Peace Mission Islamic association

Peace Mission Islamic association This is the official page of peace-mission Islamic association which is based in Ethiopia, Amhara regional state

23/08/2026
18/08/2026
ﷺ
14/08/2026

08/08/2026

A Smile From Gaza❤️
May Allah ease the affairs of our brothers and sisters there .

24/07/2026

ቱርክን ጨምሮ ስምንት ሀገሮች የእስራኤል ባለሥልጣናት በመስጂደል አቅሳ ላይ የፈፀሙትን ጥሰት በጽኑ አወገዙ

ቱርክን ጨምሮ ስምንት ሀገራት የእስራኤል ባለስልጣናት በመስጂደል አቅሳ ላይ የፈፀሙትን ጥሰት በጽኑ ያወገዙት ባወጡት የጋራ መግለጫ ነው።

የሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባወጡት መግለጫ፤ አክራሪ የእስራኤል ካቢኔ ሚኒስትሮች በፀጥታ ኃይሎች ታጅበው በመስጊደል አቅሷ ቅጽር ግቢ ውስጥ የፈጸሙትን ሕገ ወጥ መግባት እና ትንኮሳ ፈፅመዋል ብለዋል።

ሀገራቱ ቱርክ፣ የተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ኳታር፣ ግብፅ፣ ፓኪስታን፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ዮርዳኖስ ናቸው። የሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያወጡት መግለጫ፣ የፀጥታ ኃይሎቹ በመስጅዱ ቅጽር ግቢ ውስጥ የእስራኤልን ሰንደቅ አላማ መትከላቸውን እና ድንኳኖችን መዘርጋታቸውን "ግጭት ቀስቃሽ እና ተቀባይነት የሌለው" ድርጊት እንደሆነ ገልጸዋል።

መግለጫው የወጣው የእስራኤል የብሔራዊ ደኅንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ግቪር በጸጥታ ሃይሎች ታጅበው ከአይሁድ አክቲቪስቶች ጋር ወደ መስጅዱ ግቢ መግባታቸውን ተከትሎ ነው።

ድርጊቱ ዓለም አቀፍ ሕጎችን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውሳኔ ሃሳቦችን፣ እንዲሁም በወረራ በተያዘችው ምሥራቅ ቁድስ የሚገኙ ቅዱሳን ስፍራዎችን ታሪካዊ እና ሕጋዊ ነባራዊ ሁኔታ የጣሰ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

አናዶሉ እንደዘገበው እንዲህ አይነት ቀስቃሽ ድርጊቶች ጥላቻን እና አክራሪነትን ከማባባሳቸውም ባለፈ፣ በሁለት ሀገር ምስረታ መፍትሄ ላይ የተመሰረተውን የሰላም ጥረት የሚያደናቅፉ መሆናቸውን ሀገራቱ አስጠንቅቀዋል።

ስምንቱ ሀገራት በመግለጫቸው እስራኤል በወረራ በተያዘችው ቁድስ እና በሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያን ቅዱሳን ስፍራዎች ላይ ምንም አይነት ሉዓላዊነት እንደሌላት አጽንኦት ሰጥተዋል። የእስራኤል ስልታዊ ጥሰቶች እና ድርጊቶች የምስራቅ ቁድስን ታሪካዊ፣ ህጋዊ እና የስነሕዝብ ባህሪ ለመቀየር እና የሙስሊም እና የክርስቲያን ቅዱሳን ስፍራዎቿን ቅድስና እና ደረጃ ለማዳከም ያለመ ነው ብለዋል።

የመስጂደል አቅሳ ግቢ ለሙስሊሞች ብቻ የተፈቀደ የጸሎት ስፍራ መሆኑንም በመግለጽ፣ የቦታው ብቸኛ ህጋዊ አስተዳዳሪ በዮርዳኖስ መንግስት ስር የሚተዳደረው የቁድስ አውቃፍ እና የአል-አቅሳ ጉዳዮች መምሪያ እንደሆኑ በመግለጫቸው ዳግም አረጋግጠዋል።

በመጨረሻም ሚኒስትሮቹ እስራኤል በቁድስ ጥንታዊት ከተማ እና በመስጊዱ ላይ የጣለችውን እገዳ በአፋጣኝ እንድታነሳ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እስራኤል ይህንን ሕገ-ወጥ ድርጊት እና የእምነት ስፍራዎች ላይ የምታደርገውን ጥሰት እንድታቆም የሚያስገድድ ጠንካራ አቋም እንዲወስድ ጥሪ አቅርበዋል። (ሚንበር ቲቪ)

Address

Harbu

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Peace Mission Islamic association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Peace Mission Islamic association:

Shortcuts

Share