Debre Zeit Full Gospel Believers Church-Air Force Area Chappel

Debre Zeit Full Gospel Believers Church-Air Force Area Chappel ይህ የቢሾፍቱ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን - ቁጥር 2 አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ኦፊሺላዊ የፌስቡክ ገፅ ነው፡፡

 # በቢሾፍቱ ቁጥር ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤ/ክ 👉 የእሁድ ቋሚ ፕሮግራሞቻችን ዘውትር እሁድ - ጠዋት ከ 12:30 - 3:00 የማለዳ ፀሎት - ከ3 : 00 - 3 :50 የማለዳ ትምህርት...
19/08/2026

# በቢሾፍቱ ቁጥር ሁለት
ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤ/ክ
👉 የእሁድ ቋሚ ፕሮግራሞቻችን ዘውትር እሁድ
- ጠዋት ከ 12:30 - 3:00 የማለዳ ፀሎት
- ከ3 : 00 - 3 :50 የማለዳ ትምህርት
-ከ 3:50 - 6:ዐዐ በዝማሬ የአምልኮና የእግዚአብሔር ቃል ግዜ በመቀጠል
- ከሰዓት በኋላ ከ 9:00 - 10:00 የወጣቶች አገልግሎት፣

👉 # በ ቢሾፍቱ ቁጥር ሁለት አጥቢያ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ በየሣምንቱ ዓርብ ቀን ላይ በሁለት ፈረቃ በ ቤተ ክርስትያን መንፈሳዊ አገልግሎቶች አሉን፣
1ኛ ✍ የጠዋቱ ክፍለ ግዜ ከ ማለዳ 3:00 - 7:00
የፀሎት፣የአምልኮ፣ የእግዚአብሔር ቃል ግዜ፣ እንዲሁም የፈውስ፣ የነፃ መውጣትና የኃይል አገልግሎት ፣ በመጨረሻም ከአርብ የፀሎት ግዜው ጋር ተያይዞ አማኞች ጌታ በህይወታቸው ያደረገላቸውን የሚመሰክሩበትና ሌሎችም የሚፅናኑበት ክፍለ ግዜ ይኖረናል፣

2ኛ ✍ የማታው ክፍለ ግዜ ላይ ከ 11:00 - 1:30 የመንፈስ ቅዱስ የፀጋ ስጦታ እንቅስቃሴ ላይ በማተኮር የፀሎት፣የአምልኮና የእግዚአብሔር ቃል ግዜ ፣ እንዲሁም በተለያዩ መንፈሳዊ ይዘት ባላቸው ህይወት ለዋጭ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በትምህርት አማኞችን ለማስታጠቅ ቤተ ክርስትያን ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች።
✍ ስለሆነም ሁሉም የቤተ ክርስትያን አማኞች እና በዚህ አገልግሎት መጠቀም የሚፈልግ ሁሉም ሰው በሚመቸው ግዜ ተገኝቶ መገልገል የሚችል መሆኑን ቤተ ክርስትያን ታሳስባለች።

“ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው።”
— ዕብራውያን 13፥8
#👉 #🙏በጨመረ መንፈስ እንቀጥላለን።

💥💥ቀን አምስት 💥💥የእግዚአብሔር እርዳታ እንደቀጠለ ነዉ። ዛሬም እንደሰሞኑንን  መልካም ጊዜ ነበረን። ስሙ ይክበር 🙏🙏 ዛሬ ደግሞ የአምልኮን ምንነት ወንድም አፈወርቅ ያስተማረን ሲሆን🎤🎤 እ...
14/08/2026

