Debre Zeit Meserete Kristos Church

Debre Zeit Meserete Kristos Church “ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥11

ቀን:- 14/12/18የሀሙስ የትምህርት መርሃ-ግብርፀሎት:- ወ/ም ዮዳሄ ጌቱቃል:- መ/ቢ ወንደሰንየቃል ክፍል፥  ዮሃ 6:1-15ቁጥር 1-9 የደቀመዛሙርቱ አለማመን· ታሪኩ በአራቱም ወንጌላት...
24/08/2026

ቀን:- 14/12/18
የሀሙስ የትምህርት መርሃ-ግብር
ፀሎት:- ወ/ም ዮዳሄ ጌቱ
ቃል:- መ/ቢ ወንደሰን
የቃል ክፍል፥ ዮሃ 6:1-15
ቁጥር 1-9 የደቀመዛሙርቱ አለማመን
· ታሪኩ በአራቱም ወንጌላት ከተዘገቡት ታሪኮች መካከል ነው።
· ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ያለውን አገልግሎት ጨርሶ ወደ ገሊላ የሄደበት ጊዜ ነው
·በክፍሉ ኢየሱስ ካደረጋቸው ተዓምራት የተነሳ ብዙ ሰዎች እስከ 150 ኪሜ የሚደርስ ርቀት እንደተከተሉት ክፍሉ ያስረዳናል
·በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ወደ ተራራ ወጣ፣ ኢየሱስ ወደ ተራራ ከወጣ የግል የጽሞና ጊዜ ሊወስድ እንደሆነ እናውቃለን።
·200 ዲናር ማለት በወቅቱ የአንድ ሰው የ 8ወር አካባቢ ደሞዝ ነው
·እስካሁን ድረስ ብዙ ተዓምራቶችን ኢየሱስ ሲያደርግ ቢያዩትም አሁንም ሊያደርገው እንደሚችል አላስተዋሉም
·እንድርያስ 5 ትንንሽ የገብስ እንጀራና 2 ትንንሽ አሳ ነው ያለው (አመት) እናም ትንሽ ትንሽ እንኳን ቢበሉ አይደርስም ነው ያለው
ቁጥር 10-13 የኢየሱስ ተዓምራት
·እንድርያስ ትንሽ ትንሽ ቢቃምሱ እንኳን አይበቃም ያለውን እንጀራና አሳ ኢየሱስ ይዞ አመሰገነ ለደቀ መዛሙርቱም ሰጠ ደቀመዛሙርቱም ለህዝቡ፣ 5000 ሰዎች ከሴቶችና ከህጻናት በቀር ጠግበው 12 መሶብ ተመልሷል
ቁጥር 14-15 ኢየሱስ ማን እንደሆነ አወቁ
·ይህ ወደ አለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ
·ፖለቲካዊ ፍላጎት የነበራቸውም ሰዎች ነበሩ
·እነዚህ ኢየሱስን ከሮማውያን ቅኝ አገዛዝ ነጻ የሚያወጣ አድርገው ስለሚቆጥሩት ሊያነግሱት ይፈልጉ ነበር
·ኢየሱስ ግን ከነዚህም ዘወር ብሎ ወደ ተራራ ነው የሄደው።
ምን እንማር
1 ኢየሱስን የምንከተለው ለምንድነው? ለዚህ ጥያቄ እያንዳንዳችን መልስ ሊኖረን ይገባል፣ በጸሎት ፣በቃል በጥናትም ጊዜ ልናሰላስለው የሚገባ
2 ኢየሱስ ጥያቄ የሚጠይቀን መልሱን አጥቶት ሳይሆን አቅማችንን ፍንትው አድርጎ ሊያሳየን ፈልጎ ነው፣ እኛ አንችልም አንተ ተረከበን ማለት እድንችል
3 .በእኛ እጅ ላይ ትንሽ የሆነ ነገር በእግዚአብሔር እጅ ስንተወው ይበዛል
4 .እውነተኛ በረከት የሚጀምረው ከማመስገን ነው፣ ጌታ ኢየሱስ ጥቂቱን እንጀራና አሳውን ይዞ አመሰገነ፣ ከዛም በቅቶ የሚተርፍ ነገር መጣ
5 የእግዚአብሔር በረከት የሚትረፈረፍ እንጂ የሚያጥር አይደለም
6. ጊዜውን ካልጠበቀ ክብር፣ ከፍታ፣ ሹመት መሸሽ ያስፈልገናል

የእሮብ ማታ የፈውስ መርሃ-ግብር 13/12/18ፀሎት:- ወ/ዊት የምስራች ታምራት ዝማሬ:- ወ/ም ሰናይ ሙሉነህቃል መ/ቢ ደመቀ በዛብህየስብከት ርዕስ:- ቀአታውያን ሁኑልኝ የስብከት ክፍል:- ...
24/08/2026

