Full Gospel Believers' Church, Hawassa

Full Gospel Believers' Church, Hawassa Welcome to the official page of Hawassa Full Gospel Believers' Church. Talk to the Church, put your prayer requests and be part of it.

የንጹህ አምልኮ ጣምራ ገጾች - ረድኤት እና ቅዱስ ሕይወትመጋቢ አዳነ አየለበሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነሃሴ 17/2018 ዓ.ም እሁድ ጥዋት የተካሄደው የጉባኤ አምልኮ ፕሮግራም...
23/08/2026

የንጹህ አምልኮ ጣምራ ገጾች - ረድኤት እና ቅዱስ ሕይወት
መጋቢ አዳነ አየለ

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነሃሴ 17/2018 ዓ.ም እሁድ ጥዋት የተካሄደው የጉባኤ አምልኮ ፕሮግራም

በዕለቱ በነበረው የቃል አገልግሎት መጋቢ አዳነ አየለ ያዕ. 1፡27ን መሰረት በማድረግ የቀረበ “በረድኤት ዝሩ በጸጋው መንዝሩ” የሚለው መልዕክት ቀጣይ ክፍል ሲሆን “የንጹህ አምልኮ ጣምራ ገጾች - ረድኤት እና ቅዱስ ሕይወት” በሚል ርዕስ ቀጥለው በቀረቡት ነጥቦች ላይ የእግዚአብሔርን ቃል አስተምረዋል።

የመግቢያ ሀሳብ፡-

ይህ ​ትምህርታዊ ስብከት ዓላማ ያደረገው በሁለት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ሲሆን ቀዳሚው በቤተ ክርስቲያን የረድኤት አገልግሎት ሥር ለታቀፉ ወላጅ/አሳዳጊ ላጡ ሕጻናት፣ መሠረታዊ ወጪዎቻቸውን መሸፈን ላቃታቸው አቅመ ደካሞች እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችን ከቃል ያለፈና በተግባር የተደገፈ የበረከት ስጦታዎችን ለማሰባሰብ ይቻል ዘንድ ቅዱሳንን ለማበረታታት ነው። ከዚህም ባሻገር በረድኤት የምንዘራው ዘር እውነተኛ የአምልኮአችን ክፍል እንደመሆኑ መጠን ራስን ከዓለም እድፍ በመጠበቅ ነውር አልባ ንጹህ ሕይወትን የምንገልጥበት እንዲሆን ዘንድ ለማሳሰብ ነው፡፡ ይህ የረድኤት አገልግሎት በእግዚአብሔር በራሱ መስፈርት የሚለካ፣ በንጽህና በፊቱ የሚቀርብ እና ሆን ተብሎ የሚደረግ ቀጣይነት ያለው የርኅራኄ ምግባር ነው።

ዋናው የመልዕክቱ ሀሳብ

ያዕቆብ ከኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን አዕማድ ከሆኑት መካከል ግንባር ቀደሙ አባት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ የድሆችን መከራና ስቃይ ከቃል ባለፈ በተግባር የሚያውቅ፣ ጠባቂ የሌላቸውንና የማኅበራዊ ቀውስ ተጋላጭ የሆኑ ወገኖችን ሁኔታ በቅጡ የሚረዳ ሰው ነው፡፡ በመልዕክቱም ስለ እውነተኛ አምልኮ ሞጋች ሃሳብ ያነሳ ሲሆን ለወላጅ አጥ እና ለመበለቶች አባት እና ዳኛ በሆነው በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ተቀባይነት ያለውን የፍቅር መንገድ ያመለክታል፡፡ በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ታላቅ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ስለሚሰጡት እርዳታ እነ ጳውሎስን ከማሳሰብ (ገላ. 2፡10)፣ ይህንን የረድኤት ተግባር በመላው ዓለም ላቀጣጠለው ለጳውሎስ (2ኛ ቆሮ. 8-9) አነሳሽ ከመሆን አልፎ በዚህ መልዕክቱ የእውነተኛና ነውር አልባ አምልኮ መገለጫ አድርጎ አቅርቧል፡፡ ያዕቆብ የረድኤት አገልግሎትን ችግረኞችን በችግራቸው ደርሶ ከመጠየቅ ባለፈ ከአለም እድፈት ራስን በማንጻት መመላለስ በእግዚአብሔር አብ ፊት የአምልኮ ውስጣዊ እና መንፈሳዊ መገለጫ አድርጎ ያቀርብልናል፡፡

