ዉዴታ እስከ ጀነት

ዉዴታ እስከ ጀነት "ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሰራ
«እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው
ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማነው?"
( ፍሲለት;33)

01/10/2025

🤲 አላህ አፊያህን ይመልስልህ
ውዱ ኡስታዛችን?

اللهم ربّ الناس، أذهب البأس، اشفِ أنت الشافي، لا شفاء إل شفاؤك، شفاءً لا يغادر سقماً".

01/10/2025

ትንሽ መሻሻሎች እንዳለው ነግሮኛል። የማን ዱዓ መቅቡል እንደሆነ አይታወቅምና፣ እስኪ ከልብ ዱዓ እናድርግለት! ህመሙ ተመልሶም አይምጣበት! የዓፊያን ካባ አላህ ያከናንበው! ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው!

ኢንና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን!"በፊዳከ 1"፣ "በስጦታዬ"፣ "በዓሰላሙ ዓለይክ" እና "አፈር እየጫሩ" የመውድሰ ረሱል (ሰዐወ) ሥራዎቹና ሌሎች በርካታ የኅብረትና የግል ነሺዳዎቹ የሚታወ...
10/04/2025

ኢንና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን!

"በፊዳከ 1"፣ "በስጦታዬ"፣ "በዓሰላሙ ዓለይክ" እና "አፈር እየጫሩ" የመውድሰ ረሱል (ሰዐወ) ሥራዎቹና ሌሎች በርካታ የኅብረትና የግል ነሺዳዎቹ የሚታወቀው ሙንሺድ ሙሐመድ ሰዒድ በገጠመው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ አመሻሹን ወደ አኼራ ተሻግሯል።

የደሴው ፈርጥ ሙንሺድ ሙሐመድ ሰዒድ በወርሐ ረመዷን የዑምራ ስርዓት ለመከወን ተጉዞ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን፤ ከዑምራ ጉዞው ከተመለሰ በኋላ በገጠመው ድንገተኛ ህመም ማለፉ ነው የተነገረው።

ሚንበር ቲቪ ለሙንሺድ ሙሐመድ ሰዒድ አላህ ቀብሩን ኑር ማረፊያውን ጀነት እንዲያደርግለት እየተመኘ፤ ለመላው ወዳጆቹና ቤተሰቦቹ ሶብርንና መፅናናትን ይመኛል።
/ሚንበር ቲቪ

********************ሰላምን ከማስጠበቅ አንፃር  ምን ይጠበቅብናል=======1. እንደ ተቋም2. እንደ ህዝብ========ትከታተሉ ዘንድ ግብዣየ ነው።
02/04/2025

********************
ሰላምን ከማስጠበቅ አንፃር ምን ይጠበቅብናል
=======
1. እንደ ተቋም
2. እንደ ህዝብ
========
ትከታተሉ ዘንድ ግብዣየ ነው።

TikTok | Make Your Day

31/03/2025
አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁየዒድ ዉሎ ገጠመኞቸ  በደሴ / ሸዋል 01/1446==============*****************============== የዚህ ጽሁፍ ብቸኛ ዓላማ ፡-...
31/03/2025

