ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል Mahibere Kidusan Harar Center

  • Home
  • Ethiopia
  • Harar
  • ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል Mahibere Kidusan Harar Center

ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል Mahibere Kidusan Harar Center Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል Mahibere Kidusan Harar Center, Religious Center, Harar.

25/05/2026
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።“ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!” (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ)የእመቤታችን ቅድስት ድንግል...
10/05/2026

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!” (ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ)

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በዓል እና የማህበራችን ማህበረ ቅዱሳን 34ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ግንቦት 1 በማህበረ ቅዱሳን የሐረር ማእከል ከጤናና ህክምና ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ተከብሯል፡፡
በዕለቱም በዓሉን በማስመልከት ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን ዝማሬ፡ ስነጽሁፍ፡ የማህበረ ቅዱሳን ምስረታን በተመለከተ እና የ34 ዓመት የአገልግሎት ጉዞ ገለጻ፡ የበገና ዝማሬ ቀርበዋል በመጨረሻም የማህበሩን መልእክት በሐረር ማእከል ዋና ጸሐፊ ተነቦ በጸሎት ተጠናቋል፡፡

ግንቦት 2/2018 ዓ/ም

መልካም የትንሣኤ በዓል
12/04/2026

መልካም የትንሣኤ በዓል

ለሐረር እና አካባቢዋ ማዘዝ ይችላሉ√ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል ልማት ተቋማት
01/04/2026

ለሐረር እና አካባቢዋ ማዘዝ ይችላሉ

√ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል ልማት ተቋማት

ዕለተ አኮቴትGuyyaa Galataa"Waaqayyooniis Hojii Hundaan Galateeffadhaa" K.Siiraaki 39:14Jimaata Bitootessa 25/2018iddoon: Har...
01/04/2026

ዕለተ አኮቴት

Guyyaa Galataa

"Waaqayyooniis Hojii Hundaan Galateeffadhaa" K.Siiraaki 39:14

Jimaata Bitootessa 25/2018

iddoon: Harar kawaala qulqulluu filiphoos

28/03/2026
 #ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር እና ድሬደዋ ማእከላት በቀርሳ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የተሳካ ሐዊረ ሕይወት/የሕይወት ጉዞ ማዘጋጀታቸውን ገለፁ።መጋቢት 15/2018 ዓ/ም++++++...
24/03/2026

#ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር እና ድሬደዋ ማእከላት በቀርሳ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የተሳካ ሐዊረ ሕይወት/የሕይወት ጉዞ ማዘጋጀታቸውን ገለፁ።
መጋቢት 15/2018 ዓ/ም
+++++++++++++
#መጋቢት 13/2018 ዓ/ም ማኅበረ ቅዱሳን የሐረር እና ድሬደዋ ማእከላት ወደ ቀርሳ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የሐረር እና የድሬደዋ ምዕመናንን በማስተባበር መንፈሳዊ የሕይወት ጉዞ አዘጋጅተዋል።

#በዕለቱ ከአዲስ አበባ እንዲሁ ከሐረር እና ድሬደዋ የተወጣጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የተገኙበት ሲሆን
የዝማሬ፤ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት፤ ምክረ አበው፤እንዲሁም ደብሩን ለመደገፍ እና ለመርዳት የገንዘብ ማስተባበር ስራ ተከናውኗል።

#ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነ መርሃ ግብር በማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት ውስጥ ኦርቶዶክሳዊያን እርስ በእርስ የሚረዳዱበት፤ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት እንዲሁም ምዕመናን እንዲመለስላቸውን ኦርቶዶክሳዊ ጥያቄዎችን እየመለሰ የሚገኝ እና ማኅበራዊ አገልግሎትን ከማጠናከር አንፃር ጉልህ ሚና እያበረከተ የሚገኝ መርሃ ግብር ነው።
ምስጋና፦
1) ለምስራቅ ሐረርጌ ሀገር ስብከት ፅ/ቤት
2) ለድሬደዋ ሀገረ ስብከት ፅ/ቤት
3) ለምስራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳደር ፅ/ቤት
4) ለምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
5) ለቀርሳ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት
6) ለቀርሳ ወረደ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ
7) ለቀርሳ ወረዳ ፓሊስ ቢሮ
8) ለሐረር ዙሪያ ወረዳ ቤተክህነት
9) ለቀርሳ ደ/ፀ/ቅ/ጊዮርጊስ ሰ/መ/ጉባኤ ፅ/ቤት

#እንዲሁም ለዚህ ሐዊረ ሕይወት ጉልህ ድርሻ የተጫወቱ እግዚአብሔር አምላክ የሚያውቃቸው በጎ አድራጊ ምዕመናን በግልም እንደ ማኅበርም፤ በጉዞው ለተሳተፉ የመኪና ሹፌሮችን ሁሉ በማኅበረ ቅዱሳን ሐረር እና ድሬደዋ ማእከላት ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ያግኙን፦[email protected]
👇👇👇
የፌስ ቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/profile.php?id=61558650947731
👇👇👇
የቴሌ ግራም ገጻችን
https://t.me/maheberesanhararcenter

በጉግት ሲጠበቅ የነበረው ሐዊረ ሕይወት ፩ ቀን ብቻ ቀረውትኬት ቆርጠዋል?
20/03/2026

በጉግት ሲጠበቅ የነበረው ሐዊረ ሕይወት ፩ ቀን ብቻ ቀረው

ትኬት ቆርጠዋል?

