ሳሙኤል ይማነ ቸርነት ዘተዋሕዶ

ሳሙኤል ይማነ ቸርነት ዘተዋሕዶ በብር ለመደገፍ የኢትዬጲያ ንገድ ባንክ1000523215926 ሳሙኤል ይማነ ቸርነት በኢብር 0901777681
ይህ ፔጅ ከዚ በበለጠ ለብዙ ህዝብ ይደርስ ዘንድ በማርያም ስም አግዙን ድንግል በድንግልና አምላካን ወለደችው፡፡

ለኢራን ሳይሆን ለአርሲ እንጩህ።።
04/03/2026

ለኢራን ሳይሆን ለአርሲ እንጩህ።።

ዝምታችን ገዳዮቻችንን አበዛቸው።
01/03/2026

ዝምታችን ገዳዮቻችንን አበዛቸው።

''አርሲ የደ*ም ምድር'' እስከ ምፅዋ ድረስ ሰላም የማስፈን አቅም አለው ያሉት ሰራዊት አርሲ ርርቆት ነው?''ከሀገራችን አልፎ ከሶማልያ እስከ ምፅዋ ድረስ ሰላም የማስፈን አቅም ያለው ብቁ ...
01/03/2026

''አርሲ የደ*ም ምድር'' እስከ ምፅዋ ድረስ ሰላም የማስፈን አቅም አለው ያሉት ሰራዊት አርሲ ርርቆት ነው?''

ከሀገራችን አልፎ ከሶማልያ እስከ ምፅዋ ድረስ ሰላም የማስፈን አቅም ያለው ብቁ ሀይል (elite force) ተዘጋጅቷል ሲባል ከጠቅላይ ሚንስትሩ አንደበት ተሰምቶ ነበር።

ነገር ግን እዚሁ ሀገራችን ውስጥ ከጉያችን ስር ''አርሲ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚፈፀመውን የንፁሀን ግ*ድያ ማስቆም እንዴት አቃተ?''

ትናንት ብቻ በአርሲ ውስጥ ከ30 በላይ ምዕመናን በአ*ሰቃ*ቂ ሁኔታ መገ*ደ*ላቸው ተሰምቷል። ሞ*ትን ተላምደን ነፍስ ይማር ማለት እንኳን እየከበደን መጥቷል'' እየሆነ ያለው ነገር እጅግ ያሳዝናል!😭
ምንጭ
Meseret Media

ዝምታችንም ሞታችንም ቀጥላል።
01/03/2026

ዝምታችንም ሞታችንም ቀጥላል።

28/02/2026
በአርሲ በእምነታቸው ምክንያት 21 ኦርቶዶክሳዊያን በግፍ ተጨፈጨፉ።አሁንም ቢሆን ቤት ማቃጠሉ ቀጥላል። እባካቹ ሼር በማድረግ እንካን መከታ እንሁንላቸው።
28/02/2026

በአርሲ በእምነታቸው ምክንያት 21 ኦርቶዶክሳዊያን በግፍ ተጨፈጨፉ።
አሁንም ቢሆን ቤት ማቃጠሉ ቀጥላል። እባካቹ ሼር በማድረግ እንካን መከታ እንሁንላቸው።

ማርያም ሲባል ቅር የሚልህ ወንድሜ ኢየሱስ አፉን የፈታው ማርያም እያለ መሆኑን ላስታውስህ እወዳለሁ:: መቼም ለዚህም ጥቅስ እንደማትጠይቀኝ ተስፋ አደርጋለሁ::ኢየሱስ ሲባል ቅር የሚልሽ እኅቴ...
09/12/2025

ማርያም ሲባል ቅር የሚልህ ወንድሜ ኢየሱስ አፉን የፈታው ማርያም እያለ መሆኑን ላስታውስህ እወዳለሁ:: መቼም ለዚህም ጥቅስ እንደማትጠይቀኝ ተስፋ አደርጋለሁ::

ኢየሱስ ሲባል ቅር የሚልሽ እኅቴ ማርያም ከሰማይ ሰምታ ለልጅዋ ያወጣችው ስም ኢየሱስ እንደሆነ ላስታውስህ እወዳለሁ::

