ASER Z Samuel

ASER Z Samuel Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ASER Z Samuel, Religious Center, Harer gahe, Hawassa.

Neway Beyene Teshome
Orthodox Tewahedo Christian | Ethiopia ✝️
Finance & Banking Professional
Siinqee Bank – Boke T'ko
By the grace of God, striving to live in faith, uphold truth, and serve the Church, community, and nation with e

17/07/2026

ሐምሌ ፯ የቅድስት ሥላሴ በዓል ነው፤የአብ ጸጋ፥የወልድ ቸርነት፥የመንፈስ ቅዱስ ፍቅር አንድነት ይደርብን ይደርባችሁ ።
ይህ ዕለት:-በመለኮት አንድ በስም፣በአካል፣በግብር ሦስት የሆኑ ቅድስት ሥላሴ በአንድነት በሦስትነት ለአብርሃምና ለሣራ የተገለጡበት፥በአብርሃም ድንኳን በእንግድነት የተስተናገዱበትና ሣራ ካረጀች ካፈጀች በኋላ ይሥሐቅን እንደምትወልድ የተናገሩበት ዕለት ነው።ዘፍ:፲፰፥፩።

ሥላሴ በሴት አንቀጽ “ቅድስት” የተባሉበት ምክንያት:-፩ኛ:-እናት በወለደችው ልጅ ላይ እናት መሆኗ እንደማይጠረጠር ሁሉ ሥላሴም የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም መፍጠራቸው ፈጽሞ ስለማይጠረጠር ነው፤ሮሜ: ፩፥፳። ፪ኛ:-የልጅ መወለዱ ከእናት እንደ ሆነ ሁሉ እኛም በጥምቀት ከሥላሴ በመወለዳችን ነው፤ዮሐ:፫፥፭። ፫ኛ:-እናት ፈጭታ፥ጋግራ ቤተሰቧን እንደምትመግብ ሁሉ ሥላሴም በእናት አምሳል ዓለሙን ስለሚመግቡ ነው፤ ፬ኛ:-የእናት አንጀት በተፈጥሮ ርኅሩኅ እንደሆነ ሁሉ ሥላሴም በባህርያቸው ለፈጠሩት ፍጥረት እንደ እናት አንጀት ርኅሩኅ በመሆናቸው ነው።ኢሳ:፵፱፥፲፭።ከዚህም ጋር “ቅድስት” ለአንዲት ሴት የሚሰጥ ስያሜ በመሆኑ ቃሉ ለሥላሴ መቀጸሉ አንድነታቸውን ሲያስረዳልን “ሥላሴ” የሚለው ደግሞ ሦስትነታቸውን የሚያስረዳልን በመሆኑ ነው፥ትርጉሙ ሦስትነት ማለት ነውና።

እንኳን ለጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!✝️✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✍ በየዓመቱ ሐምሌ 10 ቀን የሚከበረው የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ...
17/07/2026

እንኳን ለጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!
✝️✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝

