የምስራቅ ሐረርጌ ሐገረ ስብከት ጽ/ቤት Eastern Hararge Diocese secretary office

  • Home
  • Ethiopia
  • Harar
  • የምስራቅ ሐረርጌ ሐገረ ስብከት ጽ/ቤት Eastern Hararge Diocese secretary office

የምስራቅ ሐረርጌ ሐገረ ስብከት ጽ/ቤት Eastern Hararge Diocese secretary office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የምስራቅ ሐረርጌ ሐገረ ስብከት ጽ/ቤት Eastern Hararge Diocese secretary office, Harar.

በመላው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የሚከበሩ ቅዱሳን በዓላትና፣ዜናዎች፣መንፈሳዊ ስብከቶችና ትምህርቶች፣ እንዲሁም በሀገረ ስብከቱ የሚሰሩ ልማቶችና ሐዋሪያዊ ጉዞዎች የሚዘገብበት መንፈሳዊ ፔጅ ነው።ፈጣንና ተአማኒ መረጃዎች ለማግኘት ፎሎው ላይክ ሼር በማድረግ ቤተሰብ ሆነው እንዲከታተሉ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም ጋብዘናቹሐል።መልካም ቆይታ ከእኛ ይሁንልዎት።

እንኳን ለወርሐዊ የመድኃኔዓለም የመታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ።
04/02/2026

እንኳን ለወርሐዊ የመድኃኔዓለም የመታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ።

ጾመ ሰብአ ነነዌጥር ፳፭-፳፯/፳፻፲፰ 25-27/2018 ‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ...
02/02/2026

ጾመ ሰብአ ነነዌ
ጥር ፳፭-፳፯/፳፻፲፰ 25-27/2018

‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው (ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪)፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶ ነበር (ዮናስ ፬፥፲፩)፡፡
በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ዮናስ የስሙ ትርጓሜ ‹ርግብ› የሆነ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይን ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው (ሉቃ.፲፩፥፴)፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፤ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ በዚያን ጊዜ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናገረ (፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩)፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ሆነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል (፩ኛነገ.፲፯፥፲፱)፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ሆድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል (ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪)፡፡
እግዚአብሔር አምላክም ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡ እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለሆነ ንብረታችሁን ሳይሆን እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡ እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይሆንም›› አሉ፡፡ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡ እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መሆኑን አስረድቶታል፡፡
ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቶአል፡፡ የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል (ትንቢተ ዮናስ)፡፡ ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡
ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ነው፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ሁሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች (አስ.፬፥፲፭-፲፮)፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች (ሉቃ.፪፥፵፮)፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መሆኑን ገልጿል (ሉቃ.፲፫፥፴፪)፡፡
ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡
ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኃጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኃጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ሆነ ‹‹ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ይቅር እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡
ስለሆነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመሆኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡ ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኃጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

 ፦ በዓለ ስባረ አፅም (ጥር 24) ዛሬ ጥር 24 ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ስባረ አፅም (የአፅማቸውን መፍ...
01/02/2026

፦ በዓለ ስባረ አፅም (ጥር 24)

ዛሬ ጥር 24 ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖትን ስባረ አፅም (የአፅማቸውን መፍለስ) በታላቅ ምስጋና እና ድምቀት ታስባለች።

አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በኢትዮጵያ ምድር ወንጌልን ያስፋፉ፣ ገዳማትን ያቆሙና በጸሎት ሕይወታቸው ዓለምን ያስደነቁ የብርሃን መብራት ናቸው።

በተለይም በደብረ አሰቦ (ደብረ ሊባኖስ) ዋሻ ውስጥ ያደረጉት ተጋድሎ ለሰው ልጅ አእምሮ የማይቻል የሚመስል ቢሆንም በእግዚአብሔር ኃይል ግን ተፈጽሟል፦

የ22 ዓመታት ጸሎት፦ በዋሻው ውስጥ ምንም ሳይደገፉ በመቆም ብቻ ለፈጣሪ ምስጋና ሲያቀርቡ ኖረዋል። ከቆይታቸው ብዛትም አንዱ እግራቸው ተሰብሯል።

የ7 ዓመታት ጽናት፦ እግራቸው ከተሰበረ በኋላም ተስፋ ሳይቆርጡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመታት በመቆም ጸሎታቸውን ቀጥለዋል።

የክንፍ ስጦታ፦ ለዚህ ታላቅ ትዕግሥታቸውና ለንጽህናቸው እግዚአብሔር ስድስት ክንፎችን ሰጥቷቸዋል።

ጽድቁ አባታችን ነሐሴ 24 ቀን ቢያርፉም፣ ዛሬ ጥር 24 ቀን የምናስበው "ስባረ አፅማቸውን" ነው። ይህም አፅማቸው ከዐረፉበት ቦታ ወደ ቅዱስ ስፍራ የፈለሰበትንና የእግዚአብሔር ጸጋ የተገለጠበትን ዕለት ነው።

ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ ዛሬም የታመኑ መከታ ናቸው። በፈጣሪ ፊት ባላቸው ባለሟልነትና በተሰጣቸው የማይታጠፍ ቃል ኪዳን ሀገራችንን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቁናል፤ ያማልዱናል።
​በጸሎታቸውና በተጋድሏቸው ያገኙት ረድኤትና በረከት ከእኛ ጋር ለዘላለም ይኖራል።"

