The Lutheran Church of Ethiopia

The Lutheran Church of Ethiopia This is the Offical page of the Lutheran Church of Ethiopia

አዛኝ ፍቅር - ማክሰኞ፣ የካቲት 30/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ! የእግዚአብሔር ቃል - ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅ...
22/03/2021

አዛኝ ፍቅር - ማክሰኞ፣ የካቲት 30/2013 ዓ.ም.
እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል - ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅዱስ ማርቆስ እንደፃፈው፤ ምዕራፍ 1፤ ቁጥር 13፡-

በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ ከአራዊትም ጋር ነበረ፥ መላእክቱም አገለገሉት። (ማርቆስ 1፡13)

አዛኝ ፍቅር

“በእኔ ቦታ ሆነህ፤ አንድ ኪሎ ሜትር ካልተጓዝህ፤ እኔን አትረዳም፡፡”
እንደዚህ ያለ አሳብ ኖሮህ ወይም ኖሮሽ ያውቃልን? በየቀኑ፤ ችግሮች፣ መከራዎችና ፈተናዎች ያጋጥሙናል፡፡ በየቀኑ፤ ብዙ ሰዎች፤ የሚቀርቡንም ጭምር፤ ግማሹንም የምናልፍባቸውን ሁኔታዎች አያውቁም፡፡ አንዳንድ ጊዜ፤ እኛን እንዳይጠይቁን በጣም ሥራ በዝቶባቸው ወይም በጣም ለእራሳቸው በመጠንቀቅ ላይ ስላተኮሩ ሊሆን ይችላል፡፡ በሌሎች ጊዜያት፤ የምናስበውን፣ የሚሰማንንና የደረሰብንን በመደበቅ በውስጣችን ከመያዛችን የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡

ማንም ብትሆኑ ማንም ወይም ምንም ቢገጥማችሁ፤ እጅግ በጣም ቀርቦ የሚያውቃችሁ አንድ ሰው አላችሁ፡፡ ስሙም ኢየሱስ ነው፡፡ እናንተ ያላችሁበት እና የምታልፉበት የሕይወት እውነታዎች ያልነካው አይደለም፡፡ እናንተ የሚያስቸግሯችሁን ነገሮች መነሻዎች ሁሉ ያውቃል፡፡ በአመፅ የሚበጠብጧችሁን ነገሮች ሁሉ ያውቃል፡፡ እናንተን ባስቸገሯችሁ ቦታዎች ሆኖ ሁሉን አልፎበታል፡፡ እናንተ በምታልፉባቸው ድካሞችና ፈተናዎች ሁሉ አልፏል፡፡ ከኃጢአት በስተቀር፤ ሁሉም ነገር ደርሶበታል፡፡ እርሱ በሁሉም ነገሮች ስላለፈ፤ ሊጠብቃችሁና ሊከላከልላችሁ ይችላል፡፡

ሊጠብቃችሁና ሊከላከልላችሁ ተወለደ፡፡ የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስ፤ ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ የዲያቢሎስ ሥራ ኃጢአት ነው፤ የመጨረሻ ግቡም የእኛ መኮነን (ኩነኔ መግባት) ነው፡፡ ነገር ግን፤ ኢየሱስ ዲያቢሎስን ተዋግቶልን አሸነፈልን፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ሊያፀድቀን፤ በጭራሽ ኃጢአትን ባላደረገው ኢየሱስ ላይ፤ እግዚአብሔር የእኛን ኃጢአት በኢየሱስ ላይ አደረገ፡፡ ኢየሱስ የእኛን ሥቃይና ሰቆቃ ተቀበለ፤ ሞታችንንም ሞተ፡፡ ኃጢአታችንን፣ ሥቃያችንንና ሞታችንን ወስዶ፤ የእርሱን የፅድቅ ሕይወት ሰጠን፡፡ ኢየሱስ በመሥቀል ላይ እስኪሞትልን ድረስ ስለታዘዘ፤ በእርሱ የሚታመኑ ሁሉ፤ ፍፁም ቅዱሳን (ንፁሀን) ናቸው፡፡ እግዚአብሔር በደለኞች ናችሁ ብሎ አይፈርድብንም፡፡

ኢየሱስ የሚጠብቃችሁ፤ ወደፊት ሊመጣ ካለው ፍርድ ብቻ ሳይሆን፤ በየቀኑ ከሚደርስባችሁ ከማንኛውም ነገር፤ በኃይሉ ሊጠብቃችሁ ዝግጁም ነው፡፡ ይህ ማለት ግን፤ እንደገና ከቶ አትፈተኑም፣ መከራ አትቀበሉም ወይም አትፈተኑም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን፤ ፈተናዎች ሲመጡ፤ የኢየሱስ ጥበቃ፤ ከፀሎት የቀረበ ነው፡፡
ኢየሱስ ይረዳል (ጠበቅ ተደርጎ ሲነበብ)፡፡ ከዲያቢሎስ ሥራ ነፃ ሊያወጣህ፤ ነፃ ሊያወጣሽ ሞተና ከሞት ተነሣ፡፡ ለየትኛውም ችግርህ፤ በማንኛውም ጊዜ ወደ እርሱ ሂድ፡፡ ለየትኛውም ችግርሽ፤ በማንኛውም ጊዜ ወደ እርሱ ሂጂ፡፡ ከዲያቢሎስ ጋር ያለህን ውጊያ ለመቋቋም፤ ብርታት እንዲሰጥህ ጠይቀው፤ ኢየሱስ ብርታቱን ይሰጥሃል፡፡ ከዲያቢሎስ ጋር ያለሽን ውጊያ ለመቋቋም፤ ብርታት እንዲሰጥሽ ጠይቂው፤ ኢየሱስ ብርታቱን ይሰጥሻል፡፡ ዲያቢሎስም ይሸሻል፡፡

ፀሎት፡- ሰማያዊ አባት፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ ፈተና አታግባኝ፤ ከክፉው አድነኝ እንጂ፡፡ አሜን፡፡

ይህን የዕለት እንጀራ ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው፤ የድምፁን ፋይል እንዲሰሙ፤ መስማት የተሳናቸው፤ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!

ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0964-326486 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡

የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/dev-daily/ የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡
To access the English version, check out this link https://wels.net/dev-daily/

አዛኝ ፍቅር - ማክሰኞ፣ የካቲት 30/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ! የእግዚአብሔር ቃል - ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅዱስ ....

ሚጓጓ ፍቅር - ሰኞ፣ መጋቢት 06/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅዱስ ...
15/03/2021

ሚጓጓ ፍቅር - ሰኞ፣ መጋቢት 06/2013 ዓ.ም.
እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል - ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅዱስ ማርቆስ እንደፃፈው፤ ምዕራፍ 1፤ ቁጥር 12 እና 13፡-

ወዲያውም መንፈስ ወደ ምድረ በዳ አወጣው። በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ፤ ከአራዊትም ጋር ነበረ፥ መላእክቱም አገለገሉት። (ማርቆስ 1፡12-13)

የሚጓጓ ፍቅር

“ለአንድ ደቂቃ ብቻ ይታገሱኝ”
አንድ ሰው፤ ይህን ትህትና ያለበት ጥያቄ፤ ምን ያህል ጊዜ ጠይቋችሁ ያውቃል? “የምግብ ሰዓት ደርሷል” ብላችሁ ለቤተሰባችሁ አባል ስትነግሩ ወይም የአንድን ሰው ዕርዳታ ፈልጋችሁ ስትጠይቁ ወይም ለአንድ ሰው ጠቃሚ ዜና ልትነግሩ ስትሉ “ለአንድ ደቂቃ ብቻ ይታገሱኝ” ብለው በትህትና ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡

አንዳንድ ጊዜ፤ “ለአንድ ደቂቃ ብቻ ይታገሱኝ” የሚለው ተገቢና ጠቃሚ ምላሽ ነው፡፡ በዚያች ደቂቃ፤ ትተን መሄድ በማንችላቸው ሀሳቦች ወይም ንግግሮች ወይም ተግባሮች ተይዘን ይሆናል፡፡ በእንደዚያ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ካለን፤ የእኛን ዕርዳታ የሚፈልገውን ሰው፤ ለመርዳት ፈቃደኞች ነን፤ ነገር ግን በአካል ተገኝተን መርዳት አንችልም፡፡ በሌሎች ጊዜያት ደግሞ፤ “ለአንድ ደቂቃ ብቻ ይታሱኝ” የሚለው አባባል፤ እራስን በመውደድ የሚሰጥ ምላሽ ነው፡፡ ይህም ሌላ ሰውን መስማት ባለመፈለግ ወይም ስንፍና ተሰምቶን ወይም ትኩረታችንን በእራሳችን ሀሳቦች፣ ንግግሮችና ተግባሮች ላይ ብቻ አድርገን ሊሆን ይችላል፡፡

