የአባረጋይ አርባዕቱ እንስሳ ወአቡነ አረጋዊ ልጆች

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • የአባረጋይ አርባዕቱ እንስሳ ወአቡነ አረጋዊ ልጆች

የአባረጋይ አርባዕቱ እንስሳ ወአቡነ አረጋዊ ልጆች Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የአባረጋይ አርባዕቱ እንስሳ ወአቡነ አረጋዊ ልጆች, Religious organisation, ደቡብ ጎንደር ደብረ ታቦር, Gondar.

17/11/2025
17/11/2024

ኪሩቤል ሰረገላቲሁ ለእግዚአብሔር ስቡህ
ጸግውኒ አጋእዝትዬ እም ጸጋክሙ ብዙህ፡

እግዚአብሔር አምላክ በአንድነትና ሦስነት ከብሮ ባህሪውን ባህሪው እያመሰገነ ሲኖር ክብሩ እና ምስጋናው በባህሪው ተወስኖ እንዳይቀር፤ ክብሩ፣ ከሀሊነቱ እና ምስጋናው ይገለጥ ዘንድ ፍጥረትን መፍጠር አሰበ፡፡ አስቦም አልቀረ ከእሁድ ጀምሮ በስድስቱ ቀናት በየወገን በየወገኑ ብዙው አንድ እየተባለ ሲቆጠር ሃያ ሁለት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ በሰባተኛው ቀን ከስራው ሁሉ አረፈ፡፡

ፍጥረታትም ከተፈጠሩበት አላማ አንጻር በሁለት ይከፈላሉ፡፡ አነሱም 1. ለአንክሮ ለተዘክሮ (ፍጥረታቱን እያየን የፈጣሪን መኖርና ሁሉን ቻይነት እንድናስታውስ የተፈጠሩ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ክብሩን ለመውረስ ስሙን ለመቀደስ የተፈጠሩ ናቸው( ሰው እና መላዕክት)፡፡

መላዕክት የተፈጠሩት በመጀመሪያው የፍጥረት ቀን በዕለተ እሁድ ሲሆን እነርሱም ልዩ ልዩ ክብርና አገልግሎት ስምም አላቸው፡፡ መላዕክት በቁጥር እጅግ ብዙ እልፍ አዕላፋት ሲሆኑ በነገድ ግን መቶ እንደሆኑ ጌታችን በወንጌል በምሳሌ አስተምሮናል፡፡ ‹‹ እነሆ መቶ በጎች ያሉት አንድ ሰው ነበረ ከመቶዎቹ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጠፋውን በጉን ሊፈልግ ሔደ ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፡፡›› ሉቃ 15፡-4 የሚለው ምሳሌ ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላዕክት ትቶ በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ርቆ የነበረውን የሰው ልጅ ፍለጋ መምጣቱን የሚያሳይ ነው፡፡ በስም ደግሞ አስሩን ነገድ በአንድ ላይ አጋዕዝት፣ ኪሩቤል፣ ሱራፌል፣ ኃይላት፣ አርባብ፣ መናብርት፣ ስልጣናት፣ መኳንንት፣ ሊቃናት እና መላዕክት ይባላሉ፡፡ ለእያንዳንዳቸውም አለቃ ያላቸው ሲሆን በኢዮር በራማ እና በኤረር በሦስቱ ሰማያት አስፍሮቸዋል፡፡1ኛ ጴጥ 3፤22 በዚህ ጥቅስ ሦስቱ ነገድ ብቻ የተጠሩ ቢሁንም ግን ከሶስቱ ሰማያት አንድ አንድ ተጠቅሷል፡፡ ኃይላት ከኢዮር፣ ስልጣናት ከራማ፣ መላእክት ከኤረር ናቸው፡፡

ኪሩቤል አርባዕቱ እንስሳ

እነዚህ መላዕክት ከፍጥረታት ሁሉ ለየት ያለ ክብርና አፈጣጠር ያላቸው ሲሆን ዋናው ስራቸውም የእግዚአብሔርን ዙፋን መሸከም ነው፡፡ ራዕ 4፤6-8 መሸከምስ አይሸከሙትም እርሱ ይሸከማቸዋል ማዕረገ መላዕክትን ጫማ አድርጎ ይኖራል እንጅ ብለው አባቶቻችን ይተረጉሙታል፡፡ ስድስት ክንፍ እና ብዙ ዓይኖች ያሏቸው ሲሆን በሁለት ክንፋቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ፣ በሁለት ክንፋቸው እግራቸውን ይሸፍናሉ፡፡ በሁለት ክንፋቸው ከጽንፍ እስከጽንፍ ይበርራሉ፡፡ የእግዚአብሐርን እሳተ መለኮትነት የባህርይውን ጥልቀትና ርቀት ለማጠየቅ ነው፡፡