​አሜን! የአባታችን ጸሎታቸውና አማላጅነታቸው አይለየን።

✍️​“ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።”  — ሉቃስ 2፥52 የዕለተ ሰንበት ትምህርት ​🌟 መግቢያ፦ ከናዝሬት እስከ ኢየሩሳሌም — የጥበብ መ...
01/02/2026

✍️​“ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።”
— ሉቃስ 2፥52
የዕለተ ሰንበት ትምህርት

​🌟 መግቢያ፦ ከናዝሬት እስከ ኢየሩሳሌም — የጥበብ መንገድ

​✍️​ዛሬ የምንማረው ስለ አንድ ድንቅ ብላቴና ነው። ይህ ብላቴና እንደ ማንኛውም ሕፃን በናዝሬት መንደሮች ውስጥ በድህነት ያደገ፣ ለምድራዊ ወላጆቹ የሚታዘዝ፣ በሥጋው ቁመት የሚጨምር ተራ ሕፃን ይመስል ነበር።

​✍️ ነገር ግን በዚያ በለጋነቱ ውስጥ ዓለማትን የፈጠረ ጥበብ፣ ሰማያትን የዘረጋ ሥልጣንና መላእክትን የሚያዝዝ መለኮታዊ ግርማ ተሸሽጎ ነበር።

​✍️​ይህ ታሪክ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የ12 ዓመት ዕድሜ ታሪክ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የእኛ የሕይወት መጽሐፍ እንጂ። ክርስቶስ በኢየሩሳሌም መቅደስ በመምህራን መካከል ተቀምጦ በጠየቃቸውና በመለሰላቸው ጊዜ፣ ዓለምን ሁሉ "ትሕትና ምንድን ነው? ጥበብስ ከየት ትገኛለች?" ብሎ ሲያስተምር ነበር።
​እርሱ ፍጹም አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ለእኛ ለፍጡራኑ ሲል በሥጋ አድጓል፣ ታዟል፣ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝቷል።

​✍️ ዛሬ በዚህ ትምህርት ውስጥ፦
​ከእረኛዋ ናዝሬት እስከ ቅድስቲቱ ኢየሩሳሌም ያለውን የሥርዓት ጉዞ...
​በመምህራን መካከል የታየውን ያንን መለኮታዊ ብርሃን...
​እኛ ባለ ትዳሮች፣ መነኮሳትና አማኞች በክርስቶስ እድገት ውስጥ የምናገኘውን የሕይወት ካርታ በሰፊው እንመለከታለን።
​በተመስጦ ወደዚህ ምስጢር እንግባ፤ ምክንያቱም ክርስቶስ በማደጉ እኛ እንድንጸና፣ እርሱ በመታዘዙ እኛ ከኃጢአት ባርነት እንድንፈታ መንገድ ሆኖናልና።

​✍️ የሥርዓትና የፍለጋ ጉዞ (ቁጥር 42-45)
​"የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ... ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ"
​12 ዓመት፦ በአይሁድ ሥርዓት አንድ ልጅ "የሕግ ልጅ" የሚሆንበትና ኃላፊነት የሚጀምርበት ዕድሜ ነው።

​✍️ ​ምስጢር፦ ጌታ በሥጋ ፍጹም ሰው መሆኑንና ለሕግ መገዛቱን ያሳያል።
​ማጣቀሻ፦ ገላትያ 4÷4 "ከሴት ተወለደ ከሕግም በታች ተወለደ።"
​"ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር"፦
​ምስጢር፦ ጌታ ከሥጋዊ ቤተሰብ ይልቅ ለመንፈሳዊው ዓላማ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ማሳያ ነው።

​✍️ ​"ከዘመዶቻቸውም... ዘንድ ፈለጉት"፦
​ምስጢር፦ ክርስቶስን በሥጋ ዘመድ ወይም በጎሳ ሳይሆን በመቅደስ (በመንፈስ) መፈለግ እንዳለብን ያስተምራል።
​ምሳሌ፦ ወርቅ ከምድር እንደሚቆፈር፣ ክርስቶስንም ለማግኘት ከዓለማዊ ሐሳብ ወጥቶ በትጋት መፈለግን ይጠይቃል።

​✍️ በመቅደስ የተገኘው መለኮታዊ ጥበብ (ቁጥር 46-50)
​"በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም... አገኙት"
​"በመምህራን መካከል ተቀምጦ"፦
​ምስጢር፦ እርሱ የሕግ መምህር ሆኖ ሳለ፣ ለመምህራኑ ክብር ሲል በተማሪነት ቦታ ተቀመጠ። ይህም ፍጹም ትሕትናን ያሳያል።
​ማጣቀሻ፦ ማቴዎስ 11÷29 "ከእኔ ተማሩ፣ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና።"
​"በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ"፦
​ምስጢር፦ የመለኮት ብርሃን በሥጋዊው መጋረጃ ውስጥ ሆኖ ማብራቱን ያሳያል።

​"በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን?"፦
​ምስጢር፦ "አባቴ" ማለቱ የባሕርይ አምላክነቱን መግለጡ ነው። ዮሴፍ ምድራዊ አሳዳጊው እንጂ አባቱ አለመሆኑን በተዘዋዋሪ አሳወቀ።

