Daiwa selefya for all umah

Daiwa selefya for all umah Allah is only one the messenger is muhammed

 #ማስተንተን ለተቸረዉ አጂብ የሆነ የጌታችን ንግግር:-👇👇👇👇 قوله تعالى: ﴿زَعَمَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَن لَّن يُبْعَثُوا﴾الحمد لله، والصلاة وا...
24/04/2025

#ማስተንተን ለተቸረዉ አጂብ የሆነ የጌታችን ንግግር:-

👇👇👇👇

قوله تعالى:

﴿زَعَمَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَن لَّن يُبْعَثُوا﴾

الحمد لله، والصلاة والسلام على رسول الله، أما بعد:

🍀فقد سمعنا جميعًا قوله تعالى:

{زَعَمَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَن لَّن يُبْعَثُوا قُلْ بَلَى وَرَبِّي لَتُبْعَثُنَّ ثُمَّ لَتُنَبَّؤُنَّ بِمَا عَمِلْتُمْ وَذَلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ}

[التغابن:7].

🍀حيث إن الكفار -كفار العرب وغيرهم- إلا من رحم الله ينكرون البعث والنشور؛ لأنها حياة منتهية ويرون أن من مات مات؛ فلا عودة ولا بعث ولا نشور، هكذا قال لهم شيطانهم.

وقد بين الله جل وعلا أنه لابد من البعث والنشور، والجزاء والحساب؛ ولهذا قال:

{زَعَمَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَن لَّن يُبْعَثُوا }

↩زعموا: أي كذبوا

🌿 #እነዛ ከሀዲያን አስተባበሉ፣ዋሹ ሞገቱ አንቀሰቀስም ብለዉ ጌታችን ግን አለ፣በማላ እያረጋገጠ ትቀሰቀስዋታላችሁ ትሰሩትም በነበረ ነገር አንዳችም ነገር ሳይቀር ኸይር ይሁን ሸር ይነገራቹሀል።

قُلْ بَلَى وَرَبِّي لَتُبْعَثُنَّ ثُمَّ لَتُنَبَّؤُنَّ بِمَا عَمِلْتُمْ وَذَلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ يبعثون وينبئون بأعمالهم -خيرها وشرها- هكذا أخبر الله في كتابه العظيم أنه لابد من البعث والجزاء،

🍁 #የግልፁ ይቅርና በድብቅ፣ በሽሽግ፣ስንት ደባ ይፈፀማል ስንት ወንጀል ይፈፀማል ስንት ድንበር ይታለፋል ስንት ስንት………… الله ይወቀዉ ግን ተደብቆ፣ተሸሸጎ፣ተሰትሮ አይቀርም ያ ቀን ያ አስፈሪዉ ቀን ግርዶሹ የተነሳ እለት ያ ሁሉ በድብቅ ይሰራ፣ይፈፀም የሆነ የነበረ ሸር ይሁን ኸይር ግልፅ ይሆናል ጥያቄዉ ለዚህ ግልፅ ለምንሆንበት ቀን ዛሬ ምን ላይ ነን ነዉ ።

قال تعالى:

{وَيَسْتَنبِئُونَكَ أَحَقٌّ هُوَ قُلْ إِي وَرَبِّي إِنَّهُ لَحَقٌّ وَمَا أَنتُمْ بِمُعْجِزِينَ }

[يونس:53]،

فلابد من البعث والنشور والجزاء والحساب والجنة والنار؛ ولهذا فإن من أصول الإيمان: الإيمان بالأركان الستة التي هي أصول الإيمان: الإيمان باليوم الآخر -يوم القيامة- والبعث والنشور والجنة والنار والجزاء والحساب.

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ወድና የተከበራችሁ በወግድ ወረዳ ነዋሪወችና አካባቢዋ የምትገኙ በሙሉ እነሆ አድስ ደርስ የሙስጠለህ አለሀድስ ደርስ/ቂርአት የኡስይሚን ኪታብ ተጀመረ በ...
17/12/2024

አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ወድና የተከበራችሁ በወግድ ወረዳ ነዋሪወችና አካባቢዋ የምትገኙ በሙሉ እነሆ አድስ ደርስ የሙስጠለህ አለሀድስ ደርስ/ቂርአት የኡስይሚን ኪታብ ተጀመረ በውዱና በተናፋቂው አስተማሪያችን አቢ ሙሳ ኢማም ሰኢድ አለመዊይ ለሚ ጤና ጣቢያው አካባቢ በሚገኘው መድረሳ እየተሰጠይገኛል ይህ ኡስታዝ የሀበሻው ጀግና አቢ አብድሮህማን ጀማል ያሲን ተማሪ ነው።ኢልምን ከቦታው ከምንጩ በሰለፎች ግንዛቤ የተማረ ነው የወግድ ወረዳ ሰለፍዮ የአይን ማረፊያ ነው።
🎤ይህ ኡስታዝ ከጧት እስከማታ ወቅቱን በማስተማር ብቻ ምሺጉል የሆነነው።
🎤ይህ ኡስታዝ ሀቅን በመግለፅ ሱናን ለሰወች በማድረስ የወቃሾችን ወቀሳ የማይፈራ ነው።
🎤ይህ ኡስታዝ ለሙስሊሞች የሚተናነስ የሁስነልሁሉቅ ባለቤት ነው።
👉ከዚህ እንቁ ኡስታዝ የምትማረው፦ከኢልመ ናፊዕ በተጨማሪ፦ሁስነል ሁሉቅን ፣ተአፋፍነትን፣ሶብርን፣መተዛዘንን፣መረዳዳትን፣መተናነስን፣ከዘረኝነት መራቅን…………ትማራለህ።
🍇ስለዚህ ወንድሜ የዚህ ሰው ውርስ እንዳያመልጥህ ፍጠን የህም በወግድ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ሰለፍዮች ግሩፕ ነው ሌላ ደግሞ የተጠናቀቁ ደርሶች የሚለቀቅበትን እናስተዋወቃችሇለን ወደፊት ኢንሻ አላህ።
👉ተንቢህ ልትጠነቀቁ የሚገባው ዳዕዋ ሰለፍያ በለሚ ወግድ ተብሎ ከዚህ ግሩፕ ውጭ ካያቹህ የተክፊሪው ሙስጠፋ ደሴ ግሩፕ እንደሆነ እወቁ ተክፊሪ መሆኑንም የገለፀው እራሱ ነው ይህ ሰው ራሱን በራሱ ለማረድ እገዘገዘ ያለ የተክፊሪዮች ዋና ስራ አስኪያጂ፣ጀነራል ሊቃቸው ነው ተከታዮቹም ትርባሺ ናቸው የበላቸው ቡዳ አይታወቅም በየ ቦታው ይጮሀሉ
👁👁🦻👂የነዚህ የሱ ተከታዮች ምሳሌ፦አንድ ማየትና መስማት የተሳነው ሰውየ ነበር እና ስስቁ ነካ አርጉኝ ይላቸዋል እነሱ አውርተው ሲስቁ ነካ ያደርጉታል ይስቃል አብሮ የሳቁን መንስኤ ግን አያውቅም ልክ እነዚህም ያው ናቸው

You can view and join right away.