የእሮብ ማታ የፈውስ መርሃ-ግብር
13/12/18
ፀሎት:- ወ/ዊት የምስራች ታምራት
ዝማሬ:- ወ/ም ሰናይ ሙሉነህ
ቃል መ/ቢ ደመቀ በዛብህ
የስብከት ርዕስ:- ቀአታውያን ሁኑልኝ
የስብከት ክፍል:- ዘኡ 3:1-11
ቀአታውያን እግዚአብሔር ለጠላት መቅሰፍት ያደረጋቸው የሌዊ ዘሮች ናቸው። ለእግዚአብሔር የተነኙ፣ አርአያ የሆኑ ፣ እግዚአብሔርን በመልካም ስም ያስጠሩ ናቸው። ዘፍ 46
እግዚአብሔር በቀሪ ዘመናችንአንድ ነገር ይስራ። መንፈስ ቅዱስ እየገፋችሁኝ ነው እያለ ነው። የመጀመሪያዎቹ የቀአት ልጆች ምድርን ያንቀጠቀጡ ሙሴና አሮን ናቸው። 1ዜና 15:3-4
የእግዚአብሔር ታቦት በተማረከበት ጊዜ፤ አንድም ሰው ደፍሮ ማምጣት ባቃተው ጊዜ ሄደው ያመጡት የቀአት ልጆች የሆኑት የአሮን ልጆች ናቸው።
እግዚአብሔር ዛሬ የጨከነ በስሙ የሚወራረድ ሰው ይፈልጋል። እግዚአብሔር ሰው ይፈልጋል።
አማሌቃውያን እስራኤልን ባስጨነቁ ጊዜ ጌዲዮን ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ ገባበት ፍርሃቱ ተወግዶ ጠላቶቹን መታ። እግዚአብሔር ዛሬ ሰው አጣሁ እያለ ነው።
የእግዚአብሔር ህዝብ በብዙ ድብርት ውስጥ ነው ያለው። የእግዚአብሔር ህዝብ/ ቤተክርስቲያን ተኝታለ፤ የብዙዎች አጀንዳ ቤት መስራት ነው። የጌታ ልጆች አለ መንፈስ ቅዱስ አትሞክሩት። እግዚአብሔር ልጆቼ ሆይ ወደገፋችሁኝ ተመለሱ እያለ ነው።
ሐዋ 10:38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስና በኃይል ቀባው።
ቀአታውያን
1. መቅደሱንና የመቅደሱን እቃ ይጠብቁ ነበር።
የእግዚአብሔርን ቤት መጠበቅ ነው። ክብሩን ሳናይ አንሞትም
2. በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ነበሩ
3. ዋጋ ለመክፈል የጨከኑ ነበሩ
ማጠቃለያ
ዛሬም እኛ ልክ እንደ ቀአታውያን በመንፈስ ቅዱስ በሞላትና ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ በመሆን የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ልንጠብቅ ይገባል።

የእሁድ አምልኮ ቀን ነሐሴ 10/2018ጸሎት ፦ ወንጌላዊ ግሩም ዝማሬ ፦መጋቢ አሳፍ ማስታወቂያ ፦ መጋቢ ዘሪሁን ቃል ፦ መጋቢ አብነት ርዕስ፦ የደቀ መዝሙር (መስቀል) የተሸከመ ሰዉ ባህሪ  ...
18/08/2026

የእሁድ አምልኮ

ቀን ነሐሴ 10/2018

ጸሎት ፦ ወንጌላዊ ግሩም
ዝማሬ ፦መጋቢ አሳፍ
ማስታወቂያ ፦ መጋቢ ዘሪሁን
ቃል ፦ መጋቢ አብነት

ርዕስ፦ የደቀ መዝሙር (መስቀል) የተሸከመ ሰዉ ባህሪ
መነሻ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል
ፊሊጲስዮስ ምዕራፍ 2
በክርስቶስ አንዳች ምክር ቢሆን የፍቅር መጽናናት የመንፈስ ሕብረት ምሕረት ርኅራኄቢሆኑ ደስታዬን ፈጽሙልኝ ይላል ፀሐፊው በዋናነት የክርስቶስንሃሳብ በእናንተ ይኑር እያንዳንዱ ባልንጀራውንይውደድ ለራሱ የሚጠቅመውን ሳይሆን ለባልንጀራው በማሰብ ይመላለስ ባልንጀራው ከራሱ እንደሚሻል ይቁጠር

* ክርስቶስ ከላይ መወረድን እንደ መዋረድ አልቆጠረውም።
* የሰው ልጅን ሊያገለግል የጠፋውን ሊፈልግ መጣ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም::
* እየሱስ የባሪያን መልክ ይዞ ወደ ምድር መጣ ለመስቀል ለተዋረደው ለወንጀለኛው ለከፋው ለሞት ራሱን ሰጠ
—> ጌታ ለምን እንዲህ አደረገ?

-ለመክበር
-ለመግነን
-ለመታወቅ

ሳይሆን ብዙዎችን ከሞት ለማዳን ዝቅ ብሎ መቷል

*እየሱስ ያሳየን መንግሥተ እኔ ሳይሆን መንግሥተ እግዚአብሔር ነዉ

—> ጳውሎስ ለራሱ የራሱ ቦታ ፈላጊ ሳይሆን ተልዕኮው የክርስቶስን ሐሳብፈፃሚ ነበር
—> መስቀሉን የተሸከመ አያስከትለም እግዚአብሔር ያስከትልለታል
አቤሴሎም
#ፍልስፍናው ህዘብን መሳብ
#የህዝብን ልብ ማግኘት
#እራሱን የቀባ እና ያነገሰ አሟሟቱ ግን የከፋ ነበረ