​ምሳሌ፦ አንድ አምባሳደር በባዕድ አገር ቢኖርም፣ ንግግሩና ተግባሩ ግን የላከውን ንጉሥ እንደሚገልጥ፣ ክርስቶስም በምድር ሳለ የሰማያዊ አባቱን ክብር ገለጠ።

​✍️ ​ትሕትናና ሁለንተናዊ እድገት (ቁጥር 51-52)
​"ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር"
​"ይታዘዝላቸውም ነበር"፦
​ምስጢር፦ ፍጥረትን ሁሉ የሚገዛው ጌታ፣ ለፍጡራኑ (ለድንግል ማርያምና ለዮሴፍ) መታዘዙ "ሰው የመሆኑ" ትልቁ የትሕትና ምስጢር ነው።

​ማጣቀሻ፦ ፊልጵስዩስ 2÷8 "እስከ ሞት ድረስ የታዘዘ ሆነ።"
​"ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም... ያድግ ነበር"፦
​በጥበብ ማደግ (የነፍስ/የአእምሮ እድገት)፦ መለኮታዊ ጥበቡ ከዕድሜው ጋር አብሮ እየተገለጠ መሄዱ።
​በቁመት ማደግ (የሥጋ እድገት)፦ እንደማንኛውም ሰው በሥጋዊ ተፈጥሮ ማደጉ።

​በሞገስ ማደግ (የመንፈሳዊ/ማኅበራዊ እድገት)፦ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ተወዳጅ መሆኑ።
​ምሳሌ፦ የፀሐይ ብርሃን በማለዳ ደብዛዛ ሆኖ ታይቶ ቀስ በቀስ እያበራ እንደሚሄድ፣ የክርስቶስም ክብሩ በሰውነቱ ውስጥ እያደገ በታየ ቁጥር ለዓለም ብርሃን ሆነ።

​ማጣቀሻ፦ 1ኛ ሳሙኤል 2÷26 "ብላቴናውም ሳሙኤል እያደገ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሞገስን ያገኝ ነበር።"

​✍️ ​የትሕትና ትምህርት፦ ጌታችን የታዘዘው ለሥጋዊ ወላጆቹ ብቻ ሳይሆን፣ ለእኛ የትሕትናን መንገድ ለማሳየት ጭምር ነው።
​የቅድሚያ ትምህርት፦ ለእግዚአብሔር ቤትና ለቃሉ ቅድሚያ መስጠት (Priority) ከምንም ነገር በላይ መሆኑን አሳይቶናል።

​የተመጣጠነ እድገት፦ አማኝ በዕውቀት (ጥበብ)፣ በሥነ ምግባር (ሞገስ) እና በሥርዓት ማደግ እንዳለበት ትልቅ ምስክርነት ነው።

​✍️ ​ለእግዚአብሔር ሥርዓት መገዛት
​"እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ"
​ባለ ትዳሮች፦ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ወደ ቤተክርስቲያን የመሄድ ልማድ ይኑራችሁ። ዮሴፍና ማርያም ሕፃኑን ይዘው እንደወጡ፣ እናንተም ለልጆቻችሁ የጸሎትና የሥርዓት አርአያ ሁኑ።

​✍️ ​መነኮሳት፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሥርዓተ ኦሪት እንደተገዛ፣ መነኩሴም ለገዘተው ብፅዓትና ለገዳሙ ሕግ (ቀኖና) በታማኝነት መገዛት አለበት።
​ሁሉም አማኝ፦ "ከእኔ በቀር ማንም አያውቅም" ከሚል መንፈሳዊ ትዕቢት ወጥቶ ለቤተክርስቲያን ሥርዓት መገዛት።

​✍️ ​ምሳሌ፦ አንድ ወታደር ለጦር ሰራዊቱ ሕግ ካልተገዛ ድል እንደማይነሳ፣ ክርስቲያንም ያለ ሥርዓት መንፈሳዊ ድል አይኖረውም።
​ማጣቀሻ፦ "ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን"
(1 ቆሮ. 14÷40)።

​✍️ በቤተ መቅደስ መገኘትና መማር
​"በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም"
​✍️ ​ባለ ትዳሮች፦ በቤታችሁ ውስጥ የቃለ እግዚአብሔር ውይይት ይኑር። ልጆቻችሁ ጥያቄ ሲጠይቁ በሃይማኖት መልሱላቸው።
​✍️ ​መነኮሳት፦ ቆብ መድፋት ብቻ ሳይሆን፣ ዕለት ዕለት በቃሉ ፊት እንደ ተማሪ መቆየት። ጌታ "ሲሰማቸው" እንደነበረ፣ መነኩሴም የትሕትና ጆሮ ሊኖረው ይገባል።
​ሁሉም አማኝ፦ ከመጠየቅና ከመማር ወደ ኋላ አለማለት። መንፈሳዊ እድገት የሚመጣው በትሕትና በማዳመጥ ነው።

​✍️ ​ምሳሌ፦ ንብ ከአበባ ትቀስማለች፤ አማኝም ከመምህራን እግር ስር ተቀምጦ የሕይወትን ማር ይቀስማል።
​ማጣቀሻ፦ "ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም" (ማቴ. 4÷4)።