ሰባቱ የ ላ ኢላሃ ኢለ አሏህ መስፈርቶች:1/ ላ ኢላሃ ኢለ አሏህን በትርጉሟ እና በመሰረቶቿ ዙርያ በቂ የሆነ ግንዛቤ እና እውቀት መኖር፤(العلم بمعناها نفيا وإثباتا.).>> ...
13/12/2024

ሰባቱ የ ላ ኢላሃ ኢለ አሏህ መስፈርቶች:

1/ ላ ኢላሃ ኢለ አሏህን በትርጉሟ እና በመሰረቶቿ ዙርያ በቂ የሆነ ግንዛቤ እና እውቀት መኖር፤
(العلم بمعناها نفيا وإثباتا.).

>> ትርጉሟ ፡ከአሏህ ሌላ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ብሎ ማመን እና መናገር:

>> መሰረቶቿ፡ أركانها

∆. ከአሏህ ሌላ በሚመለክ ማንኛውም ነገር መካድ፤
✓ النفي: ( لا إله).

∆ አሏህን በብቸኝነት ማምለክ እና መገዛት፤
√ الإثبات: ( إلا الله).

2/ በላ ኢላሃ ኢለ አሏህ በማመን፤ በመመስከር፤ በመስራት ዙርያ ላይ ያለ አንዳች ጥርጣሬ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ መሆን፡
√ اليقين هو العلم التام الموجب للعمل.

3/ በቁርዓን እና በሃዲስ ላ ኢላሃ ኢለ አሏህ የተመለከተ ትዕዛዝን በአግባቡ ሰምቶ መቀበል፡
√ القبول المنافي للرد.

4/ ለ ላ ኢላሃ ኢለ አሏህ ለምታስፈርደው ማንኛውም ትዕዛዝ መጕተት እና እጅ እና እግር መስጠት። ሰምቶ እንዳልሰማ አለመሆንና አለ መሸሽ።
√ الانقياد هو الإذعان والامتثال لأوامر الله تعالى. وعدم الترك والاعراض.

5/ በ ላ ኢላሃ ኢለ አሏህ ዙርያ እውነተኛ መሆን ውስጣችን እና ውስጣችን አንድ መሆን።ከንፍቅና እና ከቀጣፊነት መራቅ።
√ الصدق هو موافقة القلب اللسان وعدم النفاق والكذب.
6/ እምነትን ንግግርን እና ተግባርን ማጥራት የአሏህን ፊት እና ጀነትን መፈለግ፤ ከስሙልኝ እዩልኝ መራቅ የአሏህን ፊት የሚፈለግበትን ስራ ዱንያን አለመፈለግ፤
√ الإخلاص: هو أن يقصد العيد بعمله رضى ربه وثوابه.
7/ ላ ኢላሃ ኢለ አሏህን መውደድ ከጥላቻ መራቅ።
المحبة: هي المحبة المنافي للكراهة والبغض.

https://t.me/abuselmanfaris

https://t.me/abumaherasalafi

لنشر الدروس العلمية والكتب والخطب والمحضرات

✯✯✯✯  - حديث سَعْدِ بْنِ أَبِي وَقَّاصٍ، عَنْ جَابِرِ بْنِ سَمُرَةَ قَالَ: شَكَا أَهْلُ الْكُوفَةِ سَعْدًا إِلَى عُمَرَ ...
30/10/2024

✯✯✯✯

- حديث سَعْدِ بْنِ أَبِي وَقَّاصٍ، عَنْ جَابِرِ بْنِ سَمُرَةَ قَالَ: شَكَا أَهْلُ الْكُوفَةِ سَعْدًا إِلَى عُمَرَ رضي الله عنه، فَعَزَلَهُ، وَاسْتَعْمَلَ عَلَيْهِمْ عَمَّارًا فَشَكَوْا حَتَّى ذَكَرُوا أَنَّهُ لاَ يُحْسِنُ يُصَلِّي، فَأَرْسَلَ إِلَيْه، فَقَالَ: يَا أَبَا إِسْحَاقَ إِنَّ هؤُلاَءِ يَزْعُمُونَ أَنَّكَ لاَ تُحْسِن تُصَلِّي قَالَ أَبُو إِسْحَاقَ: أَمَّا أَنَا وَاللهِ فَإِنِّي كُنْتُ أُصَلِّي بِهِمْ صَلاَةَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، مَا أَخْرِمُ عَنْهَا، أُصَلِّي صَلاَةَ الْعِشَاءِ فَأَرْكُدُ فِي الأُولَيَيْنِ، وَأُخِفُّ فِي الأُخْرَيينِ قَالَ: ذَاكَ الظَّنُّ بِكَ يَا أَبَا إِسْحَاقَ فَأَرْسَلَ مَعَهُ رَجُلاً، أَوْ رِجَالاً، إِلَى الْكُوفَةِ فَسَأَلَ عَنْهُ أَهْلَ الْكُوفَةِ، وَلَمْ يَدَعْ مَسْجِدًا إِلاَّ سَأَلَ عَنْهُሰው ላይ وَيُثْنُونَ مَعْرُوفًا، حَتَّى دَخَلَ مَسْجِدًا لِبَنِي عَبْسٍ؛ فَقَامَ رَجُلٌ مِنْهُمْ يُقَالُ لَهُ أُسَامَةُ بْنُ قَتَادَةَ، يُكْنَى أَبَا سَعْدَةَ؛ فَقَالَ: أَمَّا إِذْ نَشَدْتَنَا فَإِنَّ سَعْدًا كَانَ لاَ يَسِيرُ بِالسَّرِيَّةِ، وَلاَ يَقْسِمُ بِالسَّوِيَّةِ، وَلاَ يَعْدِلُ فِي الْقَضِيَّة قَالَ سَعْدٌ: أَمَا وَاللهِ لأَدْعُوَنَّ بِثَلاَثٍ: اللهُمَّ إِنْ كَانَ عَبْدُكَ هذَا كَاذِبًا قَامَ رِيَاءً وَسُمْعَةً فَأَطِلْ عُمْرَهُ، وَأَطِلْ فَقْرَهُ، وَعَرِّضْهُ بِالْفِتَنِ فَكَانَ بَعْدُ، إِذَا سُئِلَ يَقُولُ: شَيْخٌ كَبيرٌ مَفْتُونٌ أَصَابَتْنِي دَعْوَةُ سَعْد.
قَالَ عَبْدُ الْمَلِكِ- أَحَدُ رُوَاةِ هذَا الْحَدِيثَ-: فَأَنَا رَأَيْتُهُ بَعْدُ، قَدْ سَقَطَ حَاجِبَاهُ عَلَى عَيْنَيْهِ مِنَ الْكِبَرِ، وَإِنَّهُ لَيَتَعَرَّضُ لِلْجَوَارِي فِي الطُّرُقِ يَغْمِزُهُنَّ.
[أخرجه البخاري في: 10 كتاب الأذان: 95 باب وجوب القراءة للإمام والمأموم في الصلوات كلها].