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
የዒድ ዉሎ ገጠመኞቸ በደሴ / ሸዋል 01/1446
==============*****************==============
የዚህ ጽሁፍ ብቸኛ ዓላማ ፡- ፍላጎቱ ካለን ከስህተቶቻችን ትምህርት በመዉሰድ ለቀጣይ ተሽሎ በመገኘት ህዝበ ሙስሊሙ በመሪ ተቋሙ ላይ ምንም ዓይነት ትችት ሳያቀርብ ዒድ የሚሰገድበት ሁኔታ እንድፈጠር ማድረግ ብቻ ነዉ፡፡
==============*****************==============
1ኛ. ሰዓትን በተመለከተ
==============*****************==============
ህዝበ ሙስሊሙ ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ እስቴዲየም በመምጣት የመስገጃ ቦታዉን በመያዝ ሙሉ በሙሉ ስቴዲየሙ እስከ 2፡17 ድረስ የሞላ ቢሆንም ሶላቱ የተሰገደዉ 3፡45 አካባቢ ነዉ፡፡ ይህን ያክል ሰዓት ፀሃይ ላይ ሱናን ፈልጎ ፤ የጀመዓየን ብዛት ላሳይ ብሎ ህፃናት ልጆችን በመያዝ ከተለያየ ቦታ የመጣን ህዝብ የፀሀይ ቀለብ ማድረግ ተገቢ አልነበረም፡፡ ይህ ተግባር በየጊዜዉ ባልተስተካካለ ቁጥር ልምዳቸዉ ነዉ ዘግይተዉ ነዉ የሚሰግዱት በሚል ህዝበ ሙስሊሙም ዘግይቶ መምጣትን ልምድ እንድያደርግ መጋበዝ ይሆናል፡፡ ይህንን ጉዳይ የዒዱ አስተባባሪዎችም ሆነ የከተማ አስተዳደሩ መጅሊስ አመራሮች በግልፅ በመወያየት የዒድ አል-ፈጥር በዚህ ሰዓት ይሰገዳል ፣ ዒደል አዶሃ አረፋ በዚህ ሰዓት ይሰገዳል በሚል ቁርጥ ያለ ሰዓት ቢወጣለት መሪና ህዝብን ከመተማማት ይልቅ የበለጠ ያቀራርባል ፤ ያጠናክራል የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡
==============*****************==============
2ኛ. የ መድረክ መሪዎችና እና የ Sound System በተመለከተ
==============*****************==============
2.1 የ Sound System ከቦታ መረጣ ጀምሮ ትክክል ያለልሆነ ፣ቴክኒሽያኖቹ በፍጥነት መፍትሄ መስጠት ላይ ችግር ያለባቸዉ ፣ የሆነች ብልሽት ሲጋጥም ደህና የነበረዉን መስመር ጭምር በመነካካት ሙሉ በሙሉ ፀጥ እንዲል የሚደረግበት ብዙ አጋጣሚዎች ታይተዋል፡፡ በፕሮግራሞች ላይ የሚመጡ የድምጽ ሲስተም ባለሞያዎች ብቃት ያላቸዉ ፤ የትኛዉን መስመር ባስተካከል የትኛዉ ባላንስ ይመጣል የሚለዉን በጥንቃቄ መተንተን የሚችሉ መሆን አለባቸዉ፡፡ በዒዱ ቀን ግን ይህን አላየንም ለማጅ ይመስል የሆነች ሰበብ ፍልጎ ደህና የምትሰማዋን ድምጽ ሙሉ በሙሉ ፀጥ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል ይህ የበለጠ ሊታረም የሚገባዉ ተግባር ነዉ፡፡ ሲሆን ሲሆን በመጅሊሱ በኩል የራሱ የሆነ የ Sound System በመግዛት ችግራችንን በራሳችን መቅረፍ ብንችል የትልቅነተታችን መገለጫ ነዉ ብየ አስባለሁ፡፡
==============*****************==============