በእርግጥ ድንግል ማርያም ኢየሱስ ብላ ብትሰይመውም ስሙን ግን ለመጥራት ግን አንድ ቃል አልበቃት ብሎ ተቸግራ ነበር::

ገና በሆድዋ ውስጥ እያለ ወደ እርሱ ስትጸልይ "ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች:: መንፈሴም በአምላኬና በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች" ስትል ሰማናት:: ልጅዋ ከሆድዋ ሳይወጣ ከልጅዋ ጋር ንግግር የጀመረች እናት እንዴት ያለች ናት? ወደ ሆድዋ ራስዋን ዘንበል አድርጋ "ጌታዬ አምላኬ መድኃኒቴ" እያለች የምትጣራ እናት አይታችሁ ታውቁ ይሆን? በሆድዋ ውስጥ ዙፋኑን ለዘረጋው ንጉሥ ጸሎት የምታሰማ እናት እንደምን ያለች ናት?

ከወለደችው በኋላስ ማን ብላ ጠርታው ይሆን? ገና ሕፃን ሳለ ምን ብላ አቅፋ አስተኛችው ይሆን? ምን ብላስ መገበችው?
የልደት መዝሙሩን "እሹሩሩ" (lullaby) ብሎ የሰየመው ቅዱስ ኤፍሬም ድንግል ማርያም ልጅዋን ምን እያለች ታስተኛው ይሆን? ብሎ በእርስዋ ቦታ ይጨነቃል:: በእርስዋ አንደበት ሆኖ እንዲህ ሲል ወደ ልጅዋ ይዘምራል::

" አንተ ምንጭ ሆይ ለአንተ ለማጠጣት የጡቶችን
ምንጭ እንዴት ልከፍታቸው ይቻለኛል? ሁሉን
ከገበታህ የምትመግብ ሆይ እኔ አንተን ልመግብህ
እንዴት ይቻለኛል? የክብርን ነጸብራቅ የተጎናፀፍከው
ሆይ እንደምን በጨርቅ ልጠቀልልህ እችላለሁ?"

ለአንተ እንዴት ያለ የማባበል ዜማን ላዜምልህ
እችላለሁ? እንደማንኛውም ሕፃን ለአንተ እሹሩሩ ብዬ
እንዳልዘምርልህ እንደ ማንኛውም ሰው ተራ ልደትን
የተወለድህ አይደለህም፡፡ ፅንሰትህ አዲስ ነው ፤
ልደትህም ተአምር ነው፡፡ በመንፈስ ካልሆነ ለአንተ
ሊዘምር የሚችል ማን ነው?’

ድንግል ማርያም ሆድዋ ውስጥ ሳለ አምላኬ መድኃኒቴ ያለችው ልጅዋን ካደገ በኋላ ምን ብላ ጠርታው ይሆን ብዬ በዐሥራ ሁለት ዓመቱ በቤተ መቅደስ እስክታገኘው ጠብቄ ተከትያት ገባሁ:: ከአይሁድ መምህራን ሥር ቁጭ ብሎ በንግግሩ ያስደንቃቸዋል:: (ሉቃ. 2:48)

ምን ብላ ትጠራው ይሆን ብዬ አንደበትዋን ስጠባበቅ
"ልጄ ሆይ" አለችው:: እኛ አባታችን ሆይ የምንለውን ፈጣሪ ልጄ ሆይ አለችው::

ድንግል ማርያም ለልጅዋ የሚበቃው ስም አጥታለት ነበርና እርሱን የምትጠራበት ብዙ ስም ነበራት:: በእናቶቻችን "ማን ብዬ ልጥራው ስምህን" ዜማ ድንግሊቱ ተጨንቃለች::

"ማን ብዬ ብጠራህ ይሻለኛል? ልጄ ብዬ ልጥራህ? ወንድሜ ልበልህ? ሙሽራዬስ ብዬ ልጥራህ? ጌታዬስ ልበልህ? ከዳዊት ቤት እንደመሆኔ እኅትህ ነኝ፡፡ ስለፀነስሁህ እናትህ ነኝ ፤ ስለ ንጽሕናህ ሙሽራህ ነኝ ፤ መድኃኒቴ ነህና ባሪያህና ልጅህ ነኝ’

አምላኬ ጌታዬ መድኃኒቴ ልጄ!

