27/01/2022
ሰፊ እርሻ!
“ከምንገምተው ሁሉ በላይ.. ኤፌ. 3፡20
እኛ አገልጋዮች ለወንጌል መተላለፍያ መንገዶች እጅግ የጠበበ ልብ ካለን፤ ይልቁኑ በስራችን ያሉ ሰዎች ምን ያህል ይጠቡ ይሆን? ስለ ወንጌል ያለን ግንዛቤ በጣም አናሳ ከሆነ፣ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ስራ ዉስጥ ሊጠቀምብን ያዘጋጀውን መንገድ ሁሉ እንዘጋለን።ይህ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄርን ስራ በተከፈተላቸው እድል የሚሰሩትን አንተባበርም፤ ይልቁኑ እንቃወማለን፣እንቅፋት እንሆናለን። ሁሉን አቀፍ አብያተ ክርስቲያናት በምድራቸው ላይ ለመላሁ የሰው ልጆች አገልግሎት ይሰጣሉ ።አገልግሎታችን ሁለንተናዊ ሲሆን ሰዎችን ሁሉ በእግዛብሄር አይን እየተመለከትን መሆኑን ያሳያል።ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም የሰው ልጅ ፍላጎቶች ታገለግላለች እና በሁሉም የህብረተሰብ ደረጃ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች፣ ማህበረሰቦች፣ ብሔሮች፣ ዉስጥ ራስዋን ትገልጣለች።ጨው ቀለም፣ ዘር ፣ደረጃ የለውም በየትኛውም ገባታ ውስጥ እሱ አለ።ያን የጨውነት ሚና ትጫወት ዘንድ ይሄንን ችሎታ ለቤተክርስትያን መሰጠቱን ሁላችንም አገልጋዮች እናውቃለን እያልን ይሆን????።
F C Hawassa
F C Hawassa
F C Hawassa