​✍️ ለሰማያዊ ጥሪ ቅድሚያ መስጠት
​"በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን?"
​ባለ ትዳሮች፦ ልጆቻችሁ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ሲተጉ አትከልክሏቸው። ከእናንተ ይልቅ የእግዚአብሔር መሆናቸውን እወቁ።
​መነኮሳት፦ ዓለምንና ሥጋ ዘመድን ንቆ "አባቴ" ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ፊት መቅረብ። የቆብ ምስጢር ከዓለም ተለይቶ ለአምላክ መሰጠት ነው።

​✍️ ​ሁሉም አማኝ፦ በምድራዊ ሥራና በሰማያዊ ግዴታ መካከል ምርጫ ሲመጣ፣ የእግዚአብሔርን ቤት (መንፈሳዊ ሕይወትን) ማስቀደም።

​✍️ ​ምሳሌ፦ አንድ ተጓዥ ዋናው ዓላማው መድረሻው እንደሆነ፣ ክርስቲያንም ዋና ዓላማው "የአባቱ ቤት" (መንግሥተ ሰማያት) ነው።

​ማጣቀሻ፦ "አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ" (ማቴ. 6÷33)።

​ ​✍️ ፍጹም ትሕትናና ታዛዥነት
​"ይታዘዝላቸውም ነበር"
​ባለ ትዳሮች፦ በትዳር ውስጥ እርስ በእርስ መሸናነፍና መታዘዝ። ክርስቶስ ለዮሴፍ ከታዘዘ፣ እናንተም ለሰላም ስትሉ ትሕትናን ልበሱ።

​✍️ ​መነኮሳት፦ የታዛዥነት ስልጣን ትልቁ የመነኮሳት መሣሪያ ነው። ያለ ታዛዥነት ቆብ ብቻውን አያድንም።
​ሁሉም አማኝ፦ ለበላይ አካል፣ ለቤተክርስቲያን አባቶችና ለሕሊና ሕግ መታዘዝ።

​✍️ ​ምሳሌ፦ ውኃ ዝቅተኛ ቦታን እንደሚፈልግ፣ የእግዚአብሔር ጸጋም ዝቅ የሚሉትንና የታዘዙትን ይፈልጋል።
​ማጣቀሻ፦ "መታዘዝ ከመሥዋዕት ይበልጣል"
(1 ሳሙ. 15÷22)።

​✍️ ​ሁለንተናዊና ቀጣይነት ያለው እድገት
​"በጥበብና በቁመት በሞገስም... ያድግ ነበር"
​ባለ ትዳሮች፦ ልጆቻችሁን በሥጋ ብቻ ሳይሆን በሞገስ (በመንፈሳዊ ስነ-ምግባር) አሳድጓቸው። ቁመታቸው ሲጨምር ጥበባቸውም አብሮ ይጨምር።

​✍️ ​መነኮሳት፦ በቆብ ዕድሜ መቆጠር ብቻ ሳይሆን፣ በትሩፋትና በምስጢር ማደግ። "ትላንት ከነበርኩበት ዛሬ የት ነኝ?" ብሎ ራስን መመርመር።
​ሁሉም አማኝ፦ በእምነትም፣ በዕውቀትም፣ በሰዎች ዘንድ ባለን አክብሮትም ማደግ። በክርስቲያናዊ ሕይወት ውስጥ "ቆሜያለሁ" ማለት የለም፤ እድገት እንጂ።
​ምሳሌ፦ አንድ ተክል ውኃና ፀሐይ ካገኘ ሁልጊዜ እንደሚያድግ፣ አማኝም በጸሎትና በቅዱስ ቁርባን ካደረ ሁልጊዜ ያብባል።

​ማጣቀሻ፦ "በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ" (2 ጴጥ. 3÷18)።

​✍️ ​ይህ ክፍል ክርስቶስ ለእኛ ያለውን ፍቅርና ትሕትና ብቻ ሳይሆን፣ እኛም በምድር ላይ ስንኖር እንዴት መመላለስ እንዳለብን የሚያሳይ ፍጹም ካርታ ነው። "ክርስቶስ ማደግ ካስፈለገው፣ እኛማ ምን ያህል እድገትና ትጋት ያስፈልገን ይሆን?" አምላካችን እግዚአብሔር በጥበብ በሞገስ ያሳድገን

​✍️ ​“ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤”
በወንጌል አላፍርምና፤
አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም
ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ
የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።
ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና። ሮሜ 1÷14

እግዚአብሔር ሆይ የሚሳንህ ነገር የለምና የራቀውን አቅርበህ የረቀቀውን አጉልተህ እየሰማነው ካለነው መርዶና ሰቀቀን ዕረፍተ ሥጋንና ዕረፍተ ነፍስን አትንሣን

ጸልዩ በእንተ ሰላም
ስለ ሰላም እንጸልይ
ስለ ሀገራችን እንጸልይ
ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ
በጭንቅ በመከራ ስላሉት እንጸልይ
በረሀብ በስደት ስላሉት እንጸልይ
በጽኑ ሕመም ተይዘው ስለሚሰቃዩት እንጸልይ
ስለ ሃይማኖት መሪዎች አባቶቻችን እንጸልይ
ስለ ሀገር መሪዎች እንጸልይ
የሰላም የምህረት የቸርነት ባለቤት እግዚአብሔር ሰላሙን ምህረቱን ቸርነቱን አይንሳን
ጥር 23/5/2018 ✍️
⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️