(St. Ephrem The Syrian, Harp of Spirit)

ማርያምና ኢየሱስ የሚሉት ስሞች ወንጌላውያን ሁለት ጎራ ይዘው የተጣሉባቸው ሳይሆኑ በምናከብረው ወንጌል ላይ አብረው የተጻፉ ስሞች ናቸው::ኢየሱስ የሚለው ስም ከድንግል ማርያም አፍ በፍቅር የሚፈስስ ጥዑም ስም ነበረ:: ማርያም የሚለው ስም ደግሞ ኢየሱስ ከሰው ልጆች ሁሉ በላይ በእናት ፍቅር ሆኖ የጠራው ጥዑም ስም ነው::

የልጅዋ ስም ሲጠራ የምታዝን ማርያም የእናቱ ስም ሲጠራ የሚናደድ ኢየሱስም የለም::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር ጽዮን 2018 ዓ.ም.

📝መረጃ 👉በምዕራብ እና በምሥራቅ ሐረርጌ ዳር ዳር ባሉ ቦታዎች ላይ ክርስቲያኖችም ስጋት ላይ ያሉ መሆናቸውን ከቦታው በሚገኙ የመረጃ ምንጮች ያደረሱን ሲሆን👉ይህንን ተከትሎ  በቅርቡ በምዕራብ...
19/11/2025

📝መረጃ

👉በምዕራብ እና በምሥራቅ ሐረርጌ ዳር ዳር ባሉ ቦታዎች ላይ ክርስቲያኖችም ስጋት ላይ ያሉ መሆናቸውን ከቦታው በሚገኙ የመረጃ ምንጮች ያደረሱን ሲሆን

👉ይህንን ተከትሎ በቅርቡ በምዕራብ ሐረርጌ በጉባ ጉቱና አው ጉዲና ወረዳዎች እንዲሁም በጭሮ ወረዳ በረብሱ አካባቢ እስከ አሁን ድረስ የስድስት ሰዎች ህይወት በአስቃቂ ሁኔታ ያለፈ ሲሆን መንጋውን እንዲጠብቁ አደራ የተሰጣቸው አባቶች ዛሬም ዝምታን መርጠዋል ። ይህም መረጃ ለሀገረ ስብከቱም ሆነ ለቤተክህነቱ የደረሰ ሲሆን እስካሁን ለሞቱትም አዝኖ የሀዘን መግለጫም ሆነ አንድም መልእክት አለመተላለፉ ልብ ይሰብራል ፦

👉ዛሬም ኦርቶዶክሳውያን ክርስትያኖች በተለያዩ የኦሮምያ ክልል በስጋት እና በፍራቻ ፣ ገዳይ በዙሪያቸው ቃታውን እየሳበ ፣ ሀብት ንብረታቸውን እየዘረፈ ፣ ገሚሶቹን በአሰቃቂ ሁኔታ እገደለ ይገኛል ፣ ምንም የሕግ ከለላ የላቸውም ፣ ድምፃችንን በጋራ እናሰማ ፣ ሼር ቤተሰቦች 🙏

🙏በግፍ ለሞቱ ኦርቶዶክሳውያን ድምፅ እንሁን 🙏

አሳዛኝ መረጃ:-  ሐረርጌበምዕራብ ሐረርጌ በጉባ ጉቱ እና አው ጉዲና ወረዳዎች እንዲሁም በጭሮ ወረዳ በረብሱ አካባቢ እስከ አሁን ድረስ የስድስት ኦርቶዶክሳዊያን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀጥ...
19/11/2025

አሳዛኝ መረጃ:- ሐረርጌ

በምዕራብ ሐረርጌ በጉባ ጉቱ እና አው ጉዲና ወረዳዎች እንዲሁም በጭሮ ወረዳ በረብሱ አካባቢ እስከ አሁን ድረስ የስድስት ኦርቶዶክሳዊያን ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ተቀጥፏል ።

በምስራቅ ሐረርጌ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዳር ዳር ባሉ ቦታዎች ላይ ኦርቶዶክሳዊያን አሁንም በስጋት ላይ ናቸው።

ይህ መረጃ መንጋውን ለሚጠብቁ አደራ ለተሰጣቸው ለሀገረ ስብከቱም ለቤተ ክህነቱም የተላለፈ ቢሆንም አባቶች ዝምታን መርጠዋል ።

ነፍስ ይማር!