✯✯✯✯✯
እስቲ ለነዛ ተበደልን ተበደልን ለሚሉ አንቡቡላቸው መቸም በየ ጊዜው አንዳንድ አሸጋሪ እና ስው ላይ ጭኖሽ ሲጭን ምንም የአላህ ፍራቻ የሌለው አይጠፋምና ሰእድ ኢብኑ ወቃስ ላይ ኡሳመተ ኢብኑ ቀታዳ የሚባለው:-
❌ከዘማቾች ጋር አይዘምትም
❌እኩል እኩል አያከፋፍልም
❌በትክክል በሰዎች መሀል አይፈርድም ባለው ጊዜ
ሰእድ ነገሩን ወደ አላህ አስጠግቶ
☝️እድሜውን አርዝመው
☝️ድህነቱንም አርዝምበት
☝️በፊትና ላይ ጣደው ብሎ ዱአ አደረገበት
✍️ አስቡት በሶስት ነገር ድንበር አለፈበት በሶስት ነገር ዱአ አደረገበት ምን ያክል ጥንቃቄ እድላችው አስቡት አላህም የተበዳይን ዱአ ዝም አይልም እና ሰማው ሁሉም ተከሰተበት ።ሰለፎች እድህ ናቸው ከተበደልክ ነገርህን ወደ አላህ አስጠጋ ሁል ጊዜ ችክክክክክክ ባንድ ነገር ላይ ያስጠላል በጣም እና እንመከርበት ተበደልኩ ብለህ ሰውን አትበድል!!!!!!

ፀረ መንጀኒቅ

هذه القناة تعتني بنشر الردود العلمية ونقد العقائد المخالفة للمنهج السلف الصالح والفرق المنحرفة المخالفة لصحيح السنة - والرد على الشبهات اخوكم ابي عبيدة الحبشي الول...

ብዙ ነን ግን አረፋ ምን ይጠቅማል⁉️٢٣ دولة عربية23 አረባዊ ሐገር....٢٣ جيش عربي23 የአረብ ጦር....٤٥٣ مليون عربي453 ሚሊዮን አረቦች...٥٧ دولة إسلامي...
20/10/2024

ብዙ ነን ግን አረፋ ምን ይጠቅማል⁉️

٢٣ دولة عربية
23 አረባዊ ሐገር....
٢٣ جيش عربي
23 የአረብ ጦር....
٤٥٣ مليون عربي

453 ሚሊዮን አረቦች...
٥٧ دولة إسلامية
57 ኢስላማዊ ሀገሮች...
٢ مليار مسلم

2 ቢሊየን ሙስሊሞች.......!!⁉️

لكن الكثرة ليست في الثبات على الحق بل العدد فقط

ግና ብዛታችን በሐቅ ላይ በመፅናት ሳይሆን በቁጥር ብቻ ነው።

حينئذ تذكر كلام النبي
بل أنتم يومئذ كثير ولكنكم غثاء كغثاء السبل...

👉ይህኔ የነብዩን ትንቢት አስታውስ፦
«እናተ ያኔ ብዙ ናችሁ ነገር ግን እንደ ወንዝ አረፋ ናቸው አረፋ ምን ዋጋ አለው!!»


✍አንደሉስ ሲከፈት የሙስሊም ሰራዊቶች አስራ ሁለት ሺህ ነበሩ ተባለ;

✍ አንደሉስ ስትወድቅ ግን በውስጧ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ነበሩ።

♻️ቁም ነገሩ፦ የኢማን ጥንካሬ እንጂ የቁጥር ብዛት አ ይ ደ ለ ም!!

https://t.me/daiwaselefiaforallumah/506

📮إعلان هام وبشرى سارة لجميع أهل السنة في بلاد الحبشة✍በናፍቆት የሚጠበቀዉ ኢጅቲማዕ ሙሐደራ:-  👇👇🕌 አንዋር መስጂድ ነዉ🕌📶አጓጊዉ እና ተናፋቂዉ የኢጅትማዕ ሙ...
22/09/2024

📮إعلان هام وبشرى سارة لجميع أهل السنة في بلاد الحبشة

✍በናፍቆት የሚጠበቀዉ ኢጅቲማዕ ሙሐደራ:-

👇👇

🕌 አንዋር መስጂድ ነዉ🕌

📶አጓጊዉ እና ተናፋቂዉ የኢጅትማዕ ሙሀደራ በአይነቱ
ልዩ በሆነ ሁኔታ በالله ፈቃድ ይደረጋል‼️

🏔🕌ነገ አንዋር መስጅድ በሰለፊዮች ይደምቃል ።

سيكون بإذن الله تعالى اجتماع كبير لجميع أهل السنة والجماعة في بلاد الحبشة يوم غد الأحد

👉የነገዉ እለተ እሁድ ሙሀደራ ከዝሁር በኋላ ሁኖ በከተማችን መሀል አዲስ አበባ

🕌በታላቁ አንዋር መስጂድ ነዉ።

📌في جامع الأنور وسط عاصمة الحبشة أديس أبابا بعد صلاة ظهر يوم الأحد

📲ነገ እሁድ በالله ፈቃድ አይደለም:-

☞ መቅረት
☞ ማርፈድ
☞በፍፁም አይታሰብም።

⛱ #አጠቃላይ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የሚገኙ ሰለፍዮች በአንድነት ይታደሙበታል‼️

إن شاء الله

🛍ይህን የሰማችሁ ሁሉ ላልሰሙት በማሰማት ላይ የአጅሩ ተቋዳሽ ሁኑ ጥሪያችን ነዉ።🩸

👇👌🏻فاحرصوا على الحضور ودلوا غيركم فالدال على الخير كفاعله*

🟢=∞======🟢=∞=====🟢

⛲️አጠቃላይ ፕሮግራሞችን ለመከታተል ደግሞ ይህን ቻናል ተቀላቀሉ:-

👇👇👇

https://t.me/AlEmanhabssha

🛬አል_ኢማን የሰለፍዮች ቻናል!!