የቅዱስ ዑራኤል የሹመቱ በዓል በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረር ደብረ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን የመልአኩ የመታሰቢያው በዓል መጋቤ አእላፍ ቀሲስ ብንያም ጎንፋ የሀገረ ስብከቱ...
30/01/2026

የቅዱስ ዑራኤል የሹመቱ በዓል በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረር ደብረ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን የመልአኩ የመታሰቢያው በዓል መጋቤ አእላፍ ቀሲስ ብንያም ጎንፋ የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች በተገኙበት የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል በዓለ ሢመት ተከበረ።
++++++++++++++++++++++++
ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ share like follow ያድርጉ
ቤተሰብ ይሁኑ ለመከታተል ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100024740059321





#ሐረር

የአስተርዕዮ ማርያምን በዓል በበደኖ ማርያም ተከበረ።✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ጥር 21/2018 ዓ.ም(ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት( #ሐረር)⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪በብ...
30/01/2026

የአስተርዕዮ ማርያምን በዓል በበደኖ ማርያም ተከበረ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ጥር 21/2018 ዓ.ም(ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት( #ሐረር)
⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪
በብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ የምሥራቅ ወለጋ እና የሆሮ ጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከት ጳጳስ መልካም ፈቃድ በዛሬው ዕለት ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ክቡር የሀገረ ስብከቱ ዋና ፀኃፊ መጋቤ አዕላፍ ቀሲስ ብንያም ጎንፋ በተገኙበት የሚባረከውን የበደኖ ማርያም መቃኞ ቤት እንዲባረክ በሰጡት አባታዊ መመሪያ መሠረት፥

በቆሞስ አባ ዕዝራ ተስፋዬ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የማሕበራት ማደራጃ ክፍል ሓላፊ መቃኞው ተባርኮ አገልግሎት እንዲጀምር ተደርጓል።

በመቃኞው መባረክ እና በበዓሉ መከበር ደስታቸውን የገለፁ የበደኖ ወረዳ አስተዳደር ርዕስ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዩዬ እና በካቢኔ አባልሎቻቸው ጥምረት ከ100'000 ብር በላይ የተገዛ ሰንጋ በሬ በመለገስ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

የደብሩ ምዕመናን በከፍተኛ ደስታ በዓሉን ያከበሩ ሲሆን መቃኞው እንዲባረከ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቀረበው ጥያቄ የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ፈቃድ ሰጥተው ባራኪ ቆሞስ በመላካቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

በመጨረሻም የበዓሉ ሥነሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ታቦተ ሕጉ ወደ መቃኞው ገብቶ የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።
የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤትና በረከት አይለየን...አሜን!
++++++++++++++++++++++++
ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ share like follow ያድርጉ
ቤተሰብ ይሁኑ ለመከታተል ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100024740059321





#ሐረር

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍቷ መታሰቢያ የአስተርዮ ለማርያም ዓመታዊ በዓለ ንግስ በደማቅ ሥርዓት ተከበረ።✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ጥር 21/2018 ዓ.ም(ምሥ...
29/01/2026

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍቷ መታሰቢያ የአስተርዮ ለማርያም ዓመታዊ በዓለ ንግስ በደማቅ ሥርዓት ተከበረ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ጥር 21/2018 ዓ.ም(ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት( #ሐረር)
⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪
በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በሐረር ደከር ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ክቡር መልአከ ገነት ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሀገረ ስብከቱ የየክፍል ኃላፊዎች ልዩ ልዩ ሠራተኞች ፣ የገዳማት እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤት ወጣት አገልጋዮች በርካታ ምዕመናን እና ምዕመናት በተገኙበት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍቷ መታሰቢያ (የአስተርዮ ለማርያም)በዓለ ንግስ በሐረር ደከር ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በልዩ ድምቀት የተከበረ ሲሆን በደብሩ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣት አገልጋዮች በዓሉን አስመልክቶ ወረብ ቀርቧል የዕለቱን በዓል አስመልክቶ ትምህርተ ወንጌልም የተሰጠ ሲሆን የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው በመጨረሻም በፀሎት የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።የእመቤታችን አማላጅነቷ ፍቅሯ በሁላችን ላይ ይደር...አሜን
+++++++++++++++++++++++
ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ share like follow ያድርጉ
ቤተሰብ ይሁኑ ለመከታተል ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100024740059321





#ሐረር

 #እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት ለጥር አስተርዮ ማርያም በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! የአስተርዮ ማርያም በሐረር ደከር ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን...
29/01/2026

#እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት ለጥር አስተርዮ ማርያም በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! የአስተርዮ ማርያም በሐረር ደከር ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
++++++++++++++++++++++++
ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ share like follow ያድርጉ
ቤተሰብ ይሁኑ ለመከታተል ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100024740059321





#ሐረር

ጥር ፳፩በዓለ አስተርዕዮ ማርያምጥር ሀያ አንድ በዚህች ቀን አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም የእረፍቷ በዓል መታሰቢያ ነው።ያን ጊዜ እመቤታችን በልጇ በጌታችን በፈጣሪ...
29/01/2026

