ኦርቶዶክሳዊ የመረጃ ማዕከል/Orthodoxy center of Information

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • ኦርቶዶክሳዊ የመረጃ ማዕከል/Orthodoxy center of Information

ኦርቶዶክሳዊ የመረጃ ማዕከል/Orthodoxy center of Information Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኦርቶዶክሳዊ የመረጃ ማዕከል/Orthodoxy center of Information, Religious organisation, ደብረማርቆስ, Gondar.

16/01/2026
🌷🌷   እነሆ🌷🌷"""ሸር በማድረግ ስለ ጎንደር በሞራል ለተጎዱ ኦርቶዶክሳውያን አድርሱልን"""◉ በጎንደር ያዘናችሁ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ እውነታውን  በአጭሩ ተመልከቱ። ➾ ሰሞኑን ጎንደር ላይ...
11/12/2025

🌷🌷 እነሆ🌷🌷

"""ሸር በማድረግ ስለ ጎንደር በሞራል ለተጎዱ ኦርቶዶክሳውያን አድርሱልን"""

◉ በጎንደር ያዘናችሁ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ እውነታውን በአጭሩ ተመልከቱ።

➾ ሰሞኑን ጎንደር ላይ በተፈጠረው ነገር ብዙ ኦርቶዶክሳውያን አዝናችኋል ኀዘናችሁም አግባብነት ያለው ነው።

➾ ሆኖም ግን የነገሩን እውነታ ከብዙ በጥቂቱም ማወቅና ወደ ፊት መደረግ ስላለበት ነገር መወያየትና ሀሳብ መለዋወጥ ተገቢ ነው።

1️⃣. መጀቅመሪያ ከሃይማኖት ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌለው የርዳታ ድርጅት እንደሆነ ለማሳዎቅ ጎንደር ቀበሌ 18 ማራለም ት/ቤት ላይ ርዳታውን በመጀመር ሰውን ሲያዘናጉ ቆይተዋል።

2️⃣. ርዳታውን የበለጠ ታማኝና ከሃይማኖት ጋር ንክኪ የሌለው ለማስመሰል እስከ ዛሬም ድረስ የሚረዷቸውን ሰዎች ከቀበሌ የድሃ ድሃ መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንዲያጽፉ በማድረግ ሲያዘናጉ ቆይተዋል። ሌላው ቀርቶ የንስሐ አባቶች እንኳ ልጆቻቸው እንደተቸገሩ ሲነግሯቸው ወደዚህ የርዳታ ድርጅት ሳይቀር አመላክተው ይልኳቸው የነበሩም እንደነበሩ አውቀናል።
3️⃣. ከዚህ በኋላ የማራለም ት/ቤትን በመልቀቅ ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ዝቅ ብሎ ወደ አበራ ጊዮርጊስ መገንጠያ መንገድ ወደ ቀኝ በኩል ገባ ብሎ የሚገኝ ቦታ ወላጅ አልባ ሕፃናትንና ዳካሞችን እንረዳለን በሚል ሰበብ የዛሬ 10 ዓመት ገዳማ ይህንን ቦታ በመንግሥት ተቀብለዋል።

4️⃣. ደካሞችንና ሕፃናትን እንረዳለን በሚል ሰበብ በተቀበሉት በዚህ ቦታ አካባቢ የፕሮቴስታንት አማኝ መቶ በመቶ ፈጽሞ አንድ ሰው እንኳ የለም።

5️⃣. እነዚህ ሰዎች የጎንደር ኦርቶዶክሳውያንን በፕሮቴስታንት አዳራሽ ወስደው ለማስተማርና አጋንንታዊ ፈውሳቸውን ለማስኬድ ፈጽሞ የማይታሰብ መሆኑን ሲረዱ ይህንን ቦታ በማን አለብኝነት ለርዳታም ለአምልኮም መጠቀሚያ አደረጉት።