🍙 #በሶሻል ሚዲያ ላይ ብዙ ተከታይ በማየትህ አትገረም‼️☞ #ጠማማ አንጃዎች፣ተክፊሮች ኢኽዋኖች፣ጀምዕዮች መጅሙዓቸዉ ሶሻል ሚዲያ በሚልዮን የሚቆጠር ተከታይ ሊኖራቸዉ ይችላል ደግሞም አላቸዉ።...
12/09/2024

🍙 #በሶሻል ሚዲያ ላይ ብዙ ተከታይ በማየትህ አትገረም‼️

☞ #ጠማማ አንጃዎች፣ተክፊሮች ኢኽዋኖች፣ጀምዕዮች መጅሙዓቸዉ ሶሻል ሚዲያ በሚልዮን የሚቆጠር ተከታይ ሊኖራቸዉ ይችላል ደግሞም አላቸዉ።

☞አለፍ ሲል ደግሞ እነዛ ኩፋሮች ኳስ ተጫዋቾች፣ዘፋኞች፣ስፖርተኞች፣
የፖለቲካ ሰዎች…… ወዘተ በሺ ሳይሆን በሚልዮን በል ከ50ሚልየን በላይ ተከታይ ሊኖራቸዉ ይችላል።

☞ምን ለማለት ነዉ ምንም ለማለት አይደለም ነገር ግን በእነዚህ ቁጥሮች አትገረመም ከሀቅ ጋር ግንኙነት የላቸዉም ለማለት ነዉ።

☞ #በእኛም አገር ኢኽዋኖች፣ ጀምዕዮች፣ተክፊሮች ብዙ ተከታይ ወወወ አለን ብለዉ በጉራ ሲበጠረቁ ይሰማል ይህም ከሀቅ ጋር ከትክክለኛ ዳዕዋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለዉም።

☞የእነዛ ባጢል ሰዎች ዳዕዋ፣ሾዉ የተንጠለጠለዉ ሶሻል ሚዲያ ላይ ነዉ በመቶ ሺዎች በሚልየን ተከታይ ልታዩላቸዉ ትችላላችሁ እና አትገረሙ።

☞ሁሌም ሶሻል ሚዲያ ላይ የተተከለ ዳዕዋ ዉጤቱ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም አይማዎቻችን ዑለማዎቻችን ከዚህ መንደር የተገኙ አይደሉም ሶሻል ሚዲያ በርና መስኮት የሌለዉ ሜዳ ስለሆነ ኢንሱም፣ጂኒዉም፣ፋሲቁም ካፊሩም የሚፈነጭበት አዉላላ ሜዳ ነዉ።


☞ብዙ ጊዜ የሶሻል ሚዲያ ዳዕዋ ተብዬ እንደ መዝናኛነት ደርሶኛል፣ ሰምቸዋለዉ ለማለት እንጂ ይህን ያህል ትልቅ ለዉጥ የሚያመጣ ሜዳ አይደለም በል ፈሳዱ የበዛ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን ቦታ ነዉ ይህ ለማንም ግልፅ ነገር ነዉ።

☞አልሰማንም አላየንም ፌስቡክም ይሆን ጎግል ወይም ሌላዉ ሶሻል ሚዲያ አንድ ሸይኽ፣አንድ ዳዒ ኮትኩተዉ አስተምረዉ አሳድገዉ አወጡ ሲባል አልሰማንም አላየንም የሰማ ያየ ከአለ በመረጃ ይንገረን።

☞ዛሬ ዛሬ ተክፊሮች ሙስጦፋ አብደላና ባልደረቦቹ ንቅናቄ ሶሻል ሚዲያ ላይ ነዉ እግሩን የተከለዉ የታለ መስጅድ፣የት አለ መድረሳ??

☞በተለያየ የቴክኖሎጂ ዉጤት ድምፁ እያወፈረና እያቀጠነ የተክፊርን ፅንሰ ሀሳብ ሲያስተጋባና እንደሱ ወፈፌ የሆኑ አብረዉ ዉርዉር ሲሉ እና የድጋፍ ጭብጨባ ሲያሰሙ አትገረም።

☞እስኪ ማነወ? ከእነሱ ዉስጥ ከዓሊም ነቅል ያደረገዉ❓ማን ሸይኽ ያለዉ❓ማነዉ ዓቂዳን የሚያህል ነገር ከዑለማ የተማረዉ❓ነጅድ ነጅድ ይልሀል ከየትኛዉ የነጅድ ዓሊም ሳይሆን የተማሪ ተማሪ እዉቀትን የወሰደዉ ወይም አንድ ሪሳላ ነቅል ያደረገዉ❓❓❓ማነዉ ማነዉ❓

እወቅ እነዚህ ተክፊርዮችና ሌሎች ፊረቆች ዳዕዋቸዉ የቆመዉ ሶሻል ሚዲያ ላይ ነዉ ዳዕዋቸዉ መሬት የረገጠ አይደለም እና አትገረም።

☞ምን አልባት አረፋ ግብስብስ አጃቢ በዝቶላቸዉ ወይም ሲያጅባቸዉ ብታይ ከእነሱ በብዙ ሚልዮን የሚበልጡ ተከታይ ያላቸዉ ዚንዲቆችም አሉና❓

👌

አንተ ሰልፊይ ወንድሜ ሆይ‼️

📮 #እዉቀትን፣ዓቂዳ ከማን እንደያዝክ በደንብ እወቅ አንገትህን ቀና አድርግ እንጂ ሰነድ አለህ ሲልሳላህ ኢማሞች ጋር ነዉ የሚደርሰዉ❓❓

ለምሳሌ:-አንተ ሰለፊዩ ከየመንም ከነጅድም፣ከሻምም……የተሳሰረ ሰነድ አለህ እኮ በደንብ ተረዳ ለቂጥን ተክፊርን እንዴት ትሰማለህ❓