2.2 የመድረክ መሪዎች ጋር በተያያዘ መድረኩን ከዚህ የተሻለ መምራት የሚችል ሰይ አጥተን ነው ወይስ የግድ የምናዉቃቸዉ ሰዎች ብቻ ካልሆኑ መድረክ መምራት ዕድሉ አይሰጥም ነዉ? መድረክ መሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የማይክ አጠቃቀም ችግር እንዳለ ጭምር መታዘብ ችለናል፡፡ ቦታዉን ከመስጠታችን በፊት ቀድሞ ቸክ ማድረግስ ግደታችን አለነበረም ወይ? የመጅሊስ አመራሮች ህዝበ ሙስሊሙን እየዞሩ ሲከከታተሉ አይቻለሁ፡፡ በነዛ አጋጣሚዎች ያለዉንም የድምጽ መቆራረጥ እና ታዳሚን ከልብ ማናገር እና መቆጣጠር የሚችል የማይክ አጠቃቀም ሂደት መኖር አለመኖሩን በማየት በፍጥነት መልስ መስጠት ይገባ ነበር ፣ ይንንም ተግባር እዛዉ መድረክ አካባቢ ያሉ ወንድሞች ጭምር ሲወቅሱና ሲናገሩ ነበር ፤ በዝምታ መታለፉ የዒዱን ድባብ ቀንሶታል፡፡ ለዚህ ማሳያ ካላችሁኝ በፕሮግራም መሪዎች እድል ያገኙ ወንድሞች ሲናገሩ ድምፃቸዉ በሚገባ ሁኔታ ህዝቡ ጋር መድረስ እንደቻለ አይተናል ሰምተናል፡፡ ረመዷን 27 ለይልን ጨምሮ በተለያዩ ፕሮግራሞች መደራረብ ድካም ቢኖርም መድረኩ በነዛ መንድሞች ቢመራ በራሱ ጥሩ ድባብ ይኖረዉ ነበር፡፡
==============*****************==============
3ኛ. የመድረክ ላይ መልዕክቶች
==============*****************==============
ሙሉ ፕሮግራሙ ስለባንክ ማስታወቂ የተሰራበት መድረክ ነበር ፣ ዕዉነት ነዉ እነዚህ ባንኮች ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ለነሱ ቅስቀሳ መሰራት የነበረበት ዛሬ ኃላፊነታቸዉ የሆነዉን ብድር ሲሰጡ ሳይሆን ያኔ ተመስርተዉ ወደስራ ሊገቡ ሲሉ Commercial Bank of Ethiopia without Windows ራሱን ችሎ ለብቻዉ IFB Branch ብሎ ሲከፍት የዛኔ ምን ሊፈጠር ነዉ ብሎ analysis በመስራት ነበር፡፡የዛኔ የዚህ ዓይነት ማስታወቂና ቅስቀሳዎች በሰዓቱ ተሰርቶ በነበር የዛሬዋ "ቀርዱል ሀሰና" ብዙ ቦታ በተሰራበት ነበር፡፡ የ ZemZem and Hijira Bank መፈጠር ሌሎች Conventional ባንኮች ለህዝበ ሙስሊሙ ዕድል እንድሰጡ ፣ የሙስሊሙን ዉለታ እንድያዉቁ ፤ ከመስኮት ይልቅ እራሱን የቻለ ቅርንጫፎች እንድከፍቱ የተደረገዉ ፣ ትላልቅ ዑለሞችና ኡስታዞቻችን በአማካሪነት ደረጃ በየባንኮቹ መስራት እንዲችሉ የተደረገዉ በነዚህ ባንኮች ምክንያት መሆንኑ በማሰብ ቀድሞ ስራን መስራት ፣ ህዝበ ሙስሊሙ ጋር ማድረስ የዉደታ ግደታ መሆኑን አዉቆ ቀድሞ መሰራት ነበረበት፡፡ በእርግጥ አይደለም መጅሊሱ ሊያግዛቸዉ ባንኮቹ እርስ በራሳቸዉ የተጠላለፉ ፣ ከዛም አልፎ የአንድ ባንክ ቅርንጫፍ ከቅርንጫፍ የሚያያዙ በመሆናቸዉ እስካሁን ህዝበ ሙስሊሙ ጋር በትክክል መድረስ ባለመቻሉ ብዙ ቅርንጫፎች አልተከፈቱም፡፡ እነዚህ ችግሮች እራሱን በቻለ ፕሮግራም እንጅ ለዒድ የተሰበሰበ ህዝብ ላይ ብር አበድረዉናል ብሎ እሱን እንደዉለታ ቆጥሮ ህዝብን ፀሃይ ላይ ማሰቃየት ተገቢ አልነበረም፡፡የግል አቋሜ ህዝበ ሙስሊሙ በነሱ መጠቀም ግደታዉ ሲሆን ለ Interest Free Bank ደግሞ ለህዝበ ሙስሊሙ ከመለድ ነፃ ብር ማበደር በተመሳሳይ ግደታ ነዉ የሚል አቋም አለኝ ፤ ተሳስተሃል የሚል አካል ካለ ለመወያት ዝግጁ ነኝ፡፡
==============*****************==============
4ኛ. ከ Ethio telecom Network መዘጋት ጋር በተያያዘ
==============*****************==============
እንደትላንቱ ባይሆንም የዒድ ቀን ፉርቃንም እያለን ጭምር ኔትወርክ ይቆራረጥ ነበር ፣ ኔትወርኩ ከሶላታችን መስገድ ጋር ያለዉ ቁርኝት አስፓልት ላይ ላሉ ሰጋጆች ደዉሎ በስልክ እንድከታተሉ ለማድረግ አስበን ከሆነ አሁንም ይቀረናል በጣም ስህተት ነዉ፡፡ ቀደም ብለን አስበን ሸል እና መነሃሪ አካባቢ ድረስ ገመድ ብንዘረጋ ትልቅ ስኬት ነበር፡፡ ከዛ ዉጭ ግን የድምጽ ግንኙነታችን wireless ሆኖ ለድምፅ አስተላላፊ ሞንታርቦዎች ድምጽ በ Ethio telecom Network በኩል የሚተላለፍ መሆኑ ታዉቆ አጥፍተዉብን ከሆነ ሆንብሎ ዒዱን ለማበላሸት የተደረገ ጥረት ስለሆነ ትግል ይጠበቅብናል የሚል ዕምነት አለኝ፡፡