ለምን አራት እንስሳ ተባሉ ?
ራዕ 4፤7 ‹‹ፊተኛው እንስሳ አንበሳ ይመስላል፣ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃ ይመስላል፣ ሦስተኛውም እንስሳ እንደሰው መልክ ነበረው አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል፡፡›› ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳን መላዕክት ጸወርተ መንበሩ ለእግዚአብሔር ለፍጥረተ ዓለሙ ሁሉ ምህረትን የሚለምኑ፣ ለሰው በሰው የተመሰለው፣ ለእንስሳት በጥጃ የተመሰለው ለአራዊት በአንበሳ የተመሰለው፣ ለአዕዋፋት ደግሞ በንስር የተመሰለው መላክ ይለምናሉ፡፡ ስለዚህም እለዚህ መላዕክት ለእግዚአብሄር ቅርብ የሆኑ ለፍጥረተ አለሙ በሙሉ የቆሙ ቅዱሳን መላዕክት ናቸው፡፡ ለአርባዕቱ እንስሳ ችግሩን ተናግሮ የማይሰማለት የለም፡፡ በጠም የሚገርመኝ ሰዎች ከብቶቻቸው ሲታመሙባቸው ወደሀኪም አይሄዱም በቀጥታ የአርባዕቱ እንስሳን ጠበል ያጠጧቸዋል፣ይ ረጯቿል ደግሞም ይድናሉ፡፡ እኔም ለአርባዕቱ እንስሳ ለግሬ ያጣሁት አንድም ነገር የለም፡፡
በቤተክርስቲያናችን የቅድስት ሥላሴ ስዕል ሲሳል ሁሉጊዜ አርባዕቱ እንስሳ አይለዩም፡፡
ዓመታዊ በዓላቸው የሚከበረው ህዳር 8 ቀን ሲሆን በደብራችን ደብረ ትጉኃን አርባዕቱ እንስሳ ቤ/ክ በደማቅ ሁኔታ ስለሚከበር መጥታችሁ የበረከቱ ተሳታፊዎች እንትሆኑ በአክብሮት ተጋባዛችኋል፡፡
ገጸ ሰብ ወገጸ እንስሰ ገጸ ንስር ወገጸ አንበሳ
ሰዓሉ ለነ ፬ቱ እንስሳ /2 ጊዜ/

28/02/2022

ኢሳይያስ 58
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
² ነገር ግን ዕለት ዕለት ይሹኛል መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ፤ ጽድቅን እንዳደረጉ የአምላካቸውንም ፍርድ እንዳልተዉ ሕዝብ እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ።
³ ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅህም? ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
⁴ እነሆ፥ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
⁵ እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
⁶ እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የበደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፥ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፥ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፥ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
⁷ እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፥ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፥ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
⁸ የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፥ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፥ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፥ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።
⁹ የዚያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፥

03/01/2022

ውድ የጻድቁ አቡነ አረጋዊ እና የትጉኃን መላዕክት አርባዕቱ እንስሳ ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ፡፡
አዲስ ለተመረጠው የሰበካ ጉባዔ አባላት በቅድሚያ እንኳን ለዚህ የተቀደሰ ጥሪ እግዚአብሔር አበቃችሁ እያልኩ የአገልግሎት ዘመናችሁ የተሳካና የተቃና እንዲሆን ልባዊ ምኞቴን እየገለጽኩ ሁላችንም በምታዝዙን ሁሉ ከጎናችሁ ለመቆምና የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን፡፡ የዚህ ግሩፕ አባላትም ላይክ በማድረግ አጋርነታቸውን ይገልጹላችኋል፡፡
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን፡፡

እንኳን አደረሳችሁ
16/11/2020

እንኳን አደረሳችሁ

ኪሩቤል ሰረገላቲሁ ለእግዚአብሔር ስቡህ
ጸግውኒ አጋእዝትዬ እም ጸጋክሙ ብዙህ፡

እግዚአብሔር አምላክ በአንድነትና ሦስነት ከብሮ ባህሪውን ባህሪው እያመሰገነ ሲኖር ክብሩ እና ምስጋናው በባህሪው ተወስኖ እንዳይቀር፤ ክብሩ፣ ከሀሊነቱ እና ምስጋናው ይገለጥ ዘንድ ፍጥረትን መፍጠር አሰበ፡፡ አስቦም አልቀረ ከእሁድ ጀምሮ በስድስቱ ቀናት በየወገን በየወገኑ ብዙው አንድ እየተባለ ሲቆጠር ሃያ ሁለት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ በሰባተኛው ቀን ከስራው ሁሉ አረፈ፡፡

ፍጥረታትም ከተፈጠሩበት አላማ አንጻር በሁለት ይከፈላሉ፡፡ አነሱም 1. ለአንክሮ ለተዘክሮ (ፍጥረታቱን እያየን የፈጣሪን መኖርና ሁሉን ቻይነት እንድናስታውስ የተፈጠሩ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ ክብሩን ለመውረስ ስሙን ለመቀደስ የተፈጠሩ ናቸው( ሰው እና መላዕክት)፡፡