☞ከነጅድ ከተባለ ኢማም ሸይኽ ሙቅቢል رحمه الله የኢማም ኢብኑ ባዝ رحمه الله ተማሪ እኮ ናቸዉ።

☞ከየመን ካልክ ኢማም ሸይኽ የህያ الله ይጠብቃቸዉ የኢማም ሸይኽ ሙቅቢል رحمه الله ተማሪ ናቸዉ።

☞ከሻም ሸይኽ ሰሊም الله ይጠብቃቸዉ የኢማም ሸይኽ አልባኒ رحمه الله ተማሪ ናቸዉ።

👉 #የየመን ሌሎች ታላላቅ ዓሊሞችን ሸይኾችህን ጨምርበት እና አንገትህን ቀና አድርግ እነዚህን ወራዳ ተክፊሮች የሚሉትን አሸቀንጥረህ ወርውር እንጂ የሶሻል ሚዲያ ጋጋታቸዉ እኮ ቦታቸዉ ነዉ ማረፊያቸዉ ነዉ የአባቶቻቸዉ መንገድ ነዉ እና አያጅብህ።

✍ዳዕዋ አሰለፊያ መሬት የረገጠ ዳዕዋ ነዉ ቁርአን ሀዲስ በሰለፎች ግንዛቤ አቤት ደስ ሲል ስትናገር እራሱ ፏ ብለህ ነዉ በዛ ላይ ሰነድ ሲኖርህ።

☞ዳዕዋችን ሶሻል ሚዲያ ላይ የተንጠለጠለ አይደለም።

☞ዳዕዋችን የዓቂዳ ኪታብ ይዘህ አንገትህን ደፍተህ እየቀራህ፣ እየሀፈዝክ፣በተግባር እየፈፀምክ ዳዕዋ እያደረክ የምትኖረዉ ሀያት ነዉ።

☞ሶሻል ሚዲያ እንደ ተጨማሪ ግብአት ነዉ የምንጠቀመዉ በቦታዉ ላይ መገኘት ያልቻሉ እሩቅ ቦታ ያሉ የማይመቻቸዉ ዳዕዋዉ በሆነ መንገድ ተረድተዉ እንዲመጡና እንዲቀላቀሉ እንዲያዉቁ እንዲረዱ እንጂ እንደ መሰረት አድርገን አንይዝም በዚህም ሸይኾቻችን አይመከሩም።

♦️የቴክኖሎጂ ዉጤትና ሶሻል ሚዲያ እየተጠቀሙ ዉርዉር ቢሉና ቢበጠረቁ አይምሰልህ መሬት የረገጡ አይደሉም ከእነሱ በብዙ ሚልዮን አጃቢ ያላቸዉ ምንም አላመጡም አያመጡም።

☞እና መሬት በረገጠዉ ዳዕዋ ላይ ተንተርሰን ወደፊት የምንሔድ ሰለፊዮች እንጂ በሶሻል ሚዲያ ኳኳታ የምንጫጫ ተክፊርዮች ኢኽዋንዮች አይደለንም።

☞አስተማሪዎቻችንም የሚመክሩን ትኩረታችን ደርስ ላይ፣ሂፍዝ ላይ ተግባር ላይ ዳዕዋ ላይ እንዲሆን እንጂ በሶሻል ሚዲያ እንድናተኩር አይደለም።

👉ሸይኾቻችን በሶሻል ሚዲያ ላይ አታገኛቸዉም መገኛ ቦታቸዉ መስጅድ ነዉ፣መድረሳ ነዉ በዲኑ ጉዳይ ላይ ወቅት የላቸዉም ወላ ፌስ ቡክ ወላ ወላ የሚባል ግሩፕ ብሎ ነገር የላቸዉም እንደ ግል ሶሻል ሚዲያ ከዑለማ ለመገናኘት፣ምክራቸዉን ለመስማት በግል ካልሆነ አታገኛቸዉም ወቅት የለም በዲኑ ሀጃ ተወጥረዋል።

✍ተክፊሩ ሙስጦፋ ሶሻል ሚዲያ ላይ ተዘፍዝፎ እየዋለ እዛ የተዘፈዘፉ ስራ ፈቶችን እያጠመደ ፏ ብሎ ዉልዉል ብሎ የተክፊርን መንገድ ይሰብካል ምድረ የጃሂል ጥርቅም ለቂጥ ደግሞ አበጀህ በለዉ አስፈሳዉ ዉቀጠዉ ይለዋል… … እዉነት እየመሰለዉ ማንኪያ ጭልፋ የያዘዉ ነገር ይወረውራል ድንቄም ወርዋሪ…… ተበርቼ ሰላም አሉ።

☞ለማንኛዉም ለምን በሚልዮን የሚቆጠር የሶሻል ሚዲያ ተከታይ አይኖረዉም እዛዉ ሶሻል ሚዲያ ላይ ተተክሎ ይቀራል እንጂ ወደ መሬት አይወርድም ለማለት ነዉ።

10/09/2024

📮 እንቁጣጣሽ ማን ኣመጣሽ❔

🔭 "ጳጉሜ" የሚለው ቃል "ኤጳጉሚኖስ" ከሚለው ከግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ "ተጨማሪ" ወይም "የተጨመረ" ማለት ነው።

🔜 ጳጉሜ የወር ስም ሲሆን በነባሮች 12 ወራት ላይ የተጨመረ 13ኛ ወር ነው።

🔜 ይህም ወር በነሐሴ እና በመስከረም መካከል የሚገኝ የመጨረሻው ወር ነው።

🔜 ጳጉሜ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በዘመነ ዮሐንስ ስድስት ቀናት ሲኖሩት በዘመነ ሉቃስ ዘመነ-ማቴዎስ እና በዘመነ -ማርቆስ ደግሞ አምስት ቀናት ይሆናል።

🔜 ልብ በሉ ይህ ወር ከግሪክ ሄለኒዝም ጊዜ ከአሌክሳንድርያ ወደ ኢትዮጵያ የገባ እንጂ በዕብራውያን አቆጣጠር ላይ 12 ወራት ብቻ ነው ያለው።

♻️ አላህም የወሮች ቁጥር በእርሱ መጽሐፍ በለውሀል መህፉዝ ማለትም በጥብቁ ሰሌዳ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ነው፦

