ዱከም ደብረ ገሊላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ

ዱከም ደብረ ገሊላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ይህ ቤጂ የዱከም ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም እና የዱከም ደብረ ?

14/04/2024
09/10/2022

እንኳን ደህና መጡ!!!
ይህ ፔጅ የዱከም ደብረ ገሊላ ቅዱስ ሚካኤ ቤ/ክ ነው።ወደ ፔጃችን ስለተቀላቀሉ እናመሰግናለን።

09/10/2022

+ ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባችው እንስሳ +

የኖኅ መርከብ ጉዳይ በጣም አስገራሚ ከሚሆኑብኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች አንዱ ነው:: በዓለማችን አሁን ያሉ እንስሳት ሁሉ "ከነ ባለቤትዎ" እንዲገኙልን እንደሚባልበት ሰርግ ጥንድ ጥንድ ሆነው የገቡባት ትልቅ መርከብ ታሪክ : ዳግም ለሰው ልጆች ወላጆች ለመሆን የተመረጡ አራት ወንዶችና አራት ሴቶች ብቻ የተሳፈሩባት ትልቅ መርከብ ሁኔታ ትኩር ብሎ ላየው አስገራሚ እውነቶችን ያዘለ ነው::

ከሁሉም በላይ ግን መርከቢቱ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ መሆንዋ ብዙ ነገር እንድናስብ ያግዘናል:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ወደ ኖኅ መርከብ ተኩላ ገብቶ ሲወጣም ተኩላ ሆኖ ይወጣል:: ወደ ቤተክርስቲያን ግን ተኩላ ሆነው ገብተው በግ ሆነው የወጡ ብዙዎች ናቸው" ብሎአል::

እውነትም ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን መለወጥ የምትችል መርከብ ናት:: ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጅብ ሆዳም ሆነው ገብተው ጾመኞች ሆነው የወጡ አሉ:: እንደ የሌሊት ወፍ በቀን መኖር አቅቶአቸው ሌሊቱን የልባቸው ዓይን ታውሮ በኃጢአት ጨለማ ሲደናበሩ የኖሩ ሰዎች ወደ መርከቢቱ ገብተው እንደ ንስር አርቀው አጥርተው ቀኑን የሚያዩ ሆነዋል:: ቤተ ክርስቲያን ወደ እርስዋ የገቡትን የምትለውጥ መርከብ ናት:: ውኃ ወደ እርስዋ ሲገባ ጠበል ይሆናል:: አፈር ወደ እርስዋ ሲገባ እምነት (እመት) ይሆናል:: ዘይት ወደ እርስዋ ሲገባ ቅዱስ ቅባት ይሆናል:: ኅብስትና ወይን ወደ እርስዋ ሲገባ ወደ ቅዱስ ቁርባን ይለወጣል::

ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ያልተለወጠ ሰው ግን ሲገባም ጅብ ሲወጣም ጅብ ሆኖአል:: ኖኅ ከመርከብ መልእክት ልኮት የቀረው የቁራ ነገርስ? ከቤተ ክርስቲያን ወጥተው ስንቶች በዚያው ቀርተዋል? ለዓለም ጨው እንዲሆኑ ተልከው በዚያው ሟሙተው የቀሩ ስንት አሉ:: ርግብ ግን ማረፊያ ስታጣ ተመልሳ ነበር:: ከመርከቢቱ የራቅን ሁላችን "ልባችን በእግዚአብሔር እስካላረፈ ድረስ ዕረፍት የለውም" እንዳለ ሊቁ ወደ መርከቢቱ ፈጥነን መመለስ አለብን::

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ጥያቄ በአእምሮዬ ተመላለሰብኝ:: "ወደ ኖኅ መርከብ ለመጨረሻ ጊዜ የገባው እንስሳ ማን ሊሆን ይችላል?" የሚል:: ይህን ጥያቄ በግልም በጉባኤ ላይም ሰዎችን ጠይቄ ነበር:: መቼም ለዚህ ጥቅስ አያስፈልገውም:: ኖኅ ቆሞ እንስሳቱ እስኪገቡ ድረስ እንደጠበቀና ማንንም እንስሳ ጥሎ እንዳልገባ የታወቀ ነው::
በዚህ ምክንያት እንስሳቱ ወደ መርከቢቱ የሚገቡት እንደደረሱበት ቅደም ተከተል ነው:: ክንፍ ያላቸው በርረው ቀድመው ይገባሉ:: እንደ ጥንቸል እንደ ካንጋሮ እንደ ሚዳቁዋ ያሉትም እየዘለሉ ፈጥነው ይገባሉ::

ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነፍሳቸውን ለማዳን ፈጥነው በርረው የገቡ እንደ ሚዳቋ ዘልለው የደረሱ ብርቱዎች አሉ:: እንደ ፒኮክ ያሉ ባለ ውብ ክንፎች : እንደ ቀጭኔ ያሉ ባለ ረዥም አንገቶች እንደ ጃርት ያሉ ሌላው ላይ የሚሰኩት እሾኽ የለበሱ እንስሳት ወደ መርከብዋ ገብተዋል:: በቤተክርስቲያን እንደ ፒኮክ አምሮ መታየት መዘባነን የሚወዱ ለታይታ የሚገዙ ብዙዎች ገብተዋል:: እንደ ቀጭኔ አንገታቸውን ከፍ አድርገው ሰውን ቁልቁል የሚመለከቱና "አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ የዕብራውያን ሴቶች" ዓይነት ሕይወት ያላቸውም ገብተዋል:: እንደ ጃርት በክፉ ንግግር የሰው ልብ ላይ የሚሰኩት ጥላቻ የተላበሱ ሰዎችም ገብተዋል:: የኖኅ መርከብ ያልያዘችው እንስሳ እንደሌለ ቤተ ክርስቲያንም ያልተሸከመችው ዓይነት ሰው የለም::