💥💥ቀን አምስት 💥💥
የእግዚአብሔር እርዳታ እንደቀጠለ ነዉ። ዛሬም እንደሰሞኑንን መልካም ጊዜ ነበረን። ስሙ ይክበር 🙏🙏 ዛሬ ደግሞ የአምልኮን ምንነት ወንድም አፈወርቅ ያስተማረን ሲሆን
🎤🎤 እግዚአብሔር እንድናመልከዉ ይፈልጋል፣ለዚያም ጠርቶናል ።
🥁ምስጋና🙏 እግዚአብሔር ስላደረገልን ነገሮች የምናመሰግንበት ሲሆን
🥁 ውዳሴ 🙏 ደግሞ እግዚአብሔር ስለሰራቸዉ የእጆቹ ስራዎች እሱን የምናወድስበት መንገድ ሲሆን
🥁አምልኮ ደግሞ ስለ ባህሪዉ ስለ ማንነቱ የምንሰጠዉ የምናቀርብለት መገዛታችንን የምናሳይበት መንገድ እንደሆነ ዛሬ በነበረን ጊዜ ተምረናል።
ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ ይሁን ።💥💥💥💥ይቀጥላል💥💥💥

💥💥ቀን አራት💥💥እንደቀጠለ ነዉ ።ክብሩን እሱ ይዉሰድ🙏🙏 ዛሬ በነበረን ፕሮግራም ላይ ስለ ንፅህና ተምረናል። መገኘት የሌለብን ቦታ መገኘት እንደሌለብን የመዝሙረኛዉን ዳዊት ህይወት ዋቢ በማድ...
14/08/2026

💥💥ቀን አራት💥💥
እንደቀጠለ ነዉ ።ክብሩን እሱ ይዉሰድ🙏🙏 ዛሬ በነበረን ፕሮግራም ላይ ስለ ንፅህና ተምረናል። መገኘት የሌለብን ቦታ መገኘት እንደሌለብን የመዝሙረኛዉን ዳዊት ህይወት ዋቢ በማድረግ ተምረናል። በሶሻል ሚዲያ ላይ የሚገባን ቦታ ላይ ነዉ የምንገኘዉ? ወይስ ለተከፈተዉ ሁሉ ነዉ አቤት ምንለዉ? ምንድነዉ ምንሰማው፣ምናየዉ፣ባውንደሪ አለን? ወይስ ሁሉም ነዉ ሚወስደን?
ሌላኛዉ😄😁 የምናደርገዉ ፣የምናየዉ፣የምንሰማዉ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ውስጣችን ስላለ ሁሉን ያያል ስለዚህ መጠንቀቅ አለብን።🎤🎤 ልክ እንደ ዮሴፍ ቢሚያየኝ በእግዚአብሔር ፊት ይህንን ነገር አላደርግም እንዳለዉ እኛም መጠንቀቅ ፣መለየት፣መውሰን፣መጨከን፣መውጣት አለብን። እግዚአብሔር ደግሞ ፀጋዉን ያበዛልናል💥💥💥ይቀጥላል💥💥

💥💥ቀን ሶስት💥💥💥ዛሬ ቸርች የነበረ  ሰዉ አተረፈ የሚለዉ ቃል አይገልፀዉም😁  የነበረን የትምህርት ጊዜ ከፖስተር ተስፉለም ጋር ነበር የእምነታችን መሰረቶች እና ዶክትሪናል ኢሺዎችን በማንሳት...
13/08/2026

💥💥ቀን ሶስት💥💥💥
ዛሬ ቸርች የነበረ ሰዉ አተረፈ የሚለዉ ቃል አይገልፀዉም😁 የነበረን የትምህርት ጊዜ ከፖስተር ተስፉለም ጋር ነበር የእምነታችን መሰረቶች እና ዶክትሪናል ኢሺዎችን በማንሳት እኛ ምን ላይ መቆም እንዳለብን እና መሰረታችን በሆነው የእምነት አቋማችን ላይ መደራደር እንደሌለብን በሚገባን መልኩ አስተምሮናል ። የተለያዩ ቤተ እምነቶችን አስተምሮዎችን በማንሳት እኛ ግን
🎤🎤 በስላሴ እንደምናምን
🎤🎤 መዳን የምንችለዉ
በፀጋ ብቻ፣በቃሉ ብቻ፣በእምነት ብቻ እንደሆነ 🤙 መዳን የሚቻለዉ ብቸኛው መንገድ ❤️ኢየሱስ ብቻ መሆኑኑ እና ሌላ የመዳን መንገድ ደባል እንደሌለ ብቻውን የሚያድነዉ የተሰቀለልን፣ የሞተልን ፣የተነሳልን፣ደግሞም ዳግመኛ ሊወስደን የሚመጣዉ ብቸኛዉ አዳኝ ❤️❤️ኢየሱስ ብቻ ነዉ ዛሬ የተገኛችሁ ሰዎች ምንኛ የታደላችሁ ናችሁ 🤙 የህይወት ስንቅ የሰነቃችሁ 💥💥💥 ይቀጥላል💥💥💥💥