አዶንያስ

#ከወንድሙ ወድቀት የተማረ
#ሊቀካህንን የያዘ
#አብያታርን ያሰለፈ ሹመቱ ግን ያልከረመ ነበረ

—> መስቀሉ የተሸከመው ሰው ለራሱ አይኖርም፤ ነገር ግን ለሚጠሉት ይኖራል እየሱስም አለ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው

* መስቀሉ የተሸከመው ሰው ይታዘዛል፤ ለመስቀል ሞት
* ደቀ መዝሙር ይታዘዛልሰዉ ለሚታዘዝለት ነገር፤ ለዛው ባርያ ነው:: የጽድቅ ባሪያ እንጂ የሀጢያት ባሪያ አንሁን

—> መስቀሉ የተሸከመ ሰው ፦

#ፈጣሪን ያመልካል
# ፈጣሪን ይታዘዛል
#ፀሎት ይፀለያል
#ከሰማይ እርዳታ ይጠይቃል
#ትሁት ነዉ

ትሕትና፡ ከሰማይ የሚወርድ ሳይሆን ሁኑ የተባልነውን የእግዚአብሔርን ሃሳብ ስንፈፅም የሚገኝ ነዉ
-> መስቀል የተሸከመ ሰዉ የሚናፍቀው ሀገር አለው እርሱም ለምድር ሳይሆን ለላይኛው ለሰማዩ ይኖራል
#መስቀል የተሸከመ ሰዉ ፍሬን ያፈራል
ማጠቃለያ ሀሳብ

መስቀል የተሸከመ ሰዉ ለሌላው የሚኖር በመሆኑ ራሱን አና የራሱን ጥቅም አስወግዶ ለእግዚአብሔር ፍቃድ ለሆነው ይሮጣል እየሱስ የወንጌል ማህበርተኛ እንደሆነ ሁሉ እራሱን እንደ ባርያ አስገዝቶ አይሁድን ይጠቀም ዘንድ እንደ እነርሱ ልማድ ተመላለሰ መሰዋትን በማቅረብ ከሕግ በታች በመሆን ስለወንጌል ሁሉን በሕይወቱ ከፍሏል

ቀን 7/12/2018የሀሙስ የትምህርት ፕሮግራምበዚህ ሳምንት መምህር ዮዳሄ ጌቱ በዮሐንስ ወንጌል 1–5 ማጠቃለያ መርሀ ግብር ላይ የተለያዩ ጠቃሚ ነጥቦችን አንስቷል።  1️⃣ የዮሐንስ ወንጌል...
16/08/2026

ቀን 7/12/2018
የሀሙስ የትምህርት ፕሮግራም
በዚህ ሳምንት መምህር ዮዳሄ ጌቱ በዮሐንስ ወንጌል 1–5 ማጠቃለያ መርሀ ግብር ላይ የተለያዩ ጠቃሚ ነጥቦችን አንስቷል።
1️⃣ የዮሐንስ ወንጌል ደራሲ ማን ነው? — ከ“ማን?” ወደ “ምን እንማራለን?”
በመጀመሪያ የተመለከትነው የዮሐንስ ወንጌል ጸሀፊ ማንነት ጥያቄ ነበር። አንዳንዶች ደራሲውን ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ያያይዙታል፤ ሌሎች ደግሞ በወንጌሉ ውስጥ ከተጠቀሰው “የሚወደው ደቀ መዝሙር” (Beloved Disciple) ጋር ያያይዙታል። አላዘርን ከዚህ ምስጢራዊ ሰው ጋር የሚያያዙ አቀራረቦች አሉ።
ነገር ግን ከChristopher W. Skinner አቀራረብ የተማርነው ጠቃሚ ነገር፦ ትኩረታችንን ማንነቱን ብቻ በመፈለግ ላይ ሳናቆም፣ ወንጌሉ ይህን ባሕርይ ለምን እንዳሳየን መጠየቅ አለብን። Skinner የተወደደውን ደቀ መዝሙር እንደ ምሳሌያዊ/ተምሳሌታዊ የደቀ መዝሙርነት ባሕርይ ለመመልከት ይረዳናል።
ዮሐንስ 1፥18 እና 13፥23–25ን ስናነጻጽር፣ አንዱ ኢየሱስ ከአብ ጋር ባለው ቅርበት ሲያሳይ፣ ሌላው የተወደደው ደቀ መዝሙር ከኢየሱስ ጋር ባለው ቅርበት ያሳያል።
👉 ስለዚህ ዋናው ጥያቄ፦
“የዮሐንስን ወንጌል የጻፈው ማን ነው?” ብቻ ሳይሆን፣ “እኔ ከኢየሱስ ጋር ምን ያህል ቅርብ ደቀ መዝሙር ነኝ?” የሚለው ነው።
2️⃣ ዮሐንስ መጥምቅ — ጥምቀት የውጭ ምልክት፣ እውነተኛ ንስሐ ግን የውስጥ ለውጥ
በሁለተኛው ነጥብ ዮሐንስ መጥምቅን እና የንስሐ መልእክቱን ተመለከትን። በተለይ ሉቃስ 3፥8 የሚያስታውሰን፦
“እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ።”
ይህ ንስሐ ቃልን ብቻ መናገር ወይም የውጭ ሃይማኖታዊ ምልክት መፈጸም እንዳልሆነ ያሳያል። እውነተኛ ንስሐ የውስጥ ለውጥ ነው፤ የውስጥ ለውጡም በሕይወት ፍሬ ይታያል።
ጥምቀት የዚህ ለውጥ ምልክት ነው፤ ምልክቱ ግን ራሱ የለውጡ ምትክ አይደለም።
👉 የንስሐ እውነታ የሚታየው በፍሬ ነው።
3️⃣ 🗺 ኢየሱስ በዮሐንስ 1–5 — ወንጌልን በካርታ ማንበብ
በዮሐንስ 1–5 የኢየሱስን ጉዞ በካርታ ላይ ተከታትለን ተመልክተናል። ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ወደ ይሁዳ፣ በሰማርያ በኩል እንደገና ወደ ገሊላ እና ወደ ኢየሩሳሌም የሚደረጉ ጉዞዎችን ተመልክተናል።
በዚህ ጉዞ ውስጥ የምናየው አንድ ነገር አለ፦
ኢየሱስ የሚጓዘው በአጋጣሚ አልነበረም፤ ጉዞው ከተልዕኮው ጋር የተያያዘ ነበር።
ከቦታ ወደ ቦታ የሚሄደው ሰዎችን ለመፈለግ፣ ለማስተማር፣ ለመፈወስና ሕይወትን ለመስጠት ነበር።
ይህ ለእኛም ትልቅ ትምህርት ነው፦
“የምሄድበት ቦታ፣ የምጠቀመው ጊዜና የማደርገው ነገር ከእግዚአብሔር ተልዕኮ ጋር የተያያዘ ነውን?”
ዛሬ ያለን ቴክኖሎጂ ጉዞን በጣም አቅልሎታል። ነገር ግን የዘመናዊ መጓጓዣ መኖር የኢየሱስን ተልዕኮና አኗኗር በሀብታምነት መለኪያ ለመተርጎም ምክንያት አይሆንም።
አንዳንድ የብልጽግና ወንጌል አቀንቃኞች “ኢየሱስ ዛሬ ቢኖር ኖሮ የግል አውሮፕላን ይጠቀም ነበር” የሚል አስተሳሰብ ሊያቀርቡ ይችላሉ። ነገር ግን ከወንጌል ውስጥ ይህን መደምደም አንችልም።
የኢየሱስ ጉዞ የሚያስተምረን የመጓጓዣ ዘዴን ሳይሆን የተልዕኮ ዓላማን ነው።
ብዙ ኪሎ ሜትር ተጓዘ — ግን ዓላማው አንድ ነበር፦ የአብን ፈቃድ መፈጸምና ሕይወት መስጠት።