ይህ “ለአንድ ደቂቃ ብቻ ይታገሱኝ” ብለን በትህትና የምንናገርበት ምክንያታችን፤ በአንድ ጊዜ፤ እንዴት ያለ የውጤት ልዩነት እንደሚያመጣ፤ አስተውለን እናውቃለን ወይ? ሰዎች እንዲረዱን ወይም እንዲሰሙን በፈለግናቸው ጊዜ ሁሉ፤ ትኩረት ሰጥተው በመስማት፤ በአካል ተገኝተው በችግሮቻችን ቢረዱን፤ ድንቅ ነገር አይደል! ሁላችንም፤ በችግሮቻችን ሊሰማንና ሊረዳን፤ የሚጓጓ ፍቅር ያለው ሰው ቢኖር፤ ዕድሉን እንጠቀማለን፡፡ ሌሎች ሰዎችም፤ ይህን ሊሰማና ሊረዳ የሚጓጓ ፍቅር፤ ዕድል ቢጠቀሙ ደስ ይለናል፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅር፤ ሊሰማና ሊረዳ የሚጓጓ ፍቅር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ፤ በዮርዳኖስ ወንዝ ከተጠመቀ በኋላ፤ እግዚአብሔር፤ ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ ቀብቶ፤ እኛን የማዳን ሥራውን እንዲጀምር፤ ቶሎ ብሎ ወደ ምድረ በዳ ላከው፡፡ እኛን የማዳን ሥራው፤ ከዲያቢሎስ ጋር በመታገል ተጀምሮ፤ በመሥቀል ላይ በመሞት ተጠናቀቀ፡፡ ኢየሱስም ሥራውን ሁሉ፤ ፍፁም በትክክል የሠራ መሆኑን በማረጋገጥ፤ እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት አስነሣው፡፡ አንተም ኢየሱስን በማመን፤ ለኃጢአትህ ከሚገባህ ዕዳና ቅጣት፤ ወዲያውኑ ነፃ ሆንህ፡፡ አንቺም ኢየሱስን በማመን፤ ለኃጢአትሽ ከሚገባሽ ዕዳና ቅጣት ወዲያውኑ ነፃ ሆንሽ፡፡ ስለዚህ፤ ኢየሱስን እመን፤ ኢየሱስን በማመንህም ቀጥል፡፡ ስለዚህ ኢየሱስን እመኚ፤ ኢየሱስን በማመንሽም ቀጥዪ፡፡

እግዚአብሔርም በዚህ ዓይነት መንገድ ሊወድድህ ካላመነታ፤ አንተን ደስ እያለው በነፃ መውደዱን አያቆምም፡፡ እግዚአብሔርም በዚህ ዓይነት መንገድ ሊወድድሽ ካላመነታ፤ አንቺን ደስ እያለው በነፃ መውደዱን አያቆምም፡፡ እንዲረዳህ ስትጠራው፤ ለአንተ ትክክል የሆነውንና ከሁሉ የተሻለውን፤ በዚያችው ደቂቃ ሊያደርግልህ፤ እግዚአብሔር ወዳንተ ይፈጥናል፡፡ እንዲረዳሽ ስትጠሪው፤ ለአንቺ ትክክል የሆነውንና ከሁሉ የተሻለውን፤ በዚያችው ደቂቃ ሊያደርግልሽ፤ እግዚአብሔር ወዳንቺ ይፈጥናል፡፡

እግዚአብሔር፤ ወድዶ፣ ፈቅዶ፣ ጓጉቶ እና ፈጥኖ፤ አንተን የሚወድህ፤ እንደዚያ ነው፡፡ እግዚአብሔር፤ ወድዶ፣ ፈቅዶ፣ ጓጉቶ እና ፈጥኖ፤ አንቺን የሚወድሽ እንደዚያ ነው፡፡

ፀሎት፡- ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተሥፋዬና ደህንነቴ ነህ፡፡ አንተ አትጥለኝም፤ አትተወኝም፡፡ በፈተናና በመከራ ሁሉ፤ ልትረዳኝ ፈጥነህ ናልኝ! አሜን፡፡

ይህን የዕለት እንጀራ ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው፤ የድምፁን ፋይል እንዲሰሙ፤ መስማት የተሳናቸው፤ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!

ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0964-326486 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡

የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/dev-daily/ የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡

To access the English version, check out this link https://wels.net/dev-daily/

ሚጓጓ ፍቅር - ሰኞ፣ መጋቢት 06/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅዱስ ማር.....

ክርስቶስ የሚጫነን ከባድ ሸክም ያስወግዳል! - ዕሁድ፣ መጋቢት 05/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከሐዋርያው ...
15/03/2021

ክርስቶስ የሚጫነን ከባድ ሸክም ያስወግዳል! - ዕሁድ፣ መጋቢት 05/2013 ዓ.ም.

እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል - ከሐዋርያው የጳወሎስ መልዕክት፤ ወደ ሮሜ ሰዎች፤ ምዕራፍ 8፤ ቁጥር 10፡-

ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን፤ ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው። (ሮሜ 8፡10)

ክርስቶስ፤ የሚጫነን ከባድ ሸክም ያስወግዳል!

ከጊዜ ወደ ጊዜ፤ ከዚህ በፊት የማናውቃቸውን፤ ወጣ ያሉ ነገሮች፤ ሰዎች እያደረጉ መሆናቸውን እንሰማለን፡፡ በተለይም ሰዎች፤ በጣም አስቸኳይ የሆነ ዕርዳታ የሚያስፈልገው አደጋ ውስጥ ሲሆኑ፤ ለማንሳት የሚከብዱ ትልልቅ ሸክሞችን፤ ባልተጠበቀ ብርታት ሲያነሱ ይታያሉ:: በውስጣቸው ተደብቆ የተቀመጠውን ጥንካሬ እና በአዕምሯቸው የተከማቸውን ዕውቀትና ብልሃት፤ ድንገት ሳያውቁ፤ ይጠቀሙታል፡፡ ይህንን ሁሉ የሚያደርጉት በእራሳቸው ነው? ወይስ ይህ ተዓምራዊ የእግዚአብሔር ዕርዳታ ነው?

የዕብራውያን መልዕክት ፀሐፊ፤ 11ኛውን ምዕራፍ፤ ስለ ብሉይ ኪዳን ወንዶች የዕምነት ጀግኖች እና ሴቶች የዕምነት ጀግኖች፤ ለመፃፍ ተጠቅሞታል፡፡ እነዚህ የዕምነት ጀግኖች፤ ብርታታቸውን ያገኙት ከእግዚአብሔር ነበር፡፡ የሰው ብርታት ግን፤ በአንድ ወሳኝ የሕይወት አቅጣጫ ሊጠቅም አይችልም፤ ከኃጢአት ኃይልና ቅጣት፤ እራሳችንንም ሆነ ሌሎችን ማዳን አይችልም፡፡ ደህንነትን ለማግኘት፤ በእጆቻቸን የሥራ ውጤት፤ እግዚአብሔር የሚጠብቅብንን ያህል ለማሟላት ወይም መልካም ለማድረግ እራሳችንን ማበረታታት እና ማድረግ የሌለብንን ነገሮች ከማድረግ፤ እራሳችንን መቆጠብ አንችልም፡፡

ከዚህም በላይ፤ መዝሙረኛው፤ በመዝሙረ ዳዊት 49፡7 ላይ፤ “ወንድም ወንድሙን አያድንም፥ ሰውም አያድንም ቤዛውን ለእግዚአብሔር አይሰጥም” በማለት ይናገራል፡፡ ለቤዛነት የሚከፈለው ክፍያ እጅግ በጣም ትልቅ ክፍያ ነው፡፡ እኛ ልንከፍለው የማንችለው ስለሆነ፤ ኢየሱስ ለእኛ ከፈለልን፡፡ ኢየሱስ ነፍሱን ቤዛ አድርጎ በመስጠት፤ የዓለምን ሁሉ የኃጢአት ዕዳ በመክፈል፤ እኛን ከሞት ፍርሃት በማዳን፤ የተጫነንን ከባድ ሸክም አስወገደ፡፡ እንዴት ያለ ወደር የሌለው ተዓምር ነው! የተጫነንን ከባድ ሸክም ከእኛ ላይ በመውሰድ፤ ወደ እራሱ ሊያመጣን፤ ኢየሱስ በመሥቀል ላይ ተሠቀለ፡፡

ፀሎት፡- የሰማይና የምድር አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በድካሜ ፍፁም በሚያደርገኝን ኃይልህ፤ በአጠገቤ ሆነህ እንድታበረታኝ፤ በኢየሱስ ስም እፀልያለሁ፡፡ አሜን፡፡

ይህን የዕለት እንጀራ ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው፤ የድምፁን ፋይል እንዲሰሙ፤ መስማት የተሳናቸው፤ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!

ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0964-326486 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡

የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/dev-daily/ የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡

To access the English version, check out this link https://wels.net/dev-daily/

ክርስቶስ የሚጫነን ከባድ ሸክም ያስወግዳል! - ዕሁድ፣ መጋቢት 05/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከሐዋርያው የጳ.....

በዓብይ ፆም 1ኛ ዕሁድ - የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፤ ዋና ሐሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶች፡፡  ዕሁድ፣ መጋቢት 05/2013 ዓ.ም.ኢየሱስ ዲያቢሎስን ያሸንፋል!በዓብይ ፆም፤ ኢየሱስ ስለእኛ...
15/03/2021

በዓብይ ፆም 1ኛ ዕሁድ - የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፤ ዋና ሐሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶች፡፡ ዕሁድ፣ መጋቢት 05/2013 ዓ.ም.

