05/07/2016
ከክብር ወደ ክብር የሆነ ሰላምታ በኢየሱስ ስም ይሁንላችሁ
በሰኔ ወር 2016 በተለያዩ ግንኙነቶች በልዕለ ተፈጥሮአዊው ለመስራት እያንዳንዳችሁ ኃይልን እንደታጠቃችሁ አምናለሁ፡፡ ይህ አይነቱ ልምምድ በፊታችን ባሉት አመታቶች ማስረጃዎችን በማምጣት በኢየሱስ ስም ይቀጥል፡፡ አሜን፡፡
ነገር ግን ጌታ ለሐምሌ ወር 2008 ምን እያለ ነው ያለው ?
በመጀመሪያ ይህ ወር የአመቱ መካከል የማጠቃለያ ወር ነው፡፡ ይህም በእግዚአብሔር አጀንዳ የፀሎት መነቃቃት ወር ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ጥሬ የሆነው ኃይል የሚገለጥበት ወቅት ነው፡፡ ከዛም የተነሳ የዘላለም ተራሮች በሙሉ የሚንቀጠቀጡበት እና የዘላለም ኮረብቶች የሚቀልጡበት ጊዜ ነው፡፡
ይህም በተጨባጭ የሚያካትተው ለረጅም ጊዜ የቆዩ በሽታዎችና ህመሞች በሙሉ፣ ከዘር ተወራርሶ የመጡ በሽታዎች እንዲሁም ብዙ የቆዩ የክፉ ጭቆናዎች ናቸው፡፡
በተጨማሪም የአመቱ መካከል ከልባችን በሒደት ላይ ባለው መነቃቃት ተሳታፊዎች ስንሆን ለእኛው የደረጃችን ለውጥ የተወሰነ ጊዜ ነው – ዕምባ. 3:1-2/4-6/17-19
ከዚህም ባሻገር ከእያንዳንዱ በሽታ እና ህመም ጀርባ የድካም መንፈስ የሚባል እንዳለ እና ይህም በግልጥ ሲተረጎም የበሽታ መንፈስ ተብሏል፡፡ – ሉቃ. 13:11-13/ ሐዋ 19:11-12
እንዲሁም ኢየሱስ ለዲያቢሎስ የተገዙትን እየፈወሰ እንደዞረ እንመለከታለን፡፡ – ሐዋ 10:38
ስለዚህ በግልጥ ከእያንዳንዱ የበሽታ እና የህመም ጭቆና ጀርባ ያለው የዲያቢሎስ የክፋት ስራ ነው፡፡ ; “....ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ ጫማ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መታው።.” – ኢዮብ 2:7
የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው; “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” – ኤፌ. 6:12
የዲያቢሎስ ጠንካራ ምሽግ ስለዚህ ጨለማ ነው ኢየሱስ ሲናገር ; “…ይህ ግን ጊዜያችሁና የጨለማው ሥልጣን ነው አላቸው።” – ሉቃ. 22:53
ሰይጣን የሚገዛው በጨለማ ውስጥ ነው የክፋት ስራውንም የሚያከናውነው በጨለማ ነው፡፡ – ኤፌ. 6:12-13/ መዝ. 22:20
ነገር ግን እግዚአብሔር ይመስገን የእግዚአብሔር ቃል በጨለማ ላይ የሚበራ እና ጨለማም የማያሸንፈው ብርሀን ነው፡፡ – ዮሐ. 1:5/ ኢሳ . 58:8/ ኢዮብ 33:21-25
ሆኖም ግን የእግዚአብሔርን ቃል መረዳት ያም ማለት የቃሉ መገለጥ ያነው ለውጥን፣ ፈውስን እና አርነትን የሚያመጣው፡፡ – መዝ. 119:130/144
ለዚህም የእግዚአብሔር ቃል ሁሉንም አይነት በሽታ እና ህመም የሚፈውስ በገለአድ ያለው የሚቀባ መድሐኒት ነው፡፡ – መዝ. 107:20 (ማቴ. 8:8/13/ ሉቃ. 5:17/ ሉቃ. 6:17-19)
ስለዚህ በዚህ ወር ታላቁን ሐኪም ኢየሱስ ክርስቶስን ስናገኘው፣ በሚገባ ስንረዳውና ያዘዘልንን መድሐኒት(ቃሉን) ስንጠቀም በእርግጥም የሙሉ ጤንነት ፓኬጆች ሙሉ በሙሉ እንደምንቀበል እርግጠኞች ነን፡፡ – ማቴ. 9:12-13/ ኢዮብ 33:21-25/ ምሳ. 4:20-22
ስለሆነም የሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም ትንቢታዊ ትኩረት የሚሆነው
እኔ ጤናህን እመልሳለሁ - ኤር 30፡17
I WILL RESTORE HEALTH UNTO YOU – Jer. 30:17
ከእያንዳንዱ በሽታ እና ህመም እያንዳንዱ ዊነር ለዘላለም የሆነ እውነተኛ እና ሙሉ የሆነ አርነት በዚህ ወር ይለማመዳል፡፡ ይህ ወር በእርግጥ ለእያንዳንዱ ዊነር ሙሉ ጤና የሚመለስበት ወር በኢየሱስ ስም ይሆናል፡፡
በዚህ ወር እንድናነባቸው ከሚመከሩ መጻህፍቶች መካከል
በቢሾፕ ዴቪድ ኦ. ኦዬዴፖ የተፃፉ
*Keys to Divine Health የመለኮታዊ ጤንነት ቁልፎች
*The Healing Balm የፈውስ ቅባት
*The Miracle Meal ተአምራታዊው መብል
*Fulfilling Your Days ቀኖቻችሁን መፈፀም
በፓስተር ፌዝ ኦዬዴፖ የተፃፉ
*Rescued From Destruction ከጥፋት መዳን
*Healing, Health and Wholeness ፈውስ፣ ጤና እና ሙሉነት
*The Power of the Communion የቅዱስ ቁርባን ኃይል
*The Healing Ministry of Jesus Christ የኢየሱስ ክርስቶስ የፈውስ አገልግት
ሁላችሁንም በጌታችን በመድሐኒታችን እና በፈዋሻችን ስም ወደ ሙሉ ጤንነት አለም እንኳን ደህና መጣችሁ እላችኃለሁ፡፡ አሜን እና አሜን
ሁሌ ተባረኩ
ኢየሱስ ጌታ ነው
ዴቪድ ኦ. ኦዬዴፖ
From Glory to Glory greetings in Jesus’ name.
I believe every one of us must have been empowered to operate in the supernatural through the diverse encounters in the month of June 2016. May this experience continue to engender proofs all through the years ahead of us in Jesus’ name, amen.
But what is the Lord saying for the month of July 2016?
