Shegger Media ሸገር ሚድያ

Shegger Media ሸገር ሚድያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Shegger Media ሸገር ሚድያ, Religious organisation, Oromia, Gimbi.
(1)

" #ፍትሕ የሀገር መሠረት፣ ሰላም ደግሞ የልማት ምንጭ በመሆናቸው፣ ቅድስት ክርስቲያናችን ለዘመናት ያበረከተችውን ታሪካዊ የፍትሕ አቅራቢነት ሚና ዛሬም በተደራጀ መልክ እንድትወጣ የቤተ ክርስ...
27/06/2026

" #ፍትሕ የሀገር መሠረት፣ ሰላም ደግሞ የልማት ምንጭ በመሆናቸው፣ ቅድስት ክርስቲያናችን ለዘመናት ያበረከተችውን ታሪካዊ የፍትሕ አቅራቢነት ሚና ዛሬም በተደራጀ መልክ እንድትወጣ የቤተ ክርስቲያን ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲያገኝና በዐዋጁ መጽደቅ የፍትሕ ሥርዓቷን በራሷ እንድታስቀጥል ሁላችሁም የበኩላችሁን ታሪካዊ እንድታደርጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ
የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ፍርድ ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ውይይት መርሐ ግብር ላይ ካስተላላፉት የመክፈቻ መልእክት የተወሰደ

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራአፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም Sheg...
16/06/2026

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ
አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።

ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም
Shegger Media ሸገር ሚድያ

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅና የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም የደረሰበትን ሁኔታ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በዚሁ ጊዜ የሕንጻ ቤተክርስቲያኑ የዕድሳት ሥራ በተያዘለት ጊዜ ገደብ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ እየተካሔደ የሚገኝ ሲሆን የግንባታ ሥራውም ሰባ ፐርሰንት ተሠርቶ የተጠናቀቀ መሆኑንና በቀሪው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ የግንባታ ሥራው ተጠናቆ
ሐምሌ 17 ቀን ታቦተ ሕጉ ከመቃኞ በመውጣት ወደ ሕንጻ ቤተክርስቲያኑ እንደሚገባ አማካሪ መሐንዲሱ ፕሮፌሰር ፋሲል
እና የሕንጻ ሥራ ተቋራጩ የአዶር ኮንስትራክሽን ባለቤት ኢንጂነር አዲሱ ደመቀ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ባስተላለፉት አባታዊ የሥራ መመሪያ ቀደምት አባቶች ሠርተው ያቆዩልንን ይህን የመሰለ ጥንታዊ ገዳም ተንከባክቦና ጠብቆ ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ በሚቻለው መጠን በርካታ ሥራዎች እየሠራን መሆኑን በተግባር የሚያረጋግጥ ሥራ በዚህ ታላቅ ገዳም እየተከናወነ ስለሆነ ቀሪ ሥራዎች የቤተክርስቲያኑን ጥንታዊነትና ታሪካዊነትን በጠበቀ መልኩ በጊዜው ተጠናቆ ለምርቃት እንዲበቃ።ጠንክራችሁ ሥሩ ካሉ በኋላ የዕድሳት ሥራውን በማከናወን ላይ የሚገኘው አዶር ኮንስትራክሽን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ይህን ሥራ እዚህ ደረጃ ላይ ማድረስ በመቻላቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

በመቀጠልሞ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት የዚህ ታሪካዊ ሥራ አካል በመሆናችን እድለኞች
ነን ካሉ በኋላ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አባታዊ አመራር ሰጪነት
ይህን ታሪካዊ ቤተክርስቲያን ለማደስ በመቻላችን ደስተኞች ነን ብለዋል።አያይዘውም እየተሠራ ያለው ሥራ በጣም የሚደነቅና አፈጻጸሙም የሚያስመሰግን በመሆኑ ሥራውን የምታከናውኑ ባለሙያዎችም ምስጋና ይገባችኋል ካሉ በኋላ ይህ አንጋፋ ቤተክርስቲያን የእድሳት ሥራው እጅግ በጥንቃቄ መሰራት
የሚገባው መሆኑን ተገንዝባችሁ ሥራችሁን ከአሁን በበለጠ ትጋት እንድትፈጽሙ አደራ እንላለን በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

©የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኝነት መምሪያ

በሸገር ሀገረስብከት በ5600 ካ.ሜ ላይ በኮንክሪት ብቻ እየተገነባ የሚገኘው በአፍሪካ ግዙፉ ቤተመቅደስ የሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል ህንጻ ቤ/ክ🥰👌
16/06/2026

በሸገር ሀገረስብከት በ5600 ካ.ሜ ላይ በኮንክሪት ብቻ እየተገነባ የሚገኘው በአፍሪካ ግዙፉ ቤተመቅደስ የሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል ህንጻ ቤ/ክ🥰👌