📖 قال الله تعلى:- ﴿ ﺇِﻥَّ ﻋِﺪَّﺓَ ﭐﻟﺸُّﻬُﻮﺭِ ﻋِﻨﺪَ ﭐﻟﻠَّﻪِ ﭐﺛْﻨَﺎ ﻋَﺸَﺮَ ﺷَﻬْﺮًۭﺍ ﻓِﻰ ﻛِﺘَٰﺐِ ﭐﻟﻠَّﻪِ ﻳَﻮْﻡَ ﺧَﻠَﻖَ ﭐﻟﺴَّﻤَٰﻮَٰﺕِ ﻭَﭐﻟْﺄَﺭْﺽَ ﻣِﻨْﻬَﺂ ﺃَﺭْﺑَﻌَﺔٌ ﺣُﺮُﻡٌۭ ۚ ﺫَٰﻟِﻚَ ﭐﻟﺪِّﻳﻦُ ﭐﻟْﻘَﻴِّﻢُ ۚ ﻓَﻠَﺎ ﺗَﻈْﻠِﻤُﻮﺍ۟ ﻓِﻴﻬِﻦَّ ﺃَﻧﻔُﺴَﻜُﻢْ ۚ ﻭَﻗَٰﺘِﻠُﻮﺍ۟ ﭐﻟْﻤُﺸْﺮِﻛِﻴﻦَ ﻛَﺂﻓَّﺔًۭ ﻛَﻤَﺎ ﻳُﻘَٰﺘِﻠُﻮﻧَﻜُﻢْ ﻛَﺂﻓَّﺔًۭ ۚ ﻭَﭐﻋْﻠَﻤُﻮٓﺍ۟ ﺃَﻥَّ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﻣَﻊَ ﭐﻟْﻤُﺘَّﻘِﻴﻦَ ﴾
سورة التوبة [ 9:36]

📖 አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር በአላህ መጽሐፍ ዉስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት # ወር ነው፤ ከነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፤ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፤ በነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፤
[ሱረቱ ተውባህ 9፥36]

🔜 ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያው ዘመን መለወጫ በልምድ ከግሪክ የመጣ ሰርጎገብ እንጂ አገር በቀል አይደለም።

🔜 ከዚያም ባሻገር መለኮታዊ ትእዛዝ ያለው ሳይሆን ሰው ሰራሽ ቢድዓ ነው ዓመተ-ምህረትን ያማከለ ዘመነ-ሉቃስ ዘመነ-ዮሐንስ ዘመነ-ማቴዎስ እና ዘመነ -ማርቆስ ሰው ሰራሽ ትምህርት ነው።

♻️ በዛ ላይ የባእድ አምልኮ የሚፈፀምበት ቀን ነው።

🔭 በጳጉሜ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች ዶሮዎች ድመቶች ጥንቸሎች ወዘተ... ታርደው ይጣላሉ።

🔜 በደም የተነከሩ ሳንቲሞች ብሮች ጌጣ-ጌጦች እና የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ።

♻️ ይህ ቀን ሲያልቅ የቀኑ መጨረሻ በጉጉት ስለሚጠበቅ "እንቁ" ተባለ።

♻️ የሚያመጣው ጣጣና መዘዝ ደግሞ "ጣጣሽ" ተባለ በጥቅሉ "እንቁ-ጣጣሽ" ተባለ።

📌 ጥንቆላና ድግምት ከትልቁ ሽርክ የሚመደቡ የፈጣሪያችንን የአላህን ሃቅ የሚነካ ትልቅ በደል ነው።

📖 قال الله تعلى:- ﴿ واتبعوا ما تتلو الشياطين على ملك سليمان وما كفر سليمان ولكن الشياطين كفروا يعلمون الناس السحر وما أنزل على الملكين ببابل هاروت وماروت وما يعلمان من أحد حتى يقولا إنما نحن فتنة فلا تكفر فيتعلمون منهما ما يفرقون به بين المرء وزوجه وما هم بضارين به من أحد إلا بإذن الله ويتعلمون ما يضرهم ولا ينفعهم ولقد علموا لمن اشتراه ما له في الآخرة من خلاق ولبئس ما شروا به أنفسهم لو كانوا يعلمون ﴾ .
سورة البقرة [2:96]

📖 አላህም እንዲህ አለ:- በነብዩ ሱለይማን (ዐለይሂሰላም) ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም ድግምት ተከተሉ ሱለይማን ግን አልካደም ድግምተኛ አልነበረምና ግን ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ.....

📖 قال الله تعلى:- ﴿ قال فإنا قد فتنا قومك من بعدك وأضلهم السامري ﴾
سورة طه [20:69]

📖 አላህም እንዲህ አለ:- ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም አልን ይላል። ሱረቱ ጧሀ [20፥69]

📌 እንቁጣጣሽን ማክበር አቆጣጠሩ አገራዊ ሳይሆን እምነታዊና ባህላዊ መሰረት ያለው ሲሆን ከእርሱ ጋር የተያያዙት ባእድ አምልኮ አስበን ከዚህ ሰው ሰራሽ በአል እራሳችንን እንጠብቅ።

08/09/2024

#ጥቆማ ቢድዓ ስለ ሆነዉ መዉሊድ‼ ……………………
بسم الله الرحمن الرحيم

#የነብዩ ሙሐመድ ﷺ መውሊድ [የልደት ቀን] በዓል ማክበር ብሎ ከዲናችን የተደነገገ ነገር የለንም።

#መዉሊድ ግልፅ የሆነ ቢድዐ ነዉ።መዉሊድ ለማክበር ለመረጃ የሚሆን አንድም ከቁርአንም ከሀዲስም ከሰለፎቻችንም የሆነ የሚጠቁም ንግግርም ይሁን ስራ የተገኘና የተነገረ ነገር የለም።

#በመሰረቱ መውሊድ ይከበር ወይስ አይከበር የሚል መነሻ ሀሳብ ማቅረብ በራሱ ትልቅ ስህተት ነዉ።

#ምክንያቱም ቢዳዓ የሆነዉን መረጃ የሌለዉን መዉሊድ ይከበር አይከበር ብሎ መነሻ የሚሆን ሀሳብ መናገር መሰረትና መረጃ የለዉም።

#መነሻና መድረሻ የሌለዉ እንደ ቀትር ፀሀይ ፍንትዉ ብሎ የሚታይ ቢድዓ ላይ ስለ ማክበር መነጋገር ተገቢ አይሆንም መዉሊድ ያለ ምንም ኺላፍ ቢድዓ ነዉ፣ጥመት ነዉ ስለዚህ ይከበር ብሎ መነሻ ሀሳብ ይዞ ማቀንቀንና ሙግት መግጠም ትልቅ ጥፋት ነዉ።

#መዉሊድ የነብዩ ﷺ ወዳጅ ነን የሚሉ ነገር ግን ሀቂቃዉ ሲታይ የነብዩ መሐመድ ﷺ ጠላት የሆኑ ሰዎች የፈጠሩት ቢድዓ ፈጠራ ነዉ ስለዚህ መዉሊድ ለማክበር የሚሆን መነሻ ነጥብ ሆነ ሀሳብ የለም።