ወደ ጥያቄው ስመለስ በእኔ ግምት ወደ መርከቡ በጣም ዘግይታ የገባችው ኤሊ ነበረች:: በላይዋ ድንጋይ የተጫናት እጅግ ቀርፋፋዋ ኤሊን የማይቀድም እንስሳ መቼም አይኖርም:: ምንም ብትዘገይም ኖኅ እስከመጨረሻው ጠብቆ አስገብቶ ለዘር አትርፎአታል:: የኤሊ ዘሮችም "ኖኅ ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ዳይኖሰር በጠፋን ነበር" ብለው ኖኅን ማመስገናቸው አይቀርም:: እግዚአብሔር ምንም ብትዘገይ ኤሊ ሳትገባ መርከቡን አልዘጋውም::

የኤሊ በመርከቡ መትረፍ በቤተ ክርስቲያን ልንተርፍ ተስፋ ለምናደርግ ለእኛ ትልቅ መጽናኛችን ነው::

ወዳጄ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት እንደ ወፍ ትበርራለህ? እንደ ሚዳቋ ትዘልላለህ? ወይንስ እንደ ኤሊ ትጎተታለህ? እግሮችህ ለመንፈሳዊ ነገር ሲሆን አቅም እያጡ አልተቸገርህም?
ልብህ ቢፈልግም እንደ ኤሊዋ የተጫነህ የኃጢአት ድንጋይ አላንቀሳቅስ ብሎህ አልዘገየህም?

እንዲህ ከሆነ አትጨነቅ መርከብዋ ቤተ ክርስቲያን አንተን ሳትይዝ ጥላህ ወዴትም አትሔድም:: ጉዞህን እስካላቆምህ ድረስ ትጠብቅሃለች:: እየተጎተትህም እየተሳብህም ቢሆን አንተ ብቻ ወደ ደጁ ገስግስ::
አንተ ብቻ መንገድ ጀምር እንጂ ፈጣሪ በሩን የሚዘጋው አንተ እስክትገባ ጠብቆ ነው::

ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር እንዲህ ብለህ ለምነው :-
"ብበድልህም እንኳን አሁንም በርህን እያንኳኳሁ ነው:: እየተጎተትሁም ቢሆን አሁንም የምጉዋዘው ወደ አንተ ለመምጣት ነው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 5 2013 ዓ ም

08/10/2022
እንኳን ደስ አላችሁ ተመርቋል
08/10/2022

እንኳን ደስ አላችሁ ተመርቋል

@ዱከም   2014
19/08/2022

@ዱከም 2014

መልካም ክብረ በዓል  ሰኔ ፲፪ ፳፻፲፬ብፁዕነታቸው እና ሥራ አስኪያጃቸው የሀረ ስብከቱ ሰራተኞች እና የወረዳችን ስራ አስኪያጅ በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት ክቡር መልአከ ምህረት አምሀ የተገኙበ...
21/06/2022

መልካም ክብረ በዓል ሰኔ ፲፪ ፳፻፲፬
ብፁዕነታቸው እና ሥራ አስኪያጃቸው የሀረ ስብከቱ ሰራተኞች እና የወረዳችን ስራ አስኪያጅ በአዲስአበባ ሀገረ ስብከት ክቡር መልአከ ምህረት አምሀ የተገኙበት ደማቅ በዓል ነበር።የዓመት ሰው ይበለን።

ሰኔ ፲፪ ፳፻፲፬
21/06/2022

ሰኔ ፲፪ ፳፻፲፬

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ዛሬ ሰኔ ፲፪ ፳፻፲፬ ዓ.ም በዱከም ደብረ ገሊላ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራ በድምቀት ተክብሮ ዋለ። በእለቱ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አባታችን አቡ...
19/06/2022

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ዛሬ ሰኔ ፲፪ ፳፻፲፬ ዓ.ም በዱከም ደብረ ገሊላ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራ በድምቀት ተክብሮ ዋለ። በእለቱ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የስራ አመራር ኮሌጂ የበላይ ጠባቂ እና የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መ/ምህረት ቆሞስ አባ ገብረ መድህን ንጉሤ እንዲሁም መልአከ ብርሃን ቆሞስ አባ ገብረ ህይወት ሌሎችም የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞች እና ክቡር የወረዳው ስራ እስኪያጅ በርካታ ሊቃውንት እና ምእመናን በበዓሉ ላይ ተግኝተዋል።
ትምህርተ ወንጌል በሀገረ ስብከቱ ሥራአስኪያጅ ተሰጥቷል ።በመቀጠልም በብፁዕነታቸው ትምህርት እና ቃለ ምእዳን ተሰጥቷል።
መለያየት መጠላለፍ መነካከስ እና ግጭትን አጥብቀው ያወገዙት ብፁዕነታቸው የባህራንን የሞት ደብዳቤ ደምስሶ የቀየረው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም ሰዎች በሰዎች ላይ የሚለጥፉትን የጥላቻ እና የሞት ደብዳቤ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ረዳትነት ይደመሰሳል ብለዋል።አያይዘውም ሰው በተስፋ ነገን ማየት እንዳለበት አስገንዝበዋል ።

30/05/2022

Address

Dukem

Telephone

+251911965944

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዱከም ደብረ ገሊላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ዱከም ደብረ ገሊላ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ:

Share