World Peace

World Peace ሰላም ኢስላማዊ ወንድማማችነት በአንድነት እስከ ጀነት።

══════════════════════════
╭─┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅─╮
http://telegram.me/WorldPeacefully
https://mobile.twitter.com/PeacefullyWorld
https://www.facebook.com/WorldPeacefully
https://www.instagram.com/WorldPeacefully
╰─┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅─╯
══════════════════════════
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
Like � Follow� Comment� Invite �Share

""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""

20/12/2025

17/12/2025


World Peace

17/12/2025

15/12/2025

World Peace




ሙሐመድ ﷺ ምስጉኑ ❤اللَّهُمَّ صل عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍإِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِ...
05/12/2025

ሙሐመድ ﷺ ምስጉኑ ❤
اللَّهُمَّ صل عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
(አል-አሕዛብ፡ 56)
World Peacefully

ነብያችን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲያልፉ ብዙዎቹ ድንጋጤ ዉስጥ ገብተው ነበር። ከፊሎቹ አልሞቱም ብለዉ እስከ መሞገት ደርሰዋል ። የተቀሩት ደግሞ እግራቸው ለመቆም ምላሳቸው ለመናገር አቅም...
21/10/2025

ነብያችን (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲያልፉ ብዙዎቹ ድንጋጤ ዉስጥ ገብተው ነበር። ከፊሎቹ አልሞቱም ብለዉ እስከ መሞገት ደርሰዋል ። የተቀሩት ደግሞ እግራቸው ለመቆም ምላሳቸው ለመናገር አቅም ገደደው።

ህልፈተ ዜናው የደረሳቸዉ አቡበክር ሲዲቅ ከእናታችን አዒሻ ቤት ገብተዉ ያንን በሻሻ ፊት ደጋግመው ሳሙት ። ከዚያዉ ወደ መስጂድ አመሩ ። ሰይድ ዑመር ከመስጂድ ዉስጥ እየተናገሩ ሳለ አቡበክር መናገር ጀመሩ ። የመስጂዱ ታዳሚ ትኩረቱን ወደ አቡበክር ሲዲቅ አዞረ። አቡበክር ሲዲቅም እንዲህ ሲሉ ተናገሩ ፤

"من كان يعبد محمدا فإن محمدا قد مات ومن كان يعبد الله فإن الله حي لا يموت."

"ሙሐመድን የሚያመልክ ሰው ካለ መሐመድ በርግጥ ሞተዋል ። አላህን የሚያመልክ ሰው ግን አላህ ህያው ነው አይሞትም።

አስከትለዉም እንዲህ የሚለዉን የቁርዐን አያት አነበቡ ፡

وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ ۚ أَفَإِن مَّاتَ أَوْ قُتِلَ انقَلَبْتُمْ عَلَىٰ أَعْقَابِكُمْ ۚ وَمَن يَنقَلِبْ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ فَلَن يَضُرَّ اللَّهَ شَيْئًا ۗ وَسَيَجْزِي اللَّهُ الشَّاكِرِينَ

“ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ ታዲያ ቢሞት ወይም ቢገደል ወደ ኋላችሁ ትገለበጣላችሁን ወደኋላው የሚገለበጥም ሰው አላህን ምንም አይጎዳም፡፡ አላህም አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል፡፡”

World Peacefully

20/10/2025

إنا لله وإنا إليه راجعون
እኛ የአላህ ነን ወደ አላህም ተመላሾች ነን

{كُلُّ نَفْسٍۢ ذَآئِقَةُ ٱلْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ ۖ فَمَن زُحْزِحَ عَنِ ٱلنَّارِ وَأُدْخِلَ ٱلْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَآ إِلَّا مَتَٰعُ ٱلْغُرُورِ }

(( ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡))

Every soul will taste death, and you will only be given your [full] compensation on the Day of Resurrection. So he who is drawn away from the Fire and admitted to Paradise has attained [his desire]. And what is the life of this world except the enjoyment of delusion.

Al-Imran [3:185]
World Peacefully

በ  #አፋር ክልል ዳሎል ወረዳ  ዶሮባ የሚባል ገጠራማ አከባቢ የሚገኝ ውብ  #መስጅድ 🕌
26/07/2023

በ #አፋር ክልል ዳሎል ወረዳ ዶሮባ የሚባል ገጠራማ አከባቢ የሚገኝ ውብ #መስጅድ 🕌

ጁመዓ ሙባረክ!!
21/07/2023

ጁመዓ ሙባረክ!!

||ይህን ያውቁ ኖሯል||  አስሩ የግመል ወተት የጤና ጥቅሞች *******************************************1. ለአመጋገብ ስርዓት (Nutritional value ) ~ ...
19/07/2023

||ይህን ያውቁ ኖሯል|| አስሩ የግመል ወተት የጤና ጥቅሞች
*******************************************
1. ለአመጋገብ ስርዓት (Nutritional value ) ~ የግመል ወተት እንደ ፕሮቲኖች፣ ቫይታሚን (ኤ፣ ቢ1፣ ቢ2፣ ሲ እና ዲ)፣ ማዕድናት (ካልሲየም፣ ብረት፣ ፖታሲየም እና ማግኒዚየም) እና ያልተሟላ ቅባት አሲድ ባሉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ነው። እንደ ጥሩ የካልሲየም ምንጭ ተደርጎ ይቆጠራል፣ ከላም ወተት ጋር ሲነጻጸር በአንድ አገልግሎት ሶስት እጥፍ የሚበልጥ ካልሲየም ያቀርባል።