ጥር ፳፩
በዓለ አስተርዕዮ ማርያም

ጥር ሀያ አንድ በዚህች ቀን አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም የእረፍቷ በዓል መታሰቢያ ነው።ያን ጊዜ እመቤታችን በልጇ በጌታችን በፈጣሪያችንና በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ መቃብሩ ቦታ ትፀልይ ነበረ ከዚህም ዓለም እንደምትለይ መንፈስ ቅዱስ ነገራት። ከዚህም በኋላ ከደብረ ዘይት ደናግል መጡ ጌታችን ነግሯቸዋልና እርሷም ነገረቻቸው።

በዚያንም ጊዜ እመቤታችን እንዲህ ብላ ፀለየች፦ "ልጄ ወዳጄ ጌታዬና ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ልመናዬን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚች ሰዓት አምጣው።እንዲሁም ህያዋን እንደሆኑ ሐዋርያትን ሁሉንም ነፍሳቸውንም የለየሀቸውን አምጣቸው አንተ የህያዋንና የሙታን አምላክ ነህና ላንተም ምስጋና ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።"

በዚያንም ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ ከኤፌሶን አገር ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ወደ እመቤታችን ማርያም አደረሰችው ሰገደላትና በፊቷ ቁሞ እንዲህ አላት "ሰላምታ ይገባሻል ጌታችንን ፈጣሪያችንንና መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለድሺው ፀጋን የተመላሽ ደስ ይበልሽ አንቺ ከዚህ ዓለም ተለይተሽ በክብር በምስጋና ወደ ዘለዓለም ህይወት ትሄጃለሽና። ይህም ስሙ ክቡር ምስጉን የሆነ ጌታችንና ፈጣሪያችን ድንቆች ተአምራቶችን በአንቺ ላይ ከገለጠ በኋላ ነው።"

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ይህን በሰማች ጊዜ እጅግ ደስ አላት እግዚአብሔርንም እንዲህ ብላ አመሰገነችው "ፈጣሪዬ ጌታዬ ላንተ ምስጋና ይሁን አንተ የለመንኩህን ሰጥተኸኛልና አሁንም ነፍሴን ተቀብለው ወደ ሰማይ ወደ አንተ ሊያሳርጓት ከሚመጡ መላእክቶችህ ጋር በመምጣትህ የምለምንህን ሁሉ ስጠኝ።"

በዚያንም ጊዜ ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል መጣ "እነሆ አሁን መላእክት ይደርሳሉ ሐዋርያትም ሁሉ ከምድር ዳርቻ በደመና ተጭነው ለሰማይና ለምድር ጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ወደ ሆነች ወደ ቅድስት ድንግል ይደርሳሉ።"

ወዲያውኑ ሁሉም ሐዋርያት የሞቱትም ከመቃብራቸው ተነስተው ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት "አምላካችን ከአንቺ የተወለደ ፀጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። እርሱ ከዚህ ዓለም ለይቶ ቃል ኪዳን እንደሰጠሽ በክብር በምስጋና ከርሱ ጋር ያሳርግሻልና" አሏት።

በዚያንም ጊዜ እመቤታችን በአልጋዋ ላይ ተቀመጠች ሐዋርያትንም እንዲህ አለቻቸው "ፈጣሪዬ ፈጣሪያችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚመጣ እናንተንም እንዳየኋችሁ እንደማየው አሁን አወቅሁ ከዚህ ከስጋዬም ወጥቼ ወደዘለዓለም ህይወት እሄዳለሁ ነገር ግን ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ ከዚህም ዓለም እንደምለይ ከወዴት አወቃችሁ?"

ጴጥሮስና ሐዋርያት ሁሉም "ወዳንቺ እንመጣ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን በደመና ላይም በተጫንን ጊዜ ወዳንቺ እንደ አይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን።" አሏት።

እመቤታችን ማርያምም ይህን ነገር ከሐዋርያት በሰማች ጊዜ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች "ጌታዬና ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈፅሜ አመሰግናለሁ።የእኔን የአገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ ኃይልህን አድርገህልኛልና ከእንግዲህ ወዲያ ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሰግኑኛል።"

ፀሎቷንና ምስጋናዋን ስትጨርስ ሐዋርያትን እንዲህ አለቻቸው "እጣን አምጥታችሁ በማጠን የጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ጥሩት" እነርሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ። በዚያንም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፍት መላእክት አጅበው እያመሰገኑት መጣና አረጋጋት ያዘጋጀላትንም ተድላ ደስታ ነገራት በዚያንም ብዙዎች ድንቆች ተአምራቶች ተደረጉ እውሮች አይተዋልና፣አንካሶች ቀንተው ሄደዋልና ደንቆሮዎች ሰምተዋልና ለምፃሞች ነፁ አጋንንትም ከሰዎች ወጥተው ሄዱ ዲዳዎች ተናገሩ በሽታና ደዌ ያለበት ሁሉ ዳነ እመቤታችን ድንግል ማርያም ወዳለችበት ቤት በቀረቡ ጊዜ ከደዌያቸው ይፈወሳሉና።