መላዕክት የተፈጠሩት በመጀመሪያው የፍጥረት ቀን በዕለተ እሁድ ሲሆን እነርሱም ልዩ ልዩ ክብርና አገልግሎት ስምም አላቸው፡፡ መላዕክት በቁጥር እጅግ ብዙ እልፍ አዕላፋት ሲሆኑ በነገድ ግን መቶ እንደሆኑ ጌታችን በወንጌል በምሳሌ አስተምሮናል፡፡ ‹‹ እነሆ መቶ በጎች ያሉት አንድ ሰው ነበረ ከመቶዎቹ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጠፋውን በጉን ሊፈልግ ሔደ ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፡፡›› ሉቃ 15፡-4 የሚለው ምሳሌ ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠና ዘጠኙን ነገደ መላዕክት ትቶ በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር ርቆ የነበረውን የሰው ልጅ ፍለጋ መምጣቱን የሚያሳይ ነው፡፡ በስም ደግሞ አስሩን ነገድ በአንድ ላይ አጋዕዝት፣ ኪሩቤል፣ ሱራፌል፣ ኃይላት፣ አርባብ፣ መናብርት፣ ስልጣናት፣ መኳንንት፣ ሊቃናት እና መላዕክት ይባላሉ፡፡ ለእያንዳንዳቸውም አለቃ ያላቸው ሲሆን በኢዮር በራማ እና በኤረር በሦስቱ ሰማያት አስፍሮቸዋል፡፡1ኛ ጴጥ 3፤22 በዚህ ጥቅስ ሦስቱ ነገድ ብቻ የተጠሩ ቢሁንም ግን ከሶስቱ ሰማያት አንድ አንድ ተጠቅሷል፡፡ ኃይላት ከኢዮር፣ ስልጣናት ከራማ፣ መላእክት ከኤረር ናቸው፡፡

ኪሩቤል አርባዕቱ እንስሳ

እነዚህ መላዕክት ከፍጥረታት ሁሉ ለየት ያለ ክብርና አፈጣጠር ያላቸው ሲሆን ዋናው ስራቸውም የእግዚአብሔርን ዙፋን መሸከም ነው፡፡ ራዕ 4፤6-8 መሸከምስ አይሸከሙትም እርሱ ይሸከማቸዋል ማዕረገ መላዕክትን ጫማ አድርጎ ይኖራል እንጅ ብለው አባቶቻችን ይተረጉሙታል፡፡ ስድስት ክንፍ እና ብዙ ዓይኖች ያሏቸው ሲሆን በሁለት ክንፋቸው ፊታቸውን ይሸፍናሉ፣ በሁለት ክንፋቸው እግራቸውን ይሸፍናሉ፡፡ በሁለት ክንፋቸው ከጽንፍ እስከጽንፍ ይበርራሉ፡፡ የእግዚአብሐርን እሳተ መለኮትነት የባህርይውን ጥልቀትና ርቀት ለማጠየቅ ነው፡፡

ለምን አራት እንስሳ ተባሉ ?
ራዕ 4፤7 ‹‹ፊተኛው እንስሳ አንበሳ ይመስላል፣ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃ ይመስላል፣ ሦስተኛውም እንስሳ እንደሰው መልክ ነበረው አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል፡፡›› ስለዚህ እነዚህ ቅዱሳን መላዕክት ጸወርተ መንበሩ ለእግዚአብሔር ለፍጥረተ ዓለሙ ሁሉ ምህረትን የሚለምኑ፣ ለሰው በሰው የተመሰለው፣ ለእንስሳት በጥጃ የተመሰለው ለአራዊት በአንበሳ የተመሰለው፣ ለአዕዋፋት ደግሞ በንስር የተመሰለው መላክ ይለምናሉ፡፡ ስለዚህም እለዚህ መላዕክት ለእግዚአብሄር ቅርብ የሆኑ ለፍጥረተ አለሙ በሙሉ የቆሙ ቅዱሳን መላዕክት ናቸው፡፡ ለአርባዕቱ እንስሳ ችግሩን ተናግሮ የማይሰማለት የለም፡፡ በጠም የሚገርመኝ ሰዎች ከብቶቻቸው ሲታመሙባቸው ወደሀኪም አይሄዱም በቀጥታ የአርባዕቱ እንስሳን ጠበል ያጠጧቸዋል፣ይ ረጯቿል ደግሞም ይድናሉ፡፡ እኔም ለአርባዕቱ እንስሳ ለግሬ ያጣሁት አንድም ነገር የለም፡፡
በቤተክርስቲያናችን የቅድስት ሥላሴ ስዕል ሲሳል ሁሉጊዜ አርባዕቱ እንስሳ አይለዩም፡፡
ዓመታዊ በዓላቸው የሚከበረው ህዳር 8 ቀን ሲሆን በደብራችን ደብረ ትጉኃን አርባዕቱ እንስሳ ቤ/ክ በደማቅ ሁኔታ ስለሚከበር መጥታችሁ የበረከቱ ተሳታፊዎች እንትሆኑ በአክብሮት ተጋባዛችኋል፡፡
ገጸ ሰብ ወገጸ እንስሰ ገጸ ንስር ወገጸ አንበሳ
ሰዓሉ ለነ ፬ቱ እንስሳ /2 ጊዜ/

