Remnant Youth & kid's Holistic Nonprofit Corporation

Remnant Youth & kid's Holistic Nonprofit Corporation VISION
To Save generation from distraction & bondages of this evil world & bridge generational gap

07/12/2025
You can Get at “Amazon” three books.    Let's save the generation by buying the book .     BRIDGING GENERATIONAL    PART...
19/06/2025

You can Get at “Amazon” three books.
Let's save the generation by buying the book .
BRIDGING GENERATIONAL
PART I- Understanding Generation
PART II- Cause of Generational Gap
PART III- Bridging & Solution
BY “Author” Askale Asfaw Weldearegay (PhD)

***ክፍል 29***“የእግዚአብሔር ጥበብ ለወጣቶችና ለልጆች”(ምሳሌ 4፡1-27) †  ወደ መልካም መንገድ የሚመራን ልክ እንደ እግዚአብሔር ውድ ካርታ ነው። †  ጥበብን ከተከተልን ደስታን፣ ...
01/06/2025

***ክፍል 29***
“የእግዚአብሔር ጥበብ ለወጣቶችና ለልጆች”
(ምሳሌ 4፡1-27)
† ወደ መልካም መንገድ የሚመራን ልክ እንደ እግዚአብሔር ውድ ካርታ ነው።
† ጥበብን ከተከተልን ደስታን፣ ሰላምን እና ዓላማን እናገኛለን።
† ዓለም ግራ በሚያጋባበት ጊዜ እንኳን የእግዚአብሔር እውነት መንገዱን ያሳየናል፣ ይመራናል።
1. ከሚወዷችሁ ተማሩ
“እናንተ ልጆች፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤” (ምሳሌ 4፡1)
† ልጆቼ ሆይ የአባትን ምክር ስሙ
† ወላጆችህ፣ አስተማሪዎችህ እና መሪዎችህ ከስህተት እንድትርቁ ሊረዱ ይፈልጋሉና ተማሩ።
† በጆሮ ብቻ ሳይሆን ከልብ አዳምጡ። እናንተን ለመርዳት እየሞከሩ ነውና ተማሩ!
2. ጥበብ ከወርቅ ትበልጣለች
“ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።” (ምሳሌ 4፡7)
† ማስተዋልና ጥበብን በብርቱ ፈልጉ
† ብልህ መሆን፥ ሀብታም ከመሆን ይበልጣል፣
† አዋቂ መሆን፥ ታዋቂ ከመሆን ይበልጣል።
3. ከመጥፎ ጎዳና ራቁ
“በኃጥኣን መንገድ አትግባ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ። ከእርስዋ ራቅ፥ አትሂድባትም፤ ፈቀቅ በል ተዋትም።” (ምሳሌ 4፡14-15)
† የክፉ ሰዎችን መንገድ አትከተሉ።
† አንዳንድ ነገሮች አስደሳች ቢመስሉም ወደ ችግር ያመራሉና ተጠንቀቁ።
† ከሐሜት፣ ከውሸት፣ ከጠብ ወይም ከማንኛውም ነገር ከእግዚአብሔር ከሚያርቁ ነገሮች ራቁ።
4. መልካምና ትክክለኛውን ማድረግን ቀጥሉ።
“የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።” (ምሳሌ 4፡18)
† የደግ ሰዎች መንገድ እንደ ንጋት ፀሀይ ነው፤ ወደ ትክክለኛ መንገድ ይመራል።
† መልካም ሥራ እየበራ እና እያደገ ይሄዳል።
† ከእግዚአብሔር ጋር ስትኖሩ ነገሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዋቡ ይሄዳሉ።
† ደግነትን፣ እውነትን፣ እና ፍቅርን ማሳየቱን ቀጥሉ።
5. ልብህን ጠብቅ
“አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።” (ምሳሌ 4፡23)
† ከሁሉ በላይ ልብባችሁን ጠብቁ፤ የምታደርጉት ነገር ሁሉ ወደ መልካም ይመራችኋል።
† ወደ ልባችሁ የገባው መልካም ያልሆኑ ነገሮች፥በህይወታችሁ ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉና ተጠንቀቁ።
† ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ??? ወዴት ነኝ?? ከማንና ከምን ጋር ነኝ???
† ልቤ የእግዚአብሔርን መንገድ እየጠበቀ ነው???
6. የምትሄዱበትን መንገድ ተመልከቱ
“የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና። ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከክፉ መልስ።” (ምሳሌ 4፡26-27)
† በመልካም መንገድ ላይ ቆዩ።
† ከክፉ መንገድ ተመለሱ።
† ትኩረትን ከሚከፋፍሉ ነገሮች ራቁ።
† ከመልካም መንገድ ሊያወጣችሁ ካለው ተጠበቁ።
† ሌሎችንና ራሳችሁን ለመርዳት ወደ መልካም ግቦች ተመልከቱ።

