Quo Vadis? Catholic Youth Hossana

Quo Vadis? Catholic Youth Hossana Creating powerful, strong and influential youth.

19/03/2026

የካቶሊክ አስተምህሮ

"....የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ በውብ አንፂ ተጠርቦ የተገነባ የድንጋይ ክምር ቤት ሳይሆን በአምሳያው የፈጠረው ክቡር የሰው ልጅ ነው። የሰው ልጅን በትህትና እና ፍቅር ስታገለግሉ አምላካችሁን አገለገላችሁ ማለት ነው!..."

በምስሉ የምትመለከቱት ሳንፍራንሲስኮ የሚገኝ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዘወትር ምሽት "በጎዳና ለሚኖሩ" ወገኖች ገብተው እንዲተኙ ተፈቅዶላቸው ጎናቸውን አሳርፈው ነው።

Via: Tekione Tsega

01/03/2026

ፖፕ ሊዮ ወደ አፍሪካ

| የአለም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛው እ.ኤ.አ. ከኤፕሪል 13 እስከ 23 ቀን 2026 ባሉት ቀናት በአራት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እንደሚያደርጉ ቫቲካን ዛሬ አስታውቃለች።

ይህ ጉብኝት ቅዱስነታቸው በ2026 የሚያደርጉት የመጀመሪያው ትልቅ የባሕር ማዶ ጉዞ ሲሆን፣ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ወደምትገኝበት አህጉር የሚያደርጉት መሆኑ ልዩ ትርጉም ተሰጥቶታል።

ጳጳሱ በዚህ ጉዟቸው አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ካሜሩንን ይጎበኛሉ።

በቆይታቸውም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ እንደሚታደም የሚጠበቅ ሲሆን፣ የዓለም መሪዎች ለአፍሪካ ልማት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮችን ውይይት የሚያጠናክሩ መልዕክቶችን እንደሚያስተላልፉ ተመልክቷል።

እ.ኤ.አ. በግንቦት ወር የሟቹን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን በመተካት የተመረጡት ሊዮ 14ኛው፣ እስካሁን ያደረጉት ብቸኛ የውጭ ሀገር ጉብኝት ባለፈው ኅዳር እና ታኅሣሥ ወራት ወደ ቱርክ እና ሊባኖስ የተደረገውን ብቻ ነው።

የቫቲካን ባለሥልጣናት እና የአፍሪካ ቤተክርስቲያን መሪዎች እንደሚሉት፣ ይህ ጉብኝት ቤተክርስቲያኒቱ ለአፍሪካ አህጉር የሰጠችውን ከፍተኛ ቅድሚያ የሚያሳይ ነው።

በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ካሉ የካቶሊክ እምነት ተከታዮች መካከል 20 በመቶ ያህሉ በአፍሪካ እንደሚኖሩ የቫቲካን ስታቲስቲክስ ያሳያል።

አልጄሪያ ከአሁን ቀደም የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ጉብኝት አስተናግዳ የማታውቅ ሲሆን፣ ሊዮ 14ኛው ሀገሪቱን የሚጎበኙ የመጀመሪያው ጳጳስ ይሆናሉ።

ጳጳሱ የኦገስቲኒያን የሃይማኖት ሥርዓት አባል በመሆናቸው፣ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የኖሩት የታዋቂው ቅዱስ አውግስጢኖስ የትውልድ ስፍራ የሆነችውን አልጄሪያን ለመጎብኘት ልዩ ፍላጎት አላቸው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከአፍሪካ ጉዟቸው በፊት መጋቢት 28 ቀን ወደ ሞናኮ የአንድ ቀን ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን፣ ከሰኔ 6 እስከ 12 ቀን ደግሞ ስፔንን ይጎበኛሉ።

በስፔን ቆይታቸው ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመግባት እንደ ዋና መሸጋገሪያ የሚጠቀሙባቸውን የካናሪ ደሴቶችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለመጨረሻ ጊዜ የአፍሪካ ጉብኝት የተደረገው በ2023 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን እና ደቡብ ሱዳንን በጎበኙበት ወቅት ነበር።

አንጎላ እና ካሜሩን በ2009 በጳጳስ ቤኔዲክት 16ኛው፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ ደግሞ እ.ኤ.አ. በ1982 በዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ተጎብኝተዋል።

#ጌጡ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ዛሬ ሚያዚያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ዛሬ ሚያዚያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በ88 ...
22/04/2025

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ዛሬ ሚያዚያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ዛሬ ሚያዚያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም. በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

15/11/2024
✝️አባ ዳንኤል ጌታቸው እንኳን ለ24ኛ ዓመት የክህነት በዓል አደረሶ✝️✝️ወደ እውነት እና ወደ ጽድቅ የሚያደርስ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሁላችን ጋር ይሁን ብለው የጀመሩት ስብከቶ ላይ ከአን...
16/07/2024