በስመ አብ ወወልድ  ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አመ ሰሙኑ ለኅዳር በዛቲ ዕለት ኮነ በዓሎሙ ለአርባዕቱ እንስሳ እለ አልቦሙ ስጋ፡፡ ወ እሉ እሙንቱ ፀዋርያነ መንበሩ በከመ ኮነ ስምዓ በእን...
17/11/2018

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አመ ሰሙኑ ለኅዳር በዛቲ ዕለት ኮነ በዓሎሙ ለአርባዕቱ እንስሳ እለ አልቦሙ ስጋ፡፡ ወ እሉ እሙንቱ ፀዋርያነ መንበሩ በከመ ኮነ ስምዓ በእንቲአሆሙ ዮሐንስ ወንጌላዊ፡፡

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ስምንት በዚህች ቀን ስጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ፡፡

እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሰረገላዎቹ ናቸው፡፡ ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ፡ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባህር አለ፣ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ፣ በፊትም በኋላም ዐይንን የተሞሉ ናቸው፡፡

የፊተኛው አንበሳ ይመስላል፡ሁለተኛውም ላም ይመስላል፣ ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል፣ አራተናውም የሚበር አሞራ ይመስላል፡፡
የእሊህም የአራቱ እንስሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው፣ ሁለንተናቸውም አይኖችን የተሞሉ ናቸው፣ የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑ ክቡር ልዩ ነው፣ እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም፡፡
ሁለተኛም እርሳቸውን ኢሳይያስ እንዲህ አለ፤ ከዚህም በኋላ ንጉሱ ኦዝያን በሞተ ጊዚ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ብርሃኒም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቆመው አየሁት፡፡

የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው፣ በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ፣ በሁለቱ ግንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ፡፡
እንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ፡፡
ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ፣ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ፡፡

ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ትልቅ ነፋስ ሲመጣ አየሁ፣ ታላቅ ደመና አለ፣ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል፡፡ በደመናውም መካከል ባለ እሳቱ ውስጥ እንደ አራት እራስ አሞራ የሚመስል አለ፣ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ፡፡

መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊት አራት ነው፡፡ እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው፡፡ ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው፣ ከእሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል፡፡

ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ፤ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላዕክትን ድምጽ ከእንስሶቹም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ፣ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሏቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው፡፡

ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን ባለጸግነትን፣ ጥበብን ጽናትን መንግስትን ክብርን ጌትነትን ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ፡፡
በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባህር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥርት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለም ይገባዋል አሉ፡፡ በእውነት ይገባዋል፡፡

እለህም አራት እንስሶች አሜን ይላሉ፡፡እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ፡፡
ስለ ልዕልናቸው እና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንስሳ ከብሉይና ከሀዲስ ብዙ መጽሐፍት መስክረዋል፣ መሐሪኛ ይቅር ባይ እርዚአብሔርም ስለሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው፡፡ ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል፣ ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል፣ ገጸ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል፣ ገጸ ንስር ስለ አዕዋፍ ይለምናል፡፡ ከሰማይ ሰራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና፡፡

ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚህችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተክርስቲያን መምህራን አዘዙ፣ እነረሱም ስለሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ኪሩቤል አማላጅነት ይማረን፣ በረከታቸውም ለዘላለሙ ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን፡፡

ሰላም ለክሙ ኪሩባውያን አፍራሱ፡፡ ለመሐይምን ወጻድቅ እንተ ወርቅ አክሊለ ርእሱ ኀበ ዝ አምላክ ዘትጸውርዎ በአትሮንሱ፡፡ ለእለ ጌገዩ ወእለሂ አበሱ፡፡ ሰዓሉ መድኃኒተ ወምህረተ ኅሡ፡፡
''ስንክሳር ዘኅዳር ስምንት ቀን''
ውድ ኦርቶዶክሳውያን እንኳን ለአርባዕቱ እንስሳ ኪሩቤል ዐመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ዛሬ በደብራችን መካነትጉኃን ዐርባእቱ እንስሳ ቤተክርስቲያ (ደብረ ታቦር) በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡

ኅዳር ስምንት ቀን 2011 ዓ.ም

+++ ጥቅምት 14 የአባታችን አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ በዓል! +++ ኑ የጻድቁ አባታችን በዓል በጋራ እናክብር እንኳን አደረሰን!የአባታችን የጻድቁ አቡነ አረጋዊ አጭር የህይወት ታሪክ======...
23/10/2017

+++ ጥቅምት 14 የአባታችን አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ በዓል! +++ ኑ የጻድቁ አባታችን በዓል በጋራ እናክብር
እንኳን አደረሰን!

