Yeqedemechw Tewahdo

Yeqedemechw Tewahdo የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃል?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሰባቱን ሚስጥራተ ቤተክርስትያን ትቀበላለች:: እርስዎስ ስባቱንም ሚስጥራተ ቤተክርስትያን ማለትም ምሥጢረ ጥምቀትን ምሥጢረ ሜሮንን ምሥጢረ ቁርባንን ምሥጢረ ክህነትን ምሥጢረ ተክሊልን ምሥጢረ ንስሓና ምሥጢረ ቀንዲልን ሙሉ በሙሉ ይቀበላሉ ??
1 ምሥጢረ ጥምቀት
ጥምቀት ማለት ከውሃ ውስጥ መጥለቅ መነከር መጠመቅ ማለት ነው። ጥምቀት አጠመቀ ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን በገቢር መንከር መድፈቅ፣ አካልን ውሃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው ። ጥምቀት ሌሎችን ሚስጢራተ ቤተክርስቲያን ለመሳተፍ የቤተክርስቲያን አባል ለመሆን የመጀመሪያው መግቢያ በር ነው።
እግዚአብሔር ማንኛውንም ነገር ሲሰራ ትንቢት

ያስነግራል ወይም ምሳሌ ያስቀድማል። በብሉይ ኪዳንም ለሀዲስ ኪዳን የተመሰሉ ምሳሌዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ ስለጥምቀት የተመሰሉ ምሳሌዎች
• ኖህ ከጥፋት ወሃ ይድን ዘንድ መርከብ ሰራ ስለዚህ እርሱም ቤተሰቦቹም ወደ መርከቡ ገብተው የሰው ዘር ሁሉ ሲጠፋ ስምንት ሰዎች ብቻ ዳኑ። ይህም የጥምቀት ምሳሌ ነው። ኖህና ቤተሰቦቹ የምእመናን ፣ ባህሩ የጥምቀት ፣ መርከቡ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናቸው። ከመርከብ ወጭ የዳነ ሰው እንደሌለ በጥምቀት በር ያልገባ እና በቤተክርስቲያን ወስጥ ያልተገኘ አሁንም ድኅነት የለውም ሊኖረው አይችልም። ዘፍ 6፣1422 1ኛ ጴጥ 3፣20-21 ።
• ግዝረተ አብርሃም የጥምቀት ምሳሌ ነው (ሮሜ 6፣18 ኤፌ 4፣18 ቆላ 2፣19-21 ቆላ 2፣9-12 ።
• እስራኤላውያን ባህረ ኤርትራን መሻገራቸው ዘፍ 14፣14 -22 1ኛቆሮ 10፣1-2።
• ኢዮብ በዮርዳኖስ ወንዝ መታጠቡ
• ንዕማን የተባለው የሶሪያ ንጉሥ በዮርዳኖስ ወንዝ ታጥቦ ከለምጽ በሽታ መዳኑ 2ኛ ነገ 5፣1-16።
የጥምቀት አስፈላጊነት
• ድህነት የሚገኘው በጥምቀት ነው በእምነት ብቻ አይደለም ማር፣10፣16 ሐዋ 2፣37 ሐዋ 8 ፣37።
• በጥምቀት ዳግም ልደት ይገኛል(ዮሐ3፣5-8 ዮሐ 3.3)
• ሥርየተ ኃጢአት ይገኛል ( ሐዋ 9፣15-16)
• የክርስቶስ የሞቱና የትንሳኤው ተባባሪ መሆን ነው (ሮሚእ 6፣3-8)
• አዲስ ህይወት ይገኛል (ሮሜ 6፣4)
• የቤተክርስትያን አባል ለመሆን
የጥምቀት ስርዓት በ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ወንድ በተወለደ በአርባ ቀኑ ሴት በተወለደች በሰማንያ ቀኗ የጥምቀት ስርአት ይፈጸምላቸዋል የህጽኑ ጤንነት የሚያሰጋ ከሆነ ከዚህ ቀን በፊት ሊፈጸም ይችላል። በችግርና በሌላ ምክንያት ከተጠቀሰው ቀን ቢዘገይ ቤ/ክ የመጡትን ወደኃላ አትመልስም ታጠምቃለች።በ 40 እና በ80 ቀን የሆነበት ምክንያት አዳም በተፈጠረ በ40 ቀን ሔዋን በተፈጠረች በ80 ቀን ገነት እንዲገቡ ስለተፈቀደላቸው ነው (ኩፋ 4፣9)። እንዲሁም በኦሪት ይደረግ የነበረው ሥርዓት ለሃዲስ ምሳሌ በመሆኑ(ዘሌ12፣12 1-8. ሉቃ 2፣22)። ልጆችም እንደየጾታቸው በ 40 እና በ 80 ቀን የጸጋ ልጅነት ያገኛሉና ነው።(ዘሌ 12፣1-8)።