6️⃣. የትምህርት አሰጣጣቸውም ሃይማኖት ተኮር አድርጎ በመጀመር ሳይሆን በምንሰጣችሁ ገንዘብ እንዴት ሥራ መፍጠር አለባችሁ በማለት የሥራ ፈጠራ ሥልጠና ብለው በመጀመር የኑፋቄ ትምህርታቸውን ያስቀጥላሉ።

7️⃣. እነዚህ ተረጅዎች የበለጠ እነርሱን እንዲያደምጡ ከሰሩበት መንገድም አንዱ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፈጽሞ ለአማኞቿ ምንም የማይጨንቃትና የማይመለከታት አድርጎ በማሳየት የእነርሱ እምነት ግን አንዱ ሌላውን ደግፎ የሚኖር በመሆኑ አንድም የሚቸገር ሰው የሌለ መሆኑን በተደጋጋሚ በመስበክ ብዙ ሰርተውባቸዋል።

8️⃣. በርዳታ ስም የመጡ እኒህ ሰዎች ከሰፈሩ እናቶች በድብቅ ከ15000 ብር ጀምሮ እየከፈሏቸው ውስጥ ለውስጥ የእነርሱን ሥራ እንዲያስፈጽሙ ያደረጓቸውም እናቶች አሉ።

9️⃣. በተለይ በዓላትን አስመልክቶ የልደት፣ የትንሳኤ፣ የዘመን መለወጫ ዶሮ፣ ዘይት፣ ስኳርና መሰል የበዓል መዋያ በመስጠት፣ የልጆችን ደብተርና እስክብሪቶ በመስጠት የርዳታ ቦታ እንጅ የአምልኮ ቦታ እንዳልሆነ ለማሳየትና ማህበረሰቡን ለማደንዘዝ ይሞክራሉ።

🔟. ሌላው ቀርቶ ቦታው በአምልኮ ቦታ ሳይሆን በርዳታ ድርጅት ስም ስላለ የድርጅቱ ጠባቂ ዘበኞች ኦርቶዶክሳውያን ስለሆኑ ያላመነ ሰው ከቦታው ድረስ በመሄድ ዘበኞቹንም ማናገርና መረዳት ይችላል።

⓫. በዚህ ሁኔታ ከተለማመዱ በኋላ እንኳ አሁንም ከራሳቸው የአምልኮ ቦታ ላይ እናስተምር ወይም ፈውስ እንስጥ ቢሉ ማንም እንደማይሄድላቸው ያውቃሉና ይህንን የርዳታ ቦታ እንደ ሽፋን በመጠቀምና አስቀድመው በመሰለል ገንዘብ እንረዳለን በማለት ሰዎችን አሁንም እንደቀድሞው ሰሞኑን ሰበሰቡ። ከተሰበሰቡት ሰዎች በዙሪያው ቁመው የምታይዋቸው ወጣቶች የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሮቴስታንት አማኞች ናቸው። ሌሎችም ከፓስተሩ ጋር አብረው ለዚህ ተልእኮ የመጡ ሰዎች ነበሩ።
በመጨረሻም የወላጅ አልባ ሕፃናትና ደካሞች መርጃ በተባለው ቦታ ይህንን አጋንንታዊ ፈውስና የምንፍቅና ትምህርታቸውን በግልጽ አስኪደዋል።

⓬. በቀጣይም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ መድበው የጎንደርን ስም ለማጠልሸት የሄዱበትን ድብቅ ሴራዎች ሁሉ ከዚህ ላይ መግለጽ ባልፈልግም በትኩረት እየሄድንባቸው ያሉ ጉዳዮች ሳላሉ እናንተም ማገዝ በምትችሉት ሁሉ አግዙን።

እኔ እንዳጋጣሚ ቀበሌ 18 ላይ የነበረውን መረጃ ብቻ አስቀመጥሁ እንጅ እነዚህ በርዳታ ስም የተመረጡ ቦታዎች በዋናነት 5 ሲሆኑ
1ኛ. ጎንደር ቀበሌ 18
2ኛ. ፒያሳ አሌፍ ሕንፃ
3ኛ. ትክል ድንጋይ
4ኛ. ትክል ድንጋይ
5ኛ. በቅርቡ ጭልጋ ናቸው።

ስለዚህ ከዚህ በመነሳት

⓵. በርዳታ ስም በማጭበርበር የጎንደርን ገጽታ ያበላሸን ሰው በሕግ መንገድ መጠየቅ አይቻልምን?