የአባታችን የጻድቁ አቡነ አረጋዊ አጭር የህይወት ታሪክ
=======================================
የፃዲቁ የአቡነ አረጋዊ አባት ይስሐቅ እናቱም እድና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የተባረከ ልጅ ሰጣቸው ስሙንም ዘሚካኤል አሉት እሱም አቡነ አረጋዊ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት፣ ህገ ኦሪትን ትምህርተ ነቢያትንና ቅዱሳት መፃህፍትን እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ እሱም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየፀና እየበረታ አደገ፡፡
ሚስት ያገባ ዘንድ አጩለት፡፡ ፃዲቁ አባታችን አቡነ ዘሚካኤል/አረጋዊ/ ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ከብዙ ዘመን በኋላ ከሮም ወደ ግሪክ ሀገር አባ ጳኩሚስ የሚኖርበት ደውናስ ወደምትባል ገዳም የምንኩስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ ሄደ፡፡ አባ ጳኩሚስንም አገኘው፡፡ አባ ጳኩሚስም ልጄ ሆይ አንተ የንጉስ ልጅ እንደ መሆንህ መጠን የመንግስቱ ወራሽ ነህና መንኰሰህ ለመኖር ይቻልሃልን አለው፡፡ ብፁዕ አባታችንም አባቴ ሆይ የምድር መንግስት ኃላፊ ጠፊ ነው ነገር ግን የማታልፈውን የማትጠፋውን ዘለዓለማዊት መንግስት እወርስ ዘንድ እፈልጋለሁ አለው፡፡ በፈተናም ከፀና በኋላ በአስራ አራት ዓመቱ በአባ ጳኩሚስ እጅ የምንኩስናውን ልብስ ለበሰ፡፡ ከአመነኮሰውም በኋላ ስሙን ዘሚካኤል ብሎ ሰየመው፡፡ ከዚህም በኋላ በጾም በፀሎት ተጠምዶ ኖረ፡፡

ዕድሜው አነስተኛ ሲሆን ስለጥበቡ ስለምክሩና በእውቀቱ የልጅ አዋቂ ስለሆነ አረጋዊ ተባለ፡፡ የፃዲቁ ዜና በሀገሩ ተሰማ፡፡ እናቱ ንግስት እድና እርሱ ወዳለበት መጥታ መነኮሰች፡፡ በሴቶችም ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኢትዮጵያን ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም አስራት ይሆናት ዘንድ በቃል ኪዳን እንደሰጣት ከቅዱሳት መጽሐፍት አገኘ፡፡ በኢትዮጵያም ፍቅር ልቡ ተነደፈ፡፡ ማንም ሰው ሳያውቅበት ሁለት ደቀ መዝሙሮቹን ይዞ ቅዱስ ሚካኤል እየመራው ንጉሱና ጳጳሱ ካሉበት አክሱም ከተማ ደረሰ፡፡

በዚያም ጥቂት ቀን ከተቀመጠ በኋላ ተመልሶ ወደሮም ሄደ፡፡ በኢትዮጵያ በዓይኑ የተመለከተውን በጆሮ የሰማውን ሁሉ በዚያ ላሉ ወንድሞቹ ነገራቸው፡፡
ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበው መነኮሳት ነገሯቸው፡፡ እርስ በራሳቸውም እኛም ወደዚህች ሀገር መሄድ አለብን ተባባሉ፡፡ ስምንቱ ሁሉ ያላቸውን የመገልገያ ዕቃ ይዘው ከታቦቶቻቸውና ከካህናቶቻቸው ጋር ንዋየ ቅዱሳትና መጽሐፍቶችን ይዘው በሮም ነግሶ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉስ አልአሜዳ በነገሰ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ480 ዓ.ም አባታችን ዘሚካኤል እየመራቸው ራሳቸውን ዘጠኝ ሆነው ንጉሱና ጳጳሱ ካሉበት አክሱም ከተማ ደረሱ፡፡

በዚያን ጊዜ እንደነሱ የመነኮሱት በአንዲት የፀሎት ቤት በአንድነት ሆነው ለፀሎት ተጠመዱ፡፡ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረጉ ቆዩ፡፡ መልአክት ዘወትር ባለመለየት ይጎበኟቸዋል፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር እየተገለፀ ይጎበኛቸው ነበር፡፡ እያንዳንዳቸውም የሃይማኖታቸውን ኃይል አሳዩ፡፡ ከነሱ መካከልም ተራራ ያፈለሱ፣ ባህሩን ከፍለው ደረቅ መንገድ ያደረጉ ፣ስንዴ ዘርተው ወዲያው ለዘጠኝ ሰዓት መስዋዕተ ቁርባን ያደረሱ አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ምድር በነዚህ የቅዱሳን ኪደተ እግር ተቀደሰች በውስጧም በመመላለሳቸው አውራጃዎቿና አደባባዮቿ ሁሉ ታደሱ፡፡ ማር 9፡23