2. ለምግብ እንሽርሽሪት (Digestibility) - በግመል ወተት ውስጥ ያሉት የስብ ሞለኪውሎች ከላም ወተት ውስጥ ካሉት ያነሱ እና በቀላሉ የሚፈጩ ናቸው። ይህ የላክቶስ አለመስማማት ወይም የጨጓራና ትራክት ችግር ላለባቸው ሰዎች ተስማሚ አማራጭ ያደርገዋል። በተጨማሪም የግመል ወተት የምግብ መፈጨት የጤና ጠቀሜታ እንዳላቸው የሚታመኑ የተወሰኑ ፕሮቲኖችን ይዟል።

3. በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያዳብሩ ባህሪያት፡- የግመል ወተት በተፈጥሮ የተገኘ ኃይለኛ ፀረ እንግዳ አካላትን በውስጡ የያዘው በሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ ለማድረግ እና ከተለያዩ ኢንፌክሽኖች እና በሽታዎች ለመከላከል ይረዳል።

4 . የስኳር በሽታን መቆጣጠር፡- ጥናቶች እንደሚያሳዩት የግመል ወተት ዝቅተኛ የላክቶስ መጠን እና ከፍተኛ የኢንሱሊን ይዘት ያለው በመሆኑ የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር አጋዥ ያደርገዋል። በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር እና የኢንሱሊን ስሜትን ለማሻሻል የሚረዳ ሆኖ ተገኝቷል።

5. የልብ ጤና፡- የግመል ወተት ከላም ወተት ጋር ሲነፃፀር በኮሌስትሮል እና በቅባት የበለፀገ ነው። በተጨማሪም በውስጡ ከፍተኛ መጠን ያለው ኦሜጋ -3 ፋቲ አሲድ ይዟል። እነዚህም የልብ ጤናን እንደሚያሻሽሉ እና የልብ እና የደም ቧንቧ በሽታዎችን አደጋን ይቀንሳል.

6 . የኦቲዝም አስተዳደር፡ አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የግመል ወተት ኦቲዝም ስፔክትረም ዲስኦርደር ባለባቸው ግለሰቦች ላይ ጠቃሚ ተጽእኖ ይኖረዋል። በአንዳንድ የኦቲዝም ልጆች ውስጥ ባህሪን ፣ የእውቀት (ኮግኒቲቭ) ተግባራትን እና ማህበራዊ ግንኙነቶችን ለማሻሻል ተስተውሏል። ይሁን እንጂ እነዚህን ግኝቶች ለማረጋገጥ ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ።

7. የቆዳ ጤንነት፡- በግመል ወተት ውስጥ ያለው ከፍተኛ የቫይታሚንና ማዕድን ይዘት ለቆዳ ጤናማነት አስተዋጽኦ ያደርጋል። ፀረ-እርጅና ባህሪያት እንዳለው ይታመናል። የቆዳን ድርቀት ይከላከላል ፣እብጠትን ይቀንሳል ፣ እና እንደ ኤክማ እና psoriasis ባሉ ሁኔታዎች ላይ ሊረዳ ይችላል.

8. አለርጂ እና አስም፡- የግመል ወተት ከላም ወተት ጋር ሲወዳደር የተለያዩ ፕሮቲኖችን ይይዛል ይህም ለአንዳንድ ግለሰቦች አለርጂ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጥናቶች የግመል ወተት ከበሉ በኋላ ለአለርጂ እና አስም ላለባቸው ሰዎች አወንታዊ ውጤቶችን አመልክተዋል።

9. ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪያት፡- በግመል ወተት ውስጥ የሚገኙ የተወሰኑ ፕሮቲኖች እና peptides ፀረ-ተህዋስያን ባህሪ ስላላቸው ከተለያዩ የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖች ጋር ለመዋጋት ይረዳሉ።

10.ከባህላዊ የወተት እርባታ ጋር ሲነጻጸር የግመል ወተት ምርት በጣም ያነሰ ውሃ፣ መኖ እና መሬት ይፈልጋል። ግመሎች ለከባድ በረሃማ አካባቢዎች የተላመዱ በመሆናቸው ለአየር ንብረት ለውጥ የበለጠ የመቋቋም ችሎታ ያላቸው እና የወተት ምርታቸው ዝቅተኛ የአካባቢ ተፅእኖ አለው ።

World Peacefully

19/07/2023

እንኳን ለ1445ኛው አመተ-ሂጅራ በሰላም አደረሰን
ሂጅራ የነፃነት አየር ፍለጋ የተደረገ ስደት ነው፤ ያ ነፃነት የአላህን መንገድ የመከተል እውነተኛ ነፃነት ነው።
ሂጅራን ስናስብ ነፃነትን እናስባለን፤ ነፃነትን ስናስብ ከመሬት ስበት ከፍ ብሎ ለአንድ አምላክ አላህ(ሱ.ወ.) ታዛዥ መሆንን እናስባለን።

“ሙእሚን ማለት ሰዎች በንብረታቸው የሚያምኑት ሰው ነው፤ ስደተኛ(ሙሃጅር) ማለት ወንጀሎችንና ኃጢአቶችን የሚርቅ ሰው ነው።” ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዓ.ወ.)

ባለፉት አመታት የሰራናቸውን መልካም ተግባራት ይበልጥ የምናጠናክርበት፣ አስበን ያላሳካናቸውን እቅዶቻችንን የምንከልስበትና የምንተገብርበት፥ በአጠቃላይ ከፈጣሪና ከፍጡራን ጋር እርቅ ፈጥረን በምድር ላይ መልካም አሻራችንን የምናሳርፍበት ዓመት ይሆንልን ዘንድ እመኛለሁ።

1 Muharram 1445 AH

Address

Dessie
WOLLO

Website

http://telegram.me/WorldPeacefully

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when World Peace posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to World Peace:

Share