ኢየሱስ ዲያቢሎስን ያሸንፋል!

በዓብይ ፆም፤ ኢየሱስ ስለእኛ ሊሠቃይና ሊሞት፤ ወደ መሥቀሉ ሲሄድ እናያለን፡፡ እግዚአብሔር ሲፈትሸን እና ዲያቢሎስም በየቀኑ ሲፈትነን፤ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ፊት ቅድስናችን መሆኑን፤ የዛሬው ትምህርቶች ያሳዩናል፡፡ ኢየሱስ ብርታታችንና ምሳሌያችንም ነው፡፡ ኢየሱስ፤ ሰው በእንጀራ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር የተሥፋ ቃሎች እንደሚኖር ተናገረ፡፡ እነዚህ የእግዚአብሔር የተሥፋ ቃሎቸ በቅዱስ ጥምቀት፣ በቅዱስ ቁርባንና እያንዳንዲቱ ቃል፤ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር ካለባት፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ወደ እኛ ይመጣሉ፡፡

በዚህ የዓብይ ፆም ወቅት፤ ለእኛ ለኃጢአተኞች የተደረገው ጥሪ፤ ከኃጢአታችን ንሥኃ እየገባን እና የእግዚአብሔርን ይቅርታ እየተቀበልን፤ መንፈሳዊ ጠላቶቻችን ከሆኑት፤ ከአሮጌው አዳማዊ ባህሪያችን፣ ከዓለምና ከዲያቢሎስ ጋር አምርረን እንድንታገል ነው!

የመጀመሪያው ትምህርት - ዘፍጥረት 22፡1-18

ጥያቄ፡- አብርሃም በእግዚአብሔርን ማመኑ፤ ይስሐቅን በፍጥት ከሞት አስነሳው (ዕብራውያን 11፡19ን ይመልከቱ)፡፡ አብርሃም፤ ይህንን ለባሪያዎቹ እንዴት አሳየ?

መልስ፡- የቁጥር 5ን መጨረሻ ይመልከቱ፡፡ አብርሃምና ይስሐቅ በሞሪያ ተራራ ጫፍ ላይ መሥዋዕት ካቀረቡ በኋላ፤ ሁለቱም ማለትም አብርሃምና ይስሐቅ ከተራራው ወርደው እንደሚመለሱ፤ አብርሃም ለባሪያዎቹ አረጋግጦላቸዋል፡፡

ጥያቄ፡- የጌታ መልዓክ ማንነው?

መልስ፡- የጌታ መልዓክ፤ እራሱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡ በቁጥር 12 እና 16 ላይ፤ የጌታ መልዓክ ስለ እራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ይናገራል፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡4 የጌታ መልዓክ፤ ክርስቶስ ነበር ይላል፡፡ እንደዚህ ማለት፤ ኢየሱስ የተፈጠረ መልዓክ ነው፤ ማለት አይደለም፡፡ በዕብራይስጥም፤ በግሪክም፤ መልዓክ ማለት በዋናነት “መልዕከተኛ” ማለት ነው፡፡ ስለዚህ፤ ኢየሱስ ሰው ሆኖ ከድንግል ማርያም ከመወለዱ በፊትም እንኳ፤ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ፤ ከአብ የተላከልን መልዕክተኛ ነበር፡፡

ጥያቄ፡- በኢየሱስ እንድንተማመን ሊያበረታታን፤ እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገራቸው፤ ሁለት የማይለወጡ ተሥፋዎች ምንድን ናቸው?

መልስ፡- እግዚአብሔር ለአብርሃም የተሥፋ ቃል ሰጠው ወይም ቃል ገባለት፤ በእራሱም ማለለት፡፡ እግዚአብሔር በእራሱ ስለማለለት፤ ከዚህ የበለጠ ምን አርግጠኛ ሊሆን ይችላል? (ዕብራውያን 6፡18ን ይመልከቱ)፡፡

ሁለተኛው ትምህርት - ሮሜ 8፡31-39

ጥያቄ፡- ስለ እግዚአብሔር ብለን፤ መታገሥ ያለብን ምንድን ነው? (8፡36ን ይመልከቱ)

መልስ፡- ስለዚህ ቀኑን ሙሉ እንገደላለን፡፡ በብዙ ሐዘንና ሕመም እንሠቃያለን፤ የሚለውን ጳውሎስ ከመዝሙረ ዳዊት 44፡22 እያጣቀሰ ይናገራል፡፡

ጥያቄ፡- በክርስቶስ አሁን እናሸንፋለን ወይስ ለዘላለም እናሸንፋለን፣ ወይስ ሁለቱንም ጊዜ እናሸንፋለን? (8፡37ን ይመልከቱ)፡፡

መልስ፡- በክርስቶስ አሁንም፤ ለዘላለምም እናሸንፋለን፡፡ ከመከራዎቻችን በኋላ ሳይሆን፤ በመከራዎቻችን ሁሉ፤ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን፡፡

ጥያቄ፡- የእግዚአብሔር ፍቅር የት ነው ያለው? (8፡39ን ይመልከቱ)፡፡

መልስ፡- የእግዚአብሔር ፍቅር ያለው፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ኢየሱስ ለዘላለም ሕያው ስለሆነ፤ ለእኛ ያለው የእግዚአብሔር ፍቅር ከቶ አያልቅም፡፡

የወንጌል ትምህርት - ማርቆስ 1፡12-15

ጥያቄ፡- በምድረ በዳ እንዲፈተን፤ ኢየሱስን የላከው ማን ነበር?

መልስ፡- በምድረ በዳ እንዲፈተን፤ ኢየሱስን የላከው፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነበር፡፡ በግሪክ ቋንቋ፤ ቃል በቃል ሲተረጎም ወደ ምድረ በዳ “አወጣው ወይም ወረወረው” የሚል ትርጉም አለው፡፡ ከዚህ የምንፅናናው፤ እግዚአብሔር ካልፈቀደ በስተቀር፤ ዲያቢሎስ እንኳን በጭራሽ ሊፈትነን አለመቻሉን ነው፡፡

ጥያቄ፡- የማርቆስ ወንጌልን፤ በመጀመሪያ ያነበቡትን ጥቂት የጥንት ክርስቲያኖች፤ በእስታዲየሞች ውስጥ፤ እንደ አንበሳ ያሉ ክፉ አራዊት ታግለዋቸዋል፤ ቦጫጭቀውም በልተዋቸዋል፡፡ የኢየሱስ በአራዊት መካከል ለ40 ቀናት መፈተን፤ ለእነዚህ የጥንት ክርስቲያኖች፤ የሚሰጣቸው መፅናናት ምንድን ነው?

መልስ፡- ኢየሱስ በምድረ በዳ ሲፈተን፤ ለ40 ቀናት ከአራዊት ጋር ነበር፡፡ የሮም ባለሥልጣኖች፤ በአንበሶች ያስበሏቸውን ሰማዕታት ልብ ባፀናበት፤ የእግዚአብሔር ቃል፤ ኢየሱስ፤ ሁሉንም ፈተናዎች አሸነፈ፡፡ እግዚአብሔር እንድንፈተን ቢፈቅድም እንኳ፤ እርሱ ሁልጊዜ፤ ከፈተናው ጋር መውጫውን ያዘጋጅልናል (1ኛ ቆሮንቶሰ 10፡13ን ይመልከቱ)፡፡

እነዚህን የተነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዋና ሃሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው የድምፁን ፋይል እንዲሰሙና መስማት የተሳናቸው ደግሞ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!

ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0964-326486 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡

የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/worship-help/
የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡

To access the English version, check out this link https://wels.net/worship-help/

በዓብይ ፆም 1ኛ ዕሁድ - የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፤ ዋና ሐሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶች፡፡ ዕሁድ፣ መጋቢት 05/2013 ዓ.ም.ኢየሱስ ዲያቢሎስን ያሸንፋል!በዓብይ ፆም፤ ኢየሱስ ስለእኛ ሊሠ.....

የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ መልክ የተለወጠበት ዕሁድ - የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፤ ዋና ሐሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶች፡፡  ዕሁድ፣ የካቲት 14/2013 ዓ.ም.ኢየሱስ፤ የወ...
23/02/2021

የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ መልክ የተለወጠበት ዕሁድ - የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፤ ዋና ሐሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶች፡፡ ዕሁድ፣ የካቲት 14/2013 ዓ.ም.

ኢየሱስ፤ የወደፊት ክብሩን ይገልጣል፡፡

ክርስቲያኖችን ሁሉ፤ በዚህች ዓለም ጊዜያዊ መከራዎች እንደሚገጥማቸው፤ በእግዚአብሔር ፀጋ ግን፤ በሰማይ ዘላለማዊ ክብር እንደሚጠብቃቸው ሊያመለክት፤ ኢየሱስ የመለኮታዊ ክብሩን ብልጭታ፤ ለደቀ መዛሙርቱ አንድ ጊዜ ብቻ አሳየ! ይህን የክብር ብልጭታ የተመለከቱት ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ነበሩ፡፡ ከፊት ለፊታቸው፤ አስቸጋሪ ጊዜያት አሉ፡፡ መሢሃቸው ሲሠቀል ያያሉ፤ ነገር ግን ያ መጨረሻው አይደለም፤ በእግዚአብሔር ፀጋ፤ በሰማይ ዘላለማዊ ክብርም እንዳለ ያያሉ፡፡

የመጀመሪያው ትምህርት - 2ኛ ነገሥት 2፡1-12

ጥያቄ፡- ኤልሳዕ የተናደደው ለምን ነበር?