⓶. በርዳታ ስም አንድም አማኝ ሳይኖር ከተሠራ በኋላ የርዳታም ሆነ የአምልኮ ቦታ የሆነውን ይህን ቦታስ ማስነሳት አይቻልምን?

🌷 ይህ ጥብቅ ማሳሰቢያም ጭምር ነው፦ በጎንደር ከተማም ይሁን በወረዳዎቿ ጭልጋና ትክል ድንጋይ በሌሎችም ቦታዎች ሁሉ የርዳታ መስጫ ቦታዎች እየተባሉ የተቀመጡትን ሁሉ የሚመለከታቸው ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ እነዚህን ቦታዎች በመከታተል በሚመለከታቸው አካላት እርምጃ እንዲዎሰድባቸው ማድረግ ይኖርበታል ባይነኝ።

ጎንደር ላይ መጥቶ የነበረውም ይሁን ሌሎች ፓስተሮች ሲናገሩ የሰማችሁት እውነታ ይሄንኑ ነውና። በቅርቡ ጎንደር ላይ ብዙ ቸርቾች ይኖሩናል ያሏቸው በርዳታ ስም የተቀበሏቸውንና የገዟቸውን ቦታዎች ሁሉ ወደ አምልኮ ቦታነት ለመለወጠ ያሰቡትን ድብቅ ሴራ በይፋ እያወጡት ነው። ስለዚህ በየአካባቢያችሁ እየተመሩም ይሁን እየገዟቸው ያሉ የርዳታ ቦታ ሽፋን የለበሱ ቦታዎች ሁሉ የፕሮቴስታንት ቸርቾች እንደሆነ እወቁ። ሻጮችም ይህንን ጉዳይ ግምት ውስጥ አስገቡ።

⓷. ሌሎችም ከላይ የተዘረዘሩትን በመመልከት የሆነውን ሁሉ መታዘብና ከዚህ በማያያዝ እውነታውን በእነዚህ ሀሰተኞች ለተደናበሩ ወገኖቻችን እውነቱን በማስረዳት የበኩላችሁን ተወጡ እላለሁ።

➃. በጎንደር ሊቃውንትና በጎንደር ወጣቶች በኩል እየተሠሩ ያሉ እንቅስቃሴዎች ካሉ በሂደት የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

◉◉ በስብከት እንደማይሳካላቸው ሲረዱ የተራቡትን ድሆችና በሱስ የተጠመዱትን አንዳንድ ወጣቶች በገንዘብ፤ እንዲሁም የታመሙትን በሽተኞች አጋንንታዊ ፈውስ እንሰጣጣለን በሚል በስስ ብልታቸው የገቡ እንጅ ከእነዚህ ሰዎች ውጭ አንድም ሰው የሄደ አለመኖሩን እንድታውቁ እንፈልጋለን።

ባለፈው ያሳወቅናችሁ ሁለተኛውን መቄዶንያ "ፍኖተ ሳምራዊን" ግን በሚገባ ተረባርበን ለተቸገሩ ኦርቶዶክሳውያን እንድረስ!

◉ በሞራል ጎድተናችሁ አንቀርም እንጠግናችኋለን ፓስተር ዘካርያስን ግን አመስግኑልኝ ብዙ ብርታቶችን ሰጥቶናል፣ ከተኛንበት ቀስቅሶናል፣ በድህነት የወደቁትን ሳይሆን በግዴለሽነት የወደቅነውን አንስቶናል!!!

◉ የማስጠንቀቂያ መልእክት፦ በግል ኮሌጆች ውስጥ ተማሪ ነን ብላችሁ ገብታችሁ ከፕሮቴስታንቶች ብዙ ገንዘብ በመቀበል ውስጥ ለውስጥ ሥልጠና የምትሰጡ ሆድ አደሮች መረጃው ሙሉውን ደርሶናል።

ለአብነትም ጂቲ እና ቤዝማሪ ኮሌጅ !