06-12-2018 የእሮብ አገልግሎትፀሎት:- ወ/ዊ ግሩም በየነዝማሬ:- እ/ት በረከት ዳግማዊስብከት:- መ/ቢ አሳፍ ደበበየስብከቱ ርዕስ: እግዚአብሔር ለእኛየቃል ክፍል መዝ 46:1-2፣7፣11...
16/08/2026

06-12-2018 የእሮብ አገልግሎት
ፀሎት:- ወ/ዊ ግሩም በየነ
ዝማሬ:- እ/ት በረከት ዳግማዊ
ስብከት:- መ/ቢ አሳፍ ደበበ
የስብከቱ ርዕስ: እግዚአብሔር ለእኛ
የቃል ክፍል መዝ 46:1-2፣7፣11
መግቢያ
የሰው ልጅ በሂይወቱ ውስጥ ብዙ የሚያስፈሩ ሁኔታዎችን ያልፋል። አንዳንዴም ችግሩ ከቤት አንዳንዴም ከስራ ቦታ አንዳንዴም በግንኙነት የሚገጥመን ነገር ምን እንደሆነ አናውቅም። ሁኔታዎች ሊለዋወጡ ይችላሉ፤ ብዙ ነገሮች ሊቀያየሩ ይችላሉ፤ ችግር ሊመጣና በብዙ መከራ ውስጥ ልናልፍ እንችላለን፤ ነገር ግን መጠጊያችን የሆነው አምላካችን ከእኛ ጋር ነው።
አማኝ(ክርስቲያን) ማለት ችግሩ የማያገኘው ሰው ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ችግር ቢገጥመውም መጠጊያ ያለው ሰው ማለት ነው። ችግሩ እያለ እንዴት እንደማይፈራና እንደማይሰጋ ነው የሚያስደንቀው ነገር። ስለዚህ አይፈራም ጌታ አለው።
አለ ጌታ
1. እግዚአብሔር መጠጊያችን ነው።
✏️ ኢሳያስ 4:5-6
መጠጊያ ማለት በአደጋ ጊዜ የምናመልጥበት ቦታ ማለት ነው።
ዝናብ ሲመጣ ቤት እንፈልጋለን፣ ፀሃይ ሲበራታ ጥላ እንፈልጋለን፣ አደጋ ሲመጣ ደህንነት ያለበት ቦታ እንፈልጋለን።
ለእኛ ግን እግዚአብሔር ራሱ መጠጊያችን ነው።
✏️መጠጊያችን የሚለው ቃል እግዚአብሔር ከህይወት ማዕበል የሚጠብቅ መሆኑን ከአደጋው የምናመልጥበት አምባ መኖሩን ያመለክታል።
✏️እግዚአብሔር የመጨረሻ አማራጫችን ሳይሆን የመጀመርያ መጠጊያችን ይሁን!
2. እግዚአብሔር ኃይላችን ነው።
✏️ዕብ 4:16
አንዳንድ ጊዜ ችግሩ ከአቅጣቻችን በላይ ይሆናል። ለመፍታት የማንችለው ነገር ይሆናል፤ ኃይል ይከደናል። እዚ ላይ ነው የእግዚአብሔር ኃይል የሚገለጠው።
የእኛ ኃይል ሲያበቃ የእግዚአብሔር ኃይል አያበቃም ።
✏️ኃይል የሚለው ቃል እርሱ ጠላታችንን ሲደመስስልን ሳላ በውስጣችን የሚሰራውን ብርታትንና የህይወት እንቅፋትን እንድናሸንፍ የሚያበቃንን ጉልበት ያመለክታል።
✏️የሚያበረታ፣ የሚያነሳ፣ የሚያግዝ፣ ኃይሉን በድካማችን የሚገልጥ አምላክ አለ።
3. ባገኘን በታላቅ መከራ ረዳታችን ነው።
✏️ ኢዮብ 26:1-2
እምነት ችግር አይገጥመኝም ማለት አይደለም ይልቁንም ችግር ቢገጥመኝም ጌታ ከእኔ ጋር ነው ማለት ነው።
✏️እግዚአብሔር ሁልጊዜ ችግሩን አያስወግድም፤ አንዳንዴ በችግሩ መካከል(ውስጥ) ይደግፈናል።
✏️የእኛ ድፍረት የሚመጣው ከእኛ ብርታት አይደለም ከጌታ መኖር እንጂ። የትናቱ አምላክ ዛሬም አምላክ ነው የትናቱ ታማኝነት ዛሬም አለ።
✏️ይህ መዝሙር ያልተረጋጋና አስተማማኝ ያልሆነ ሁኔታ ሲደርስ በእግዚአብሔር እንድንታመንና እርሱን አለኝታ እንድናደርግ ያሳስባል።
✏️ችግርና ስጋት የመቋቋም ኃይልና ችሎታ የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው።
ማጠቃለያ
✏️አምላካችን መጠጊያችንና አይላችን ባገኘንም በታላቅ መከራ ረዳታችን ነው።
✏️አምላካችን ለእኛ መጠጊያችን ነው!
✏️አምላካችን ለእኛ ኃይላችን ነው!
✏️ አምላካችን በመከራ ጊዜ ረዳታችን ነው!
የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏ጌታ ሆይ፣ አንተ ለእኛ መጠጊያችን፣ ኃይላችንና በመከራ ጊዜ ፈጣን ረዳታችን ስለሆንህ እናመሰግንሃለን።