ወላጆች ተጠማቂውን ህጻን ይዘው ወደ ቢተክርስቲያን ይመጣሉ። ቄሱ ውሃውን በብረት(በርሜል) አድርጎ ስርአተ ጸሎቱን ይጀምራል፣ መጸሀፈ ክርስትና ይደግማል። በጸሎቱ መግቢያ ላይ የክርስትና እናት ወይም አባት ለመሆን የመጡ የህጻኑን አውራ ጣት ይዘው ተጠማቂውን ሊለው የሚገባውን ሶስት ጊዚ “እክህደከ ሰይጣን” እያሉ ያወግዛሉ ትርጉሙም ሰይጣንን ክጄዋለሁ ማለት ነው። ስርዓተ ጸሎቱ ተገባዶ ዲያቆኑ “ጸልዩ በእንተ ዛቲ ..” የሚለውን ጸሎት በዜማ ካዜመ በኋላ ጸሎተ ሃይማኖት ይደገማል። የሃይማኖት ጸሎትን ተጠማቂው፣ ተጠማቂው ህፃን ከሆነ የክርስትና አባት ወይም እናት የህጻኑን አውራ ጣት በመያዝ ሰለ ህጻኑ ፈንታ ይደግማሉ።
ተጠማቂው በቅዱሳን ስም ለቤተክርስትያን ከተሰጠ በእለቱ የሚያገለግለው ዲያቆን ጸሎተ ሃይማኖትን እየደገመ የህጻኑን አውራ ጣት ይይዛል።ይህ ሲፈጸም ይተጠማቂው ልብስ ይወልቃል በምዕራብ ፣ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምስራቅ እሰግድ ለአብ እሰግድ ለወልድ እሰግድ ለመንፈስ ቅዱስ እያለ ዲያቆኑ ተጠማቂውን በአራት አቅጣጫ እያሰገደ ያዞራል። በዚህ የስግደት ኡደት ጊዜ ካህኑም የተጠማቂውን ግንባር በመስቀል እያሻሸ “ስምከ ይኩን እገሌ” እያለ ስም በመሰየም ይባርከዋል።
ይህም ሲፈጸም ውሃውን ብሩክ ብሎ ባርኮ “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ውልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ካለ በኋላ “አጠምቀከ በአብ አጠምቀከ በወልድ አጠምከከ በመንፈስ ቅዱስ እያለ ሶስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያረገ ካህኑ ያጠምቃል። የክርስትና ስም አወጣጥም በ/ኢ/ኦ/ቤ/ክ ካህን የሚሰየመውን የእለት በአልን ምክንያት በማድረግ ነው። ለምሳሌ የጌታችን ፣የመቤታችን፣ እለት ከሆነ ገብረ መድኅን ኃ/ማርያም…የቅዱሳን መላእክት የፃድቃን ሰማእታት ከሆነ ወ/ሚካኤል ኃ/ጊዮርጊስ ወ.ዘ.ተ በሚል ስያሜ ይሰጠዋል።
ስያሜው ጥምቀት ሲያበቃ ካህኑ (ዲያቆኑ) ለክርስትና እናቱ(አባቱ) ያስረክባሉ። ከልጅህ (ከልጅሽ) የማትለየውና በክርስትያናዊ ምግባርና በሐይማኖት የምታሳድገው የቃል ኪዳን ልጅህ (ልጅሽ) ነው እያለ ካህኑ ይመክረዋል። እርሱም እሺ እያለ ይቀበላል በዚህ ጊዜ 36 ቦታዎች ሜሮን ይቀባል ይህብረት ቀለማት ያለው ፈትል ተገምዶ በአንገቱ ላይ ይታሰራል ይህ በግእዝ ማዕተብ በአማርኛ ቡራኬ(ስጦታ) ይባላል። ቀለሙ ሶስት ዓይነት ነው። ነጭ ቀይ፣ ቢጫ፣ (ነጭ የአብ ቀይ የወልድ ቢጫ የመንፈስ ቅዱስ ሶስት የመሆኑ ምስጢር ስላሴ አንድ ሆኖ መገመዱ የአንድ አምላክ መሳሌ ነው። ህፃኑ ልብሱን ከመልበሱ በፊት ቄሱ ህፃኑን በሁለት እጃቸው ከፍ አርገው ይይዙታል “ንሳ መንፈስ ቅዱስ” እየተባለ እፍ ይባልበታል። ከዚህ በኋላ ተጠማቂው ሜሮን ተቀብቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ይቆርባል የጥምቀቱ ስርዐት የሚፈጸውመው ተጠማቂው ሲቆርብ ብቻ ነው። አለበለዚያ ጥምቀቱ ሙሉ አይሆንም ምክንያቱም የጥምቀቱ ማህተብ ስጋወ ደሙ ነው።

11/01/2026

በቤተ ልሄም ተወልደ መድኃኔዓለም

11/01/2026

ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ በዜማ...