ከዚህም በኋላ እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን እንዲህ አለችው "በአየር ውስጥ ተበትነው ከሚኖሩ ከሚያስደነግጡ ግሩማን መላእክት የተነሳ ከእሳት ባህርም እፈራለሁ" ጌታችንም "ከእናንተ ለማንም በአለሁ ላይ ስልጣን የለውም" አላት።

ከስጋዋም የምትለይበት ጊዜ ሲደርስ ሐዋርያትና ደናግል ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ለመኗት እጇን በላያቸው ዘርግታ ባረከቻቸው በዚያንም ጊዜ ጌታችን ንፅህት ነፍሷን ከስጋዋ ለይቶ በመለኮታዊ እጆቹ ይዞ በብርሀን ልብስ አጎናፅፎ ወደ ከፍተኛ መኖሪያ ከእርሱ ጋር አሳረጋት ስጋዋን ግን እንደሚገባ ገንዘው ወደ ጌቴሴማኒ ተሸክመው እንዲወስዷት ሐዋርያትን አዘዛቸው።

ነፍሷ ከስጋዋ ከመውጣቷ በፊት በሰው አንደበት ይህ ነው ተብሎ የማይነገር ብርሀንን እያየች ነበር የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስም "እንግዲህ ስጋሽን ተድላ ወዳለበት ገነት አፈልሳለሁ። ዳግመኛም ስጋሽን ከነፍስሽ ጋር አዋህጄ አስነስቼ መላእክት በውስጡ በፊትሽ ሆነው በሚያመሰግኑበት ተመሳሳይ በሌለው ተድላ ደስታ በአለበት ማደሪያ አኖርሻለሁ" አላት።

እመቤታችንም እንዲህ አለች "አቤቱ በረቀቀ ጥበብህ ይህን ሁሉ የሰራህ አመሰግንሀለሁ ሁለተኛም ልመናዬን ትሰማ ዘንድ እለምንሀለሁ በስሜ ወደ አንተ የሚለምነውን ሁሉ ልመናውን ተቀበለው በመከራም ውስጥ ሆኖ ስሜን ጠርቶ ወዳንተ የሚለምነውን ከመከራው ሁሉ አድነው በሰማይም በምድርም በስራው ላይ ሁሉ አንተ ከሀሊ ነህና መታሰቢያዬን በውስጧ የሚያደርጉትን ቦታ ሁሉ ባርክ በእኔ ስም የሚያቀርቡትን የሁሉንም መስዋእታቸውን ተቀበል።"

ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰላት "የለመንሽኝን ሁሉ አደርግልሻለሁ ደስ ይበልሽ ከእኔ ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ፀጋ ክብር ባለሟልነት ተሰጥቶሻልና ስምሽንም ጠርቶ የሚለምን ሁሉ በዚህም ዓለም በሚመጣውም አለም አይጠፋም።"

እመቤታችንም ካረፈች በኃላ ጌታችን እንዳዘዘ ወደ ጌቴሴማኒ ሊወስዷት ሀዋርያት ገንዘው ተሸከሟት። አይሁድም በሰሙ ጊዜ ስጋዋን ሊያቃጥሉ ወጡ ከእነርሱም አንዱ ከምድር ላይ ይጥላት ዘንድ የእመቤታችንን አልጋዋን ያዘ ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እጆቹን በእሳት ሰይፍ ቀጣውና እጆቹ በአልጋዋ ላይ ተንጠለጠሉ።

ያን ጊዜ በጌታችን አምኖ ወደ እመቤታችን እያለቀሰ እንዲህ ብሎ ለመነ "የእውነተኛ አምላክ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናት አንቺ በእውነት ድንግል የሆንሽ በእኔ ላይ ይቅርታ ታደርጊ ዘንድ እለምንሻለሁ" በሐዋርያትም ልመና እጆቹ ተመልሰው እንደቀድሞው ደኅነኞች ሆኑ።

በቀበሩዋትም ጊዜ ከዚያ ሶስት ቀን ኖሩ እረፍቷም የሆነው እሁድ ቀን በጥር ወር በሀያ አንድ በዚች ቀን ነበረ ጌታችንም ብርሀናውያን መላእክትን ላከ እነርሱም ስጋዋን ከመቃብር ወስደው በገነት ውስጥ በእፀ ህይወት ስር አኖሩዋት።

ሐዋርያ ቶማስ ግን ያን ጊዜ አልነበረም በደመና ላይ ተጭኖ እርሱ ሲመጣ መላእክት ሲያሳርጓት እመቤታችንን አገኛት መላእክትም ለአምላክ እናት ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ና እጅ ንሳ አሉት እርሱም ሰገደላትና ተሳለማት ከእርሷም ተባረከ ከዚህም በኃላ ወደ ሐዋርያት ደረሰ ። እነርሱም እመቤታችንን ማርያምን እንደ አረፈችና እንደ ቀበርዋትም ነገሩት ቶማስም ስጋዋን እስከማይ አላምንም አላቸው።