በመሆኑም ዛሬ ለእኛ ለአማኞች፣ እውነተኛ አምልኮ ከመሰብሰቢያ አዳራሻችን ባሻገር በውጪ ወዳሉት ችግርተኞች በመዘርጋት መቆረስ መሆኑን ያስተምረናል፡፡ ለዚህም ይረዳን ዘንድ አስበንበት ወገኖቻችንን መጠየቅ፣ በሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ መርዳት፣ ከጊዜያችን፣ ከሃብትና ንብረታችን በደስታ ቆርሰን የተሰበረ ልባቸውን መጠገን ይገባናል፡፡ ከዚህም ባሻገር ወደ ውስጣችንም የምንመለከትና የግል ሕይወታችንን ንጽሕና በመጠበቅ አምልኮአችን በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ዘንድ መትጋት አለብን፡፡ የእውነተኛ አምላኪ ሕይወት በለጋስ እጅ ብቻ ሳይሆን በንጹሕ ልብም የሚታወቅ መሆኑን ተረድተን መመላለስ ያስፈልገናል፡፡ በመጨረሻም፡- የቃላችንና የተግባራችን አንድነት የእውነተኛ አምልኮ ወሳኝ ማረጋገጫ መሆኑን ተረድተን ሁልጊዜ ባልተሸራረፈ ማለትም ቃል-በተግባር በሆነ ሕይወት ልንመላለስ ይገባናል፡፡

የትምህርቱ የማጠቃለያ ሀሳብ

እንግዲህ የልብ ለውጥ የሌለው የአንደበት ጣፋጭ ቃል ብቻውን ምንም ረብ እንደሌለው ሁሉ ለረድኤት አገልግሎት በንጹህ እጅና ልብ መዘርጋትን የሚያክልም እውነተኛ አምልኮም እንደሌለ ልናውቅ ይገባናል፡፡ በመሆኑም፣ እንደ ቤተ ክርስቲያን አዕማድ አባቶች በትጋት ስለ ድሆች መከራና ስቃይ ልንሰራ፣ ልንቆረስ፣ እንደነ ጳውሎስ፣ “ድሆችን እናስብ ዘንድ ብቻ ለመኑን፣ ይህንም ደግሞ ላደርግ ተጋሁ” እንዳለው ልንተጋ (ገላ 2፡10)፣ በቤተ ክርስቲያን መበለቶችንና ወላጅ አጥ ሕጻናትን ለመርዳትና በፍቅር ለመንከባከብ ተግባራዊ ስራን ልንሰራ (1ኛ ጢሞ. 5፡3-16)፣ በሥራና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ከመዋደድ እልፍ እንድንል (1ኛ ዮሐ. 3፡17-18) እግዚአብሔር አምላካችንና አባታችን ይርዳን፡፡ እርሱ እግዚአብሔር “ለደሃ አደጎች አባት ለባልቴቶች ዳኛ” (መዝ. 68፡5) መሆኑን አውቀን እኛም የአባታችንን ዳና ተከትለን የምንነጉድና ባለን አቅም ሁሉ ከረድኤት አገልግሎት ጎን እንድንቆም እንደ ቤተ ክርስቲያን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ በረድኤት ዝሩ፣ በጸጋው መንዝሩ!!! ረድኤት እና ቅዱስ ሕይወት ይብዛልን፡፡ ጌታ ይባርካችሁ፡፡

Follow Us
◽️ YouTube
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
◽️Facebook
https://fb.me/FGBCHawassa
◽️Instagram
https://ig.me/FGBCHawassa
◽️Telegram
https://t.me/FGBCHawassa

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚዲያ አገልግሎት
ነሃሴ 17 /2018 ዓ.ም

የስብሰባ ጥሪየሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን  ቅዳሜ፣ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ  የአባላት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የሚካሄድ በመሆኑ፣  ሁሉም  አባላ...
21/08/2026