አባታችን ዘሚካኤልም የበላይ ጠባቂያቸው ወይም መሪያቸው አደረጉት፡፡ ለየብቻቸው ለመኖር ተስማሙ፡፡ በዚያን ጊዜ መሪር እንባ እያነቡ ለየራሳቸው ተለያዩ፡፡ አባታችንንም ስሙን አረጋዊ ብለው ሰየሙት ብልህ አዋቂ ማለት ነው፡፡ አባታችንም ወደመረጠው ቦታ ሲሄድ ከዛፍ ጥላ ስር አረፈ፡፡ እስዋም እስከ ዛሬ ድረስ የቅድሳን ማረፊያ ሆኖ ትገኛለች፡፡ ቅድስት ቦታ ዳሞን ባያት ጊዜ ሶስት ጊዜ ሰገደ፡፡ በተራራዋ ስር ለመኖር ወደደ፡፡ ነገር ግን ወደ ተራራዋ መውጫ አላገኘም፡፡ ተመልሶ ወደ ሌላ ተራራ ሄዶ አማረጠ ነገር ግን እንደ ደብር ዳሞ የበረከት ቦታ አላገኘም፡፡ ተመልሶ ወደ ደብረ ዳሞ ሄደ፡፡ በዚያም የምንጭ ውሃ አገኘ፡፡ ውሃውን እየተንከባከበች የሴት መነኮሳቶችን ታስተዳድር ዘንድ እናቱ ቅድስት እድናን አስቀመጣት ይህችንም ደብረ በአተልሞ አላት ትርጓሜውም የእናቴ ማረፊያ ቤት ማለት ነው፡፡

ከዚያም ሲሄድ ጠፍጣፋ ድንጋይ አገኘና ከዚያ ላይ ትንሽ ምንጣፍ አነጠፈና ተቀመጠ፡፡ በትሩንም በድንጋይዋ ላይ አቆመ፡፡ በተነሳም ጊዜ ደቀመዝሙሩ ማቲያስ በትሩንና ምንጣፉን ባነሳው ጊዜ ያች ድንጋይ ቁመቷም ጎኗም ልክ በዚያች ምንጣፍ ዓይነት ቅርጽ አወጣች፡፡ የቀድሞ መልኳ ነጭ ሲሆን አሁን ግን የማይፋቅ የማይላጥ ቀይ ቀለም ሆኗል፡፡ ስለአባታችን አቡነ አረጋዊ ስለታላቅነቱና ስለክብሩ ከዚያ የደረሰ ሁሉ ይሳለሟታል፡፡
ከዕለታት በአንደኛው ቀን መንገድ ሲሄድ ውሎ ከተራራ አጠገብ ወደ ታች የተንዠረገገች ሀረግ/ገመድ/ አገኘና በስሯ ሶስት መዓልት ሶስት ሌሊት ሲፀልይ ከቆየ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ እግዚአብሔር ያከበረህ ቅዱስ ሆይ ምን ያስጨንቅሃል አለው፡፡ አባታችንም ከዚህ ተራራ ላይ ወጥቼ ስለኃጢአቴ ይቅርታን እጠይቅህ ዘንድ እወዳለሁ አለው፡፡ ሊቀ መልአኩም ወደ ተራራው የምትወጣበትን እግዚአብሔር እስኪልክልህ ድረስ ጥቂት ጊዜ ታገስ አለው፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊ በተራራው ፍቅር ልቡ ስለተነደፈ አዘነ፡፡ አጥብቆም አለቀሰ፡፡
ከእግረ ደብር ሆነው አሁን ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝሙር 90/91፡11-16 ላይ “በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ። በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ። ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።” እንዳለው የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ዳግመኛ መጥቶ አረጋዊ ሆይ አይዞህ አትፍራ ስልጣን ተሰጥቶሃል፡፡ በሐረጓ በስተቀኝ በኩል ባለችው ቦታ ተቀመጥ ወደ ተራራው ጫፍ ያወጣህ ዘንድ በገመድ ፋንታ ቁመቱ ስድሳ ክንድ የሆነ ታላቅ ዘንዶ እግዚአብሔር ይልክልሃል አለው፡፡ እሱም በጾም በፀሎት ሁለት ሱባኤ ወይም አስራ አራት ቀን በዚያ ተቀመጠ፡፡ የታዘዘውም ዘንዶ በሶስት ሰዓት መጣ በዘንዶው ጅራት ላይ ወጥቶ በቅጽበት ከተቀደሰው ተራራ ጫፍ ላይ ደረሰ፡፡ እንደደረሰም ሶስት ጊዜ ሰገደ፡፡ ስለዚህም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሎ ተሰየመ፡፡በመሸም ጊዜ አነስተኛ ዳቦ አንስቶ ባረከ መብላትም ጀመረ፡፡ ዳቦዋ ግማሽ ስትሆን ጠገበ የዳቦውን ግማሽ አምሳል ለኋለኛው ትውልድ ምልክት ትሆን ዘንድ እንጨት ጠርቦ/ቀርጾ አስቀመጠ፡፡ ይህች ምልክት እስከዛሬ ድረስ አለች፡፡ ደቀ መዝሙሮቹም ከታች ወደ ላይ የሚወጡበትን መሰላል ሰሩ፡፡