#ነብዩﷺ የሚወድ ያዘዙትን ይሰራል፣ የከለከሉትን ይከለከላል እሳቸዉን በአዘዙት በሰሩት መልኩ ይከተላል እንጂ አዲስ ፈጠራ ቢድع የሆነ መጤ ነገር አይፈጥርም አዲስ መጤ ነገር አይሰራም፣አያመጣም ዲናችን በወህይ የተገነባ በመሆኑ መከተል እንጂ መፍጠር ጥመት ነዉ ።الله ይላል:-

{قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ}

#የነብዩﷺ ወዳጅ የሆነ ሰዉ መዉሊድን በፍፁም አያከብርም ይሰመርበት ጠላት ጠላት ነዉ የሚያሳዝነዉ ጠላት መሆናቸዉ አለማወቃቸዉ።

#ወደድንም ጠላን መዉሊድ አክባሪ የነብዩ ﷺ ጠላት ነዉ ጃሂል ሆኖ ሳያዉቅ መረጃ ያልደርሰዉ ኡዝር ይሰጠዋል ነገር ግን መረጃ እየተነገረዉ ኢናድ ይዞት እንቢኝ ያለ ድንብን ያለ ጠላት ነዉ።

#ያለዘዙትን፣ያልሰሩትን ያልመጡበትን መንገድ ከመስራት የበለጠ ጠላትን አለ እንዴ? እሳቸዉ ከመጡበት ከተላኩበት መንገድ ዉጪ መስራት መከተል ትልቅ ጠላትነት ነዉ መዉሊድ አክባሪዎች ወዳጅ ነን ቢሉም እንላለን ጠላትነት መዉሊድ በማክበርም ይገለፃል እንላቹሀለን ምክንያቱም ያልመጡበት መንገድ ነዉ፣ያላዘዙት ነገር ነዉ ያልሰሩት ስራ ነዉ።

#እኛ የነገሩንን ያዘዙንን እንድንሰራ፣እንድንከተል ነበር የታዘዝነዉ አዲስና መጤ ነገር እንድንፈጥር እንድናመጣ አይደለም የታዘዝነዉ الله በተከበረዉ ንግግሩ ይላል:-

{وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ}

#ዛሬ ዛሬ የስልጣን ጥመኛ ኢኽዋኒዮች የሽርክ መናኸሪያ ሱፍዮች መዉሊድን እንደ አንድ የዲን አካል አድርገዉ እየቆጠሩ እየተሰባሰቡ በሽርኪያት መንዙማ እየጨፈሩ ለዉይይት፣ለስልጣን ለወንበር ማግኛ መንገድ አድርገዉ ሲጠቀሙት ይታያል ምንም ቢያኳኩሉት ቢያጋጌጡት ቢወጡ ቢወርዱ መዉሊድ መረጃ የለዉም ቢድዐ ከመሆን አይወገደም።

قال تعالى:-

{أَفَمَن كَانَ عَلَىٰ بَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّهِ كَمَن زُيِّنَ لَهُ سُوءُ عَمَلِهِ وَاتَّبَعُوا أَهْوَاءَهُم} (14)

"ከጌታው በኾነች መረጃ ላይ የኾነ ምእመን ክፉ ስራቸው ለነርሱ እንደ ተሸለመላቸውና ዝንባሌዎቻቸውን እንደ ተከተሉት ነውን"

#ብዙ ጊዜ መዉሊድ ሲቃርብና በመዉሊዱ እለት መዉሊድ አክባሪዎች የተለያየ ሽፋን እየሰጡ የልዩነት አጀንዳ እንዳይሆን ይሰራሉ ይንቀሳቀሳሉ ሀቂቀተን መዉሊድ ካልያየን ምን ሊለያየን ነዉ።

#ሱፍዮች አልያም ስለ መዉሊድ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅራቢ #ኢኽዋኒዮች ሁሉ በመዉሊድ ስም የሚያደርጉት ነገር ሁሉ መረጃ አልባ ነዉ እነዚህ የጥመት አንጃዎች አጭበርባሪና የዲን ነጋዴዎች ናቸዉ ይሄ ሊታወቅ ይገባል።

#መረጃ አልባ የሆነዉን ቢድዐ የሆነዉን ነገር እንዴት ለጥናታዊ ፅሁፍ ይቀርባል?እንዴት ለዉይይት ይቀርባል??ይህ ጥመት ነዉ፣ግልፅ የሆነ ሌብነት ነዉ በፍፁም ሊሆን የሚችል ነገር አይደለም እነዚህ የጥመት አንጃዎች ልናዉቃቸዉ ይገባል ምንም እንኳን የስሜት ተከታይ ቢበዛም እንኳን ማጋለጡና ማስጠንቀቁ ግድ ይላል።

#ለማንኛዉም እኛመረጃ አልባዉ፣ቢዳዐ የሆነዉ የስንት ሽርክያት መናኸሪያ የሆነዉን #መዉሊድ ቢድዐ መሆኑን ከመግለፅ ወደ ኋላ አንልም።

#ማንም ይጎርብጠዉ እንናገራለን ሀቅ ሀቅ ነዉ።መዉሊድ ብሎ ማለት ሙስሊሞችን የሚከፋፍል ቫይረስ ነዉ መዉሊድ አዎ ይለያየናል በቢድዐ መሰባሰብ የለም።

#አንድነት በተዉሒድና በሱና ነዉ የሚገኘዉ በቢድዐ በሽርኪያት አንድነትን ማረጋገጥ በፍፁም አይቻልም ሊሆንም አይችልም።

#ዲናችን የመረጃ ሀይማኖት ነዉ ፍልስፍና አልያም ጆግራፊ አይደለም የተለያዩ አገሮች እየጠቀሳችሁ በዚህ አገር በዚህ አካባቢ መዉሊድ ይከበራል፣ተከበረ እያላችሁ ህዝቡን አታደናቁሩት የህዝብ ብዛት ወይም የአገር ብዛት የሀቅ መለኪያ አይደለም ሀቅ በብዛት የሚለካ ነገር አይደለም።

#መረጃ:-

♂ #ከቁርአን
♂ከሀዲስ

#ስጡን አንድ አንድ መረጃ እንኳን አስቀምጡልን ዲናችን የመረጃ ሀይማኖት ነዉ።

#ከአራቱ ኸሊፋዎች:-

☞ከአቡበከር ሲዲቅ رضي الله عنه

☞ከኡመር ኢብኑል ኸጣብرضي الله عنه

☞ከኡስማን ኢብኑ አፋንرضي الله عنه

☞ከዐሊይ رضي الله عنه

#የተገኘ ደካማ የሆነ መረጃ እንኳን ካላችሁ አስቀምጡት እንዲሁም

♂ከአራቱ መዝሀቦች:-

①ኛ=ከኢማሙ አቡ ሀኒፋرحمه الله

②ከኢማሙ ማሊክرحمه الله

③ከኢማሙ ሻፊዒرحمه الله

④ከኢማሙ አህመድرحمه الله

>>የተገኘ አንድ አንድ መረጃ እንኳን ጥቀሱ።

☞አስከ ቅርብ ጊዜ የነበሩትና አሁንም በህይወት ያሉት ዑለማዎች አምጡ የለም ልታመጡ አትችሉም። መዉሊድ መረጃ የለዉም ቢድዐ ነዉ አራት ነጥብ።