የለገጣፎ ደብረ ብፁዓን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አቡነ ሀብተ ማርያም እና አቡነ ሐራ ድንግል ዘመናዊ የፀበል ቤት በብፁዕ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተባርኮ ተመረቀ።ግንቦት ...
18/05/2026

የለገጣፎ ደብረ ብፁዓን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አቡነ ሀብተ ማርያም እና አቡነ ሐራ ድንግል ዘመናዊ የፀበል ቤት በብፁዕ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ተባርኮ ተመረቀ።

ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም
Shegger Media ሸገር ሚድያ

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣ በለገጣፎ ለገዳዲ እና ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ ሥር የሚገኘው የደብረ ብፁዓን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ አቡነ ሀብተ ማርያም ወአቡነ ሐራ ድንግል በዘመናዊ መልክ ያስገነባው የፀበል ቤት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ቡራኬ ተባርኮ ተመረቀ።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የለገጣፎ ለገዳዲ እና ኩራ ጂዳ፣ የቡራዩ ገፈርሳ፣ የጉጄ መልካ ኖኖ ክፍላተ ከተማ እንዲሁም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኃይል አባ አፈወርቅ ዮሐንስ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ጸሐፊ መጋቤ አእላፍ ስዩም ብዙአየሁ፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ሐዲስ ሙሴ በለጠ፣ አባቶች ካህናት እና በርካታ ምዕመናንና ምዕመናት ተገኝተዋል።

በዚሁ መርሐ ግብር ላይ የደብሩ አስተዳዳሪ መጋቤ ሐዲስ ሙሴ በለጠ የደብሩን አጠቃላይ የሥራ ሪፖርት ለብፁዕነታቸው አቅርበዋል።

ብፁዕነታቸው በእለቱ ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት፤ "በጌጠኛ ቤትህ ልማት ይሁን" በሚል ኃይለ ቃል ሰፊ ትምህርት የሰጡ ሲሆን፣ ቤተ ክርስቲያን ሁለት ዓይነት ልማቶችን እንደምታከናውን አብራርተዋል።

የመጀመሪያውና ዋናው ልማት የክርስቶስ ሕንጻ የሆነውን የሰውን ልጅ አእምሮ በወንጌል ማልማትና የጠፉትን በጎች ፈልጎ ወደ በረቱ መመለስ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ምዕመናን የሚፈወሱበትን የፀበል ቤት ማዘጋጀትና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንጻዎችን በመገንባት ቤተ ክርስቲያን ራሷን እንድትችል ማድረግ ነው ብለዋል። አክለውም ፀበሉ ለሕሙማንና ለድውያን ትልቅ የፈውስ ቦታ መሆኑን ገልጸዋል።

በመቀጠልም የፀበል ቤቱን ግንባታ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ሙሉ በሙሉ ያሠሩትን ለኃይለ ሚካኤል እና ለባለቤታቸው ለወይዘሮ ሥርጉተ ገብርኤል ብፁዕነታቸው የላቀ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክተውላቸዋል።

በተመሳሳይ መልኩ በዕውቀታቸው፣ በጉልበታቸውና በሐሳባቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምዕመናን የሽልማትና የምስጋና መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በመጨረሻም መርሐ ግብሩ በብፁዕነታቸው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ተጠናቋል።
Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/
Ortoodoksummaan Ulfina
Dirree Tajaajiltootaa የአገልጋዮች መድረክ

17/05/2026

Ethiopia synod’s 🥰🥰✝️🥰

17/05/2026
  በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ከ29 በላይ አዲስ አማንያን በቋንቋቸው ተምረው የሥላሴን ልጅነት አገኙ።|ግንቦት  09 ቀን 2018 ዓ.ምበሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በፉሪ ክፍለ ከተማ ሥር በ...
17/05/2026




በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ከ29 በላይ አዲስ አማንያን በቋንቋቸው ተምረው የሥላሴን ልጅነት አገኙ።

|ግንቦት 09 ቀን 2018 ዓ.ም

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በፉሪ ክፍለ ከተማ ሥር በሚገኘው የጀሞ ደብረ ብርሃን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን፣ በቋንቋቸው ትምህርተ ወንጌልን ሲከታተሉ የቆዩ 29 አዲስ አማንያን በዛሬው ዕለት በብፁዕ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ጥምቀታቸው ተፈጽሞ የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል።

በተያያደ ዜና፣ ብፁዕነታቸው 25 ደቀ መዛሙርት ሥልጣነ ክህነትን የሰጡ ሲሆን፣ ለ18 ዲያቆናት ደግሞ ማዕረገ ቅስናን ሰጥተዋል።

ምንጭ:-ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ
Miidiyaa Shaggar/ሸገር ሀገረ ስብከት ሚዲያ/

Address

Oromia
Gimbi
430123

Telephone

+251925297606

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shegger Media ሸገር ሚድያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Shegger Media ሸገር ሚድያ:

Shortcuts

Share