✍ በየዓመቱ ሐምሌ 10 ቀን የሚከበረው የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ የልደት በዓለ ንግሥ በድምቀት ተከብሮ ዋለ!!!
✍ ይልቁንም ለ9 ዓመታት ሲገነባ የቆየው የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ቤተ መቅደስ በመጠናቀቁ ትናንት ሐምሌ 9/2018 ዓ/ም በብፁዕ አቡነ እንጦንስ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሥርዓተ ቡራኬው ተከናውኗል።
✍ በበዓሉ ላይ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ፍቅረ ዮሐንስ ብርሃኑ
✍ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ መጋቤ ሥርዓት ቴዎድሮስ ዓለሙ
✍ መልአከ ፀሐይ ዮሐንስ ገ/ጻድቅ የሀገረ ስብከቱ ሰበካ ጉባኤ ማደራጃ ክፍል ኃላፊ
✍ የሀገረ ስብከቱ የየክፍሉ ኃላፊዎች
✍ በርካታ ሊቃውንትና ካህናት
✍ እጅግ ብዛት ያለው ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
✍ በዓሉ ከሥርዓተ ዋዜማው ጀምሮ ሥርዓተ ማኅሌቱና ሥርዓተ ቅዳሴው በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባታችን አቡነ እንጦንስ መሪነት፣በክቡር የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ፍቅረ ዮሐንስ ብርሃኑ አስተባባሪነት ተከናውኗል።
✍ የቃል ኪዳኑ ታቦትም ከመንበረ ክብሩ ተነስቶ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከባረከ በኋላ፣በእንገዶችና በገዳሙና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያሬዳዊ ዜማ አቅርበዋል።
✍ በመቀጠልም የዕለቱ ትምህርተ ወንጌል በብፁዕ አባታችን ከተሰጠ በኃላ በበዓሉ ላይ ለሕንጻ ቤተክርስቲያኑ መጠናቀቅና ለምርቃት መብቃት ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ፥ የሞያና የጉልበት ድጋፍ ላደረጉ አካላት የሸልማትና የምስክር ወረቀት ስጦታ በብፁዕ አቡነ እንጦንስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እጅ ተበርክቷል።
✍ በመጨረሻም በሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ፍቅረ ዮሐንስ ብርሃኑ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋባዥነት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አባታችን አቡነ እንጦንስ ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

✍ ታቦታተ ሕጉም በእልልታና በዝማሬ ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።

በአገልግሎታችን ሁሉ የረዳን አምላከ ሳሙኤል ስሙ የተመሰገነ ይሁን !!!

የጻድቁ ሳሙኤል በረከት አይለየን !!!

ሐምሌ 10/2018 ዓ/ም

አሰቦት ገዳም/ምዕራብ ሐረርጌ ኢትዮጵያ

"እባካችሁ ድምፅ ሁኑን!" — ከምስራቅ አርሲ ጫካዎች የተሰማ የድረሱልን ጥሪ! መላው አገር በምርጫው ትኩረት በተጠመደበት በዚህ ወቅት፣ በምስራቅ አርሲ አሰኮ ወረዳ በንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን ...
06/06/2026

"እባካችሁ ድምፅ ሁኑን!" — ከምስራቅ አርሲ ጫካዎች የተሰማ የድረሱልን ጥሪ!

መላው አገር በምርጫው ትኩረት በተጠመደበት በዚህ ወቅት፣ በምስራቅ አርሲ አሰኮ ወረዳ በንጹሐን ኦርቶዶክሳውያን ላይ ዘግናኝ ጥቃት እየተፈጸመ ይገኛል።

ከ37 በላይ ንጹሐን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።
234 መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል።

ታሪካዊው የጠላታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል እና የኩፍቴና መድኃኔዓለም አብያተ ክርስቲያናት ወድመዋል።

ጥቃቱ አሁንም በተለያዩ ቀበሌዎች (ዘዲቡ፣ እሬቻ ሚካኤል፣ ሱንቴ ማርያም...) የቀጠለ ሲሆን፣ አቅመ-ቢስ እናቶችና ሕፃናት ሕይወታቸውን ለማዳን ንብረታቸውን ጥለው በጫካዎች ውስጥ ተደብቀው ይገኛሉ።

የቀሩት በሕይወት እንዲተርፉ የንጹሐንን ድምፅ ለዓለም እናሰማ!

👉 ይህ መረጃ ለሁሉም እንዲደርስ በማድረግ የተጎጂዎች መጠጊያ እና ድምፅ እንሁን! 🙏

ነፍስ ይማር!

< እኔ ክርስቲያን ነኝ>   ብሎ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የመሰከረ በፈላ ውሃ ውስጥ ከእናቱ ጋር የተጣለ እናቴ ገድላችን እንፈጽም  #አትፍሪ እያለ ከእናቱ ጋር ሰማዕት የሆነ የኢየሉጣ ልጅ ቅዱስ...
23/05/2026

< እኔ ክርስቲያን ነኝ> ብሎ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የመሰከረ በፈላ ውሃ ውስጥ ከእናቱ ጋር የተጣለ እናቴ ገድላችን እንፈጽም #አትፍሪ እያለ ከእናቱ ጋር ሰማዕት የሆነ የኢየሉጣ ልጅ ቅዱስ ቂርቆስ በረከቱ ይደርብን🙏✝(15)✅🍀🌿🌷!!☦️❤️‍🩹