24/05/2025

***ክፍል 28***
በልጆችና በወላጆች መካከል ያለውን የትውልድ ልዩነት እንዴት ማቃለል ይቻላል?
1. በመግባባትና በመተሳሰብ፡- በወላጆችና በልጆች መካከል ግልጽ እና ታማኝ የሆነ ግንኙነት እንዲኖር ማበረታታት። አንዳችሁ የሌላውን አመለካከት ሳይነቅፉ በአክብሮት ያዳምጡ።
2. ልዩነቶችን በማስወገድ፡- እያንዳንዱ ትውልድ የተለያየ እሴት፣ እምነት እና ልምድ እንዳለው መቀበል። እነዚህን ልዩነቶች ለመረዳት እና ለማክበር ይሞክሩና መፍትሔ መሆን
3. አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ፡- የሚወዷቸውን ነገሮች በማድረግ ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ይሞክሩ። የበለጠ ጠንካራ ግንኙነት እና ግንዛቤ ለመፍጠር ይረዳል።
4. ተሞክሮዎችን ያካፍሉ፡- ልምዶቻችሁን አካፍሉ እና ከልጅዎ ተሞክሮዎች ጋር ያዛምዷቸው። ክፍተቱን ለማጥበብ እና የጋራ ግንዛቤን ለመፍጠር ይረዳል።

17/05/2025

*** ክፍል 27***
"የወንድማማችነት ፍቅር በተግባር"
በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤ (ሮሜ 12:10)
ልጆችን ደግነትን፣ ክብርንና ወንድማማችነትን በስሜት ብቻ ሳይሆን በእውነተኛ ተግባራት ላይ የተመሰረተ መዋደድና መከባበርን እንዲረዱና እንዲለማመዱ መርዳት።
1.“በደግነት መዋደድ” ሲባል ምን ማለት ነው?
† በቅርብ ቤተሰብ ውስጥ እንዳለ ፍቅር ለሌሎች ጥልቅ፣ ልባዊ ፍቅርና እንክብካቤ መስጠት
† ያዘኑትን ማጽናናት
† ከሌሎች ምንም ነገር ሳንጠብቅ ሌሎችን መርዳት
† በግጭት ጊዜ ትዕግስትና ጸጋን ማሳየት
2. በእውነተኛ ህይወት ውስጥ "የወንድማማችነት ፍቅር" ምን ይመስላል?
† በእውነተኛ ህይወት ውስጥ ሌሎችን እንደ ቅርብ ወንድምና እህት ወይም የቅርብ ጓደኛ በምትሰጡት የመውደድ አይነት መውደድ፣ አክብሮት እና ታማኝነት መስጠት።
† ሌሎችን የሚያስቀድም ፣ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር። በስሜት ብቻ ሳይሆን፣ በመልካም ቃላት፣ አጋዥ ድርጊቶች እና ተከታታይ ድጋፍ መስጠት።
“የወንድማማች መዋደድ ይኑር። እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ በዚህ አንዳንዶች ሳያውቁ መላእክትን እንግድነት ተቀብለዋልና። (ዕብራውያን 13፡1-2)
3. ራሳችንን ላይ ብቻ እንድናተኩር በሚያበረታታ ዓለም ውስጥ ‘ሌሎችን ልንወድ’ የምንችለው እንዴት ነው?
† “ሌሎችን መውደድ” ስሜታቸውን እና ፍላጎታቸውን ከራሳችን በፊት ማስቀደም ።
† “ራስህን አስቀድም” በምትል ዓለም ውስጥ፣እውነተኛ ፍቅር እና ክብርን ማሳየት፣
“በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤” (ሮሜ 12:10)