© መምህር ሲሳይ ተስፋ

31/10/2025

የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ "ሐሰት ነው" ሲሉ ተፈጽመዋል የተባሉትን ግድያዎች ማስተባበላቸው ተገለጸ!

ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ]

ቢቢሲ አማርኛ ትናንት ባሠራጨው ዘለግ ያለ ዘገባ በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የተፈጸሙትን ግድያዎች ዘርዘር ያለ ዘገባ አዘጋጅቷል፤ ተቋሟችን ይህንን ዘገባ እንደሚከተለው አዘጋጅቶታል፡፡

ቢቢሲ አማርኛ በመግቢያው ላይ “በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ውስጥ በአንድ ሳምንት ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች ሕጻናትን ጨምሮ "25 ሰዎች" መገደላቸውን የተጎጂዎች ቤተሰቦች እና በአካባቢው የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሓላፊዎች ተናገሩ።” ሲል ይጀምራል፡፡

ባለፈው ሳምንት ረዕቡ እና ሐሙስ ዕለት በተፈጸመው የመጀመሪያው ጥቃት ከተገደሉ ሰዎች ውስጥ "ስምንቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት" እንደሆኑ ሦስት ምንጮች መግለጣቸውን ጠቁሟል።

በአንድ ሳምንት ውስጥ ተከታታይ ጥቃቶች የተፈጸሙባቸው በአርሲ ዞን ውስጥ በሚገኙት ጉና፣ ሽርካ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች ነው። ጥቃቶቹን በተመለከተ ያነጋገራቸው ሁለት የተጎጂዎች ቤተሰብ አባላት እና ሦስት የቤተክርስቲያን ሓላፊዎች በደኅንነት ስጋት ምክንያት ስማቸው እንዳይጠቀስ መጠየቃቸውንም አክሎ ገልጿል።

ምንጮቹ እንደሚገልጹት በዞኑ በሚገኙት ጉና፣ ሽርካ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች ተከታታይ ግድያዎች የተፈጸመው ካለፈው ሳምንት ረቡዕ ዕለት ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም. አንስቶ ነው ሲል ግድያው የተጀመረበትን ቀን እንዳገኘም ጭምር።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የተገደሉት ሰሞነኛው ጥቃት በጀመረበት ጉና ወረዳ ነው። ታጣቂዎች ባለፈው ሳምንት ረቡዕ እና ሐሙስ በፈጸሟቸው ጥቃቶች 14 ሰዎች መገደላቸውን ሁለት የተጎጂዎች ቤተሰብ አባላት እና የአካባቢው የቤተክርስቲያን አመራር ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሌላ ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን አመራር ደግሞ "አባ ጀማ" በተባለው አካባቢ ከተፈጸመው ጥቃት ጋር በድምሩ "17 ሰዎች" መገደላቸውን ገልጸዋል።

አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ተከታይ ጥቃት የተፈጸመው በዚህ ሳምንት ሰኞ ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም. ሌሊት እንደሆነ አንድ የቤተ ክርስቲያን አመራር ገልጸዋል። በዚህ ጥቃት "ሦስት ሰዎች" መገደላቸውንም አስረድተዋል ይላል ዘገባው።

በማግሥቱ ማክሰኞ ሌሊት አምስት ሰዓት ገደማ ላይ ደግሞ ሌላኛው የአርሲ ዞን ወረዳ በሆነው ሆንቆሎ አቤ ሦስተኛ ጥቃት መፈጸሙን ሁለት ምንጮች ተናግረዋል።

በዚህ ጥቃት "አምስት ሰዎች" መገደላቸውን የሚገልጹት አንድ ወረዳው ቤተ ክርስቲያን ሓላፊ፤ ሟቾቹ "የአንድ ቤተሰብ አባላት" መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