First, this is the closing month of the midst of the year, which is ordained a revival prayer month in God’s agenda, a season of raw demonstration of the power of God, where all everlasting mountains shall be scattered and perpetual hills levelled out.
This, evidently, includes all sicknesses and diseases of long continuance, all hereditary diseases and all long-term oppressions of the wicked.
In addition, the midst of the year is ordained for our change of levels as we engage with our hearts in this ongoing revival – Hab. 3:1-2/4-6/17-19
Furthermore, we discover from scriptures that behind every sickness and disease is the spirit of infirmity, which literarily translates to spirit of sickness – Lk. 13:11-13/ Acts 19:11-12
We also saw that Jesus was going about healing all those oppressed of the devil – Acts 10:38
Obviously therefore, behind every affliction of sickness and disease is the wickedness of the devil at work; “....So went Satan forth from the presence of the LORD, and smote Job with sore boils from the sole of his foot unto his crown.” – Job 2:7
According to scriptures; “For we wrestle not against flesh and blood, but against principalities, against powers, against the rulers of the darkness of this world, against spiritual wickedness in high places.” – Eph. 6:12
Therefore, the devil’s stronghold is darkness. Jesus said; “…but this is your hour, and the power of darkness.” – Lk. 22:53
Satan rules in darkness and he carries out his wicked acts in darkness – Eph. 6:12-13/ Ps. 22:20
But thank God, the word of God is the light that shines in darkness and darkness cannot resist it – Jn. 1:5/ Is. 58:8/ Job 33:21-25
However, it is the understanding of the word, that is, revelation of the word that transforms, heals and delivers – Ps. 119:130/144
This is why God’s word is the ‘Balm in Gilead’ for the cure of all manner of sicknesses and diseases – Ps. 107:20 (Matt. 8:8/13/ Lk. 5:17/ Lk. 6:17-19)
Therefore, as we meet Jesus Christ, the Great Physician, this month, understand and apply His prescriptions – the Word, we are sure to take full delivery of our total health package – Matt. 9:12-13/ Job 33:21-25/ Pro. 4:20-22
Therefore, the prophetic focus for the July 2016 is:
I WILL RESTORE HEALTH UNTO YOU – Jer. 30:17
This month every Winner shall experience true and total liberty from every harassment of sickness and disease forever. It shall be a month of total restoration of health indeed for every Winner in the name of Jesus.
Recommended books of the month include:
*Keys to Divine Health Authored By *Rescued From Destruction Authored by
*The Healing Balm David O. Oyedepo *Healing, Health and Wholeness Pst. Faith A. Oyedepo
*The Miracle Meal *The Power of the Communion
*Fulfilling Your Days *The Healing Ministry of Jesus Christ
I welcome you all to a world of total health in the name of our Lord, Saviour and Healer; Jesus Christ, amen and amen.
Remain ever blessed!
Jesus is Lord!
David O. Oyedepo