የእሁድ 03/12/18 መርሃ- ግብርሰንበት ትምህርት:- መ/ር በላይ አየለፀሎት:- መ/ቢ ዘሪሁን መንገሻዝማሬ:- ዘማሪ ቢኒያምና ዘማሪ ኤልያስቃል:- መ/ቢ አብነት ታደሰየቃል ክፍል:- ማቴ 1...
15/08/2026

የእሁድ 03/12/18 መርሃ- ግብር
ሰንበት ትምህርት:- መ/ር በላይ አየለ
ፀሎት:- መ/ቢ ዘሪሁን መንገሻ
ዝማሬ:- ዘማሪ ቢኒያምና ዘማሪ ኤልያስ
ቃል:- መ/ቢ አብነት ታደሰ
የቃል ክፍል:- ማቴ 16:24-27
ርዕስ: የደቀመዝሙር ሸክም
ይሄ ክፍል የሚጀምረው ከምዕራፍ 15 ጀምሮ ነው። ኢየሱስን በተለያየ ምክንያት የሚፈልግ ብዙ ነበር። ደቀመዛሙርቱን ከፈሪሳውያን እርሾ (ትምህርት) እንዲጠበቁ ነገራቸው። ከምዕራፍ 15:21-16:21 የተለያዩ ተአምራት በተለያየ ቦታና ጊዜ ሲያደርግ የሚተርክ ክፍል ነው። ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል? ብሎ ጠየቃቸው።
ኢየሱስ ራሱን በማቴዎስ 30 ጊዜ፣ በማርቆስ 14 ጊዜ፣ ሉቃስ 25 ጊዜ፣ ዮሐንስ 12 ጊዜ ራሱን የሰው ልጅ ብሎ ጠርቷልደ እነርሱም ሲመልሱ መጥምቁ ዮሐንስ፣ ኤልያስ ፣ ኤርምያስ ከነብያት አንዱ ይሉአል ብለው መለሱለት፤ መልካም እናንተስ ማን እንደሆንኩ ትላላችሁ ሲላቸው ጴጥሮስ አንተ መሲህ፣ የተቀባው ክርስቶስ፣ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ። ኢየሱስ በሽማግሌዎችና በካህናት አለቆች እጅ መከራን እንደሚቀበል፣እንደሚሰቀል፣እንደሚገደል፣ በሶስተኛውም ቀን ከሙታን እንደሚነሳ ሲናገር ጴጥሮስ ገሰፀው ኢየሱስም ሂድ አንተ ሰይጣን የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብም አለው። እሺ የእኛስ እጣ ፈንታ ምንድነው ሲሉት እናንተም ቁርጣችሁን እወቁ ማንም የእኔ ደቀመዝሙር ሊሆን የሚወድ ራሱን ይካድ መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ።
መስቀል ምንድነው?
መስቀል ቶሎ የማይሞቱበት መቅጫ ነው። መስቀል መሸነፍ ነው፣ ውርደት ነው፣መሣለቂያ ነው፣ የህዝብ መዘበቻ መሆን ነው፣ አውቆ መሞኘት ነው፣ ነቀፌታን መጥገብ ነው፣ በሰው የተገፋ በአምላክ የተተወ የሚመስል መንገድ ነው።
መስቀል ያጎብጣል፣ ብቻን ያስቀራል የሚያውቀንን ያርቃል
መስቀል ሁሉን ስለ ክርስቶስ መተው፣ ማጣት ነው።
ሊከተለኝ የሚወድ፣የእኔ ሊሆን የሚወድ፣ሊያገለግለኝ የሚወድ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ። ከእኔ ይልቅ እናቱን፣ አባቱን ወንድ ልጁን የሚወድ መስቀሉን የማይሸከም ከኋላዬ የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባም።
መስቀልን መሸከም ምንድነው?
እግዚአብሔር በሰጠንና በፈቀደልን ክልል ውስጥ በታማኝነት ማገልገል ነው። መስቀል ፍፁም መሰጠት ነው። መስቀል መስዋዕትነት ነው። ፈቃድን፣ መብትን፣ ስልጣንን አሳልፎ መስጠት ነው።
ምን ተሸክመናል? እግዚአብሔር ለሰጠን አደራ ምን ያህል ታማኝ ነን? መስቀል የውርደት፣ የሞት፣ የመገፋት መንገድ ይሁን እንጂ ፍፃሜው ትንሳ፣ ክብር ነው።
ዋጋ ስለ ምን እንከፍላለን?
ስለ ጌታ ብለን በልዮ ልዮ ሁኔታ እያለፍን ያለን ያ መስቀል ነው ጌታ ይከፍላል።
ማጠቃለያ:-
ክርስትና ዳር ዳሩን አይኖርም ዳር ዳሩን የሆነ አገልግሎት የለም።መስቀል የሌለበት ወንጌል የለም። እውነተኛ ደቀመዝሙር መስቀሉን ተሸክሞ ጌታን መከተል አለበት፣