የስብሰባ ጥሪ

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሜ፣ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የአባላት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የሚካሄድ በመሆኑ፣ ሁሉም አባላት በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በአምልኮ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪ ታስተላልፋለች።

አመታዊ የስነጽሁፍ ምሽት"ቅድስና ለእግዚአብሔር" በሚል ርዕስ የተዘጋጀነሃሴ24፣ እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮበሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን  በዕለቱ ከሚቀርቡት ፕሮግራሞች ...
21/08/2026

አመታዊ የስነጽሁፍ ምሽት

"ቅድስና ለእግዚአብሔር" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ

ነሃሴ24፣ እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን

በዕለቱ ከሚቀርቡት ፕሮግራሞች መካከል

የዝማሬ አምልኮ
- በሚንጃ ሻመና ሀዋሳ ታቦር መካነየሱስ

መንፈሳዊ ድራማ
-በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል ይዲድያ ድራማና ስነፅሁፍ ህብረት

ስነ ግጥም፣ ትረካ፣ እና ሌሎች አጫጭር የስነ ጽሑፍ ሥራዎች

ለውድድር ከቀረቡ ጽሑፎች መካከል አሸናፊዎቹ ይፋ ይደረጋሉ፣ ጸሐፊዎቹ ይሸለማሉ፣ ጽሑፋቸውንም ለታዳምያን ያነባሉ።

እንዳያመልጥዎ !ሌሎችንም በመጋበዝ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ !

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል የሚዲያ አገልግሎት ዘርፍ የተዘጋጀ

Follow Us
◽️ YouTube
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
◽️Facebook
https://fb.me/FGBCHawassa
◽️Instagram
https://ig.me/FGBCHawassa
◽️Telegram
https://t.me/FGBCHawassa

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚዲያ አገልግሎት
ነሃሴ 15 /2018 ዓ.ም

በረድኤት ዝሩ በጸጋው መንዝሩ! መጋቢ አዳነ አየለበሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነሃሴ 10/2018 ዓ.ም እሁድ ጥዋት የተካሄደው የጉባኤ አምልኮ ፕሮግራም በዕለቱ በነበረው የቃል ...
16/08/2026

በረድኤት ዝሩ በጸጋው መንዝሩ!
መጋቢ አዳነ አየለ

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነሃሴ 10/2018 ዓ.ም እሁድ ጥዋት የተካሄደው የጉባኤ አምልኮ ፕሮግራም

በዕለቱ በነበረው የቃል አገልግሎት መጋቢ አዳነ አየለ 2ኛ ቆሮንቶስ 9፡1-15(2 ቆሮንቶስ 9:9፤ መዝሙር 112:9፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 8፡1-24 እና ያዕ. 1፡27) መሰረት በማድረግ “በረድኤት ዝሩ በጸጋው መንዝሩ!" በሚል ርዕስ ቀጥለው በቀረቡት ነጥቦች ላይ የእግዚአብሔርን ቃል አስተምረዋል።

የመግቢያ ሀሳብ፡-

ይህ ​ትምህርታዊ ስብከት ዓላማ ያደረገው የቤተ ክርስቲያን የረድኤት አገልግሎት ማለትም ለከፋ (የገረረ) ድህነት ለተጋለጡ፣ መሠረታዊ ወጪዎቻቸውን መሸፈን ላቃታቸው አቅመ ደካሞች እና ወላጅ አልባ ህፃናት ድጋፍ ለማሰባሰብ ግንዛቤ መፍጠሪያና ምዕመናንን ለዚህ የቸርነት ተግባር እንዲዘረጉ ለመቀስቀስ ነው።

ይህ የረድኤት አገልግሎት በእግዚአብሔር ቃል ላይ መሠረት ያደረገ፣ በቀድሞዋ የሐዋሪያት ዘመን ቤተ ክርስቲያን የተለመደ የአምልኮዋ አንዱ መልክ እና የእግዚአብሔር መመስገኛና መክበሪያ የበረከት ተግባሯ ነው።

