27/10/2024
=================
ጽንስ ከትክክለኛው ጊዜ በፊት ቢወለድ ጤናማ ሆኖ የማደጉ ጉዳይ ፈተና ላይ ስለሚወድቅ መቸኮል አያስፈልግም። ከመወለጃ ጊዜው ቀድሞ የሚወለድ ጽንስ ከፍተኛ የሕክምና ክትትል ካልተደረገለት በቀር በአካሉ፣ በስነልቦናውና ባጠቃላይ ዕድገቱ ላይ ዕክል ያጋጥመዋል። ከፍ ሲልም የመጨናገፍ ዕድልም ሊኖር ይችላል።
በተቃራኒው መንገድ የመወለጃ ጊዜው አልፎ በማህጸን የሚቆይ ጽንስ የእናቱን በሕይወት የመኖር ጉዳይ አደጋ ላይ ይጥላል :: አንዲት እናት የጸነሰችውን ጽንስ ለመውለድ ሌሎች ነገሮች እንዳሉ ሆነው ከ37 እስከ 42 ሳምንታት መቆየት አለባት ተብሎ ይታመናል፡፡ ለጽንስ ትክክለኛውን ጊዜ ጠብቆ መወለድ እጅግ ጠቃሚ ጉዳይ ነው፡፡
ስለዚህም አንተም የህልምህን ትክክለኛ ጊዜ አውቀህ ብትሰራበት ልክ ጤናማ ልጅ ወልዶ እንደመሳም ልብ ያሞቃል።
የተወለደውን ልጅ መንከባከብ፣ ማሳደግና ለወግ ማዕረግ ማድረስ ደግሞ የማንም ሳይሆን የወላጅ ኃላፊነት እንደሆነ ሁሉ አንተም እግዚአብሔር በውስጥህ ያስቀመጠውን ራዕይ ጊዜዉን አዉቀህ ወደሚታይ ፍሬ እንድትቀይር ይጠበቅብሃል፡፡
ከተሰኘ መፅሐፍ የተወሰደ