"የአንድ ቤተሰብ አባላት ሁለቱ ሴቶች ህጻናት ልጆች እና ሦስቱ ወንዶች ናቸው ከቤት አውጥተው የገደሏቸው" የሚሉት ሓላፊው፤ "ከአንድ ቤት ተወስደው እንደተገደሉ" ተናግረዋል።

አንድ ሰው ደግሞ ታግቶ እንደተወሰደ እና እስካሁን ድረስ ያለበት እንደማይታወቅ ጠቅሰዋል።
የመጀመሪያው ጥቃት በተፈጸመበት ጉና ወረዳ የተገደሉት 14 ሰዎች፤ በአንድ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ እና በጋብቻ የተሳሰሩ የተለያዩ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑ አራት ምንጮች ተናግረዋል ብሏል።

የተጎጂዎች ቤተሰብ አባላት እና የቤተ ክርስቲያን አመራሮች በዚህ ጥቃት ተገድለዋል ያሏቸውን 14 ሰዎች ስም ዝርዝር አጋርተዋል። ጣቢያው ካነጋገራቸው ምንጮች ያገኘው ስም ዝርዝርም ተመሳሳይነት ያለው ነው ሲል ዘግቧል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት የቤተሰብ አባላት፤ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ከጥቃቱ የተረፉ የአራት እና የስምንት ዓመት ሕጻናትን እያሳከሙ ያሉ ናቸው።

አንዱ ምንጭ እህቱ እንደተገደለች ተናግሯል። ሌላኛው ደግሞ እናቱ፣ ዘጠኝ ዓመት የሆናቸው ሁለት መንታ ወንድሞቹ እና አንድ እህቱን ጨምሮ ስምንት የቤተሰቡ አባላት እንደተገደሉ አስረድቷል።

የወንድሙ ባለቤት እና የ16 ዓመት ሴት ልጅም መገደላቸውን ጠቅሷል። የአጎቱ ባለቤት እና በቤታቸው ውስጥ ይኖር ነበረ የ12 ዓመት ልጅም ከሟቾቹ መካከል እንደሆኑ ዘርዝሯል።
ምንጮቹ እንደሚናገሩት፤ ረቡዕ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ የመጀመሪያው ጥቃት የደረሰው "የሚካኤል" ዕለትን ለማክበር በአንድ ቤት በተሰበሰቡ ስድስት ሰዎች ላይ ነው ያለው ዘገባው።

ከእነዚህ ስድስት ሰዎች ውስጥ እናቱ ፋኖሴ ወርቄ እና የአጎቱ ሚስት መስቲካ ማሞ እንደሚገኙበት ገልጿል። ሻውሌ ይፍሩ እና እታገኘው አስፋው የተባሉ ባል እና ሚስትም ከተወሰዱት መካከል መሆናቸውን አክሏል።

ስድስቱ ሰዎች "ወደ ጫካ ከተወሰዱ" በኋላ መገደላቸውን ተናግሯል።
በዚህ ጥቃት ፍርሃት የገባቸው ዘጠኝ የሟች ቤተሰብ አባላት አንድ ቤት ውስጥ ተሰብስበው እንደነበር ሁለቱ ምንጮች ገልጸዋል። ሐሙስ ሌሊት ወደዚህ ቤት የገቡት ታጣቂዎች ዘጠኙን ሰዎች እና አጠገብ ባለ ቤት የነበረ አንድ ግለሰብን ጨምረው መውሰዳቸውን አስረድተዋል።

ዘጠኙ ሰዎች እና በረት ውስጥ የነበሩ ከብቶችን እየነዱ ከወሰዱ በኋላ "ተረአሊ" የሚባል ቦታ ላይ "ሁሉንም አንበርክከው እርምጃ" እንደወሰዱባቸው አንድ ምንጭ ገልጿል። ከተወሰዱት አስር ሰዎች ውስጥ የስምንቱ ሕይወታቸው፤ ሁለት ሕጻናት እንደተረፉ ሦስት ምንጮች ተናግረዋል።