የትምህርት መርሃ-ግብር ሀሙስ ማታ 30/11/18 ፀሎት፡- እ/ት ቃልኪዳን ሙሉቃል፡- ወ/ም ሙሉጌታ በልዳየቃል  ክፍል፦ ዮሃ 5:24-47Ø  በሁለት ልንከፍለው እንችላለን ፣ ከቁጥር 24-30...
13/08/2026

የትምህርት መርሃ-ግብር ሀሙስ ማታ 30/11/18

ፀሎት፡- እ/ት ቃልኪዳን ሙሉ
ቃል፡- ወ/ም ሙሉጌታ በልዳ
የቃል ክፍል፦ ዮሃ 5:24-47
Ø በሁለት ልንከፍለው እንችላለን ፣ ከቁጥር 24-30 ያለው ኢየሱስን መከተል ምን ማለት ነው፣ ውጤቶቹን ምን ምን ናቸው? የሚለውን ሲያስዳስሰን ከ 31-47 ያለው ደግሞ ኢየሱስ አምላክ የመሆኑን ምስክርነት ያሳየናል
ክፍል-1 ቁጥር 24-30 ኢየሱስን መከተል ምን ማለት ነው፣ ውጤቶቹን ምን ምን ናቸው ?
Ø እውነት እውነት እላችኋለው (በግሪኩ Amen Amen) ፣ በዮሀንስ ወንጌል ውስጥ 27 ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ቀጥሎ ለሚነገረው ነገር አጽንዖት ለመስጠት ሲባል የሚገባ ነው
Ø ጌታ ኢየሱስ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን ከሞት ወደ ህይወት ተሻገረ ይላል፣ መዳን ቅጽበታዊ እና የአሁን ነው እንጂ ከሞትን በኋላ የምናውቀው አይደለም
Ø አንዳንዶቻችን መዳን አይሰማንም ስንል እንሰማለን ነገር ግን መዳን የስሜት ሳይሆን የቦታ (Position) ለውጥ ጉዳይ ነው ፣ ለዚህ የኖህ መርከብን እንደ ጥሩ ምሳሌ የሚጠቀሙ አሉ። ኖህ ከጥፋት ውሃ መዳኑን ያወቀው በስሜቱ ሳይሆን በመርከቢቷ ላይ በመሆኑ ነው። የኛም መዳን የተረጋገጠው በኢየሱስ ላይ በመሆናችን ነው።
Ø ቁጥር 25 ላይ ሙታን የሚላቸው በስጋ የሞቱ ሳይሆኑ በመንፈስ ሙታን የሆኑ ናቸው።፣
የእግዚአብሔርን ልጅ ድምጽ ይሰማሉ- ህይወት የሚሰጠውን ጌታ ሰምተው ምላሽ ይሰጣሉ፣ ቅጽበታዊ የሆነ ፣ መንፈሳዊ መዳን ነው (Instant Spiritual Resurrection) ነው።
Ø ቁጥር ቁጥር 25 ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ ሲለው ቁጥር 27 ላይ ግን የሰው ልጅ ብሎ ይጠራዋል። ይህ የሆነው፣ በፍርድ ወንበር ላይ የሚቀመጠው ኢየሱስ ሰው የሆነው፣ የሰውነትን ድካም የሚረዳው፣ ከሃጢያት በቀር እንደኛ በሁሉ የተፈተነው እና የሚራራው ኢየሱስ እንደሆነ ለማሳየት ነው።
Ø ቁጥር 29 ላይ በመቃብር ያሉት፥ የሞቱ ሰዎችን በሙሉ፣ ያመነውንም ያላመነውንም የሚያመለክት ነው።
መልካም ያደረጉ፦ ሲል በመልካም ስራ የዘላለም ህይወት ይገኛል ማለት ሳይሆን፣ የልጁን ድምጽ ከመስማት የሆነ ማመን እና ከማመን የሆነ መልካም ስራ ማለት ነው
ክፉ ያደረጉ፥- እንዲሁ ለመጣው ድምጽ ምላሽ ያልሰጡ፣ ከዚህም የተነሳ የኑሮ ዘይቤያቸውን ሓጢያት የተጫነው ፣ በክፉ ስራቸው የቀጠሉ ናቸው።
Ø ቁጥር 30 ፍርዴ ቅን ነው ማለት፡ ሌላ ይግባኝ ሰሚ የማያስፈልገው ትክክለኛ (Genuine) ነው።
ክፍል-2 ቁጥር 31-47 ኢየሱስ አምላክ የመሆኑ ምስክሮች
እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም ማለቱ እንደ ህጋችሁ ማለቱ ነው፣ ሙሴ በዘዳ 17:6 ላይ ምስክር ቢያንስ በሁለት አሊያም በሶስት እንደሚጸና ይደነግጋል።
1. አብ፡ ቁጥር 32 ስለ እኔ የሚመሰክረው ሌላ ነው ሲል ሌላ የሚለው በግሪክ አሎስ (Alos) የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በአይነት ተመሳሳይ (Another of the same kind) መሆኑን ያሳያል። የእርሱ ምስክርነት ደግሞ እውነት ነው
2. ዮሃንስ፦ በዮሃ 3:18 እንዲሁም 1:29-34 ዮሃንስ ስለ ኢየሱስ መስክሯል። ኢየሱስ እኔ የሰው ምስክርነት አልቀበልም ነበር፣ የአብና የወልድ ምስክርነትም በቂ ነው ብሎ የዮሃንስን ምስክርነት የሚጠራበትን ምክንያት ሲናገር እናንተ እንድትድኑ ነው ይላል።
Ø ዮሃንስን ሲገልጠው ፡ የሚነድ መብራት (Lamp) እንደነበረ ፣ እየነደደ ፣እየተቃጠለ በሓጢያታቸው ላይ መብራቱን (Lamp) (ከእውነተኛው ብርሃን ከኢየሱስ ዮሃ 1:4-5) እየወሰደ ያበራ ነበር።
ጥቂት ዘመን፦ ኢየሱስ ይሄን በሚናገርበት ወቅት በጊዜ ቅደም ተከተል (Chronology) ዮሃንስ በወህኒ ነበር፣ እናም በዚህ ሰው ልትጠቀሙ እና ወደ እውነት እና ብርሃን ወደ ሆነው ጌታ ልትመጡ አልወደዳችሁም
3. ስራው፦ ይህ እኔ የምሰራው ስራ አብ እንደላከኝ የሚናገር ነው።
ስራ የሚለው ምን ነው የሚለው ላይ ሁለት አመለካከቶች አሉ 1. ኢየሱስ ከብሉ ጀምሮ፣ በስጋ በተገለጠበት ወራት እንዲሁም ከትንሳኤው በኋላ የሰራቸውን እና የሚሰራቸውን ነው የሚሉ አሉ ደግሞ በስጋ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት የሰሯቸውን ወይኑን ወደ ውሃ መለወጥ፣ 38 አመት ሽባ የነበረውን ሰው መፈወስን የመሳሰሉ ከጌታ ፍቅርና ርህራሄ የመነጩ፣ መረጋገጥ የቻሉ እንዲሁም የሰውን የተፈጥሮ ሃይል ያለፉ ስራዎች ሊሆን ይችላል።
ቁጥር 37 ድምጹን አልሰማችሁም፦ ማር 9:2-7,ዮሃ 12:8, ማቴ3:17 ላይ የአብ ድምጽ ምስክር ሆኗል ለኢየሱስ፣ ግን ሊሰሙት አልወደዱም ነበር መልኩን አላያችሁም፡ አምላክ ስጋ ለብሶ በመካከላችሁ ሲመላለስ አላያችሁም
4. መጽሃፍት፥- ትመረምራላችሁ ሲል በጣም በጥልቀት (Diligently) ህግን ያጠኑ እንደነበር ማሳያ ነው። የአይሁድ ሰዎች ትንቢትን በጣም ይመረምሩ ነበር ፣ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ በቃላቸው ሳይቀር ይይዙት ነበር። ሄሮድስ በማቴ 2:3-4 ንጉሱ ወዴት እንደሚወለድ ጻፎችን እና የካህናት አለቆችን ሲጠይቅ ወዲያው ነው ሚል 5:2ን ጠቅሰው ከቤተልሄም ይሁዳ እንደሆነ የነገሩት። ስለ ኢየሱስ የተነገሩና በኢየሱስ የተፈጸሙ ወደ 300 የሚጠጉ ትንቢቶች በብሉይ አሉ ፣እነዚህንም ያውቋቸዋል ግን ህይወት እንዲሆንላቸው ወደ ኢየሱስ ሊመጡ አይወዱም።

ይሄ ሁሉ ምስክር ካለ ለምን አይቀበሉትም?