በግፍ እየተገደ,ሉ ላሉ ኦርቶዶክሳዊያን ሁላችንም ድምጽ እንሁን !
STOP KILLING CHRISTIANS

ፍትህ ለአርሲ ኦርቶዶክሳዊያን።።።።።።
16/11/2025

ፍትህ ለአርሲ ኦርቶዶክሳዊያን።።።።።።

16/11/2025

ለምሥ/አርሲ ዞን የ ጀጁ ወረዳ ባለሥልጣናት
=======
(በ ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ )
** የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ጭፍጨፋ፣ ንብረት ውድመት እና ስደት ካለባቸው አካባቢዎች መካከል ጀጁ ወረዳ አንዱ ነው፤
Kominikeeshinii Jajuu
** ይህንን ጭፍጨፋ፣ ንብረት ውድመት እና ስደት ማስቆም የሚችሉት ሰዎች ደግሞ እነዚህ ናቸው።
======
Urgent Notice:-

The following government officials have the authority to stop the ongoing Orthodox Christian massacres in East Arsi Zone, Jeju District (Wereda):

** Redwan Jemal – Wereda Administrator

** Misbahu Seida – Wereda Deputy Administrator

** Abdulmalik Kedir – Wereda Prosperity Party Secretary
======

 #ዝቋላ  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ~~~~~~~~~~~~~~~~~  #ዝቋላ  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ  ለ100 አመት የፀለዩበት ፀበል።ይሄ ፀበል አሁንም ድረስ ድውያንን ያነፃ የታመሙትን የ...
16/11/2025

#ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
~~~~~~~~~~~~~~~~~
#ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ100 አመት የፀለዩበት ፀበል።
ይሄ ፀበል አሁንም ድረስ ድውያንን ያነፃ የታመሙትን የፈወሰ ታላቅ ፀበል ነው

ምስራቅ ሸዋ ዝቋላ ብዙ ሰው ለመዝናናት እራስን ከጭንቀት ለማራቅ ሲሉ ላንጋኖ ሶደሬ፣ወይም፣ኩሪፍቱ የመሳሰሉት የመዝናኛ ቦታዎችን መርጠው ብዙ ገንዘባቸውን ከፍለው የስጋዊ ፍላጎታቸውን ፈፅመው ይመለሳሉ።

ግን እንደነዚህ ያሉ የመንፈስ እርካታ እሚገኝባቸው ሰማያዊ ቤትን እሚታነፅባቸው በሀጢያት በበደል የቆሸሸው ልባችን እሚነፃበት ቅዱስ ስፍራ በነፃም ቢሆን ለመሄድ እንሰንፋለን።

ይህ ገዳም በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን እሚፈሱበት ታላቅ ገዳም ነው።

በተለይ ጥቅምት5 እና መጋቢት 5 ጠጠር መጣያ አይገኝም።

ይህንን ቦታ ለገዳምነት ያበቁት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ናቸው።
ከተራራው አናት ሀይቅ አለ በውብ ደን የተሸፈነ ሲያዩት ደስታን እሚፈጥር ውጡ ውጡ እማይል ድንቅ ስፍራ ነው።
ይህን የተራራ አካል በግር ተጉዞ ለመጨረስ እስከ 3 ሰአት ይፈጃል።

አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ለ 100 አመት በዚህ ስፍራ ፀልየውበታል።

እረድኤት በረከታቸው ይደርብን።!

Address

United State
Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሳሙኤል ይማነ ቸርነት ዘተዋሕዶ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ሳሙኤል ይማነ ቸርነት ዘተዋሕዶ:

Shortcuts

Share