ብፁዕ አባታችን አቡነ አረጋዊ መጠነኛ ቤት ሰራና አብሮ ይዞት የመጣውን ታቦት በውስጡ አስገባ፡፡ ስለቁርባኑ ወይም ስለመስዋዕቱ እግዚአብሔርን ለመነ፡፡ እግዚአብሔርም ልመናውን ሰመቶ የሚያስፈልገውን ሁሉ መልአክት ከሰማይ ይዘውለት ወረዱ፡፡ ለመኖሪያውም ትንሽ በዓት አገኘ፡፡ በዚያም ያለምንም መኝታ በፀሎትና በስግደት በመትጋት ተቀመጠ፡፡በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሰቃዩትን በፀሎቱ ኃይል ፈወሳቸው ያላመኑትን እያስተማረ አሳመናቸው ለዚያች ሀገር ብርሃን አበራላት፡፡ፊንሐስ የተባለ የሃማሪያው ንጉስ በናግራን ሀገር ያሉ ክርስቲያኖችን ገደለ፡፡ አብያተ ክርስቲያናቱንም ሁሉ አቃጠለ፡፡

የቁስጥንጥንያው ሊቀ ጳጳስ ጢሞቴዎስ በናግራን አገር ስለተፈጁት ክርስቲያኖች መልዕክት ወደ ኢትዮጵያ/አክሱም/ ንጉስ ወደ አፄ ካሌብ ላከ፡፡ ንጉሱም ወደ አባታችን አቡነ አረጋዊ አባቴ ሆይ በፀሎትህ አስበኝ የፃድቅ ሰው ፀሎት ግዳጅ ትፈጽማለች ኃይልም ታሰጣለች በጠላት ላይም ድልን ታቀዳጃለች ብሎ ላከበት፡፡ አባታችንም እግዚአብሔር ይርዳህ አለው፡፡ አፄ ካሌብም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዶ ፀለየ፡፡ ጦሩን አዘጋጅቶ ዘመተ በእግዚአብሔር ቸርነትና በአባታችን ፀሎት በድል አጠናቀቀ፡፡ እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ አባ ጴንጠሌዎን ገዳም ገብቶ መነኮሰ፡፡ ኢትዮጵያዊው ንጉስ አፄ ካሌብ ይህን ዓለም በመናቅ በበረሃ ዋሻ አስራ ሁለት ዓመት በጾም በፀሎት በብዙ ተጋድሎ ኖረ፡፡ ግንቦት ሃያ ቀንም አረፈ፡፡

ከዚያም የካሌብ ልጅ አፄ ገብረመስቀል ነገሰ ወደ አባታችንም ሄዶ ሀገሩንና ህዝቡን እንዲባርክ አጥብቆ ማለደው፡፡ አባታችንም እንደቃልህ ይደረግ አለው፡፡ መልሶም አፄ ገብረመስቀል አባታችን አቡነ አረጋዊን በየትኛውም ቦታ ላይ ቤተክርስቲያንህን አሳንፅ ዘንድ ትፈቅዳለህ አለው፡፡ አባታችንም ቤተክርስቲያን የሚሰራበትን ቦታ አሳየው ንጉሱ አፄ ገብረመስቀልም በተባለው ቦታ ላይ ቤተክርስቲያኑን አሳነፀ፡፡ በውስጡም በድንጋሌ ስጋ በድንጋሌ ነፍስ የፀናች በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም የተሰየመች በወርቅና በብር የተጌጠች ታቦት አስገባ፡፡ንጉስ አፄ ገብረመስቀል ከተራራው ላይ ሲወርድ ለቤተክርስቲያኑ ማሰሪያ የሆነውን መወጣጫ መሰላል ላፍርሰው ብሎ አባታችንን ጠየቀ አባታችንም አዎ አፍርሰው አትትወው ነገር ግን ስለዘንዶው ጅራት ፈንታ ሰዎች ይወጡበት ዘንድ ገመድ አብጅ አለው፡፡ ንጉሱም አባታችን አቡነ አረጋዊ እንዳዘዘው አደረገ፡፡ ስለዚህም ደብረ ደኃምሞ ተብሎ ተሰየመ፡፡