1. ቁጥር 42 እግዚአብሔርን ስለማይወዱት፣ ይህ ደግሞ የህግ ማዕከል ነው
2. በራሱ ስም ሳይሆን በአብ ስም ስለመጣ
3. የእግዚአብሔርን ክብር ሳይሆን የሰውን ክብር ስለምትፈልጉ ነው። በዚህ ጉዳይ የምከሳችሁ እኔ ሳልሆን ተስፋ የምታደርጉት ሙሴ ነው ምክንያቱም ሙሴን ራሱ አላመናችሁትም ብታምኑት ኖሮ ስለ እኔ የጻፈውን ታሙና ትቀበሉ ነበር

ምን እንማር፦

1. ስራችን ማንነታችንን ይመሰክራል። የምትናገረውን እንዳልሰማ የምትሰራውን እያየው ነው እንደሚሉት እንዳይሆን ለስራችን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ያዕ2 ፥18
2. የእግዚአብሔርን ቃል የምናጠናው ወደ ኢየሱስ ለመምጣት ሊሆን ይገባል
3. ክብር የምንቀበለው ከማን ነው፣ ከሰው ወይስ ከእግዚአብሔር?

29/11/2018
12/08/2026

29/11/2018

የእሁድ አምልኮ መረሀግብር 26/11/18በፀሎት:-ወ/ም ሉቃስበዝማሬ:- የቤተክርስቲያን የወጣት ህብረትበቃል ፦ ፓስተር ድነቅነሽ ሥላሴርዕስ፦ አባቶች ወንጌልን ለወጣቶች እንዴት አደረሱ? ወጣቶ...
07/08/2026

የእሁድ አምልኮ መረሀግብር 26/11/18
በፀሎት:-ወ/ም ሉቃስ
በዝማሬ:- የቤተክርስቲያን የወጣት ህብረት
በቃል ፦ ፓስተር ድነቅነሽ ሥላሴ
ርዕስ፦ አባቶች ወንጌልን ለወጣቶች እንዴት አደረሱ? ወጣቶችስ እንዴት ተቀበሉ?

በዚህ ስብከት ሰባኪዋ ከ2ኛ ጢሞቴዎስ መልእክት በመነሳት ወንጌል ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላ ትውልድ እንዴት እንደሚተላለፍ አስተምረዋል። ጢሞቴዎስ እምነቱን በመጀመሪያ ከቤተሰቡ እና ከታማኝ አማኞች ተማረ፤ ከዚያም በጳውሎስ መንፈሳዊ ልጅነት ስር በመሆን ወንጌልን ለማገልገል ተዘጋጀ።
ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የሰጠው መልእክት ዛሬም ለእኛ የሚመለከት ነው። የተቀበልነውን የወንጌል እውነት ለሌሎች ማስተላለፍ የእያንዳንዱ አማኝ ኃላፊነት ነው። አባቶች ለወጣቶች የእምነት ምሳሌ በመሆን፣ በማስተማር እና በመደገፍ ወንጌልን ማድረስ አለባቸው። ወጣቶችም የተሰጣቸውን የወንጌል አደራ በታማኝነት ተቀብለው ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባቸዋል።
በ2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥3-6 ላይ ጳውሎስ ክርስቲያንን እንደ መልካም ወታደር፣ እንደ ሕጉን የሚጠብቅ አትሌት፣ እና እንደ ታታሪ ገበሬ ያመሳስለዋል። ይህም የወንጌል አገልግሎት ትጋት፣ ትዕግሥት እና መስዋዕትነት እንደሚጠይቅ ያሳያል።
ጳውሎስ ይህን መልእክት በእስር ቤት ሆኖ ጻፈ፤ ነገር ግን ሁኔታው ወንጌሉን ሊያቆም አልቻለም። “የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም” (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥9) በማለት የወንጌል ኃይል ከማንኛውም ሁኔታ በላይ እንደሆነ አሳየ።
ስለዚህ እኛም የቀደሙት ትውልዶች በመስዋዕትነት ያደረሱልንን ወንጌል በእምነት ተቀብለን፣ በሕይወታችን አሳይተን፣ ለቀጣዩ ትውልድ በታማኝነት ማድረስ አለብን።
ዋና መልእክት፦ ወንጌል የተቀበልነው አደራ ነው፤ ለማስተላለፍ የተጠራን ነን።

በደብረዘይት መሀል መሠረተ ክርስቶስ ደምቢ መሠረተ ክርስቶስ ስርጭት ጣቢያ የተዘጋጀ የፈውስ ፕሮግራም ለተከታታይ 5  አርቦች የሚቆይ ነሀሴ 1-8-15-22-29/2018
05/08/2026

በደብረዘይት መሀል መሠረተ ክርስቶስ ደምቢ መሠረተ ክርስቶስ ስርጭት ጣቢያ የተዘጋጀ የፈውስ ፕሮግራም
ለተከታታይ 5 አርቦች የሚቆይ
ነሀሴ 1-8-15-22-29/2018

Address

Debre Zeyit

Opening Hours

02:00 - 06:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Zeit Meserete Kristos Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Debre Zeit Meserete Kristos Church:

Shortcuts

Share

Category