Dilla Town Kale Hiwot Church Sunday School - የዲላ ከተማ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Dilla
  • Dilla Town Kale Hiwot Church Sunday School - የዲላ ከተማ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤት

Dilla Town Kale Hiwot Church Sunday School - የዲላ ከተማ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤት ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፥ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።
— ኢሳይያስ 54፥13

 !__________________________________________________________ከነሐሴ 23 እስከ 25  2017 የምህረት ዓመት ሌላ ቀጠሮ እንዳይዙ።
26/08/2025

!
__________________________________________________________

ከነሐሴ 23 እስከ 25 2017 የምህረት ዓመት ሌላ ቀጠሮ እንዳይዙ።

የትዝታ ሰበዞችን እየመዘዝን ከወዲህ ወዲያ በሀሴት እየተንጎማለልን ማክበር የጀመርነው 31ኛው የምስጋና ክብረ በዓላችን እነሆ ዛሬ መቋጫውን አግኝቷል።ድር ከማግ ተሸምኖ የጥለቱ ቁጭት እንደሚያ...
24/08/2025

የትዝታ ሰበዞችን እየመዘዝን ከወዲህ ወዲያ በሀሴት እየተንጎማለልን ማክበር የጀመርነው 31ኛው የምስጋና ክብረ በዓላችን እነሆ ዛሬ መቋጫውን አግኝቷል።

ድር ከማግ ተሸምኖ የጥለቱ ቁጭት እንደሚያምረው ውብ ሸማ በእግዚአብሐር እርዳታ ታግዘን 31ኛውን ምዕራፍ ደምድመን ወደ 32ኛው ተንደርድረናል።

ክብር ሁሉ ለረዳን ለእግዚአብሔር ይሁን!!!! 🙏🙏🙏

እስከ አሁን በትእግስት አብራችሁን ለነበራችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው።

ዛሬም እንዲህ ባማረ መልኩ በዓሉን ማክበራችን እንደ ቀጠለ ነው።ለመሆኑ ለትዝታ የሚሆን ፎቶ ተነስተዋል?
24/08/2025

ዛሬም እንዲህ ባማረ መልኩ በዓሉን ማክበራችን እንደ ቀጠለ ነው።

ለመሆኑ ለትዝታ የሚሆን ፎቶ ተነስተዋል?

23/08/2025
ዛሬም የበዓሉ ድባብ ውብ በሆነ መልኩ እንደ ቀጠለ ነው።የስዕል ጥበብን የምትወዱ የት ናችሁ?ጥበብ እኛ ጋር ሆና ድምጽዋን ከፍ አድርጋ ትጠራችኋለች!
23/08/2025

ዛሬም የበዓሉ ድባብ ውብ በሆነ መልኩ እንደ ቀጠለ ነው።

የስዕል ጥበብን የምትወዱ የት ናችሁ?

ጥበብ እኛ ጋር ሆና ድምጽዋን ከፍ አድርጋ ትጠራችኋለች!

የሰንበት ሕጻናት መምህራንን ተዋወቋቸው።ከስንቶቹ ጋር ወዳጅ ናችሁ? እስኪ በምስሉ ላይ የምታውቋቸው መምህራንን በሜንሽን ጥሯቸው።
18/08/2025

የሰንበት ሕጻናት መምህራንን ተዋወቋቸው።

ከስንቶቹ ጋር ወዳጅ ናችሁ? እስኪ በምስሉ ላይ የምታውቋቸው መምህራንን በሜንሽን ጥሯቸው።

የሌዊ ቤተሰብን ተዋወቋቸው።
17/08/2025

የሌዊ ቤተሰብን ተዋወቋቸው።

ዛሬ ምን ይዘንሎት እንደመጣን እስቲ ገምቱ? የ31 አመታት የእግዚአብሔር የተአምራቱ ትዝታዎች ያረፉበት፣ በፍቅሩ ቀለም የቀለሙ፣ የናርዶሱ ሽቱ የተርከፈከፈባቸው ውድ ስጦታዎች እነሆ! 🎉👕 እነ...
16/08/2025

ዛሬ ምን ይዘንሎት እንደመጣን እስቲ ገምቱ?

የ31 አመታት የእግዚአብሔር የተአምራቱ ትዝታዎች ያረፉበት፣ በፍቅሩ ቀለም የቀለሙ፣ የናርዶሱ ሽቱ የተርከፈከፈባቸው ውድ ስጦታዎች እነሆ! 🎉

👕 እነዚህ ጉርድ ሸሚዞች (T Shirts) የ31 ዓመታት እምነትን፣ ደስታን እና ሞገስን ያነገቱ ናቸው።
ቲ ሽርቱን በመልበስ የክርቶስን ሞገስ ይላበሱ፣ መልካም መዓዛውንም ይጠርኑ!
በበዓሉ ላይ በመገኘት ቲሸርቱን በመልበስዎ ውስጥዎ በሚፈጥረው ሀሴት ይገማሸሩ✨🙌

👉 እያንዳንዱን ቲ ሸርት ለነገ ትውልዶች የማምለኪያ አዳራሽ ማሰሪያ በሚውል ፫ መቶ የኢትዮጵያ ብር ብቻ ይሸጣሉ ብንል መልካም ነበረ ነገር ግን ይለገሳል።

🫴 ያለን ቲ ሸርት በቁጥር 300 ፍሬ ብቻ ስለሆነ ቀድሞ በመግዛት ይድመቁበት።

እኔ ገዝቻለሁ! እናንተስ?

Address

Dilla

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dilla Town Kale Hiwot Church Sunday School - የዲላ ከተማ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share