መልስ፡- ኤልሳዕ የተናደደው፤ ጌታው ወይም አለቃው፤ ከእርሱ ሊወሰድ እንደሆነ ስላወቀ ነበር፡፡

ጥያቄ፡- ኤልሳዕ ኤልያስን የጠየቀው ምንድን ነበር?

መልስ፡- ኤልሳዕ ኤልያስን የጠየቀው፤ የኤልያስ መንፈስ በእጥፍ እንዲሰጠው ነበር፡፡ ኤልያስ ሲወሰድ፤ ብርታት እንደሚያስፈልገው፤ ኤልሳዕ አውቋል፡፡ በዚያ ዘመን፤ በኩር የሆነ አይሁዳዊ ልጅ፤ የሀብት ዕጥፍ ድረሻ ይወርስ ስለነበር፤ ኤልሳዕ እንደ ኤልያስ ወራሽ የጠየቀ ይመስላል፡፡

ጥያቄ፡- ኤልያስ ወደ ሰማይ የተወሰደው እንዴት ነበር?

መልስ፡- የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎቸ፤ ኤልያስንና ኤልሳዕን ለዩአቸው፤ ከዚያም ኤልያስ በዓውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ፡፡

ሁለተኛው ትምህርት - 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡12-4፡6

ጥያቄ፡- ጳውሎስ በዚህ ትምህርት የሚጠቅሰው፤ የብሉይ ኪዳን ክስተት የትኛው ነው?

መልስ፡- ጳውሎስ በዚህ ትምህርት የሚጠቅሰው የብሉይ ኪዳን ክስተት፤ ሙሴ ከሲና ተራራ ሲመለስ፤ የእግዚአብሔርን ክብር በከፊል አይቶ ስለነበር፤ ፊቱ ማብራቱን ነበር፡፡ ሕዝቡ ሙሴን ለማየት በፊቶ መቆም ስላልቻሉ፤ ፊቱን በመሸፈኛ ሸፍኖ ነበር፡፡ ኢየሱስን ላለመቀበል ልባቸውን ያደነደኑ አይሁድ፤ ልባቸው በመሸፈኛ የተሸፈነ መሆኑን፤ ጳውሎስ ይናገራል፡፡

ጥያቄ፡- እውነት ወይስ ሐሰት፡- አሮጌው ኪዳን - ሕጉ፤ ከአዲሱ ኪዳን - ከወንጌል የበለጠ የከበረ ነው፡፡

መልስ፡- ሐሰት፡፡ ሕጉ፤ ኃጢአትን፣ በደልንና ሞትን በኃጢአተኞች ሰዎች ላይ ያመጣል፡፡ ሕጉ፤ እውነት ሰለሆነና እግዚአብሔር ቅዱስና ፍፁም መሆኑን ስለሚያሳየን፤ የከበረ ነው፡፡ ነገር ግን፤ ወንጌል፤ ከኃጢአት ነፃ የሚያወጣ በመሆኑና ሕይወትንና ደህንነትን ስለሚያስገኝ፤ ወንጌል የበለጠ የከበረ መሆኑን፤ ጳውሎስ ይናገራል፡፡ (2ኛ ቆሮ. 3፡10፣17፣18 ይመልከቱ)፡፡

ጥያቄ፡- እንደ ወንጌል አገልጋዮች፤ ተልዕኳችንን የምንቀጥለው፤ እንዴት እየሆነን ነው?

መልስ፡- እንደ ወንጌል አገልጋዮች፤ ተልዕኳችንን የምንቀጥለው፤ የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለን፤ በተንኮል ሳንመላለስ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት ሳንንቀላቅል፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን በማመስገን ነው፡፡ እውነቱን ገልጠን በመናገር፤ በተገለጠው እውነት በኩል፤ እግዚአብሔር ሕይወትንና ደህንነትን እንደሚሠራ በመተማመን ነው፡፡ ክብር የሚመጣው በወንጌል እውነት አማካይነት ብቻ ስለሆነ፤ እውነቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ፤ ምንም ዓይነት ማግባባት ወይም መሸቃቀጥ አያስፈልግም፡፡

ጥያቄ፡- ሁሉም ሰው፤ በኢየሱስ ደም የማይተማመነው ለምንድን ነው?

መልስ፡- ሁሉም ሰው፤ በኢየሱስ ደም የማይተማመነው፤ ዲያቢሎስ፤ “የዚህ ዓለም አምላክ” የማያምኑትን ሰዎች አሳብ ስለ አሳወረ ነው። ከዚህም የተነሳ፤ የወንጌሉን ብርሃን ማየት አይችሉም፡፡

ጥያቄ፡- በአጭሩ፤ መልኩ በተለወጠበት ተራራ ላይ፤ በአስደናቂ ክብር የተገለጠው፤ ኢየሱስ የሚባለው ሰው ማን ነው?

መልስ፡- መልኩ በተለወጠበት ተራራ ላይ፤ በአስደናቂ ክብር የተገለጠው፤ ኢየሱስ የሚባለው ሰው፤ የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ ነው፡፡ ኢየሱስን ስናይ፤ እግዚአብሔር አብ ምን እንደሚመስል በትክክል እናያለን፡፡

ጥያቄ፡- በሌሎች ሰዎች እንደሆነው ሳይሆን፤ እናንተ በኢየሱስ ብትታመኑ፤ ያመናችሁት ለምንድን ነው? (4፡6ን ተመልከቱ)፡፡

መልስ፡- ከመጀመሪያ “ብርሃን ይሁን” በማለት፤ ብርሃንን የመፍጠር ተዓምር የሠራው እግዚአብሔር፤ በእናንተም ሕይወት ውስጥ ተመሳሳይ ተዓምራትን አድርጓል፡፡ ጨለማ ብቻ በነበረበት ሕይወታችሁ፤ ብርሃንን አበራ፡፡ በክርስቶስ ፊት፤ የእግዚአብሔርን ክብር እንድታውቁ፤ ብርሃንን ሰጣችሁ፡፡

የወንጌል ትምህርት - ማርቆስ 9፡2-9

ጥያቄ፡- ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ፤ ወደ ረጂሙ ተራራ ከወጡ በኋላ፤ እነማንን አገኙ?

መልስ፡- ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ፤ ወደ ረጂሙ ተራራ ከወጡ በኋላ፤ ሙሴንና ኤልያስን አገኙ፡፡ በአይሁዳውያን ዘንድ፤ ሙሴና ኤልያስ፤ ከሁሉም የብሉይ ኪዳን ነቢያት የሚበልጡ ተደርገው ይቆጠሩ ነበር፡፡

ጥያቄ፡- ጴጥሮስ በቁጥር 5 ላይ፤ የተናገረውን ሃሳብ ለምን አቀረበ?

መልስ፡- የእግዚአብሔርን ክብር፤ እዚያው ለእራሳቸው ለማቆየት ስላሰበ፤ ጴጥሮስ፤ በዚያ ተራራ ላይ ለኢየሱስ፣ ለሙሴና ለኤልያስ ዳስ ለመሥራት ፈለገ፡፡ ወንጌላዊው ማርቆስ፤ ጴጥሮስ ይህን የተናገረው፤ የሚናገረውን ባለማወቅ፤ በሞኝነት ወይም በጅልነት መሆኑን ፍንጭ ይሰጠናል፡፡ እርሱን ለሚከተሉ አማኞች፤ ዘላለማዊ ክብር ሊያስገኝላቸው፤ በመሥቀል ላይ ተሠቃይቶ ለመሞት፤ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ አስፈልጎታል፡፡ (ቁጥር 9ን ይመልከቱ)፡፡

እነዚህን የተነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዋና ሃሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው የድምፁን ፋይል እንዲሰሙና መስማት የተሳናቸው ደግሞ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!

ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0941-057792 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡

የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/worship-help/
የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡
To access the English version, check out this link https://wels.net/worship-help/

የጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ መልክ የተለወጠበት ዕሁድ - የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፤ ዋና ሐሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶች፡፡ ዕሁድ፣ የካቲት 14/2013 ዓ.ም.ኢየሱስ፤ የወደ...

ስለ ወንጌል እውነት - ቅዳሜ፣ የካቲት 13/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የጳወሎስ ...
23/02/2021

ስለ ወንጌል እውነት - ቅዳሜ፣ የካቲት 13/2013 ዓ.ም.

እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የጳወሎስ መልዕክት፤ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች፤ ምዕራፍ 9፤ ቁጥር 23፡-

በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ፤ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ። (1ኛ ቆሮንቶስ 9፡23)

ስለ ወንጌል እውነት

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ እኔን የእራሱ ከማድረጉ በፊት፤ ገና በአሥራዎቹ ዕድሜ፤ በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለሁ፤ “እግዚአብሔር የለም” የሚል ክህደት በሰፈነበትና፤ በኢትዮጵያ የኃይማኖት ነፃነት፤ ባልነበረባቸው ዓመታት፤ አንድ የምወደው የትምህርት ቤት ጓደኛዬና የተወደዱ ቤተሰቦቹ፤ ያሳዩኝን መልካምነት አልረሳውም፡፡ በተለይም ወደ ቤታቸው ስሄድ፤ ከሚያቀርቡልኝ ጥሩ ምግብ የበለጠ፤ እኔን ትንሹን ድሃ ልጅ፤ የሚቀበሉበት ፈገግታና ሰላምታ፤ እንዲሁም ልባቸውን በእውነት ከፍተው ስለሚቀበሉኝ፤ ወደ እነርሱ ቤት መሄድ፤ እጅግ በጣም ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ይህንን መልካምነታቸውን፤ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የማገለግል፤ ጎልማሳ ቄስ ሆኜም አስታውሳለሁ፡፡

ከጓደኛዬ ጋር በየቅዳሜው፤ ለቤተሰቦቻችን የማገዶ እንጨት ለማምጣት፤ ወደ ጫካ ስንሄድም፤ እንጨቱን ስንሰበስብም፤ ወደ ቤት ስንመለም፤ ከብዙ የልጅነት ጨዋታችን ይልቅ፤ ጥሩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ይዘት ያላቸው፤ መንፈሳዊ መዝሙሮችን ይዘምርልኝ ነበር፡፡ “መንግሥተ ሰማይ (2 ጊዜ) … ከሞት ወዲያ ለኛ መጠለያ (2 ጊዜ) … ካምላክ ጋራ ኑሮ እንደገና (2 ጊዜ)” የሚለውንና “እዩት ኢየሱስን … መሥቀሉም ማማሩ … ለተመራመረው … ብዙ ነው ምስጢሩ” የሚለውን፤ እንዲሁም “ከጣሪያዬ በታች ጓዳዬ … መቼ ነው የማከብርህ ጌታዬ … መቼ ነው (3 ጊዜ) … በኑሮዬ ክብርህ የሚታየው” የሚለውን መዝሙሮች ይዘምርልኝ ነበር፡፡

አንድ ቀን፤ ይህንን ጓደኛዬን፤ “እኔ የእናንተ ቤተሰብ አባል ወይም ዘመድ አይደለሁም፤ ነገር ግን፤ አንተና ቤተሰብህ፤ ለእኔ ትንሹ ድሃ ልጅ፤ ብዙ መልካም ነገሮችን፤ የምታደርጉልኝ ለምንድን ነው?” ብዬ ጠየቅሁት፡፡ እርሱም፤ “ስለ ወንጌል ብለን ነው፤ ስለ ወንጌል ከዚህ በላይም ልናደርግ ይገናባል” ብሎ መለሰልኝ፡፡

ጓደኛዬ የሰጠኝ መልስ፤ በዚያን ጊዜ ባይገባኝም፤ ከልብ የሆነው፤ ግብዝነት የሌለበት ፍቅራቸውና እንክብካቤያቸው ግን፤ በልቤ ውስጥ ተተክሎ ቀረ፡፡ እስከ ዛሬ፤ ጓደኛዬ፣ ቤተሰቡና እኔ፤ የምንኖረው የተለያየ ሐገር ቢሆንም፤ ልቤ ግን እስካሁን ከእነርሱ ጋር አለ፡፡ ስኬታቸውን ስሰማ፤ እደሰታለሁ፡፡ ሐዘናቸውን ስሰማ፤ አዝናለሁ፡፡ እጅግ በጣም ደስ የሚለው ግን፤ ጓደኛዬ ለጥያቄዬ መልስ ከሰጠኝ፤ ከአራት ዓመታት በኋላ፤ ይህ እነርሱ፤ መልካምነትን እንዲያሳዩ ያደረጋቸው ወንጌል፤ እኔንም አዳነኝ፤ ለወጠኝም፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፤ በድካምም ይሁን በብርታት፤ የዚህ ወንጌል አገልጋይ ሆንሁ፡፡ ይህ የነገርኳችሁ ታሪክ፤ እውነተኛ ታሪክ እንጂ ልብወለድ አይደለም፡፡

አባቶቼና እናቶቼ፤ ወንድሞቼና እህቶቼ አትሳሳቱ፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ምትካችን ሆኖ፤ የሠራልንን ሥራ የሚነግረን፤ የምሥራች ቃል የሆነው ወንጌል፤ የሰው ልብ፤ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምን የሚያደርግ፤ ኃይል ያለው መሆኑን፤ መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ ይናገራል፡፡ ይሁን እንጂ፤ ብዙ ክርስቲያኖች፤ ብዙ ጊዜ፤ ይህን የምሥራች ቃል፤ እንደ ልብወለድ በመቁጠር፤ በወንጌል ፊት እንቅፋትን አስቀምጠዋል፡፡ በፍፁም ግልፅነትና ቅንነት፤ ክርስቲያኖች፤ ስለዚህ በደል ንሥኃ በመግባት፤ የኃጢአታቸውን ይቅርታ ከእግዚአብሔር መቀበል አለባቸው::

እኛ ወንጌልን እንደ ወንጌልነቱ የመያዝና የማዳረስ ጉጉት ባይኖረንም፤ ለዘላለም ለሚጠፉት ሰዎች፤ ልባችን ባያዝንም፤ ሸክም ተሰምቶን ባንፀልይላቸውም፤ የወንጌል እውነት ከሁሉም ነገር የበለጠ እውነትና፤ ውብ የሆነ የምሥራች ቃል ነው፡፡ ለነገሩ፤ ብዙ ስህተቶቻችን ሕይወታችንን ሲያደቁ፤ በንሥኃ አልቅሰን፤ የእግዚአብሔርን ምህረት ለማግኘት ስንጮህ፤ ሕያው የሆነው አዳኝ፤ በደሙ ከኃጢአታችን አጥቦ በማንፃት፤ የእራሱ እንዳደረገንና፤ ከአጠገባችን እንደማይለይ፤ ተሥፋ ይሰጠናል፡፡

በዓለማችን ላይ፤ ስለ እግዚአብሔር ቃል፤ ለዘብተኛ አቋም ያላቸው፤ ብዙ ክርስቲያኖች እና በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት፤ ያላመኑ ሰዎች፤ ወንጌልን እንደ ልብወለድ ቢቆጥሩም፤ አንተ፣ አንቺና እኔ፤ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በማመን፤ ስለሚገኘው የኃጢአት ይቅርታ፤ ስለ ወንጌል እውነት፤ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡

ፀሎት፡- ውድ አዳኜ፤ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ በተገቢው መንገድ፤ ወንጌል ስላላዳረስሁባቸው ጊዜያት ሁሉ፤ እናዘዛለሁ፤ ንሥኃም እገባለሁ፡፡ ይቅር በለኝ፡፡ ስለ ወንጌል እውነት፤ የተቻለኝን ሁሉ እንዳደርግ፤ በወንጌልህ ቀስቅሰኝ። አሜን፡፡

ይህን የዕለት እንጀራ ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው፤ የድምፁን ፋይል እንዲሰሙ፤ መስማት የተሳናቸው፤ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!

ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0941-057792 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡

የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/dev-daily/ የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡

To access the English version, check out this link https://wels.net/dev-daily/

ስለ ወንጌል እውነት - ቅዳሜ፣ የካቲት 13/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የጳወሎስ መል...

መደበኛ ድግግሞሽ - ዓርብ፣ የካቲት 12/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ...
23/02/2021

መደበኛ ድግግሞሽ - ዓርብ፣ የካቲት 12/2013 ዓ.ም.

እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል - ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅዱስ ማርቆስ እንደፃፈው፤ ምዕራፍ 1፤ ቁጥር 35፡-

ማለዳም ተነሥቶ፤ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ፤ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ፤ በዚያ ጸለየ። (ማርቆስ 1፡35)

መደበኛ ድግግሞሽ

አንተ፣ አንቺና እኔ፤ በየዕለቱ የፀሎት ሕይወታችን ላይ፤ እንዴት በድንገት ጥቃት እንደሚደረስብን አስቡ፡፡ ይህ ድንገተኛ ጥቃት የሚጀምረው፤ ገና በማለዳ ከእንቅልፋችን እንደተነሳን ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም፤ ሬዲዮ በመኝታ ክፍል፤ ቴሌቪዢኑ ደግሞ በሳሎን ተከፍቶ ድምፅ ይሰማል፤ ምስልም ይታያል፡፡ ያንን እየሰማንና እያየን፤ የተለያዩ በየነ መረቦችን፤ ወይም ሶሻል ሜዲያዎችን፤ ቼክ የምናደርግበትና፤ የተላኩ የፅሑፍ መልዕክቶችን ወይም ቴክስቶችን፤ በማንበብ ምላሽ የምንፅፍበት ጊዜ ይደርሳል፡፡ ከዚያም በመኪናችን ወይም በሕዝብ ትራንስፖርት፤ ወደ ሥራ ሄደን፤ ስንሠራ እንውላለን፡፡ ከሥራ ስንወጣ፤ ለምግብ የሚያስፈልጉ ነገሮችን፤ ከሱፐር ማርኬትና ከግሮሰሪ የምንገዛበት ሰዓት ይደርሳል፡፡ ቤታችን ገብተን፤ ለእራት በተቀመጥንበት፤ ጠዋትና ቀን ያመለጡንን ዜናዎች እንሰማለን፡፡ ከዚያም ከቤተሰብ አባላት ጋር ትንሽ እየተጫወትን፤ የቴሌቪዥኑን ቻናል በመቀያየር፤ እንቅልፋችን እስኪመጣ እናያለን፡፡ በመጨረሻም ሲደክመን፤ ወደ መኝታ ክፍላችን በመሄድ እንተኛለን፡፡ በማግስቱ ከእንቅልፋችን ስንነሳ፤ ቀኑን በእነዚሁ የምንደጋግማቸው ተግባራት እንጀምራለን፡፡ እነዚህን የተለመዱ ተግባራት፤ ለቀናት፣ ለሳምንታት፣ ለወራትና ለዓመታት፤ ደጋግመን ስናከናውናቸው፤ ክርስትና ሕይወታችን ምን እንደሚሆን መገመት አያስቸግርም፡፡