በኦርቶዶክሳውያን የሚደርሰው ውጫዊ ግፍ ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ መከፋፈልም አደጋ ነው" ከሐመር  መጽሔት " መልእክት  ዐምድ  መጋቢት 2018 ༺ ༻  #የኅትመት ዘመን ፦ #መጋቢት   ፳፻፲፰ ዓ...
18/03/2026

በኦርቶዶክሳውያን የሚደርሰው ውጫዊ ግፍ ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ መከፋፈልም አደጋ ነው" ከሐመር መጽሔት " መልእክት ዐምድ መጋቢት 2018
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦ #መጋቢት ፳፻፲፰ ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በሚዲያ አገልግሎት ተቋም በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት ፴፫ኛ ዓመት ቁጥር ፫ መጋቢት ፳፻፲፰ ዓ.ም መልእክት #ዘማኅበረ ቅዱሳን " ጾም ጸሎታችን ከልብ ሆኖ ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን ሰላም
መልስ ሊኖረው ይገባልና "በሚል በመልእክት ዐምዷ ታስነብባለች። #ዐውደ ስብከት ሥር” «እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል "በሚል ርእስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው የተዘጋጀ ስብከት በስፋት ታስነብባለች።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “ #የነጻነት ጉዞና መሰናክሎቹ" በሚል ዐቢይ ሰፊ ትምህርት ይሰጣል ።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “ #መሪነት፣ አስተዳደርና ግልጽነት የጊዜው የቤተ
ክርስቲያን ተቋማዊ ህልውና ቁልፍ ጉዳዮች " በሚል ሰፊ ጉዳዮች ይዛለች።
• #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "የጠፋውን መፈለግ"በሚል ርእስ ዘመኑን የዋጀ ለወጣቶች የሚያንጽ ጹሑፍ ታሰነብባለች።
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኘውን “የፈረንሳይ ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን " ክፍል _፪ ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር “ የአገልጋዮች ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ጥቅሞች፣ ችግሮችና መፍትሔዎች ይጠቁማል ።ፍትሕቴ
#በኪነ ጥበብ ዐምድ " # የመቅደስ ቁጭት " ክፍል ሦስት በሚል ኪነ ጥበብ ታስነብባለች ።
• #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ በእንተ ጾም #" ክፍል 2 ከመጋቤ ሐዲስ ቀሲስ ሄኖክ ፈንቴ(የቀጨኔ ደብረ ሰላም መደድጋር የተደረገ ጥያቄና መልስ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት ፴፫ ኛ ዓመት ቁጥር_፫ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
magazine .org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
━━━━━༺✞༻━━━━

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ አገልግሎት በዶ/ር አለማየሁ ዋሴ‹ሁለተኛ ደጀ ሰላም አንገባም!›የባቴ ደ/ማ/ቅ/አማኑኤል ቤተክርስቲያን አገልግሎታችን ሰብሳቢ የነበረው ዘነበ ገብረ እግዚአብሔር...
17/03/2026

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ አገልግሎት በዶ/ር አለማየሁ ዋሴ

‹ሁለተኛ ደጀ ሰላም አንገባም!›

የባቴ ደ/ማ/ቅ/አማኑኤል ቤተክርስቲያን አገልግሎታችን ሰብሳቢ የነበረው ዘነበ ገብረ እግዚአብሔር የሚባል ታላቅ ወንድማችን ጥብቅ በሆነ ዲሲፕሊን ክርስትናችንን እንድንመራ፣ አገልግሎታችን እንድናስኬድ ይመክረን ነበር፡፡ ‹እኛ እዚህ ቦታ የምንመጣው ሌሎችን ልናገለግል ስለሆነ ከቅዳሴ በኋላም በቅዳሴ ጊዜም አገልግሎታችን ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን› ይለናል፡፡ በተለይ ደጀ ሰላም ገብቶ ለካህናት እና ዲያቆናት የሚቀርበውን ድግስ መካፈል (ዘኬ መብላት) እንዳናስብ አጥብቆ ይመክረን ነበር፡፡

ከወላይታ የመጣ ‹አዱኛ› የሚባል ቅንና አስቂኝ ጓደኛ ነበረን፤ እንደኛው አገልጋይ ነው፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ከዚህ ፍልቅልቅ ወንድም ጋር ከቅዳሴ በኋላ ወደ ደጀ ሰላም እንድንሄድ ተጠቃቀስን፡፡ ካህናቱም ሁልጊዜ ኑ ስለሚሉን ተከትለናቸው ገባን፡፡ ገብተን ድግሳችን እየኮመኮምን እያለን በአጋጣሚ ዘነበ አልፎ ሲሄድ አየን፡፡

