19/08/2026
1. ከሃምሳ ሺህ ብር በላይ ጥሎሽ መስጠትና መቀበል፣ የመልስ ፕሮግራም ስኬድ ከአሥር ሰው በላይ መጋበዝ፣ አላስፈላጊ የልደት፣ የቤትና የትምህርት ምርቃት ላይ በመደገስ ስራ መፍታትና ማስፈታት፣ ሀብትና ሥልጣን ለመጋራት በወላጆች ጫና የሚፈጸም ያለ አቻ ጋብቻ
2. ከፍተኛ ውጪ በማውጣት የሚደረግ የመቃብር ሐውልት ግንባታና ምረቃ፣ የሟች ፎቶ ያለበትን ቲሸርት መልበስ፣ የህይወት ታሪክ ማንበብ፣ ባነር ማሰራት፣ ጥቁር ልብስ መልበስ
3. የሴት ልጅ ግርዛት
4. ለጫ*ትና ሺ*ሻ ቤት ማከራየት
5. የመስቀል በዓል ማክበር
በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ ሸዋ ቀጠና በስሩ ለሚገኙ ከሰባት መቶ በላይ የሚሆኑ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት መሪዎችና መጋቢዎች የተሰማሙበትን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ደንብ አርቅቆ ለምዕመናን ይፋ አድርጓል።