ዋናው የመልዕክቱ ሀሳብ

የረድኤት አገልግሎት በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረተ ነው(2ኛ ቆሮ 9:1-15)። በቀድሞዋ ቤተክርስቲያን ይህ አገልግሎት ቋሚ አገልግሎት ነበር። ይህ ቤት አንዱ በጣም በልቶ የሚደሰትበት፤ ሌላው የሚበላውን አጥቶ የሚቸገርበት ቤት ሳይሆን ቅዱሳን በጋራ የሚቆርሱበት ቤት ነው።

በቆሮንቶስ ያሉ አማኞች በኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ታላቅ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ስለሚሰጡት እርዳታ፣ ስጦታ ነው ይህ ክፍል የሚያወራው። ወንድሞች እርዳታ ለመሰብሰብ ሲመጡ እንዳያፍሩ ከወዲሁ እንዲዘጋጁ ጳውሎስ እየፃፈላቸው ነው።

በዚህ ክፍል የተደጋገሙ ቃላትን እንመልከት

1. አገልግሎት:- (1፣12፣13) :- መንፈሳዊ የሆነ አገልግሎት ነው። ይህ አገልግሎት እንደ በረከት ነው የታየው። በግድ፣ በማስጨነቅ የሚደረግ ሳይሆን በበረከት የሚደረግ ነው።በስስት ሳይሆን በልግስና እንድንሰጥ መፅሐፍ ቅዱስ ያዘናል።

2. ደስታ(2ኛ ቆሮ 9:7) :- እግዚአብሔር የምንሰጠውን ስጦታ በደስታ እንድንሰጥ ይፈልጋል።

3. ሁል ጊዜ፣ በነገር ሁሉ:- ይህ የእግዚአብሔርን አቅርቦት ያረጋግጥልናል። ቅዱሳን ይህን አገልግሎት እንዳያገለግሉ የሚከለክላቸው ምንም ነገር የለም። እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ብቃትን ይሰጣል። ትጋትን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው( 2:16)።

4. ልግስና:- (8:2-3) ልግስና ቅንነት ነው። ለእግዚአብሔር የምስጋና ምክንያት ነው። ከእውነቸኛ ልብ የሚደረግ ነው። የሰጠነውን የለገስነውን ሁሉ እግዚአብሔር ለመታሰቢያ ያደርገዋል። ፅድቅ ለዘላለም ይኖራል።

5. የማይነገር ታላቁ ስጦታ(2ኛ ቆሮ 9:15)
የማይነገረው ታላቁ ስጦታ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን የሰጠን ስጦታ ነው። እግዚአብሔር የማይነገር ስጦታውን ክርስቶስን እንደሰጠን ሁሉ፤ እኛም ውድ ስጦታችንን ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን ልንሰጥ ይገባል። ወደ ቤተክርስትያናችን የረድኤት አገልግሎት እንድንመጣ፤ እንድናገለግል እግዚአብሔር ይፈልጋል።

የትምህርቱ የማጠቃለያ ሀሳብ፡-

እንግዲህ ለረድኤት አገልግሎት እንደ አንድ በቃላት የማይገለጽ ውድ ስጦታ የሆነውን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ከአብ እንደተቀበለ አማኝ በልባችን እንዳሰብን (9:7)፣ እንደ መዝራት እንጂ እንደ መጉደል ባልሆነ ለጋስ፣ ቅን እና ባልተከፋፈለ ልብ፣ እንደ አምልኮአችን ቆጥረን እና በእግዚአብሔር ብቃት ሰጪነት ላይ ተደግፈን ቅዱሳን ወገኖቻችንን እንቆረስላቸው፡፡

እኛ ከእግዚአብሔር አንድያ ልጁን መቀበላችን ሁልጊዜ እየታወሰን ደስ ብሎን ለሌሎች እንቆረስላቸው፡፡ በዚህም ለእግዚአብሔር የመመስገኛ ምክንያት እና መክበሪያው እንሆናለን።

Follow Us
◽️ YouTube
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
◽️Facebook
https://fb.me/FGBCHawassa
◽️Instagram
https://ig.me/FGBCHawassa
◽️Telegram
https://t.me/FGBCHawassa

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚዲያ አገልግሎት
ነሃሴ 10 /2018 ዓ.ም

የምስጋና ኮንፍራስ ተካሄደበሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን ከነሃሴ 2-3/2018ዓ.ም ለሁለት ቀናት የቆየ የምስጋና ኮንፈረንስ ተካሄደ።ለሁለት ቀናት በቆየው የምስጋና ኮንፍራ...
11/08/2026