==============*****************==============
5ኛ. የ ምክትል ከንቲባችን መልዕክት ጋር በተያያዘ ….
==============*****************==============
ከፕሮግራሙ አንዱ የሆነዉ የከተማ አስተዳደራችን መልዕክት በሚተላለፍበት ሰዓት ህዝቡ ተነስቶ ስለነበር ብዙ ሰዉ የተለያየ ሃሳብ ሲሰጥ ሰምቻለሁ ከነዛም ዉስጥ ፖለቲካ ሲናገር ጮሁበት ፣ አመራሩን አንፈልግም አሉ ወዘተ ይህ ከእዉነት የራቀ ዉሸት ነዉ፡፡ እኔ ያለሁበት ቦታ ለመስማትም ሆነ ለመታዘብ ይመች ስለበር የግል ዕይታየን ስገልጽ ከንቲባችን መልዕክት በሚስተላለፉበት ሰዓት ሞንታርቦዎቹ ሙሉ በሙሉ የቆሙበት ሰዓት ነበር በዛን አጋጣሚ ከኋላ ጀምሮ እንስገድ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዉ ነበር እውነታዉ ይሄ ብቻ ነዉ፡፡ የደሴ ሙስሊም ማህበረሰብ አይደለም አብሮት የዒድ ሶላት የሚሰግደዉ ወንድሙን ቀርቶ አክብሮት የመጣን ሁሉ የሚያከብር ጨዋ እና አርቆ አሳቢ ህዝብ ነዉ፡፡ እዚህ ጋር በተያያዘ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ አይነት ወሬ ለማዉራት የምትፈልጉ ስራ ፈቶች ሌላ አጀንዳ ፍልጋችሁ ታቦኩ ዘንድ እምክራችሀኋለሁ፡፡
==============*****************==============
6ኛ. አስፓልት ላይ ቆሻሻ ስለለቀቀዉ ጨለምተኛ ሆቴል በተመለከተ
==============*****************==============
ወሎ ለዛዉም ደሴ እንደሌሎች ቦታ ዓይደለም ፣ ሰዎች ያላቸዉን ታዋቂነት በመጠቀም ሙስሊሞችን ለማሻማቀቀም መሞከር በዛዉ በሰፈራቸዉ ይበቃ ነበር፡፡ ስለ ሆቴሉ ባለቤት የግል መረጃ ባላዉቅም ወሎየ ቢሆን ይህን የማድረግ ዕድሉ በጣም ያነሰ ነበር ፤ ቢያንስ ከባለፈዉ የጎዳና ላይ ዒፍጣር ገጠመኙ ትምህርት በመዉሰድ ዛሬ ሌላ ድፈረት የተሞላበት ተግባር እንዲሰራ ትዕዛዝ ባልሰጠ ነበር፡፡ በእርግጥ የ Manager ፍላጎት ሊሆን ይችል፡፡ ጉዳዩ በተቋማችን በኩል ተይዞ እስከመጨረሻዉ ዉጤቱ ሊታወቅ ይገባዋል፡፡ ከተቋም በላይ ከሆነ መንግስት ዉሳኔ በመስጠት የማይተባበርበት ሁኔታዎች ካሉ ለህዝቡ አንዲት መልዕክት ቢተላለፍ የደሴ ሙስሊም ማህበረሰብ በደንብ ይታወቃል፡፡ ከራሱ አልፎ ሰዉ ላይ አይደርስም ፣ የጨለምተኛ አመለካከት ባለቤቶች ከደረሱበት ግን እስከጥግ ድረስ የመሄድ ምንም ችግር የለበትም የሚል እምነት አለኝ፡፡
==============*****************==============
በአጠቃላይ ሀሳቤን ሳጠናቅቅ የኢድ ሶላቶቻችን በዓመት የምናገኛቸዉ ብቸኛ ፕሮግራሞች መሆናቸዉን በማሰብ ሰዓት ወጥቶላቸዉ ቅድሚያ የሚቀርቡ ፕሮግራሞች Sensor ተደርገዉ ፤ የተሻለ የ Sound System with Professional program Leader በማሟላት ዒዳችንን የወቀሳ ሳይሆን የደስታ ቀን በማድረግ እናሳልፍ ዘንድ ከስህተቶቻችን ትምህርት እንዉሰድ የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡
==============*****************==============
አጥፈቸ ከሆነ ለመታረም ዝገጁ ነኝ፡፡
በድጋሜ ዒድ ሙባረክ እያልኩ ሰላሙን ሁሉ በያላችሁበት ተመኘዉ፡፡
ወሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ፡፡