#ቂርቆስ ማለት ጣፋጭ ሽቶ[ጥዑም መዓዛ]🥰

የቅዱስ ቂርቆስ ሬድኤት በረከት ይደርብን!!☦️❤️‍🩹

🤌ሠላም ለሀገራችን ይስጠን!!☦️❤️‍🩹🥰🍀

#አሜን !!☦️❤️‍🩹🥰🍀

አሜን !!☦️❤️‍🩹🥰🍀

አሜን !!☦️❤️‍🩹🥰🍀


#ኢትዮጵያ 💚💛❤
#ተዋሕዶነት
#እለተቅዳሜ
#ይባርከን
#አምላካችን
#ህጻኑጨርቆስ
#ኢየሉጣ
!🌷

💚💚💚💛💛💛❤❤❤

🌸 ከሊባኖስ አበባ እስከ እሑድ ትንሣኤ፦ የልቦና ብርሃን ጸሎት 🌸​"እነሆ አበባዎች በምድር ላይ ታዩ፤ የዜማም ጊዜ ደረሰ!" (መኃልየ መኃልይ ፪፥፲፪)​ዛሬ ግንቦት ኹለት ነው! ምድር በአበባ...
23/05/2026

🌸 ከሊባኖስ አበባ እስከ እሑድ ትንሣኤ፦ የልቦና ብርሃን ጸሎት 🌸

​"እነሆ አበባዎች በምድር ላይ ታዩ፤ የዜማም ጊዜ ደረሰ!" (መኃልየ መኃልይ ፪፥፲፪)

​ዛሬ ግንቦት ኹለት ነው! ምድር በአበባ አጊጣ፣ አየሩ በመዓዛ ታውዷል። በዚህ ድንቅ ንጋት፣ የትንሣኤውን ድልና የእመቤታችንን ልደት እንዲህ እናገናኛለን፦

​🙏 የልቦና መስዋዕት (ጸሎት)

​ኦ! አምላኬ ሆይ፤
ከሊባኖስ በረከት፣ ከሐና ማኅፀን፣ ከኢያቄም ዕንባ የተገኘችው "ንጽሕት አበባ" ማርያም የተወለደችበት ንጋት ነው። ይህች አበባ ግን ተራ አበባ አይደለችም፤ በውስጧ "የሕይወት ፍሬ" ክርስቶስን የያዘች፣ የሞትን መውጊያ የምታጠፋ የመድኃኒት ጥበብ ናት እንጂ።

​ጌታዬ ሆይ!
የእመቤታችን ልደት የትንሣኤህ "ጎህ" ነው። እርሷ ስትወለድ ጨለማው ሊነጋ፣ መቃብሩ ሊከፈት፣ አዳምም ከሲኦል እስራት ሊፈታ ተስፋ አገኘ። እርሷ "የመዳን ምሥራቅ" ናት፤ አንተ ደግሞ ከዚያች ምሥራቅ የወጣህ "የጽድቅ ፀሐይ" ነህ። ያለ እርሷ ልደት፣ የአንተን ሰው መሆንና ትንሣኤ ባላየን ነበር። ዛሬ በልደቷ ዕለት፣ የአንተን የትንሣኤ ብርሃን በልባችን ላይ አብራው።

​እመቤቴ ሆይ!
ዛሬ ዓለም በአበቦች ስታጌጥ፣ የእኔ ልብ ግን በኃጢአት መድረቁን አውቃለሁ። ነገር ግን አንቺ "የማይጠወልግ አበባ" ነሽና፣ ወደ እኔ ጓዳ ዝለቂ። ከልጅሽ ከትንሣኤው ጌታ ዘንድ የይቅርታን ጠል አምጪልኝ። ልቤ እንደ መቃብር በድን ሆኗልና በልደትሽ ብርሃን "ትንሣኤ" ይሁንለት።

