

“ልጃችሁን ለልጃችን” ብለው ሙያውን፣ ጠባዩን ያስረዳሉ። የትውልድ ሀረጉን እንከ ሰባት ቤት ይጠይቋቸዋል፣ ሽማግሌዎቹም ይመልሳሉ። 👉🏽ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን “የአብ ልጁ፣ ከዳዊት ዙፋን የሚወለድ፣ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ የምትጸና፣ … ” እያለ እንዳስረዳት።

ወላጆች መጀመሪያ “አይሆንም” ይላሉ። 👉🏽እመቤታችን “ይህ እንዴት ይሆንልኛል፣ ወንድ አላውቅምና” ብላ እንደጠየቀች።

ከተወያዩ በኋላ የሠርግ ቀነ ቀጠሮ ይሰጣል። 👉🏽አምላካችን ከአዳም ጋር ለ5500 ዘመን የያዘው ቀነ ቀጠሮ ምሳሌ!

ሙሽራው ሚዜ ይዞ ይመጣል፤ ሙሽሪት ሚዜዎቿን ይዛ ለብቻ ወደተሠራላቸው ጫጉላ ይመጣሉ። 👉🏽እመቤታችን አምላክን የወለደችው በቤቷ ሳይሆን በውጭ በበረት የመሆኑ ምሳሌ። 👉🏽የሙሽራው ሚዜዎች የመላእክት፣ የሙሽሪት ሚዜዎች የእረኞች ምሳሌ ናቸው።

የወንድና የሴት ሚዜዎች አይተዋወቁም። ሙሽሮቻቸውን ያጅባሉ። 👉🏽መላእክትና እረኞች ያለቅድሚያ ትውውቅ በኅብረት እንደዘመሩ።

👉🏽 “ጸጋን የተመላሽ ሆይ” የተባለች የምልዕተ ጸጋ ድንግል ማርያም ምሳሌ ናትና ሙሽሪት ተሸፋፍና ዐይኗን ብቻ ያየዋል።

ሙሽሪትና ሙሽራውን በጫጉላ ባሉበት ወቅት ለማየት ሳንቲም እየከፈሉ ያዩአቸዋል። 👉🏽ሰብአ ሰገል ጌታን ለማየት ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ የማምጣታቸው ምሳሌ።

ለሙሽራው ስም ያወጡለታል። 👉🏽አምላካችን በሥጋ ተገልጦ ወደ ዓለም ሲመጣ ክርስቶስ፣ ኢየሱስ፣ አማኑኤል፣ መድኃኔ ዓለም፣ … እየተባለ እንደተጠራ!

ይህ ሁሉ የሚከናወነው በሙሽሪት መኖሪያ ነው። 👉🏽መጀመሪያ ሙሽራው መጥቶ በሙሽሪት ቤት ወደተዘጋጀው ጫጉላ መግባቱ መጀመሪያ አምላካችን ወደ ድንግል መጣ እንጂ እመቤታችን ወደ ሰማይ ያለመሄዷ ምሳሌ። መለኮት ወደ ትስብእት መጣ እንጂ ትስብእት ወደ መለኮት ያለመሄዱ ምሳሌ።

ሙሽራው ሙሽሪትን ይዞ ሲሄድ እናቶች ጥላ ይዘው “እንዳላይሽ ደመናው ዞሯል በላይሽ” እያሉ ይዘምራሉ። 👉🏽በደመና መንፈስ ቅዱስ የተዋጀች፣ በፍጹም ምሥጢር የተመሠጠረች እመቤታችን በዚህ ዓለም በሴቶች ጠባይ አለመኖሯን የመግለጥ ምሳሌ።

የሙሽራ አሳዳሪ የሚባለው ለሙሽራው የተዘጋጀውን የበግ ሽልማት ይዞ ጥሩንባውን እየነፋ ከሙሽራው ፊት ፊት ይሄዳል። 👉🏽የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ምሳሌ።

ቤት ሲደርሱ፣ ይዞ የመጣውን በግ ራሱ ሙሽራው አርዶ አወራርዶ ለሚዜዎቹ ያበላል። 👉🏽ራሱ መሥዋዕት፣ ራሱ ካህን፣ ራሱ ተቀባይ የሆነ የአምላካችን ምሳሌ።

አቤት! ውብ! እጹብ!

በምሕረት አቤሴሎም የተዘጋጀ

በእግዚአብሔር ፈቃድ በመልአኩ ርዳታ ቤተክርስቲያናችን "ደብረ ዘይት" በዓልን በሌሊቱና በጥዋቱ መርሐ ግብር በማኅሌት በቅዳሴ እንዲሁም በመጽሐፍ መምህር በሆኑት ቀሲስ ሳሙኤል የኔው "እንዳያስ...
19/03/2023

በእግዚአብሔር ፈቃድ በመልአኩ ርዳታ ቤተክርስቲያናችን "ደብረ ዘይት" በዓልን በሌሊቱና በጥዋቱ መርሐ ግብር በማኅሌት በቅዳሴ እንዲሁም በመጽሐፍ መምህር በሆኑት ቀሲስ ሳሙኤል የኔው "እንዳያስቷችሁ ተጠንቀቁ" (ማቴ 24፥4) በሚል ርዕስ በሰፊውና በጥልቀት የአውደ ምሕረት ትምህርት ተሰጦን፤ እንዲህ አክብረናል።

04/11/2021

🍇ስለውዳሴ ከንቱ ... ከአበው ሕይወት መዝገብ ፩

ሰዎች ርኩስ መንፈስ ያደረበትን ሰው ወደ አንድ ገዳም ይዘው መጡና ያድንላቸው ዘንድ
ለገዳሙ አበምኔት(አለቃ) ሰጡት። የገዳሙ አበምኔትም በተሰጠው ፀጋ ተጠቅሞ በስመ
እግዚአብሔር ሰይጣኑን ውጣ ሲለው ሰይጣኑም «መውጣቱንስ እወጣለሁ ግን አንድ ጥያቄ
ነበረኝ»ይላል።
የገዳሙ አበምኔትም «ምንድነው ጥያቄህ?» ይለዋል። ሰይጣኑም
#በወንጌል ላይ ፍየሎች
በግራ በጎች በቀኝ ይቆማሉ የሚል ቃል አለ፣ ለመሆኑ በፍየልና በበግ የተመሰሉት እነማን
ናቸው? ይኽንን በምሳሌ አድርገህ ንገረኝ አለው። የሰይጣኑ አመጣጥ የገባው ያ ደግ
አባትም እንዲህ መለሰ።

«በፍየል የተመሰሉት ኃጥአን፣ በበግ የተመሰሉት ደግሞ ፃድቃን
ናቸው። በምሳሌ ንገረኝ ላልከው፣ በፍየል ከተመሰሉት ኃጥአን መካከል ለምሳሌ አንዱ እኔ ነኝ። በበግ የተመሠሉ ፃድቃንን ግን አላውቅም። አሁን ግን ውጣ» አለው።
ተንኮሉ የተነቃበትና ያጠመደው ውዳሴ ከንቱ መረብ ያልያዘለት ሰይጣንም በኃይል ጮኾ ከሰውየው
ወጣ። በሽተኛውም ዳነ።

ትንታኔውን ለእናንተው።

++ከመምህራን የተወሰደ++

"ጸልዩ ለአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ወሀገሪትነ ቅድስት ኢትዮጵያ"

መልካሙ ዘሰዋስወ ጽድቅ
25/02/2014 ዓ.ም

Address

Injibara
Injibara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰዋስወ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት Sewaswe Tsdk Sunday School posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category