በዚህ ጥቃት ከተገደሉት ውስጥ የዘጠኝ ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሚኪያስ ሙላቱ እና ሶፎኒያስ ሙላቱ እንዲሁም የ18 ዓመቷ እህቱ ሄለን ሙላቱ እንደሚገኙበት አስረድቷል። የወንድሙ ሚስት የሺ መለሰ እና የ16 ዓመት ልጇ ስምረት ሸዋንግዛው ሲገደሉ ሌላኛዋ የወንድሙ ልጅ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት እንደተረፈች ገልጿል።

በዚህ ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች አንዷ የሆነችው የሰርካለም ተስፋዬ ልጅ የሆነ የአራት ዓመት ሕጻንም በተመሳሳይ ጉዳት ደርሶበት መትረፉን ጠቅሷል። የተረፉት ሕጻናት የተገኙት በማግስቱ ጠዋት አንድ ሰዓት "ከፖሊስ ጋር" ግድያው ወደተፈጸመበት አካባቢ በሄዱ ነዋሪዎች እንደሆነም አክሏል።
ሁለቱ ሕጻናት፤ በቀድሞ ስሙ "ኃይለማርያም ማሞ ሆስፒታል" ተብሎ በሚጠራው አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ መወሰዳቸውን ሁለቱ ምንጮች ገልጸዋል።

የቤተሰብ አባላቱ በሁለቱ ሕጻናት ላይ የደረሰውን ጉዳት ሚያሳዩ ምሥሎችን ለቢቢሲ አጋርተዋል። ምሥሎቹ የስምንት ዓመቷ ሕጻና ጭንቅላቷ እና እጇ ላይ የደረሰባትን ጉዳት ያሳያሉ።

የአራት ዓመቱ ሕጻን ደግሞ የእጁ መገጣጠሚያ እና እግሩ ላይ ጉዳት እንደደረሰበት የቤተሰብ አባላቱ ተናግረዋል። ሕጻኑ በተለይ በእግሩ አጥንት ላይ የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ የአጥንት ህክምና ወደሚሰጥበት የወላይታው የሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል መወሰዱን ገልጸዋል።
ስምንት የቤተሰቡ አባላት የተገደሉበት ግለሰብ፤ ወደ አካባቢው ተጉዞ እናቱን፣ እህቱን እና ወንድሞቹን መቅበር አለመቻሉን ይናገራል።

"'እንዳትመጡ የምትጠበቁት እናንተ ናችሁ' አሉን። ለነፍሳችን ፈራን። ኃላፊነት የሚወስድ ሰው ስለሌለ ሄደን እንኳ መቅበር አልቻልንም" የሚለው ስድስቱ የቤተሰቡ አባላት አንድ ቦታ ላይ መቀበራቸውን ገልጿል። እናቱ እና የአጎቱ ሚስት በተለያዩ አብተ ክርስቲያናት መቀበራቸውን አስረድቷል።

አባቱ ከስድስት ወር በፊት ሕይወታቸው ያለፈው በተመሳሳይ መልኩ በታጣቂዎች ከተወሰዱ በኋላ እንደነበር ያስታውሳል።

አባቱን ጨምሮ በወቅቱ የታገቱ ስምንት ሰዎችን ለማስለቀቀ ለእያንዳንዳቸው 500 ሺህ ብር መከፈሉን የሚናገረው ምንጩ፤ አባቱ ከተለቀቁ በኋላ በደረሰባቸው ድብደባ ምክንያት ከሦስት ቀን በኋላ ሕይወታቸው ማለፉን ጠቅሷል።


"ተስፋ የሚባል ነገር በውስጤ የለም። ከዚህ በኋላ ምናልባት ሕግ እንደዚህ አድርጎልን የሚለው ነገር ላይ ምንም አይነት ተስፋ በውስጤ የለም። ከዚህ በኋላ እዚያ ቦታ ላይ ተመልሰን እናገግማለን የሚለው ነገር የሚሆን አይመስለኝም" ሲል ተስፋ መቁረጡን ገልጿል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የተጎጂ ቤተሰብ አባላት እና የቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች "በሃይማኖታቸው ምክንያት ዒላማ ተደርገዋል" የሚል እምነት አላቸው። በአካባቢው ተደጋጋሚ መሰል ጥቃቶች መፈጸማቸውንም ለዚህ በማሳያነት ይጠቅሳሉ።