የምስጋና ኮንፍራስ ተካሄደ

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን ከነሃሴ 2-3/2018ዓ.ም ለሁለት ቀናት የቆየ የምስጋና ኮንፈረንስ ተካሄደ።

ለሁለት ቀናት በቆየው የምስጋና ኮንፍራንስ በዝማሬ አገልግሎት የቤተክርስትያኒቱ የአምልኮ ህብረት፣ ዘማሪ በረከት ለማ እና ዘማሪት ሰላም ደስታ ያገለገሉ ሲሆን፤ እንዲሁም በቃል አገልግሎት ነቢይ ዘነበ ማረኝ አገልግሏል።

Follow Us
◽️ YouTube
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
◽️Facebook
https://fb.me/FGBCHawassa
◽️Instagram
https://ig.me/FGBCHawassa
◽️Telegram
https://t.me/FGBCHawassa

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚዲያ አገልግሎት
ነሃሴ 5 /2018 ዓ.ም

ምን ትፈልጋለህ?በነቢይ በየነ ማረኝበሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነሃሴ 3/2018 ዓ.ም እሁድ ጥዋት የተካሄደው የጉባኤ አምልኮ ፕሮግራም በዕለቱ በነበረው የቃል አገልግሎት  ነቢ...
09/08/2026

ምን ትፈልጋለህ?
በነቢይ በየነ ማረኝ

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነሃሴ 3/2018 ዓ.ም እሁድ ጥዋት የተካሄደው የጉባኤ አምልኮ ፕሮግራም

በዕለቱ በነበረው የቃል አገልግሎት ነቢይ በየነ ማረኝ 2ኛ ነገ 2:1-22 ን መሰረት በማድረግ “ምን ትፈልጋለህ?” በሚል ርዕስ ቀጥለው በቀረቡት ነጥቦች ላይ የእግዚአብሔርን ቃል አስተምረዋል።

በሰዎች ውስጥ በርካታ ጥያቄዎች አሉ። እግዚአብሔር ወደ ሰዎች ሄዶ ምን ትፈልጋለህ? ብሎ ቢጠይቅ፣ እኛንም ቢጠይቀን ምንድነው ምላሻችን?

ኤልያስ በዘመኑ ጣዖት የሚያመልኩ ሰዎች ነበሩ። በዚያ ክፉ ዘመን እግዚአብሔርን አገልግሎ፤ ተፅዕኖ ፈጥኖ ያለፈ ታላቅ ነቢይ ነበረ። ነቢይ ኤልሳዕ ከኤልያስ እግር ስር ሆኖ ያደገ ሰው ነው። እግዚአብሔር ሲጠራው በሬዎቹን ቆራርጦ፣ ሁሉን ትቶ ኤልያስን ለመከተል የወሰነ ሰው ነው።

በኤልያስ የአገልግሎት ዘመን መጨረሻ ላይ እግዚአብሔር ወደ ራሱ ሊወስደው ፈለገ። ኤልያስ ኤልሳዕን በመተው ወደ ሰማይ ለመሄድ ጊዜው ደረሰ። በዚህ ወቅት ኤልሳዕም አልለይም ብሎት አብሮት ጉዞ ጀመረ። ኤልሳዕ አልለይህም ሲለው ኤልያስም ኤልሳዕን ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ ምን ትፈልጋለህ ብሎ ጠየቀው። ኤልሳዕም፡— መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ፡ አለ።(2:9)

በህይወታችን ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሆንልን የምንፈልገው ነገር ምንድ ነው? ምን እንዲሆንልን እንፈልጋለን? የኛ እረፍታችን እርካታችን እግዚአብሔር መሆኑን እንወቅ። የኤልሳዕ ጩኸት በውስጡ ያለው ግለት እግዚአብሔርን መፈለግ ነው። እግዚአብሔር ክብሩን እንድንፈልግ ይፈልጋል።