11/05/2025

እጅ ለእጃችን ተያይዘን

Remnant Youth & Kids Holistic***ክፍል 26***የልጆች የመታዘዝ ውጤትመጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ተግባራዊ ጥቅሞች1. መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመታዘዝ ውጤቶች• የእግዚአብሔር በረከትና ሞገ...
04/05/2025

Remnant Youth & Kids Holistic
***ክፍል 26***
የልጆች የመታዘዝ ውጤት
መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ተግባራዊ ጥቅሞች
1. መጽሐፍ ቅዱሳዊ የመታዘዝ ውጤቶች
• የእግዚአብሔር በረከትና ሞገስ፡
“ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና። መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት። (ኤፌሶን 6:2–3)
• እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት፡ “ልጆች ሆይ፥ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ።”
(ቆላስይስ 3:20)
• መንፈሳዊ እድገት እና ጥበቃ፡ የሚታዘዙ ልጆች የእግዚአብሔርን መመሪያ እንዲከተሉና በእሱ ጥበቃ ስር እንዲቆዩ ይመራቸዋል።
2.ተግባራዊ የመታዘዝ ውጤቶች
• አክብሮት እና መተማመን፡- አዋቂዎች ታዛዥ ለሆኑ በበለጠ ኃላፊነት ለመስጠት ያምናሉ።
• ደህንነት እና መመሪያ፡ መመሪያዎችን ማክበር ከአደጋና ጉዳትን ለማስወገድ ይረዳል።
• ጠንካራ ግንኙነት፡ ታዛዥ ልጆች ከወላጆች እና ከሌሎች ጋር የተሻለ ግንኙነት ይፈጥራሉ።
• ራስን መግዛት እና ስኬት፡ ወደ ጥሩ ልምዶች፣ የትምህርት ስኬት እና የግል እድገት ይመራል።

***ክፍል 20***“ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና።” (ኤፌሶን 6:1) እግዚአብሔር የቤተሰብን መዋቅር ለመምራት፣ ለፍቅር እና ለተግሣጽ “ልጆች ለወላጆቻችሁ በጌታ...
08/03/2025