ከመጀመሪያው ጥቃት በኋላ የጉና ወረዳ ኃላፊዎች ወደ ቦታው ተጉዘው በታጣቂዎች ላይ "የአጸፋ እርምጃ" ስለመውሰዳቸው ሪፖርት እንደደረሳቸው አንድ ከፍተኛ የቤተ ክርስቲያን ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሐሰን መሐመድ ትናንት ረቡዕ በወረዳው ስለተፈጸመው ጥቃት ከቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ለቀረበላቸው ጥያቄ "አጣርተን በቂ መረጃ እንሰጣለን" ብለዋል።

በተመሳሳይ ቀን ስለ ጉዳዩ ጥያቄ የቀረበላቸው የአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ከድር በበኩላቸው፤ "ሐሰት ነው" ሲሉ ተፈጽመዋል የተባሉትን ግድያዎች አስተባብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ረቡዕ ምሽት ባወጣችው መግለጫ በአርሲ ዞን በጥቅምት ወር ብቻ "ከ25 በላይ ሰዎች" መገደላቸውን አስታውቃለች ሲል ዘገባውን ፈጽሟል።
©ቢቢሲ አማርኛ

31/08/2025

ማኅበረ ቅዱሳን በያዝነው የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ከ50 ሺህ በላይ አዳዲስ አማንያንና የጠፉትን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መመለሱን አስታወቀ።

ማኅበረ ቅዱሳን እያካሄደ ባለው የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤው በያዝነው የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት 52,609 ነፍሳትን ማስጠመቁን አስታውቋል።

በዚህም 47,116 ኢ አማንያንን የሥላሴ ልጅነትን እንዲያገኙ እና 5493 ጠፍተው የነበሩትን እንዲመለሱ አድርጓል።

ይህን ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመፈጸምም ለመመለስ እና ለማስጠመቅ 87 ጉባኤያት ተዘጋጅተዋል።

በተጨማሪም በተመረጡ 4 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ትምህርቶችን በድምፅ ወምስል በማዘጋጀት ለምእመናን አድርሷል።

የስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚሰጡ መምህራን በደረጃ አንድ ከ1597 እና በደረጃ ሁለት ከ259 መምህራን ማሠልጠንና ማሰማራት መቻሉም እያካሄደ በሚገኘው የ2017 ዓ.ም የሁለተኛው መንፈቀ አመት ጠቅላላ ጉባኤ በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል።

ለአዳዲስ አማንያንም መገልገያ እና ሐዋርያዊ ተልእኮ ለማስፋፋት የሚያገለግሉ 7 አብያተ ክርስቲያናት ተሠርተዋል፡፡

ለቅድመ ጥምቀት እና ድኅረ ጥምቀት አገልግሎት የሚውሉ 3 መካነ ስብከት አዳራሾች ተሰርተዋል፡፡

በካህናት እጥረት ለተዘጉ 34 አብያተ ክርስቲያናት ካህናት መቅጠር እና አገልግሎት እንድሰጡ ተደርጓል ሲል በዋና ሥራ አስፈጻሚው መምህር ዋሲይሁን በላይ አማካኝነት አስታውቋል፡፡

29/04/2022

አክራሪዎችና ጽንፈኛ ኃይሎች 4ኛው በስልጤ ዞን የሚገኘው ታሪካዊው ጀጀቢቾ ለምለም ጻድቁ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መቃጠሉን ሀገረ ስብከቱ ለኢኦተቤ ቴቪ አስታውቋል፡፡
(ሚያዝያ ፳፩ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም)