💥💥ቀን ሁለት💥💥አላልኳችሁም ከተለያየ እስራት ይፈተታናል ብለን ጠብቀነዉ አልነበረ 🤙🤙 ዛሬ የነበረን ፕሮግራም የፀሎት ጊዜ ከነብይት ሰላም ጋር የማስተዋል መንፈስ በሚል እርስ ቃል ያካፈለችን...
12/08/2026

💥💥ቀን ሁለት💥💥
አላልኳችሁም ከተለያየ እስራት ይፈተታናል ብለን ጠብቀነዉ አልነበረ 🤙🤙 ዛሬ የነበረን ፕሮግራም የፀሎት ጊዜ ከነብይት ሰላም ጋር የማስተዋል መንፈስ በሚል እርስ ቃል ያካፈለችን ሲሆን እጅ በመጫ ለእያንዳንዱ በግል የመፀለይ ጊዜ ነበረን 🙏🙏የጠበቅነዉ፣የለመነዉ፣ያመነዉ ፣የእዉነት መንፈስ ዛሬ በመገኘቱ ታስረዉ ለነበሩት ከአጋንት ነፃ ሲያደርግ፣በመንፈስ ሲሞላ ፣ሲያፅናና ስንመለከት 😳😳እዉይ🙈😭❤️ እንኳንም ጌታ አደረኩህ🤙🤙 የሚያስብል ስሜት እንዲሰማን ሆነናል ክብሩን ሁሉ እሱ ይውሰድ። ይቀጥላል💥💥💥💥💥

💥💥ቀን አንድ💥💥በእግዚአብሔር እርዳታ ዛሬ ጀምረናል🙏🙏 በነበረን ቆይታ ፀሎት፣አምልኮ፣ጌም፣ እና ሌሎችም ፕሮግራሞች የነበሩን ሲሆን የእግዚአብሔር ንም አብሮነት አይተናል❤️❤️🙏🎤🎤 ከዚህ ፕሮ...
11/08/2026

💥💥ቀን አንድ💥💥
በእግዚአብሔር እርዳታ ዛሬ ጀምረናል🙏🙏 በነበረን ቆይታ ፀሎት፣አምልኮ፣ጌም፣ እና ሌሎችም ፕሮግራሞች የነበሩን ሲሆን የእግዚአብሔር ንም አብሮነት አይተናል❤️❤️🙏
🎤🎤 ከዚህ ፕሮግራም ምን እንጠብቅ??
🙋‍♀🙋‍♀ነፃነት ዮሐ 8:32
ይህ መሪ ቃላችን ነዉ። ሀሳቡን እንደምንረዳዉ እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችዋል። እውነት ክርስቶስ ኢየሱስ ነዉ ።እሱን በማወቃችን ድነናል ።ያዉ ያወቅነዉ እውነት ከተያዝንበት ከሀጥያት፣ከበሽታ፣ካለመታዘዝ፣ልጁን ካለመምሰል፣ካለመ ቀደስ፣ሌሎችን ደባል አድርጎ ከማምለክ ፣ለምሳሌ ሰዎችን ከማምለክ፣እራስን ከማምለክ ....... ከማይታይና ከማታይ ባርነት 😔😔 እውነት በሆነዉ በእዉነትም አርነት በሚያወጣዉ ስሙ❤️ 💥💥ነፃነትን💥💥 እንጠብቃለን። ደግሞም እናምናለን እንደአማኝ ነፃነትንም እናገኛለን። ይቀጥላል💥💥💥💥

Address

Debre Zeyit
995

Telephone

+2510118480493

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Zeit Full Gospel Believers Church-Air Force Area Chappel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share