​ኦ! ትንሣኤና ሕይወት የሆንክ ጌታ ሆይ!
በዚህ በግንቦት ንጋት፣ ነፍሴ ከአርያም በታች ካለው ዝቅታ ወጥታ ወደ አንተ እንድትሰቅል አድርጋት። በልደቷ የተገኘው በረከት፣ በትንሣኤህ ወደተገኘው ዘላለማዊ ሕይወት ይምራኝ። አእምሮዬን በተመስጦ፣ ልቤን በተጋድሎ፣ ነፍሴን ደግሞ በአንተ ፍቅር አቅልጠው።

​ከሊባኖስ በወጣው መዓዛ፣ ከመቃብር በወጣው ድል፣ በድንግል ልደትና በአንተ ትንሣኤ መካከል ያለውን ምስጢር እያሰብኩ አመሰግንሃለሁ። ዛሬ በቤቴ ሰላም፣ በልቤ ብርሃን፣ በኑሮዬም ትንሣኤ ይሁን።
​አሜን!

​📚 የታሪክና የምስጢር ማጣቀሻዎች (References)

​ይህ ጸሎት የሚከተሉትን ቅዱሳት መጻሕፍትና የሊቃውንት ትንታኔዎች መሠረት ያደረገ ነው፦

√ ​የመዳን ምሥራቅ፦ "ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጎበኝ... ማን ናት?" (መኃልየ ፮፥፲)። ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ አርጋኖን ላይ ድንግልን "የጽድቅ ፀሐይ መውጫ የምሥራቅ ደጅ" በማለት ይተረጉመዋል።
√ ​የሕይወት አበባ፦ ቅዱስ ያሬድ በግንቦት ድጓው ላይ "ለኪ ይደሉ ስብሐት... ጽጌ ረዳ ዘውስተ ገነት" በማለት የልደቷን ምስጢር ከገነት አበባ ጋር ያያይዘዋል።
√ ​የትንሣኤ ጎህ፦ የእመቤታችን ልደት ለሥጋዌ መሠረት፣ ለትንሣኤው ደግሞ መንገድ መሆኑን ሃይማኖተ አበው (ዘቅዱስ ቄርሎስ) እና የውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ያብራራሉ።

​✍️ ቀሲስ ኢዩኤል ሰሎሞን
📅 ግንቦት ፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም

​ #ትንሣኤ #ተዋሕዶ #ኢትዮጵያ #ጸሎት

23/05/2026
 “ሥላሴ” የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት ማለት ነው፡፡ቅድስት ሥላሴ ስንል ለሥላሴ ቅድስት ብለን እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት...
05/05/2026



“ሥላሴ” የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት ማለት ነው፡፡

ቅድስት ሥላሴ ስንል ለሥላሴ ቅድስት ብለን እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ይህም ሦስት ሲሆኑ አንድ፣ አንድ ሲሆን ሦስት ስለሚሆኑ ልዩ ሦስትነት ተብሏል፡፡ ሥላሴ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለና የሚኖረውን አምላክ ለመግለጽ የተጠቀመው የአንጾኪያው ቅዱስ ቴዎፍሎስ በ169 ዓ.ም ነው፡፡ በኒቅያ ጉባዔም 318ቱ ሊቃውንት አጽንተውታል፡፡ ሊቃውንቱ በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰከረውን የእግዚአብሔርን ፍጹም አንድነትና ልዩ ሦስትነት ለእኛ በሚረዳ ቋንቋ ገለጡት እንጂ አዲስ ትምህርት አላመጡም፡፡ ምስጢረ ሥላሴ ማለት የአንድነት የሦስትነት ምስጢር ማለት ነው፡፡ ምሥጢር መባሉም በእምነት የተገለጠ፣ ያለ እምነትም የማይመረመር ስለሆነ ነው፡፡

ይኸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በሕልውና፣ በመለኮት ደግሞ አንድ ናቸው፡፡ እንደዚህ ባለ ድንቅ ነገር አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ ይባላሉና፣ ይህም ልዩ ሦስትነት ረቂቅ እና በሰው አእምሮ የማይመረመር ስለሆነ ምስጢር ይባላል፡፡ ስለዚህም አንድ አምላክ፣ ሦስቱ አካላት ብለን እናምናለን፡፡ ሥላሴ ሦስት ናቸው ስንል እንደ አብርሃም፣ እንደ ይስሐቅ እንደ ያዕቆብ የተነጣጠለና በክብርም ሆነ በዘመን የሚበላለጥ የሚቀዳደም ማለታችን አይደለም፡፡ ሦስት ሲሆኑ አንድ ናቸው እንጂ፡፡ አንድ ናቸውም ስንል ከሰው ሁሉ ቀዳሚ ሆኖ እንደተፈጠረው እንደ አዳም ሦስትነትን የሚጠቀልል መቀላቀል ማለታችን አይደለም፡፡ አንድ ሲሆኑ ሦስት ናቸው እንጂ እንዲል ቅዳሴ ማርያም፡፡

የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሰው ምሳሌ ይገለጻል፡፡ ሰው በነፍሱ ሦስትነት አለው፡፡ ይኸውም ልብነት፣ ቃልነት፣ ሕይወትነት ነው፡፡ በልብነቷ አብ፣ በቃልነቷ ወልድ፣ በሕይወትነቷ መንፈስ ቅዱስ ይመስላሉ፡፡ የነፍስ ልብነቷ፣ ቃልነቷን፣ ሕይወትነቷን ከራሷ ታስገኛለችና፡፡ ቃልና ሕይወት ከአንዷ ልብ ስለተገኙ በከዊን ወይም በመሆን ልዩ እንደሆኑ በመናገርም ይለያሉ፡፡ እንዲሁም አብ ወልድን በቃል አምሳል ወለደው፣ መንፈስ ቅዱስንም በእስትንፋስ አንጻር አሰረጸው፡፡ ነፍስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ ተገኘች አንዷ ልብነቷ ቀድሞ ቃልነቷና እስትንፋስነቷ በኋላ አልተገኙም፡፡ ሥላሴም አንዱ ከአንዱ ሳይቀድሙ ተገኝተዋልና፡፡

በአሚነ ሥላሴ ያጽናን🙏🙏🙏

ተንሥአ (ተነሥቷል) ሉቃ 24፥6ነገረ ክርስቶስን በስተማርን ጊዜ ኹሉ ቅዱሳን መላእክትን እንዘክራቸዋለን። ኢየሱስ ክርስቶስን ተጸነ፣ ተወለደ፣ ተሰደደ፣ ከስደት ተመለሰ እያሉ ብሥራትን ያመጡ፣...
05/05/2026

ተንሥአ (ተነሥቷል) ሉቃ 24፥6

ነገረ ክርስቶስን በስተማርን ጊዜ ኹሉ ቅዱሳን መላእክትን እንዘክራቸዋለን።

ኢየሱስ ክርስቶስን ተጸነ፣ ተወለደ፣ ተሰደደ፣ ከስደት ተመለሰ እያሉ ብሥራትን ያመጡ፣ በሚጾምበት ጊዜ ቀርበው ያገለገሉ ማቴ 4፤ በሰርግ ቤት ሳለ መጥተው ሰማይ ዙፋንህ ምድር የእግርህ መረገጫ ስትሆን በተናቀች ጎጆ በሰርግ ቤት መገኘትህ ምን ይደንቅ? ብለው ያደነቁት (ሃ.አ.ዘቅዱስ ኤፍሬም)፤ የእኛን መከራ ሊቀበል ጊዜው በመድረሱ በጸሎተ ሐሙስ ሲጸልይ "አባት ሆይ ይኽች ጽዋዕ ከእኔ ትለፍ..." በሚል ጊዜ ከሰማይ መጥተው ያበረቱት (ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም) በማለት የሰገዱት) ሉቃ 22፤ ጎኑ በጦር በተወጋ ጊዜ በወርቅ ጽዋዕ ቀድተው ዓለምን የረጩት፣ በተነሣም ጊዜ "ተነሥቷል በዚህ የለም" ብለው ምሥራችን የሰበኩት፣ ወደ ሰማይ ሲያርግ ሲሔድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል ብለው ለደቀ መዛሙርቱ የመሠከሩ፣ ዳግመኛም ሲመጣ መለከት እየነፉ "ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት... ንቃህ መዋቲ" በማለት አዋጅ የሚናገሩ መላእክተ ብሥራት (አብሣሪ መላእክት) ናቸው። የኢየሱስን ሥጋ ሽቱ ቀብተው ለመሰናበት ፎቅሩ ሲያንገበግባቸው አድረዋልና ገና ሳይነጋ ገሥግሠው ፍለጋ ሒደው ሥጋውን አጥተው የመቃብሩን ባዶ መሆን ተመልክተው ሲጨነቁ ለነበሩ ሴቶች፦