#እነዛ #ኢኽዋኒዮች ሱፍዮች ዑመር ገነቴ፣ ጄይላን፣ሀሰን ታጁ ፣ካሚል ሸምሱ፣ አቡበከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ያሲን ኑሩ………… ስማቸዉ ለመጥቀስ የሚቀፋትና የመሳሰሉት ቢያከብሩ አትሸወድ እነሱ ለወንበር ነዉ አንተ ሀቅ ፈላጊ ግን መረጃዉን ጠይቅ።

#ሱፍይ፣ኢኽዋንና ቢጤዎቻቸዉ መዉሊድ ያበረከተዉ አስተዋፅኦ ብለዉ ጥናታዊ ፅሁፍ ቢያቀርቡ፣አልያም አብረዉ በሽርኪያት ዜማ በድቤ ቢያዜሙና ቢያከብሩ ስልጣንና የሚያለከልኩለት ወንበር ቢያገኙበት እንጂ ስለ መዉሊድ ከመረጃ አንፃር ስንዝር መራመድ አይችሉም መዉሊድ ቢዳዐ ከመሆኑም ሊታደጉት አይችሉም።

#እዉን ትግላችሁ ለዲን ከሆነ መዉሊድ ዲን አለመሆኑን ግለፁ፣ አስጠንቅቁ፣ ከመዉሊድና አክባሪዎች ራሳችሁን አርቁ በምትሉት እንይና እንቅስቃሴያችሁ ለዲን ከሆነ መዉሊድ ቢድዐ መሆኑን አስቀምጡ ካልሆነ ግን ለዲን የምትለዋን ሽፋን፣ ጭንብል ነችና አዉልቁና ጣሉ፣እኛ የዚህ ፓለቲካ ድርጅት መስራቾች ነን በሉ የፖለቲካ አቋማችሁን አሳዉቁ።

የነብዩ ﷺ መውሊድ እና የሆድ ነገርقال تاج الدّين الفاكهاني رحمه الله (المتوفى: 734هـ)” لا أعلم لهذا الْمَوْلِد أصلا في كِتَاب ولا سُ...
07/09/2024

የነብዩ ﷺ መውሊድ እና የሆድ ነገር

قال تاج الدّين الفاكهاني رحمه الله (المتوفى: 734هـ)

” لا أعلم لهذا الْمَوْلِد أصلا في كِتَاب ولا سُنّة ، ولا يُنْقَل عَمَله عن أحدٍ مِن علماء الأُمّة الذين هم القُدوة في الدّينِ ، الْمُتَمَسّكون بِآثار الْمُتَقَدِّمِين ؛ بل هو بِدْعة أحْدَثها البَطّالُون ، وشَهْوَة نَفْس اغْتَنى بها الأكّالُون !“

📚 (المورد في عمل المولد 143 )

«ለዚህ ለመውሊድ በቁርኣንና በሐዲሥ መሰረትን አላውቅም። ሥራውም ከነዚያ የዲን አርዓያ ከሆኑት፣ የቀደምቶችን ትውፊት ያዥ ከሆኑት የዲን መሪዎች ዘንድ አልተገኘም።

እንዳውም እርሱ የባጢል ሰዎችና የነፍስ ስሜት ያለባቸው ሰዎች የፈጠሩት፤ በላተኞች (ሆዳሞች) ትኩረት ሰጠው የፈጠሩት (ቢድዓ) ነው።»

▪️አይ የሱፊያ ነገር!! ያለ ምንም መግብ ዝግጅት, ያለ ምንም ሴት እና ወንድ መደባለቅ, ያለ ምንም ጭፈራ መውሊድ አክብሩ ብባሉ የሚያከብሩት ይመስላችዋል ወገኖች?

https://telegram.me/daawa_hara
♡ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ

💢ለምንድ ነው መውሊድ ቢድዓ ነው ምንለው⁉️♨️ምክንያቱም🔼 መውሊድን አክብሩ የሚል አንድም  የቁርአን አያ አልወረደም ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ሀዲስ ሰሂህም ይሁን ዶዒፍ አልመጣም...
05/09/2024

💢ለምንድ ነው መውሊድ ቢድዓ ነው ምንለው⁉️

♨️ምክንያቱም
🔼 መውሊድን አክብሩ የሚል አንድም የቁርአን አያ አልወረደም ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ሀዲስ ሰሂህም ይሁን ዶዒፍ አልመጣም ከአንድም ሶሀባ አድርጉ የሚል ወይም ያደረገበት አልመጣም

⏹ ነብዩ صلى الله عليه وسلم አላከበሩትም አክብሩልኝም አላሉም , ከሰሀባዎች رضي الله عنهم አንዳቸውም መውሊድን አላከበሩም አክብሩም አላሉም

▶️ አቡበክር ሁለት አመት በመሪነት(በኸሊፋነት) ቆይቷል መውሊድን አላከበረም እንዲከበርም አላዘዘም ለነብዩ እሱ በጣም የቅርብ ሰው ከመሆኑም ጋር

⏺ ዑመርም አስር አመት በመሪነት ቆይቷል አንድም ቀን መውሊድን አክብሩ ብሎም ይሁን አክብሮ አያውቅም

⏹ ረሱል صلى الله عليه وسلم ሞተዋል በጣም ብዙ ከመቶ ሺ በላይ ሶሀባዎችም ሞተዋል አንዳቸውም መውሊድን አክብረው አያውቁም

⏸ ከሶሀባዎች በኋላ የነበሩት ታቢዒዎችም መውሊድን አክብረው አያውቁም

▶️ አራቱ አዒማዎች ሚባሉት ኢማም አቡ ሀኒፋህ ኢማሙ ማሊክ ኢማሙ ሻፍዒይ ኢማሙ አህመድ الله ይዘንላቸው አንዳቸውም መውሊድ አላከበሩም አክብሩም አላሉም

እና እነሱ የበቃቸው ለኛ አይበቃንም

➡️ኸይር ቢሆን ኖሮ እነሱ ይቀድሙን ነበር⬅️

👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Address

Tekuam
Dessie

Telephone

+251938636185

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daiwa selefya for all umah posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share