18/11/2024
03/11/2024

ፍሬ እንድታፈሩ በኔ ላይ ቁሙ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

11/08/2024
21/03/2024

80 መፅሀፍ ቅዱሳዊ ስምች እና ትርጉማቸው…!!!

እስቲ ሁላችንም ሼር በማድረግ ለልጆቻቸው ስም ማውጣት ለተቸገሩ እህት እና ወንድምቻችን ግንዛቤን እንፍጠር

1 ዲቦራ፦ንብ ማለት ነው።
2 ዮዳሔ፦ እግዚአብሔር ያውቃል ማለት ነው።
3 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነው።
4 ኑኃሚን፦ደስታየ ማለት ነው።
5 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው።
6 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል ማለት ነው።
7 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል ማለይ ነው
8 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
9 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ ማለት ነው።
10 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል ማለት ነው።
11 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል ማለት ነው።
12 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር ማለት ነው
13 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
14 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው! ማለት ነው።
15 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል ማለት ነው።
16 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው።
17 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
18 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ ማለት ነው።
19 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ ማለት ነው።
20 ሣራ፦ልዕልት ማለት ነው።
21 ስምዖን፦ሰማ ማለት ነው።
22 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ ማለት ነው።
23 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
24 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
25 አልዓዛር፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
26 አስቴር፦ኮከብ ማለት ነው፣
27 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ ማለት ነው።
28 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው ማለት ነው።
29 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ነው።
30 አብራም፦ታላቅ አባት ማለት ነው።
31 አብርሃም፦የብዙዎች አባት ማለት ነው
32 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው ማለት ነው።
33 አክዐብ፦የአባት ወንድም ማለት ነው።
34 ባሮክ፦ቡሩክ ማለት ነው።
35 አዳም፦መልካሙ ማለት ነው።
36 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
37 ባርቅ፦መብረቅ ማለት ነው።
38 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው።
39 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል ማለት ነው።
40 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ ማለት ነው።
41 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል ማለት ነው።
42 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት ማለት ነው።
43 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
44 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ ማለት ነው።
45 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው ማለት ነው።
46 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው ማለት ነው።
47 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል ማለት ነው።
48 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው ማለት ነው።
49 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው ማለት ነው።
50 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል ማለት ነው።
51 ኤዶም፦ቀይ ማለት ነው
52 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል ማለት ነው።
53 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው ማለት ነው።
54 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ ማለት ነው።
55 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ ማለት ነው።
56 ሰሎሞን፦ሰላማዊ ማለት ነው።
57 ኬብሮን፦ኅብረት ማለት ነው
58 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል ማለት ነው።
59 ኤደን፦ደስታ ማለት ነው።
60 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው ማለት ነው።
61 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል ማለት ነው።
62 ይሳኮር፦ ዋጋዬ ማለት ነው
63 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ ማለት ነው።
64 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው ማለት ነው።
65 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው።
66 ዮሴፍ፦ይጨምር ማለት ነው።
67 ዮናስ፦ርግብ ማለት ነው።
68 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል ማለት ነው።
69 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል ማለት ነው።
70 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው ማለት ነው።
71 ምናሴ ማስረሻ ማለት ነው
72 ዮፍታሔ እግዚአብሔር ይከፍታል ማለት ነው
73 ሩሃማ ምህረት ማለት ነው
74 ዳንኤል እግዚአብሔር ፈራጅ ነው ማለት ነው
75 ጎድልያስ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው
76 ጽዮን አምባ ማለት ነው
77 ጳዉሎስ ብርሃን ማለት ነው
78 ሴት ምትክ ማለት ነው
79 ጴጥሮስ አለት ማለት ነው
80 ሄኖክ ታደሰ ማለት ነው

በትረማርያም አበባዉ
ምንጭ፦የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት

Address

Gonder

Telephone

+12067753078

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeqedemechw Tewahdo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Yeqedemechw Tewahdo:

Share