ይሄኔ ተግሳፅ እና ቁጣ እንደሚወርድብን ጠብቀን መልሳችንን ማዘጋጀት ጀመርን፡፡ ‹በቃ መብላት መብታችን ነው! ስንፈልግ እንበላለን ስንፈልግ እናገለግላለን! ማነው የሚቆጣን?› ተባባልን፡፡

ከቅዳሴ በኋላ ለምዕመናን ወንጌል ይሰበካል፤ የግቢ ወጣቶች ኮርስ ይማራሉ፤ ሕጻናት መዝሙር ያጠናሉ፡፡ ግማሹ ሰባኪ፣ ግማሹ ከበሮ መቺ፤ ሌላው መዝሙር አስጠኝ፣ ሌላው ወንበር አስቀማጭ ሆነን ብቻ አስተባባሪዎች ተከፋፍለን በየዓይነቱ እንደለደላለን፡፡

እኔና አዱኛ ከዛ ድልድል ራሳችንን አግልለን ነው ድግስ ላይ የቆየነው፡፡ ምግባችንና ድግሳችንን ስንጨርስ ይሄን መልሳችን አዘጋጅተን ወደ አውደ ምህረቱ ሄድን፡፡ ወጥ ወጥ የሚሸተውን እጃችንን እንዳንከረፈፍን ዘነበ ያለበት ጋ ሄደን ከጐኑ ቆምን፡፡ ይቆጣናል ብለን ስለገመትን መልሳችን ለማቅረብ አቆብቁበናል፡፡

ወንድም ዘነበ ዞር ብሎ አይቶን ዝም አለ፡፡ አሁን አሁን ይሰድበናል፣ አሁን አሁን ይናገረናል ብንል ዝም ጭጭ አለ፡፡ በኋላ መርሃ ግብሮቹ ሁሉ አልቀው እንደተለመደው ግብረ መልስ ለእያንዳንዱ አገልጋይ ይሰጥ ጀመር፡፡ ለሰባኪው ይሄ እንዲህ ነው፣ ይሄ እንዲህ ነው፤ እንዲህ ያልከው ልክ ነው እንዲህ ያልከው (ከዶግማ፣ ከቀኖና፣ ከትውፊት አንጻር) ስህተት ነው፡፡ ለዘማሪውም ዜማ ሰብረሃል እየተባለ ለሁሉም ግበረ መልስ ይሰጣል፡፡ ብቻ በየቀኑ መታነጽ ነው፡፡

እኔ አዱኛ ‹አሁን ነው እንግዲህ ስድብ የሚመጣው› ብለን ስንጠብቅ ይግረማችሁ ብሎ ዘነበ አሁንም ዝም አለ፡፡ መጨረሻ ኘሮግራሙ አልቆ ወደ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ልንገባ ስንል ጠርቶ ይሰድበናል ስንል አሁንም ዝም አለ፡፡

በኋላ አዱኛ አላስቻለውምና ወደ እርሱ ጠጋ አለና ‹መብላት መብታችን ነው፤ ከአባቶቻችን ጋር ብንበላ ምን ነውር አለው?› አለ፡፡ ዘነበ አሁንም ዝም አለ፡፡
ወደ ግቢ ስንመጣ በጐኑ ብንሆን፣ በኋላ ብንሆን፣ በፊት ብንሆንም ምንም ትችት የለም፤ በቃ እንዳለየ ዝም ጭጭ!
መጨረሻ ዶርም ልንደርስ ስንል አዱኛ እኔን ጠራኝና፡-
‹አሌክስ! ሁለተኛ ደጀ ሰላም አንገባም! እሽ!› አለኝ፡፡ ከት ብየ ሳቅሁ፡፡የኔም ውሳኔ ነበር፡፡

አውቆ የሚያጠፋን ሰው ደጋግሞ መጨቅጨቅ ውጤት እንደማያመጣ ይልቅስ ዝምታ የበለጠ ትልቅ ተፅዕኖ እና ቅጣት እንደሆነ የተረዳሁበት የማረሳው አጋጣሚ ሆነ፡፡ ያ ተፅዕኖ አሳድሮብኝ አሁን ድረስ ለማንም ሰው ምክርም ሆነ አስተያየት ቢበዛ ሁለት ጊዜ አለበለዚያ ከአንድ ጊዜ በላይ መናገር አልፈልግም!!

በዚህ ቅዱስ ስፍራ ክርስትናን ያስተማራችሁኝ፥ ወደ አምላክ ጸጋ የመራችሁኝ ወንድሞቼና እህቶቼ በያላችሁበት ሰላም ይብዛላችሁ!

ያግኙን፦[email protected]
👇👇👇
የፌስ ቡክ ገጻችን
https://www.facebook.com/profile.php?id=61558650947731
👇👇👇
የቴሌ ግራም ገጻችን
https://t.me/maheberekidusanhararcenter

Address

Harar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ማእከል Mahibere Kidusan Harar Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share