02/06/2022
ክፍል-6
ፍካሬ ኢየሱስ
"በዚያን ጊዜ አንዱ: ከምእራብ: ሌላው: ከምስራቅ: ሲመጡ: ይገናኛሉ፣ "ወዴት: ትሄዳላችሁ?": ይሏቸዋል: "ወደምእራብ: መሄድ: እንወዳለን": ይላሉ: "ወደምእራብ: አትሂዱ: በዛ: መከራ: አለና": ይላሉ፤ "እናንተስ: ወዴት: ትሄዳላችሁ?": "ወደምስራቅ: መሄድ: እንወዳለን": ይሏቸዋል፣ "ወደምስራቅ: አትሂዱ: ብዙ: መከራ: አለና": ይላሉ።
ራዕየ ሳቤላ
በጦርነት ብቻ አያበቃም፣ ከፍተኛ ረሀብ ቸነፈርና ችጋር እንደሚመጣ ቃሉ ይናገራል። በዛሬ ቀን የቆምን ቢያንስ በረሀቡ ሳይሆን በጦርነት እንኳን ለመሞት ፀሎት ያስፈልገናል። በጦርነት መሞትን እድለኝነት የሚይስብል በረሀብ ስቃይ የሚመጣ የከፋ ሞትም አለና። በመፅሀፍ ቅዱስም በሰይፍ የመጣ ሞት በረሀብ ከመሞት ይሻላል ተብሎ ተፅፏልና።
አባቶቻችን ሰምተዋቸው የማያውቋቸው አዳዲስ እጅግ ወራሪና ፈጣን ገዳይ በሽታዎች በሀገራችን ይገባሉ። (ምልናባትም በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ በመሰራጨት ላይ ያሉት አዳዲስ ገዳይ በሽታዎች ፍንጭ ሊሆኑን ይገባናል።)
"የሞቱትን ሰወች ንዑዳን ክቡራን ናችሁ እስኪሏቸው ድረስ ችግርና ሀዘን ይሆናል"
ራዕየ ሳቤላ
እውነቱ ይህ ነው።
በሀገራችን እግዚአብሄርን ባገለለ መልኩ፣ የሱን ሀሳብና እርዳታ፣ አብሮነት ሳንጠይቅ በምድራዊ ፖለቲካ ስጋዊ ትርምስምስ፣ እሱን አርቀን የምናደርገው የዘረኝነትና ስጋዊነት ሩጫችን ሁሉ መዳረሻው ያ ነው።
ቆርጠን ለስጋዊ ግባችን መጠሪያ ካደረግነው "የኢትዮጵያ ትንሳኤ" በፊት የሚሆነው ይህ ነው።
አይ እምነተቢስነት፣ ከትንቢቶቹ "ትንሳኤ" የምትለውን ቃል ብቻ መርጦ ይዞ በየሚዲያው፣ በየቦታው እየጮሁ ባለቤቱንና ባለቃልኪዳኑን እግዚአብሔር ግን ረስቶና ከድቶ በየቦታው መለፈፍ ቁጣና መከራውን ቢያፀናውንጂ ከዚህ ሁሉ መከራ ከቶ አያድንም። በብልጣብልጥነት የሚሆን ነገር የለምና፣ በተለይ ክርስትያን ነን የምንል ህዝቦች ከቅዱሳን መፅሀፍቱ መልካም መልካሙን በመምረጥ፣ የሚያስፈራንን መተው ከመከራ ፅናት ያለፈ ምንም አያተርፍልንም። ሌላ ለማንም ተብለው አልተፃፉምና፣ አላማቸውም ስለትንሳኤ ሊያስጎመዡን ሳይሆን ለኛው በፍቅርና ቸርነት ተፅፈው ቀድመን አውቀን ከዚህ ከሚመጣው ፅኑ ፍርድና መከራ እንድንድን መድሀኒት ይሆኑልን ዘንድ የተፃፉ ናቸውና
እንደለመድነው መልካም መልካሙን በመምረጥ ይህን ቃል ብንንቅ፣ እሳቱን መጥቶ ካላየን አናምንም ብለን ብንሸሽ በኛው ስልጣን በራሳችን ላይ ሰነፍን እንጂ፣ በማንም አልፈረድንም
ጊዜው ደርሷልና፣ ይህን መልእክት ያየን ብዙዎቻችንም በቸልተኝነትና ልባችን መደንደን ምክንያት ምንም ሳንዘጋጅ እንጠፋለንና፣ ከሞታችን በኋላ በፍርድ ጊዜ የኛው ንግስታችን ንግስተ ሳባ ሳይቀር እንደምትቆምብን መፅሀፍ ይጠቁማል
"ንግሥተ ዓዜብ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና"
ማቴ 12:42
"የነነዌ ሰዎች በፍርድ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና"
ሉቃ 11:32
ከእኛው ምእመኑ ጋር ቤተክርስትያናችንም ጭምር እጅግ በበብዙ ስውር በትሮች ብዛትና የሰወችም ችግር በመዳከሟ አብረን ለዚህ የእውቀት ክፍተት ደረስን እንጂ፣ እጅግ በበዙ ቅዱሳት መፅሀፍትና ገናም ባለልቦና ሰው አግኝተው ከግእዝ ያልተተረጎሙና ለህዝብ ባልደረሱ የቤተክርስቲያኒቷ የብራና ቅዱሳት መዛግብት በብዛት የተፃፈ ጉዳይ ነው።
ጥንት በራሳቸው ዘመን መልካም ቀን ቢሆን፣ ያ ሳያዘናጋቸው ጥበበኛ አባቶች በፍቅር ተነሳስተው ለሚመጣው ትውልድ በመጨነቅ በልመና በራእይ ያዩትን ዛሬ እንድንበት ዘንድ የተፃፉ ብዙ አሉ።