በትላንትናው ዕለት የተጀመረው ቤተ ክርስቲያንን የማቃጠል ሰይጣናዊ ተልዕኮ ቀጥሏል፡፡ እንደ ሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት መግለጫ የልዩ ኃይሉ አዛዥ ኮማንደር ሙስጠፋ በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ እየደረሰ ያውን ቃጠሎና ውድመት ሊያስቆሙ እንዳልቻሉ ሀገረ ስበከቱ በታላቅ ኃዘን ገልጸውልናል፡፡

በስልክ ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ቀሲስ ንጉሤ ባወቀ ክስተቱ ከሀገረ ስብከቱ በላይ መሆኑን በማሳወቅ ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ሥራ ሊሠሩ እንደሚገባ ገልጸው፤ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን ማጥፋት ፈጽሞ እንደማይቻል ከታሪክ ሊረዱ ይገባል በማለት ተናግረዋል፡፡

መንግሥት መግለጫ ከማውጣት ባለፈ በስልጤ ዞን በተቀናጀ መልኩ በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ እና ግፍ ሊያስቆም ይገባዋል።

© EOTC TV

31/03/2022

"እጅግ የምወዳችሁ ምእመናን ሆይ የጾም ጥቅሟ ምን ያህል የበዛ እንደሆነ ነፍሳችን ከዚህ ብዙ ጥቅምን እንደምታገኝ ከጌታችንና እና ከአገልጋዮቹ ተምረናል፡፡ ስለሆነም የጾም ወራት ሲቃረብ ግድ የለሽነትንና ሞራለ ቢስነትን ከእኛ አስወግደን ንዑድ ክቡር የሚሆን ጻውሎስ፡- የውጭው ሰውነታችን ይበልጥ ሲጠፋ የውስጡ ሰውነታችን ይበልጥ ይታደሳል’’ ብሎ እንዳስተማረን እጅግ ደስ ተሰኝተን ልንቀበለው ይገባናል ብዬ እማልዳችኃለሁ፡፡ /2ኛ ቆሮ 4፡16/

ጾም የነፍስ ምግብ ሥጋ ሰውነታችን እንዲወፍር እንደሚያደርግ ሁሉ ጾምም ነፍስን ያበረታል ፈጣንና መንፈሳዊ ክንፍን ይሰጣል፤ ወደ ሰማያዊ ምስጢር ገብታ በፅሞና እንድትያዝ ያደርጋታል የዚህን ዓለም ተድላና ደስታ እንድትንቅ ያስችላታል፡፡

ቀላል ጭነትን የተሸከሙ መርከቦች ፈጥነው ባህሩን እንደሚሻገሩ እጅግ ብዙ ጭነትን የተሸከሙት ግን ባህሩንና ወጀቡን ቶሎ ማለፍ እንደሚያቅታቸው ሁሉ ልክ እንደዚሁ ጾምም ውስጣዊ ምስጢር እንድንገባ በዚያም ስላሉ አይነገሬ በረከቶችን እንድናስብ በዚህ ዓለም ላይ ያሉት ሁሉም ነገሮች እንደ ጠዋት ጤዛ ፈጥነው የሚያልፉ እንደሆኑ እንድንገነዘብ ታደርጋለች፡፡

ከዚሁ በተቃራኒ አብዝቶ መብላትና ራስን አለመግዛት ደግሞ አእምሯችን የጠፋ ሥጋችን የወፈረ ውስጣችን በእግረ ብረት የተጠፈረ በዚህ ሁሉ ተከበን እጅግ በከፉ ምግባራት የተያዝን የዘለዓለማዊ ሕይወታችን ጠላቶች ሆነን እንድንጓዝ ያደርጉናል፡፡

ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ! መብልንና ራስን አለመግዛት ተከትለው የሚመጡትን ኃጣውእ በማወቅ ከድኅነታችን ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ቸልተኞች አንሁን፡፡"

( ኦሪት ዘፍጥረት - በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)

Address

ደብረማርቆስ
Gondar

Telephone

+251972101366

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶዶክሳዊ የመረጃ ማዕከል/Orthodoxy center of Information posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ኦርቶዶክሳዊ የመረጃ ማዕከል/Orthodoxy center of Information:

Share