25/03/2025

ረመዷን 27
ወሎ ደሴ
አረብ ገንዳ መስጅድ

"ጁሙዓ ቀን በኔ ላይ ሶለዋትን አብዙ፤ከመካከላችሁ አንዱ ጁሙዓ ቀን በኔ ላይ ሶለዋትን አያወርድም  ሶለዋቱ እኔ ዘንድ የቀረበችልኝ ቢሆን እንጂ"⚘️   #ረሱሉሏህ   #صلی‌الله‌علیه‌...
11/10/2024

"ጁሙዓ ቀን በኔ ላይ ሶለዋትን አብዙ፤ከመካከላችሁ አንዱ ጁሙዓ ቀን በኔ ላይ ሶለዋትን አያወርድም ሶለዋቱ እኔ ዘንድ የቀረበችልኝ ቢሆን እንጂ"⚘️

#ረሱሉሏህ
#صلی‌الله‌علیه‌وسلم

12/08/2024

ለኸይር ፈላጊ እህት እና ወንድሞች የቀረበ ጥሪ
============================
በደውብ ወሎ ለጋምቦ ወረዳ ይላዳ 010 በሩ አካባቢ በአንድ አኽለል ኸይር የተሰጠ ቦታ ላይ አድስ መስጅድ ለመስራ ተጀምሯል። ተነይቶ የነበረው ቦታ 250 ካሬ ስለነበር ጠባብ ሲሆን ኮሚቴዎቹ ተጨማሪ ማስፋፊያ በ130 ሽህ ብር ገዝተው ከፍተኛ እዳ ውስጥ ስለገቡ መስጅዱንም ለመስራት ስለተቸጋገሩ እርዱን የሚል የኸይር ስራ ጥሪ ቀርቦልናል።
ስለሆነም በዚህ https://chat.whatsapp.com/JC5f62KodfhAVhckU50F22 የዋትሳፕ ግሩፕ በመሰባሰብ የአላህን ቤት እንገንባ ዘንድ ታላቅ እድል ቀርቦልናል።
عن محمود بن لبيد أن عثمان بن عفان أراد بناء المسجد فكره الناس ذلك، وأحبوا أن يدعه على هيئته، فقال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: «مَن بنى مسجدًا لله بنى الله له في الجنة مثله».
[صحيح] - [متفق عليه]

15/06/2024

ያ ረቢ
ወደ ወንጀሎቼ እመለከትና እፈራለሁ! የጥፋቴ ግዝፈት ያሸማቀኛል!?
ወደ እዝነትህ ስመለከት ደግሞ ተስፋ አድርጌ እደሰታለው:: እዝነትህ ከቁጣህ የቀደመች ናትና ተስፋዬ ይለመልማል
ግና እራሴን ስመረምር በስራዬ በመሸማቀቅ አንተን መጠየቅ አፍራለው
እንዴትስ አንተን ባመፀ ምላስ ልጠይቅህ??
ወይስ አንተን ባጠራህ፣ባላቀህ እና ባስታወስህ ምላሴ ደፍሬ ልማፀንህ?
ውዱ አምላኬ ሆይ
አንተን ማስታወስ በዘነጋ ምላሴ አንተን መለመን ይቻለኝ ይሆን ?
ወይስ ባንተ ፍቅር በሰመጠው ተናናሽ ልቤ ልማፀንህ ?
ኢላሂ
በልቅናህ እና በሀያልነትህ ይሁንብኝ
ያንተን ይቅርታና መሀርታን ለመጠየቅ እደጅህ ላይ ጠዋት እና ማታ ሳልታክት እቆማለው:: እዝነትህን እከጅላለው::
ጌታዬ ይኸው እኔ ልክ እንዳዘዝከኝ ለመንኩህ ኃያሉ ጌታዬም ቃል እንደገባህልኝ አንተም ልመናዬን ተቀበለኝ
እንደ ባህር አረፋ የበዛውን ወንጀሌን ሁሉ እጠብልኝ፣ የጠየኩህን ልመና ሁሉ ተቀበለኝ:: በዚህችም አለም፤ በመጪዋም አለም ስኬትን አጎናፅፈኝ
አሚን

Address

Dessi

Opening Hours

Monday 06:00 - 18:00
Tuesday 06:00 - 18:00
Wednesday 06:00 - 18:00
Thursday 06:00 - 18:00
Friday 06:00 - 12:00
Saturday 06:00 - 18:00
Sunday 06:00 - 18:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዉዴታ እስከ ጀነት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share