የእግዚአብሔርን መንፈስ በተጠማንና በፈለግን ጊዜ በህይወታችን የሚሆኑ ሦስት ነገሮች

1. በሕይወታችን ውስጥ እግዚአብሔር ከኛ ጋር እንደሆነ ይታያል(2:15)።

የነቢያት ልጆች የእግዚአብሔር መንፈስ በኤልሳዕ ላይ አርፏል ብለው መሰከሩ። የእግዚአብሔር ክብር ሁሌ አብሮን ሲሆን እግዚአብሔር ከኛ ጋር መሆኑ ይታወቃል።

2. በዘራችን፣ በቤታችን ያለው ጭንገፋ ይወገዳል። (2:19-22)።

የከተማይቱ ሰዎች ኤልሳዕን ከከተማቸው ጭንገፋ እንዲወገድ ጠየቁት። እርሱም ከዚህ በኋላ በውሃው ላይ ጭንገፋ አይሆንም ብሎ የከተማውን ውሃ ፈወሰላቸው። የእግዚአብሔር መንፈስ በኛ ላይ በኃይል ሲመጣ ጭንገፋ ከህይወታችን ይወገዳል። በሽታ፣ ህመም፣ ሌሎችም ጭንገፋዎች ከህይወታችን እንዲወገዱ የእግዚአብሔርን መንፈስ እንፈልገው።

3. የእግዚአብሔር ክብር ሲመጣ የከበደን ነገር ቀላል ይሆናል።

ለጦርነት የወጡት ነገስታት በኤዶምያስ ምድረበዳ ለሠራዊቶቻቸውና ለተከተሏቸው እንስሶች ውሃ አጥተው በተጨነቁበት ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ኤልሳዕ ደርሶላቸው ምንም ነፋስና ዝናብ በሌለበት ምድረበዳ ውሃ እንዲፈልቅ አደረገላቸው።

የቤታችን፣ የከተማችን፣ የሀገራችን ከባዱ ችግር መፍትሔ የሚያገኘው የእግዚአብሔር አብሮነት፣ የእግዚአብሔር ክብር አብሮን ሲሆን ነው። የከበደንን ነገር ቀላል የሚያደርግልን የእግዚአብሔር ቅባት ይምጣልን።

Follow Us
◽️ YouTube
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
◽️Facebook
https://fb.me/FGBCHawassa
◽️Instagram
https://ig.me/FGBCHawassa
◽️Telegram
https://t.me/FGBCHawassa

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚዲያ አገልግሎት
ነሃሴ 3 /2018 ዓ.ም

ኦ!! ትልቅ ነህ!! የአምልኮ ድግስ ተካሄደ!በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን በወጣቶች አገልግሎት ዘርፍ፣ በአምልኮ መሪዎች ህብረት እና በኤልሮኢ መዘምራን በአንድነት የተዘጋ...
08/08/2026

ኦ!! ትልቅ ነህ!! የአምልኮ ድግስ ተካሄደ!

በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን በወጣቶች አገልግሎት ዘርፍ፣ በአምልኮ መሪዎች ህብረት እና በኤልሮኢ መዘምራን በአንድነት የተዘጋጀው "ኦ!! ትልቅ ነህ!!" የአምልኮ ድግስ ሐምሌ 30/2018ዓ.ም በቤተክርስቲያኒቱ የአምልኮ አዳራሽ ተካሄደ።

በአምልኮው ድግሱ የተለያዩ ዝማሬዎች ቀርበው ምዕመናን በዝማሬዎች የእግዚአብሔርን ስም ከፍ በማድረግ፤ በታላቅ ደስታ እግዚአብሔርን አምልከዋል፤ አክብረዋል፤ ከፍ አድርገዋል።

ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን!!

Follow Us
◽️ YouTube
https://is.gd/FGBCHawassaYoutube
◽️Facebook
https://fb.me/FGBCHawassa
◽️Instagram
https://ig.me/FGBCHawassa
◽️Telegram
https://t.me/FGBCHawassa

የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የሚዲያ አገልግሎት
ነሃሴ 2/2018 ዓ.ም

05/08/2026

ነገ በ11:00
በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን

Address

Atote Wanza
Hawassa
P.O.BOX=171

Telephone

+251-462-205433

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Full Gospel Believers' Church, Hawassa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Full Gospel Believers' Church, Hawassa:

Shortcuts

Share