የአባታችንን የጻድቁን ዜና ሰምተው አስኬማ ያቀዳጃቸው ወይም ያመነኩሳቸው ዘንድ ወደ እርሱ ብዙዎች ይመጣሉ፡፡ ለመመንኮስ የወደደ ሁሉ በተራራው ግርጌ ወዳለች ወንዝ/ውሀ/ ወስደው ያጥቡታል ከዚያም ወደ ተራራው ያወጡትና ያመነኩሱታል፡፡ ያችም ወንዝ ወይም ውሃ ማየ ምርቃይ/መጠመቂያ/ ትባላለች፡፡ እስከዛሬም ድረስ በዚህ ስም እየተጠራች አለች፡፡ፃዲቁ አቡነ አረጋዊ በብዙ ተጋድሎ ኖረ፡፡ እናቱ እድና ጥር አራት ቀን አረፈች፡፡ አባታችን አቡነ አረጋዊ ባሰራላት አዲስ መቃብር ቀበራት፡፡ አቡነ አረጋዊ በዚሁ በደብረ ዳሞ ተራራ ላይ ብዙዎችን የሃይማኖት ትምህርት አስተማረ፡፡ ልጆቹ እንደበዙ በተመለከተ ጊዜ በየወገናቸው አዛዥ ሾመላቸው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ከድካም ወደ እረፍት ከኃዘን ደስታ ወዳለበት ከአሣር ወደ ክብር ቦታ በታላቅ ደስታ እወስድህ ዘንድ ወደ አንተ መጣሁ፡፡ መታሰቢያህን ያደረገ በፀሎትህም የተማመነውን ሁሉ እኔ በመላአክት ፊት ሞገስን ባለሟልነትን እሰጠዋለሁ፣ በስምህ በተሰራው ቤተ መቅደስህ ውስጥ የፀለየ የለመነ ፈጥኜ ፀሎቱን እሰማዋለሁ፡፡ ቤተ ክርስቲያንህን ለሰራ አስራ ሁለት የብርሃን አዳራሽ አዘጋጅለታለሁ፣ የገድልህን መጽሐፍ በመታመን በንጽህና አድርጎ በቤቱ ያስቀመጠ የወረርሽኝ በሽታ ወይም ቸነፈር በቤቱ አይገባም፡፡ ድንገተኛም የሰውና የእንስሳ ሞት አይደርስበትም የእህል ችግርም አይኖርበትም፣ ከሁሉም ይልቅ የሞት ጥላ አያርፍብህም መልአከ ሞትም ሊያስደነግጥህ አይችልም እንደ ነቢያቶቼ ኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ ብሎ ብዙ ቃል ኪዳኖች ገባለት፡፡ አባታችንም ጌታ ሆይ መታሰቢያዬን ያደረገ የገድሌን መጽሐፍ የፃፈ በፀሎቴ የተማመነ እስከ ስንት ትውልድ ትምርልኛለህ አለው ጌታም እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ዳግመኛም በስምህ በተሰየመ ቤተክርስቲያን ሁሉ በዚያ የተቀበረ ኃጢአቱ ይሰረይለታል፡፡ እነዚህንም ሁሉ አስራት አድርጌ ሰጠሁህ አለው፡፡ ይህን ከነገረው በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ አረገ፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊ ደቀ መዝሙሩ ማትያስን ጠርቶ ጌታችን ተገልጦ የሰጠውን ቃልኪዳንና ይህ መጽሐፍ ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ነገረው መዝ 111/112 ፡ 6 ወንድሞቹ ደቀ መዛሙርቶቹን እንዲሰበስብም አዘዘው፡፡ ማትያስም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ አባታችን አቡነ አረጋዊም ከበዓቱ በመውጣት
እንደተለመደው በመካከላቸው ተቀምጦ አስተማራቸው ቀጥሎም ከዛሬ ጀምሮ በስጋ አታዩኝም አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ ከአባታችን እግር ስር ወድቀው መሪር እንባን አለቀሱ፡፡ ክቡር አባታችን አቡነ አረጋዊ አረጋጋቸው፡፡
ፃዲቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ የእርጅና ዘመኑ ደረሰ፡፡ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሆነው፡፡ በጥቅምት 14 ቀንም ተሰወረ፡፡ በዚያም ከመቋሚያና ከመስቀል በስተቀር ምንም የተገኘ የለም፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊ በማዕረግ ርዕሰ ባሕታውያን ከሚባሉ ፩.አባ እንጦንስ ፪. አባ መቃርስ ፫. አባ ጳኩሚስ ፬. አባ ቴዎድሮስ ቀጥሎ ፭ኛ የማዕረግ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የጻድቁ አባታችን የአቡነ አረጋዊ እና የገብረ ክርስቶስ ቃል ኪዳናቸው፣ ምልጃቸው፣ በረከታቸውና ጸሎታቸው ከሀገራችን ከኢትዮጵያ ከዓለም ሁሉ እና ለመላው ህዝበ ክርስቲያን በአማላጅነታቸው ለምናምን በሁላችን ላይ ለዘላለሙ ጸንቶ ይኑር አሜን!!!

ከውዳሴ ቲዩብ የተወሰደ

Address

ደቡብ ጎንደር ደብረ ታቦር
Gondar
88888888

Telephone

0932793622

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአባረጋይ አርባዕቱ እንስሳ ወአቡነ አረጋዊ ልጆች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share