" ? ፤ ተዘከራ ዘይቤለክን በገሊላ ሀለዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይግባእ ውስተ እደ ሰብእ፤ ወይሰቅልዎ፤ ወይቀትልዎ፤ ወይትነሣእ በሣልስት ዕለት ። "ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ ? #አንድም ስለምን ትሹታላችሁ? ተነሥቷል እንጂ በዚህ የለም ። የሰው ልጅ በኃጥአን እጅ ተላልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል፣ ሊገደል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደ ተናገረ አስቡ ።"ሉቃ 24:5-7 አሏቸው።

ዐራቱም ወንጌላውያን ይኽንን የምሥራች ዘግበውልናል።

“መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው! እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቷልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ:: ፈጥናችሁም ሂዱና፡፡ ከሙታን ተነሣ እነሆም ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው›› ማቴ ፳፰ እነርሱም መልአክ ዐይተዋልና እየፈሩ ትንሣኤውን ሰምተዋልና ደስ እያላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ይነግሯቸው ዘንድ ፈጥነው ሔደው የክርስቶስን ትንሣኤ አበሠሩ።

“ወደ መቃብሩም ገብተው ነጭ ልብስ የተጎናጸፈ ጎልማሳ በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ፡፡ እርሱ ግን አትደንግጡ ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ ፤ ተነሥቷል በዚህ የለም! ነገር ግን ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱ #ለጴጥሮስም ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፤ እንደ ነገራችሁ በዚያ ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሩአቸው አላቸው>> ብሎ አስፍሮታል። ማር 14:5

ደግሞ “እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ እነሆ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀርበው "ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቷል እንጂ በዚህ የለም። የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ ታልፎ ሊስጥና ሊስቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደ ተናገረ አስቡ" አሉአቸው። ሉቃ 28: 6

"መግደላዊት ማርያም ሁለቱን መላእክት እንዳየችና ከእነርሱም ጋር እንደተነጋገረች ሲገልጽ "ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመ

በቃልኪዳኗ : ለመጠቀም : ትንሽ : ጥርኝ : ውኃ : ብቻ የወላዲተ አምላክ ኪዳነ ምሕረት ከአብርሃም ከዳዊት ቃል ኪዳን ይልቅ የድንግል ማርያም የምሕረት ኪዳን ይበልጣል ።ምክንያቱም እግዚአብ...
05/05/2026

በቃልኪዳኗ : ለመጠቀም : ትንሽ : ጥርኝ : ውኃ : ብቻ

የወላዲተ አምላክ ኪዳነ ምሕረት ከአብርሃም ከዳዊት ቃል ኪዳን ይልቅ የድንግል ማርያም የምሕረት ኪዳን ይበልጣል ።

ምክንያቱም እግዚአብሔርን በቤቱ ካስተናገደው ከአብርሃም ይልቅ ለእግዚአብሔር ቤቱ የሆነች ድንግል ማርያም ትበልጣለችና ።

በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ከዘለለው ከዳዊት ይልቅ ለእግዚአብሔር ታቦት የሆነችው ድንግል ማርያም ትበልጣለች የድንግል ቃልኪዳን ከሁሉ ይበልጣልና ።