✝️አባ ዳንኤል ጌታቸው እንኳን ለ24ኛ ዓመት የክህነት በዓል አደረሶ✝️

✝️ወደ እውነት እና ወደ ጽድቅ የሚያደርስ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሁላችን ጋር ይሁን ብለው የጀመሩት ስብከቶ ላይ ከአንደበቶ የሚወጣው የመንፈስ ቅዱስ ቃላት ከጆሮ አልፎ አጥንት ድረስ የሚሰማን እጅግ በጣም ልዩ የነፍስ ጣፋጭ ምግብ ነው።

✝️ በእድሜያችን ዘመን ካቶሊካዊ ማንነተችንን እንድንገነባ አስተዋጾ የላቀ ነው። ከቋንቋ፣ ከዘር፣ከገንዘብ፣ እና ከሃሰተኛ ማንነት በላይ ካቶሊካዊነት እና እውነት ላይ ጸንቶ የሚቆም ወጣት ለመገንባት ቤተክርስቲያን በምታደርገው ተጋድሎ አስተዋጾ አድርገዋል።

✝️ኢትዮጺያዊ በራሱ አቅም ቤተክርስቲያንን ብሎም ሃገርን መገንባት እንደሚችል ከእቅድ አስከ ተግባር አሳይተውናል።

😭የሀዘን  መግለጫ 😭ለብዙሃኑ ሰዳማ አከባቢ ነዋሪዎች በክርስትናው ትልቅ አስተዋዕፆ ያደረጉ አባታችን ዲያቁን ወ/የሱስ መኔዴ(አባባ) ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በተለያዩ የሕክምና ማዕከላት ሲ...
06/07/2024

😭የሀዘን መግለጫ 😭
ለብዙሃኑ ሰዳማ አከባቢ ነዋሪዎች በክርስትናው ትልቅ አስተዋዕፆ ያደረጉ አባታችን ዲያቁን ወ/የሱስ መኔዴ(አባባ) ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በተለያዩ የሕክምና ማዕከላት ሲታከሙ ቆይተው በ29/10/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የቀብር ስነስርዓታቸው በ01/11/2016 ዓ/ም በቅ/ሐና ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሰዳማ መካና መቃብር ይፈጸማል ።

ለገራድ ኪዳኔ ወ/የሱስ ፦
ለቤተሰቦቻቸው ፦
ለቅ/ሐና ቤተክርስቲያን ምዕመናን ፦
ለኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን ፦
ለሆሣዕና ሀገረ ስብከት ምዕመናን ፦ እግ/ር መጽናናቱን ይስጣችሁ !

ንግደት ፦  የሚያስፈልገንን መንፈሳዊ ፀጋ ምድራዊ በረከት ፈጠራ እንድያድለን በመሉ እምነት ከቤታችን መነሳት እና ፈጠራ ስላደረገልን መልካም ነገር ሁሉ በምስጋና መሞላት ነው   "(abba S...
27/06/2024

ንግደት ፦ የሚያስፈልገንን መንፈሳዊ ፀጋ ምድራዊ በረከት ፈጠራ እንድያድለን በመሉ እምነት ከቤታችን መነሳት እና ፈጠራ ስላደረገልን መልካም ነገር ሁሉ በምስጋና መሞላት ነው "(abba Samuel donbosco)
እንኳን አደረሰን
ፍፁም የሆነው አምላካችን በብዙ በረከት እንዲሞላን ሐምሌ (6_7) በቤቱ እንገኝ

✝️🙏እውነት ነፃ ታወጣለች🙏✝️
24/06/2024

✝️🙏እውነት ነፃ ታወጣለች🙏✝️

 ✝️የዘንድሮ ይለያል አይቀርም ! በየዓመቱ ሐምሌ 6&7 በድምቀት የሚከበረው የቅድስት ሥላሴ በዓል ዘንድሮ በተለየ መልኩ ለማክበር ዝግጅቶች ተጀምረዋል። ✝️በዘንድሮው ሥላሴ ከኢትዮጵያ ከሁሉ...
17/06/2024


✝️የዘንድሮ ይለያል አይቀርም ! በየዓመቱ ሐምሌ 6&7 በድምቀት የሚከበረው የቅድስት ሥላሴ በዓል ዘንድሮ በተለየ መልኩ ለማክበር ዝግጅቶች ተጀምረዋል።

✝️በዘንድሮው ሥላሴ ከኢትዮጵያ ከሁሉም አቅጣጫ በርካታ እንግዶችን እንደሚመጡ ይጠበቃል።

✝️በቀጣይ ውድ ካቶሊካዊያንን የሚያሳትፍና በዋዜማው ቀን የሚያሸልሙ ጥያቄዎችን ወደ እናንተው ይዘን የምንመጣ ይሆናል🙏

Address

Hossana

Telephone

+251955440505

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Quo Vadis? Catholic Youth Hossana posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Quo Vadis? Catholic Youth Hossana:

Share