ስጋዋንም ያሳዩት ዘንድ ወደ መቃብሯ ባደረሱት ጊዜ በመቃብር ውስጥ ስጋዋን አላገኙም ደንግጠውም አደነቁ ያን ጊዜ ከመላእክት ጋር ወደ ሰማይ ስታርግ እመቤታችንን እንዳገኛት ቶማስ ነገራቸው። ሐዋርያትም ይህን በሰሙ ጊዜ የእመቤታችንን እርገቷን ስላላዩ እጅግ አዘኑ ስጋዋን በምድር ውስጥ ይተው ዘንድ እንዳልወደደ መንፈስ ቅዱስ አስገነዘባቸው። ከዚህም በኋላ አንድ ጊዜ ደግሞ እርሷን ያሳያቸው ዘንድ እንዳለው ጌታችን ቃል ኪዳን በማድረግ ተስፋ ሰጣቸው እነርሱም እስከ ነሐሴ አስራ ስድስት በተስፋ ኖሩ።

የእመቤታችንም የእድሜዋ ዘመን ስልሳ አራት ዓመት ነው፤ በአባትና እናቷ ቤት ሶስት ዓመት ከሰባት ወር ፣ በቤተ መቅደስም አስራ ሁለት ዓመት ፣ በዮሴፍም ቤት ሰላሳ አራት ዓመት ከሶስት ወር ፣ ከጌታ እርገት በኃላ በወንጌላዊ ዮሀንስ ቤት አስራ አራት ዓመት ነው።

የእመቤታችን ፍቅሯ፤ በረከቷ ፤ አማላጅነቷ በእኛ በምናምን ክርስቲያኖች ላይ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርብን! የአስራት ሐገሯን ኢትዮጵያን ከፈተና ትጠብቅልን! አሜን!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ እንኳን ለ፹፬ኛ ዓመት የልደት በዓልዎ በሰላምና በጤና አደ...
28/01/2026

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ እንኳን ለ፹፬ኛ ዓመት የልደት በዓልዎ በሰላምና በጤና አደረስዎ !

ቅዱስነትዎ በመንበረ ፕትርክናዎ ለረጅም ዓመታት በሰላምና በጤና እንዲቆዩ ምኞታችን ነው !

የቅዱስነትዎ ቡራኬ አይለየን !
++++++++++++++++++++++++
ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ share like follow ያድርጉ
ቤተሰብ ይሁኑ ለመከታተል ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100024740059321





#ሐረር

የጥምቀት በዓል አከባበር አስመልክቶ ግምገማ ተካሔደ።✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ጥር 19/2018 ዓ.ም(ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት( #ሐረር  #ኢትዮጵያ)⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪...
27/01/2026

የጥምቀት በዓል አከባበር አስመልክቶ ግምገማ ተካሔደ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ጥር 19/2018 ዓ.ም(ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት( #ሐረር #ኢትዮጵያ)
⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪
በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የከተራና የጥምቀት እንዲሁም የቃና ዘገሊላ በዓል አከባበር ዙሪያ በበዓሉ ዓቢይ ኮሚቴ በቀረበው ሪፖርት መሠረት በክቡር የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመልአከ ገነት ቀሲስ ንጋቱ ደሳለኝ ሰብሳቢነት ፣የሀገረ ስብከቱ ዋና ፀሐፊ መጋቤ አዕላፈ ቀሲስ ብንያም ጎንፋ የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች የገዳማት እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች ማኅበረ ካህናት የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቃነ መናብርት የሰንበት ትምህርት ቤት እና የማኅበራት ተወካዮች በተገኙበት በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ የታዩ ሊበረታታ የሚገባው እና ደካማ ጎኖች ግምገማ መርሐ ግብር ተከናወነ።
++++++++++++++++++++++++
ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ share like follow ያድርጉ
ቤተሰብ ይሁኑ ለመከታተል ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100024740059321





#ሐረር

ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ፣ የሆሮ ጉዱሩ እና የምሥራቅ ወለጋ ጳጳስ ለ299 ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ጥር 19/2018 ...
27/01/2026

ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ፣ የሆሮ ጉዱሩ እና የምሥራቅ ወለጋ ጳጳስ ለ299 ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ጥር 19/2018 ዓ.ም(ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት #ኢትዮጵያ
⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪⛪
ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ፣ የሆሮ ጉዱሩ እና የምሥራቅ ወለጋ ጳጳስ ትምህርታቸውን በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ሲከታተሉ ለቆዩ ለ271 ደቀ መዛሙርት የዲቁና ለ22 ዲያቆናት የቅስና ሥልጣነ ክህነት እንዲሁም ለ6 መነኮሳት ቁምስና ሰጥተዋል።

ብፁዕነታቸው በቅርቡ ወደተመደቡባቸው ሁለቱ የወለጋ ክፍላተ ሀገራት ተደጋጋሚ ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ ቡራኬ፣ መመሪያ እና አቅጣጫ በመስጠት አህጉረ ስብከቱን እያገለገሉ እንደሚገኙ ይታወቃል።

መረጃውን ለማጠናከር የምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከትን የፌስቡክ ገጽ ተጠቅመናል።
+++++++++++++++++++++++
ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ share like follow ያድርጉ
ቤተሰብ ይሁኑ ለመከታተል ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100024740059321





#ሐረር

Address

Harar
7513

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የምስራቅ ሐረርጌ ሐገረ ስብከት ጽ/ቤት Eastern Hararge Diocese secretary office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የምስራቅ ሐረርጌ ሐገረ ስብከት ጽ/ቤት Eastern Hararge Diocese secretary office:

Shortcuts

Share