17/01/2022
#ሞታ ከመቀበሯ ከአራት ቀን በፊት አንድ እናት ለልጇ ያስቀመጠችው በሞባይል የተቀዳ ብዙዎችን #ከእንቅልፍ ያነቃ #መልዕክት እንዲህ ይላል ፡፡
✿ ልጄ ሁሉ ነገሬ : እኔ ልሞት ነው ፡፡
♦አንተን የመሰለ ልጅ እያለኝ ፥ አውቃለሁ እኔ ለምን እንደዚህ ከነደህነቴ ከነችግሬ እንደምሞት ።
ምክንያቱም ፥ ወላጆቼ ሳላውቅ በወጣትነት ጊዜ ለበደልኳቸው በደል መቅጣት ሲገባቸው ሁሌ እንዲህ እያሉኝ ይራገሙኝ ነበረ
" ! " ፡፡
ለዚህ ነው የረሳኽኝ እንጂ አንተ ለኔ ክፉ ሆነ አይደለም ፡፡
☞ የህይወቴ ትልቁ ችግር ፥ ቁርስ በልቼ ምሳ ምን ልብላ ፣ ምሳ በልቼ እራት ምን ልብላ የሚል ነበረ ፤ አንተ ግን በቤትህ ከነቤተሰብህ መርጠህ ስጋ እና ቅቤ እየበላህ ነው ፡፡
☞ አውቃለሁ ልጄ ፥ ለቀብር ቀኔ ስጋ እና ቅቤ በብዙ ብር ለህዝቡ እንደምታዘጋጅ እኔ ግን በህይወት ዘመኔ ለምግብ ያላወጣሁትን፡፡
☞ አውቃለሁ ልጄ ፥ አስክሬነን በውድ ሽቶ እንደምትቀባ እሱን እኔ በህይወቴ ተቀብቼ የማላውቀውን ፡፡
☞ አውቃለሁ ልጄ ፥ በድነን በውድ ዘይት ብዙ ብር አውጥተህ እንደምትቀባ ፥ እሱን እኔ አይቼ የማላውቀውዉ ነዉ ፡፡
☞ አውቃለሁ ልጄ ፥ አስክሬኔን በውድ ዋጋ በብዙ ብር ከፈን ገዝተህ እንደምታለብሰኝ ፤ እኔ ግን በህይወት እያለሁ ባንድ ልብስ አረጀሁኝ አንተ መርጠህ እንድትለብስ ብዬ ፡፡
☞ አውቃለሁ ልጄ ፥ ለመቃብር በጣም ትልቅ ቤት እንደምትገነባ እኔ ግን በቀዳዳ ቤት ኖርያለሁ ፡፡
☞ አውቃለሁ ልጄ ፥ በየቀኑ ወደ መቃብሬ ስፍራ ትመጣለህ " እናቴ እወድሻለሁ " ትላለህ ፤ እኔ ግን አሁን ከመሞቴ በፊት ልባርክህ ፈልጌ አጥቼአለሁ አንዴ ላይህ ላቅፍ አጥችያለሁ ፡፡
☞ አውቃለሁ ልጄ ፥ ሰዎች ምንም ብሎ አንተን ቢናገሩም ፥ አንተ በኔ ጨክነክብኝ አይደለም ፤ የወላጆቼ መርገም ነው እንዲህ ያደረገኝ::
♦ ስለዚህ ፥ ምንም ብትበድለኝም ይቅር ብያለሁ ልጄ" " በኔ አይችያለሁና
ከኑሬ ረጋሳ