***ክፍል 20***
“ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና።” (ኤፌሶን 6:1)
እግዚአብሔር የቤተሰብን መዋቅር ለመምራት፣ ለፍቅር እና ለተግሣጽ “ልጆች ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ ይህ የሚገባ ነውና።” በማለት የእግዚአብሔር ቃል እንድንታዘዝ ያስተምረናል።
#መታዘዝ፥ ህግጋትን መከተል ብቻ አይደለም። ባህሪንና እምነትን በሚገነባ መልኩ ስልጣንን መማር፣ማደግና ማክበር ነው።
#በመታዘዝ ውስጥ በወላጆች እና በልጆች መካከል ያለውን የትውልድ ክፍተት ማጣጣም እና ማስተካከል እንችላለን።
#ልጆች ወላጆቻቸውን ለመታዘዝ ማዳመጥ እና ማክበር አለባቸው።
#ታዛዥነት እና መከባበር የበለጠ ጠንካራ እና እግዚአብሔርን ያማከለ ቤተሰቦችን እንደሚገነባ ያስተምረናል።
#ወላጆች ልጆችን ለማዘዝ በፍቅር፣ በጥበብ እና በመግባባት እንዲመሩም ይገባል።
#ወላጆች እና ልጆች በክፍት ልብ ሲደማመጡ፣ ትስስራቸውን የበለጠ ያጠናክራሉ፣ አብረውም በእምነት ያድጋሉ።
#በወላጅ እና በልጆች ግንኙነት ውስጥ በመታዘዛችን የመከባበርን አስፈላጊነት ያጎላል።
#መታዘዝ በቤተሰብ ውስጥ ስምምነትን ያሳድጋል።
# # #ለወላጆች፡
† “ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።” (ምሳሌ 22፡6)
† እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው። (ኤፌሶን 6፡4)
† የእግዚአብሔርን ሥርዓቱንም ሕጉንም አስተምራቸው።
† የሚሄዱበትን መልካም መንገድ የሚያደርጉትንም ሥራ ሁሉ አሳያቸው።
† በፍቅር፣ በትዕግስት እና በማስተዋል ምሳሌ በመሆን እናስተምራቸው።
† ከማዘዛችን በፊት በፍቅርና በርህራሄ ስለ ትዕዛዙ በማብራራት ግልጽ ውይይቶችን እንለግሳቸው።
† የልጆችን ችግሮች ተረድተን፥ ለችግሩ መፍትሄ እንሁን።
† የልጆችን ጭንቀት እናዳምጣቸው፤ በእምነትና በመልካም ግንኙነት መልስ በመሆን አርአያ ይሁኑ።
# # #ለልጆች:
† “ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ፥ ይህ የሚገባ ነውና።” (ኤፌሶን 6:1)
† “አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።” (ዘጸአት 20፥12)
† በማዳመጥ እና በጥንቃቄ ምላሽ በመስጠት አክብሮት አሳይ.
† መመሪያዎችን ችላ ከማለት ይልቅ በማይገባዎት ጊዜ ጥያቄዎችን ይጠይቁ።
† ወላጆችዎ እርስዎን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱዎ ሀሳቦችዎን እና ስሜቶችዎን በአክብሮት ያካፍሉ።
# #መግባባትን እንዴት ማጠናከር ይቻላል?
1. የወላጆችና የልጆች የአንድነት ጸሎት ይኑረን
# በቤተሰብ ግንኙነት ውስጥ ጥበብ እንዲሰጥ እግዚአብሔርን በእምነት ጠይቁ።
2.ታማኝ ውይይቶችን ማድረግ
# በመደማመጥና በመከባበር ሀሳቦችን በግልፅ ያካፍሉ።
3. በፍቅር ላይ የተመሰረተ የቤተሰብ ህግጋትን ያውጡ
# ታዛዥነት ቀላል የሚሆነው ልጆች ከህግ በስተጀርባ ያለውን ምክንያት ሲረዱ ነው።
4. መልካም ባህሪን እና ጥረትን አወድሱ
#መታዘዝ ማበረታታትን ብቻ ሳይሆን ማበረታቻን ተጠቀሙ

19/02/2025

***ክፍል 18***
“ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።
ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።” (ሉቃስ 2:51)
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ምድራዊ ወላጆቹን እናቱን ማሪያም እና ዮሴፍን ታዛዥ እንደ ነበረ ያስተምረናል። ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆንም፣ ፍጹምና ሁሉም ጥበብ ቢኖረውም እንኳን ራሱን ዝቅ በማድረግ ወላጆቹን በማዳመጥ እና መመሪያን በመከተል ይታዘዝላቸውም ነበር።
ኢየሱስ ታዛዥ በመሆኑ
† ወላጆቹን ይሰማና ይታዘዝ ነበር
† ማርያምንና ዮሴፍ ያከብራቸውና ይሰማቸው ነበር
† ምንም እንኳን የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆንም ወላጆቹን ያሉትን ችላ ሳይል ይታዘዝ ነበር
† በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር
† በእውቀት፣ በመልካም ባህርይ እና በበረከቶች ውስጥ እለት በእለት ይሞላ ነበር
† በትሕትና በአክብሮት በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ይመላለስ ነበር
† የደስታ፣የእረፍትና የሰላም ዘመን ነበረው
† መታዘዛችን በረከት እንደሆነ ለእኛ መልካም ትምህርትና ምሳሌ ሆኖልናል
# # #በመታዘዛችን
† የሰላም፣ የደስታና የስኬት ባለቤትነትን ያጎናጽፈናል
† በእውቀትና በጥበብ እንድናድግ ያደርገናል
† እግዚአብሔርን ደስ ይሰኛል
† ከወላጆቻችን እና ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን እናገኛለን
# # # የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ለምድራዊ ወላጆቹ ታዛዥና መልካም ምሳሌ ከሆነን እኛ ደግሞ የበለጠ መታዘዝ ይጠበቅብናል።