እርስዋ ምሕረትን ለማሠጠት የምታስታውሰውን የተገባላትን ኪዳን ብቻ ሳይሆን በብርድ ወራት በጨርቅ የጠቀለለችውን ድንግልናዊ ወተትዋን ያጠባችውን ፣ በስደት ይዛው የተንከራተተችውን ፣ በፊቱ ላይ የወረደውን እንባዋን እያስታወሰች እያማለደች ምሕረትን ስለምታሰጥ ነው ።

በቃልኪዳን ለመጠቀም እንደ መበለቲቱ ትንሽ ዱቄት ትንሽ መልካምነት ያስፈልጋል እግዚአብሔር ትንሹን በቸርነቱ ያበዛዋልና ።

እግዚአብሔርም ምሕረትን ለማድረግ ጥቂት ነገር ይፈልጋል ጥርኝ ዱቄት ጥርኝ ደግነት ጥርኝ ውኃ እንደ በላኤ ሰብእ ከእኛ ይጠበቃል ።

እንደ ሕዝቅያስ ጥርኝ ዕንባ ሲያገኝ ከዳዊት ቃል ኪዳን ጋር ደምሮ ይምረናል ።

እንደ ሙሴ አታጥፋቸው የሚል ጥርኝ ምልጃ ሲያገኝ ከአብርሃም ቃል ኪዳን ጋር ደምሮ ይምረናል ።

ጥርኝ ውኃ ጥርኝ ዕንባ ጥርኝ ደግነት ብቻ አንዳች ጥርኝ መልካምነት ከእኛ ዘንድ ካለ ለእናቱ በገባላት የምሕረት ቃል ኪዳን ይምረናል ይታደገናል።

ጽ ዮ ን : የ ም ድ ር : ሁ ሉ : ደ ስ ታ : ና ት !!!እስራኤልላውያን ከግብፅ ከባርነት ከወጡ በኋላ ጸልየው እንዲድኑባት ሰውተው እንዲከብሩባት ታቦተ ጽዮንን እግዚአብሔር አምላክ ሰጣቸ...
05/05/2026

ጽ ዮ ን : የ ም ድ ር : ሁ ሉ : ደ ስ ታ : ና ት !!!

እስራኤልላውያን ከግብፅ ከባርነት ከወጡ በኋላ ጸልየው እንዲድኑባት ሰውተው እንዲከብሩባት ታቦተ ጽዮንን እግዚአብሔር አምላክ ሰጣቸው በታቦተ ጽዮን እየተማፀኑ አርባ ዘመን ደመና እየጋረደ መና እያወረደ ዐለት እየሰነጠቀ ውኃ ከጭንጫ እያፈለቀ በሰላም ተንከባክቦ መግቦ ምድረ ርስት አግብቷቸዋል ።

ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች ።
የዮርዳኖስን ባሕርን የከፈለች ።
በድፍረት ሊነካት የሞከረ ኦዛንን የቀሠፈች ።
ዳጎን የተባለ የፍልስጤማውያንን ጣዖት ቆራርጣ ያጠፋች ።
በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች ።
ከብዙ ዘመን በኋላ ወደ ሀገሯ ስትመለስ ነቢየ ዳዊት በደስታ የዘመረላት ።
ንጉሥ ሰሎሞን በወርቅ የተጌጠ ቤተ መቅደስ ሠርቶ በክብር ያኖራት ።
በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ተቀምጣ ያለች ናት ።

የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ ታቦት የሆነችው ይህች በንጽሕና በቅድስና የተጌጠችው የእግዚአብሔር ወልድ እናት የሆነችው የአማናዊት ታቦት የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት ፡፡

የአምላክ ማደሪያ የሆነችው ታቦት ጽዮን ወደ ፍልስጥኤም ሀገር ሔዳ ዳጎንን ሰባብራ እንዳጠፋች ሁሉ አማናዊት የጌታ ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያምም ጌታን ይዛ ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ የግብጽ ጣዖታትን ሁሉ እየተሰባበሩ እንደወዳደቁና እንደደቀቁ በኢትዮጵያ ሀገራችን በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ጠላት ካሴረባት ሸፍጥ ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችን ይታደጋት

Address

Harer Gahe
Hawassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ASER Z Samuel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share