26/01/2025

"ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለ ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም።" (ምሳሌ 22:6)
***ክፍል 15***
“ልጆች ሆይ፥ ይህ ለጌታ ደስ የሚያሰኝ ነውና በሁሉ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ። አባቶች ሆይ፥ ልባቸው እንዳይዝል ልጆቻችሁን አታበሳጩአቸው።” (ቆላስይስ 3፡20-21)
#ለወላጆች መታዘዝና አክብሮት እንድንሰጣቸው አስፈላጊ መሆኑን የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል። ልጆችና ወጣቶች ከወላጆቻቸው ጋር በመልካም በመኖር ያላቸውን ዝምድና የማጠናከር ኃላፊነት ከወላጆች ይጠበቃል። ይህም ድርጊታቸውና እምነታቸው ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲኖራቸውና በፍቅር መመላለስ እንዴት እንደሚችሉ ምሳሌ መሆን ይገባናል። በቤተሰብ ውስጥ ስምምነትን የሚያበረታታ እና ወጣቶችና ልጆች በቤተሰብ ውስጥ ያላቸው ሚና በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኝና ዋጋ ያለው መሆኑን ቃሉ ያረጋግጥልናል።
ይህ ቃል ለወላጆችና ለልጆች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ይሰጠል። ይህም:-
1. መታዘዝ እና ክብርን መስጠት
#ልጆች የወላጆቻቸውን ስልጣን እንዲያከብሩና እንዲታዘዙ ያስተምራል። ወላጆችን ማክበር በቤተሰብ ውስጥ ጤናማ ግንኙነቶችን ለመገንባት የሚረዳ መሠረታዊ መመሪያ ነው።
2. መታዘዝ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።
#ልጆች ለወላጆች ሲታዘዙ "እግዚአብሔርን ደስ ይሰኛል።" የወላጆችን መመሪያና ደንቦችን መከተል ብቻ ሳይሆን፥ እግዚአብሔርን ማክበርና ከፈቃዱ ጋር ተስማምቶ መኖራችንን ያስረዳናል።
3. ተጠያቂነትን እና ኃላፊነት መገንባት
#ልጆች ለወላጆች ሲታዘዙ ኃላፊነት እና ተጠያቂነትን ይማራሉ፥ እንዲሁም በወላጆች እና በልጆች መካከል መተማመንን ይፈጥራል። ልጆች የወላጆችን መመሪያ ሲከተሉ፣ መልካም ምርጫን ለማድረግ እና የሌሎችን ስልጣን ማክበር እንዲችሉ ለወደፊት የህይወት ክህሎቶች መሰረት ይጥልላቸዋል።
4. የወላጅ መመሪያ አውድ
#የልጆች ታዛዥነትን የሚያጎላ ቢሆንም ወላጆች ደግሞ ልጆቻቸውን እንዳያበሳጩና ተስፋ እንዳያስቆርጡ ይናገራል። ይህ የሚያሳየው ታዛዥነት በጭፍን መግዛት ሳይሆን በፍቅር፣ በትግስት፣ በመደጋገፍና አምላካዊ በሆነ ቤተሰብ ውስጥ እንዲሆኑ የሚያስተምረን ቃል ነው።
ለወጣቶች እና ለልጆች ተግባራዊ መመሪያዎች
#በቤት፡- የቤተሰብን ትዕዛዝና ህግን መከተል፣በንግግሮች ውስጥ ማዳመጥ፣ አክብሮትን ማሳየት እና የቤት ውስጥ ስራዎችን መርዳት።
#በትምህርት ቤት/ማህበረሰብ፡- አስተማሪዎችን ማክበርና መታዘዝ፣ የምንማረውን ትምህርት ላይ ትኩረት ማድረግ።
#እምነት፡- መታዘዝን እና በእለት ተዕለት ተግባራት እግዚአብሔርን የምንፈራበትና የምናከብርበት ይሁን።
ተባረኩ!!!

Address

Debre Zeyit

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Remnant Youth & kid's Holistic Nonprofit Corporation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Remnant Youth & kid's Holistic Nonprofit Corporation:

Share