በዛሬው የማርቆስ ወንጌል ንባባችን፤ “ማለዳም ተነሥቶ፤ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ፤ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ፤ በዚያ ጸለየ።” እያለ፤ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ይነግረናል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ እያንዳንዲቱን ቀን እንዴት እንደሚጀምር ስንመለከት፤ በእኛና በእርሱ መካከል ያለው ልዩነት፤ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ከእንቅልፉ ሲነቃ፤ የመጀመሪያ የሚያደርገው ነገር፤ ምንም የሚረብሽና ጣልቃ የሚገባ ድምፅ ወደሌለበት፤ ለብቻው ወደሚሆንበት ቦታ መሄድ ነበር፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወደ እንደዚህ ዓይነት ቦታ የሚሄደው፤ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሊፀልይና የልቡን ለሰማያዊ አባቱ፤ ሊያሳይ ነበር፡፡

እስቲ ለእራሳችን ግልፅና ቅን ሆነን፤ ለጥቂት ጊዜ አስበን፤ እውነቱን ለእራሳችን እንናገር፡፡ አንተ፣ አንቺና እኔ፤ አብዛኛውን ጊዜ፤ በየቀኑ የሚረብሹንን ብዙ ዓይነት ድምፆች እየፈቀድላቸው፤ እጅግ በጣም የተወደዱ የፀሎት ጊዜያትን ማባከናችንን፤ ለእግዚአብሔር ለአምላካችንና ለእርስ በርሳችን፤ መናዘዝ አለብን፡፡ እነዚህ ጊዜያት፤ ከመልካሙና ከቸሩ አምላካችን፤ ከእግዚአብሔር ጋር፤ የምንነጋገርባቸው እጅግ በጣም የተወደዱ ጊዜያት ነበሩ፡፡ ይህ ዓይነት አካሄድ፤ ለእፍረታችንና ለውርደታችን ነው፡፡ በዚህ ዓይነት አካሄዳችን፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ቢንቀን፤ የሚገባን (ጠበቅ ተደርጎ ሲነበብ) ነው፡፡
ይሁን እንጂ፤ እግዚአብሔር ሊያደርግብን ያሰበው እንደዚያ አይደለም፡፡ እኛን በማሳፈር፣ በማዋረድና በመናቅ ፋንታ፤ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ላከልን፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ምትካችን ሆኖ፤ አንድም ቀን ፀሎትን ሳያቋርጥ፤ ከሁሉም ተግባሮቹ፤ ለፀሎት ቅድሚያ በመስጠት፤ ፍፁም የሆነ የፀሎት ሕይወት ኖረ:: ለእያንዳንዲቱ ያባከንናት የፀሎት ጊዜም፤ በመሥቀል ላይ ተሠቅሎ፤ ደሙን በማፍሰስ፤ ሞተ፡፡ አሁን፤ እርሱን በማመን፤ ሁሉም ኃጢአታችን ይቅር ተብሏል፤ ሁሉም ነገራችን ታድሷል፤ ሁሉ ደህና ነው፡፡

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሠራልንና የእርሱ ሥራ ያስገኘልን ትሩፋቶች፤ በአዲስ ዕይታ፤ ነገና ከነገ በኋላ በሚኖሩት ቀኖች፤ ከሁሉም የተለመዱ ተደጋጋሚ ተግባሮቻችን በፊት፤ ለፀሎት ቅድሚያ መስጠትን፤ ጀምረን ለመቀጠል፤ ብርታትን ይሰጡናል፡፡

ፀሎት፡- ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ የኃጢአት ይቅርታን አግኝቻለሁ፡፡ አንተ በፀሎት የምትናገረኝን እንድሰማና እኔም ለአንተ በፀሎት እንድናገር፤ የሰጠኸኝን ጊዜያት፤ በታማኝነት መጠበቅ እንድችል፤ አንቀሳቅሰኝ፡፡ አሜን፡፡

ይህን የዕለት እንጀራ ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው፤ የድምፁን ፋይል እንዲሰሙ፤ መስማት የተሳናቸው፤ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!
ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0941-057792 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡

የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/dev-daily/ የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡

To access the English version, check out this link https://wels.net/dev-daily/

መደበኛ ድግግሞሽ - ዓርብ፣ የካቲት 12/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ቅዱ...

ለዛው የተሟጠጠ፤ የማያስደስት አባባል፤  ሐሙስ፣ የካቲት 11/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐ...
23/02/2021

ለዛው የተሟጠጠ፤ የማያስደስት አባባል፤ ሐሙስ፣ የካቲት 11/2013 ዓ.ም.

እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የጳወሎስ መልዕክት፤ ወደ ሮሜ ሰዎች፤ ምዕራፍ 8፤ ቁጥር 28፡-

እግዚአብሔርንም ለሚወዱት፤ እንደ አሳቡም ለተጠሩት፤ ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28

ለዛው የተሟጠጠ፤ የማያስደስት አባባል

በብዙ ሰዎች ዘንድ፤ ለረጂም ዘመናት የታወቁ፤ ነገር ግን ሰዎች የሰለቿቸውና የማይደሰቱባቸው፤ የተወሰኑ የድሮ አባባሎች አሉ፡፡ ሰዎች፤ እነዚህን አባባሎች መስማት፣ መናገርና ማንበብ የሚሰለቹትና የማይደሰቱት፤ ምናልባትም ከእነርሱ የተሻሉ ሌሎች ብዙ አባባሎች፤ በአማራጭነት ስላሉ ይሆናል፡፡ ወይም አዳዲስ አባባሎች በተገኙ ቁጥር፤ በተለመዱ የድሮ አባባሎች፤ ብዙ ሰዎች አይደሰቱ ይሆናል፡፡ ወይም የድሮ ሰዎች አባባሎች፤ የዘመናዊ ሰዎችን አስተሳሰብ፣ ንግግርና ተግባር የሚኮንኑ ከሆኑ፤ ዘመናዊ ሰዎች፤ አባባሎቹን በቀጣይነት ለመጠቀም፤ ስለማይፈልጉ ሊሆን ይችላል፡፡

ለምሳሌ፡- “ከቀዳዳ ይሻላል ጨምዳዳ” የሚለው አባባል ቢነገር፤ የተቀደደ ሱሪ ወይም ቁምጣ ወይም ቦጌ መልበስ የሚፈልጉ የዘመናችን ሰዎች፤ በዚህ የድሮ አባባል አይደሰቱም፡፡ በተጨማሪም፤ “የምናከናውናቸው ተግባሮች፤ ከምንናገራቸው ቃላት በላይ ጮኸው ይናገራሉ” የሚለውን የድሮ አባባል፤ ተግባር የሌለው ንግግር የሚያበዙ ሰዎች፤ በዚህ የድሮ አባባል አይደሰቱም፡፡ በእንደዚህ ዓይነት የተለመዱ የድሮ አባባሎች፤ የማይደሰቱ ብዙ ሰዎች፤ “እነዚህ አባባሎች ዘመን ያለፈባቸው፤ ያረጁና ደስ የማይሉ አባባሎች ናቸው” ብለው በመናገር ይጀምሩና፤ አባባሎቹን የሚጠቀሙትን ሰዎች፤ ከዘመኑ ጋር የማይሄዱ ኋላ ቀሮች አድርገው ይንቃሉ፤ የሚናገሩትን ይቃወማሉ፤ ሊጣሏቸውም ይፈልጋሉ፡፡

ይህ ጉዳይ፤ በዓለማዊ ንግግር ብቻ ሳይሆን፤ በመንፈሳዊ ንግግርም አካሄዱ እንደዚሁ እየሆነ ነው፡፡ የዘመናችን ሰዎች፤ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ የሚፈልጉትን፤ የሚደግፉላቸው አባባሎችን በትኩረት፤ ደስ እያላቸው ይሰማሉ፡፡ ነገር ግን፤ ዛሬ እኛ የምንፈልጋቸውና የምንደሰትባቸው አባባሎች፤ እግዚአብሔር እንድናስብ፣ እንድንናገርና እንድንሠራ ከሚፈልጋቸው የተቃረኑ ከሆኑ፤ የጤናማ መንፈሳዊ ሕይወት ምልክቶች አይደሉም፡፡

በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ያነበብነው፤ “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት፤ እንደ አሳቡም ለተጠሩት፤ ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” የሚሉትን ቃላት፤ ብዙ ክርስቲያኖች፤ ለብዙ ዓመታት ተናግረዋል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ክርስቲያኖች፤ “እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ፤ ለበጎ ያደርጋል።” እያሉ ይህን ቃል፤ በሚገባ (ላላ ተደርጎ ሲነበብ) መልኩ ይጠቅሳሉ፡፡ ነገር ግን፤ በተለምዶ እነዚህን ቃላት የሚሰሙ ነፍሳት፤ በተለያዩ መንገዶች ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ እነዚህ ነፍሳት፤ በተለያዩ ዓይነት አስቸጋሪ ሁኔታዎች፤ ለምሳሌ፡- በፅኑ ሕመም፣ በየቤተሰብ መታወክ፣ በፋይናንስ ማሽቆልቆል፣ በሥራ ማጣት፣ በተፈጥሮ አደጋ እና በሚወዷቸው ሰዎች ሞት ውስጥ ሆነው፤ “እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ፤ ለበጎ ያደርጋል።” ብንላቸው፤ እነዚህን ሰዎች፤ ከማፅናናት ይልቅ የባሰ እናሳዝናቸዋለን፤ ከማበረታታት ይልቅ የባሰ እናደክማቸዋለን፤ ከመርዳት ይልቅ የባሰ እንጎዳቸዋለን፡፡

ዛሬ በሰላምና በስኬት እየኖርን፤ ያለን የመሰለን እኛ፤ በሚቀጥለው ጊዜ፤ “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት፤ እንደ አሳቡም ለተጠሩት፤ ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” የሚሉትን የተለመዱ ቃላት፤ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ለመስማት፤ ተራው የእኛ ነው፡፡ “ይህ ዘመን ያለፈበት፣ ያረጀ አባባል ነው” ብለን፤ እነዚህን ቃላት ለመስማት ያለመፈለግ ፈተና፤ ብርቱ ነው፡፡ ይህ ፈተና ሲመጣባችሁ፤ ቆም ብላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፡፡ ይህ “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት፤ እንደ አሳቡም ለተጠሩት፤ ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” የሚለው የእግዚአብሔር ቃል፤ ልባችሁንና አዕምሯችሁን ዘልቆ ይግባ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ቃል፤ ኃጢአታችሁን ሁሉ አጥቦ ባስወገደው፤ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደም የታተመ፤ እስትንፋሰ-እግዚአብሔር ያለበት፤ ሕያው የተሥፋ ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል፤ ለዛው የተሟጠጠ ባዶ ቃል አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል፤ ብዙ ጥቅም ላይ ከመዋሉ የተነሳ፤ የማያስደስት ባዶ ቃል አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል፤ እውነት ነው፡፡

ፀሎት፡- ሰማያዊ አባቴ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲገጥሙኝ፤ ሁሉንም ነገሮች፤ ለመልካም እንደምታደርግልኝ፤ የሰጠኸኝን ተሥፋ፤ ለውስጤ ደጋግመህ ተናገረኝ፡፡ አሜን፡፡

ይህን የዕለት እንጀራ ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው፤ የድምፁን ፋይል እንዲሰሙ፤ መስማት የተሳናቸው፤ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!

ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0941-057792 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡
የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/dev-daily/ የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡

To access the English version, check out this link https://wels.net/dev-daily/

ለዛው የተሟጠጠ፤ የማያስደስት አባባል፤ ሐሙስ፣ የካቲት 11/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋ...

ጠቃሚ የተለካ ጉዞ - ረቡዕ፣ 10/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የጳወሎስ መልዕክት፤...
23/02/2021

ጠቃሚ የተለካ ጉዞ - ረቡዕ፣ 10/2013 ዓ.ም.

እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የጳወሎስ መልዕክት፤ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች፤ ምዕራፍ 9፤ ቁጥር 23፡-

በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ፤ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ። (1ኛ ቆሮንቶስ 9፡23)

ጠቃሚ የተለካ ጉዞ

አንዳንድ ሰዎች፤ በልጅነት ዕድሜ በነበሩበት ጊዜ፤ በሰውነታቸው ላይ ባለማወቅ ወይም በሞኝነት፤ ከፈፀሟቸው አደገኛ ድርጊቶች ወይም ከደረሱባቸው አደጋዎች የተነሳ፤ ካደጉና ካረጁ በኋላም፤ በሰውነታቸው ላይ ጠባሳዎቹ ወይም ሰንበሮቹ ይታያሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የሰውነታቸው ቅርፅ የተዛባባቸው ወይም ማየት የተሳናቸው ወይም መስማት የተሳናቸው ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ካሉባቸው ውስንነቶች የተነሳ፤ እንደ ሌሎች ሰዎች የፈለጉትን መሆንና ማከናወን አይችሉም፤ ይታመማሉ፤ እያዘኑም ይኖራሉ፡፡

በሕይወቱ መጨረሻ አካባቢ፤ የሐዋርያው ጳውሎስን ሰውነት ብንመለከተው፤ ልክ እንደነዚህ ሰዎች፤ ጠባሳዎች፣ ስብራቶች፣ የሰውነት ቅርፅ መዛባቶችና ብዙ ውስንነቶች ልናይበት እንችላለን፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ጳውሎስን በወንጌል ከለወጠበት ጊዜ ጀምሮ፤ ብዙ ሰዎች በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው እንዲድኑ ብሎ ወንጌልን ሲያዳርስ፤ በተደጋጋሚ ብዙ ግርፋቶችና በበትር መመታት ደርሶበታል፡፡ ከዚህም የተነሳ፤ ለምሳሌ፡- ብዙ ጊዜ በተመቱ እጆቹ ድንኳን ሲሰፋና ሌሎች ተግባራትን ሲያከናውን፤ ሁሌ እያቃሰተ፤ በጣም ሲብስበትም እያለቀሰ እንደሚኖር ልንገምት እንችላለን፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ሁሉ ሥቃይ የተቀበለለት ጉዳይ፤ ቢሠቃይለት የሚገባው ጉዳይ ነበርን? ለብዙ ዓመታትስ እነዚህን ጉዳቶች መቀበሉ ተገቢ ነበርን? መጠላቱ እና ልቡን ያደከሙ ብዙ መከራዎቹ፣ ጠባሳዎቹ፣ ያለ ርህራሄ መደብደቡና መገረፉ፤ ስብራቶቹ እና ውስንነቶቹ ሁሉ፤ ሐዋርያው ጳውሎስ ሥቃይ ከተቀበለለት ጉዳይ ጋር ሲነፃፀሩ፤ እነዚህ ጉዳቶች ሁሉ ምንም አይደሉምን? እነዚህ ሁሉ ጉዳቶች፤ ለሐዋርያው ጳውሎስ ጠቃሚ የተለካ ጉዞ ተገቢ ነበሩን?

በአዲስ ኪዳን፤ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ፤ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደነዚህ ያሉ ጥያቄዎችን እንዲመልስ፤ መንፈስ ቅዱስ ኃይልን እንደሰጠው ይናገራል፡፡ ለምሳሌ፤- በዛሬው የ1ኛ ቆሮንቶስ 9፡23 ንባባችን ላይ፤ “በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ፤ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ” እያለ ሐዋርያው ጳውሎስ እራሱ መልስ ይሰጠናል፡፡

በተጓዘው ጠቃሚ የተለካ ጉዞና በዚህ ጉዞ ባጋጠሙት ጭንቀቶችና ዕንባዎች ሁሉ፤ ሐዋርያው ጳውሎስ፤ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል፤ ለእርሱ ያደረገለትን ከቶ አልረሳም ነበር፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፤ ከመለወጡ በፊት፤ የእግዚአብሔርን እውነት፤ አጥብቆ የሚቃወም ሕይወት ውስጥ ቢቆይም፤ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል፤ የእግዚአብሔር ልጅ መጥቶ እንዳዳነው፤ ከቶ አልረሳም ነበር፡፡ በሐዋርያው ጳውሎስ፤ ትዕቢት የሞላበት፤ የኃጢአተኝነት ሕይወት ፈንታ፤ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ፍፁም እና ትህትና ያለበት የአገልግሎት ሕይወት ኖረ፡፡ ከዚያም የሐዋርያው ጳውሎስን ኃጢአቶች ሁሉ በመሥቀል ላይ ተሸክመ፤ ሁሉንም ኃጢአቶቹን አጥቦ አስወገደለት፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን ከቶ አልረሳም ነበር፡፡

በዚህ ሕያው በሆነው አዳኙ በማመን፤ ሐዋርያው ጳውሎስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገለትን ፈፅሞ አልረሳም ነበር፡፡ ይህንን ወንጌል ለሌሎች ሰዎች ለማካፈል ሕይወቱን ሰጥቶ ኖረ፡፡ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚነገረው የምሥራች ቃል፤ ይህን ያህል ውድ ነው፡፡ ልክ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ፤ ወንጌል በሚያስገኛቸው በረከቶች ሁሉ እንድትካፈሉ፤ በየትኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ፤ ስለ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚነገረውን የምሥራች ቃል፤ የበለጠ ልትማሩ ትችላላችሁ፡፡

ፀሎት፡- ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ አንተ ያደረግህልኝ እና የምታደርግልኝን ሁሉ፤ የበለጠ እንድማር፤ ዕድሎችን ስጠኝ፡፡ አሜን፡፡

ይህን የዕለት እንጀራ ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው፤ የድምፁን ፋይል እንዲሰሙ፤ መስማት የተሳናቸው፤ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!

ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0941-057792 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡
የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/dev-daily/
የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡

To access the English version, check out this link https://wels.net/dev-daily/

ጠቃሚ የተለካ ጉዞ - ረቡዕ፣ 10/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የጳወሎስ መልዕክት፤ ወ...

ባሪያ - ማክሰኞ፣ 09/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋርያው ጳወሎስ መልዕክት፤ ወደ ቆሮንቶ...
23/02/2021

ባሪያ - ማክሰኞ፣ 09/2013 ዓ.ም.

እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!

የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋርያው ጳወሎስ መልዕክት፤ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች፤ ምዕራፍ 9፤ ቁጥር 19፡-

ከሰው ሁሉ አርነት የወጣሁ ስሆን፤ የሚበልጡትን እንድጠቅም፤ እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስገዛለሁ። (1ኛ ቆሮንቶስ 9፡19)

ባሪያ

በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ፤ ሰው በተለያዩ መንገዶች ባሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ በጦርነት ተማርኮ የታሠረ ሰው ባሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ በውሃ ላይ በጀልባ ወይም በመርከብ፤ ድንበር አቋርጦ ሲጓዝ፤ ተይዞ የተሸጠ ሰው፤ ባሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ ከፍተኛ የኑሮ ችግር ያለበት ቤተሰብ፤ በልጅነት ዕድሜ ካሉት ልጆች፤ አንዱን ሲሸጡት፤ ባሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ የቤተሰብ መሪ ወይም አባት፤ የተበደረውን ብድር መመለስ አቅቶት፤ እራሱን ወይም ከቤተሰቡ አባላት አንዱን አሳልፎ ሲሰጥ፤ ባሪያ ሊሆን ይችላል፡፡

ባሪያ፤ በየትኛውም ቦታ እየሠራ፤ እራሱን ልያገኝ ይችላል፡፡ በቤት ውስጥ፣ ማዕድን በሚወጣበት ቦታ፤ በፋብሪካ ውስጥ ወይም በእርሻ ቦታ ሲሠራ እራሱን ሊያገኝ ይችላል፡፡ በባሪያ ሕይወት በጣም የሚከብደው ግን፤ ያ ባሪያ፤ ለገዛው ሰው፤ እንደ ንብረት ወይም እንደ ዕቃ መቆጠሩ ነው፡፡ ባሪያውን የገዛው ሰው፤ በፈለገው ጊዜ፤ ለሌላ ሰው ሊያከራየው ወይም ሊሸጠው ይችላል፡፡ ከዚህም በላይ እጅግ በጣም የሚከብደው፤ ባሪያውን የገዛው ሰው፤ በማንኛውም ምክንያትና በማንኛውም ጊዜ፤ ባሪያውን ሊገድለው መብት አለው፡፡ ባሪያ የሆነ ሰው፤ ባሪያ ስለሆነ፤ ሕይወቱ የእርሱ አይደለም፤ ምንም ዓይነት መብትና ነፃነትም የለውም፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ፤ በቆሮንቶስ ከተማ ላሉ ክርስቲያን ወገኖች፤ ዛሬ የተነበበውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በፃፈላቸው ጊዜ፤ በአዕምሮው የነበረው የባርያ ሥዕል፤ ከላይ የተጠቀሰው ነበር፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፤ ነፃ ሰው ቢሆንም፤ በዙሪያው ላሉት ሰዎች፤ የኖረበት መንገድ ግን፤ እራሱን ባሪያ ለማድረግ በመፍቀድ ነበር፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ፤ ይህን እንዲያደርግ ያነሳሳው ምንድን ነበር? ለእራስ ማንነት ዝቅ ያለ ግምት መስጠት፤ በሚያመጣው የበታችነት ስሜት፤ እየተሰቃየ ነበርን? ላለፉት ውድቀቶቹ፤ ማካካሻ ለማድረግ እየሞከረ ነበርን? ለሌሎች ሰዎች ከፍተኛ ክብር እየሰጠ፤ እራሱን የበታችና ትንሽ ጥቅም ያለው ሰው፤ እድርጎ የመቁጠር ባህሪይ ነበረውን? ጳውሎስንና እርሱ የፃፋቸውን መልዕክቶች በጥንቃቄ ስናነብ፤ እነዚህ የዘረዘርናቸው ምክንያቶች ባሪያ እንዳላደረጉት እናውቃለን፡፡ ከእነዚህ ምክንያቶች ይልቅ፤ ጳውሎስ እራሱ “ከሰው ሁሉ አርነት የወጣሁ ስሆን፤ የሚበልጡትን እንድጠቅም ፤እንደ ባሪያ ራሴን ለሁሉ አስገዛለሁ።” እያለ ምክንያቱን ይነግረናል፡፡ ለሐዋርያው ጳውሎስ፤ ይህ እራስን ዝቅ ዝቅ ማድረግና እራስን ለሌሎች ማስገዛት፤ ከኢየሱስ የተማረውና የተገበረው ባህሪይ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወደ ምድር መጣ፡፡ በእኛ ፈንታ እራሱን ባሪያ አደረገ፣ በእኛ ቦታ ቅዱስ ሕይወትም ኖረ፡፡ ምትካችን ሆኖ ሥቃይን እና ሞትን ለመታገሥ እራሱን ሰጠ፡፡ ይህን ሁሉ ያደረገው፤ እኛን ሊያገለግል እና በኃጢአት የተጨማለቀውን ሕይወታችንን፤ አጥቦ ሊያነፃ ነው፡፡
በሐዋርያው ጳውሎስ አዕምሮ፤ ለእራሱ ኖሮ ሳይሆን፤ ለእነርሱ ኖሮላቸው፤ ለሌሎች ብዙ ሰዎች፤ የምሥራቹን ዜና ሊያመጣላቸው ዕድሉን ቢያገኝ፤ ጳውሎስ ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይል፤ ተግቶ ያደርገዋል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፤ ያዳነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ፈለግ በመከተል፤ እየኖረና እያገለገለ ነበር፡፡ በኢየሱስ ኃጢአታችን ይቅር የተባለልን፤ አንተ፣ አንቺና እኔ ይህንኑ ዓይነት ኑሮ እንድንኖር እና ይህንኑ ዓይነት አገልግሎት እንድናገለግል ይጠበቅብናል፡፡ እንግዲሀ እኛም፤ ይህን ኑሮ አንኑር፤ ይህን አገልግሎትም እናገልግል!

ፀሎት፡- ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ አጥበህ ልታነፃኝ፤ ሕይወትህን ሰጥተሃል፡፡ እኔም ሕይወቴን፤ ለሌሎች ሰዎች በመስጠት፤ እያገለገልሁ እንድኖር፤ ያንኑ መንፈስ ስጠኝ፡፡ አሜን፡፡

ይህን የዕለት እንጀራ ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው፤ የድምፁን ፋይል እንዲሰሙ፤ መስማት የተሳናቸው፤ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!
ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0941-057792 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡

የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/dev-daily/ የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡

To access the English version, check out this link https://wels.net/dev-daily/

ባሪያ - ማክሰኞ፣ 09/2013 ዓ.ም.እንኳን ወደ የኢትዮጵያ ሉተራዊት ቤተ ክርስቲያን፤ የዕለት እንጀራ መጣችሁ!የእግዚአብሔር ቃል - ከመጀመሪያይቱ የሐዋርያው ጳወሎስ መልዕክት፤ ወደ ቆሮንቶስ ...

ከጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ክብር መገለጥ በኋላ፤ 5ኛ ዕሁድ - የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፤ ዋና ሐሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶች፡፡  ዕሁድ፣ የካቲት 07/2013 ዓ.ም.ኢየሱ...
23/02/2021

ከጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ክብር መገለጥ በኋላ፤ 5ኛ ዕሁድ - የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፤ ዋና ሐሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶች፡፡ ዕሁድ፣ የካቲት 07/2013 ዓ.ም.

ኢየሱስ፤ ደከመኝ፤ ሰለቸኝ ሳይል፤ በታላቅ ፍላጎት እያገለገለ ተገለጠ!

ዛሬ በምናነባቸው ሶስት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች፤ ሰዎች ተጎድተዋል፡፡ የቅፍርናሆም ሰዎችን በመፈወስ፤ ኢየሱስ እንደ አምላክ ተገለጠ፡፡ ዛሬ ኢየሱስ ሕመሞቻችንን እና ችግሮቻችንን ሁሉ፤ ከእኛ የማይወስድልን ለምንድነው? ምክንያቱን አናውቅም፤ ነገር ግን ኢየሱስ በሕመምና በዲያቢሎስ ላይ ኃይል እንዳለውና፤ እግዚአብሔር ክፉውን ለመልካም እንደሚጠቀም፤ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይነግሩናል፡፡ ኢየሱስ፤ ተዓምራት አድራጊ ሰው ሆኖ፤ በቋሚነት በቅፍርናሆም ከመቆየት ይልቅ፤ በገሊላ ዙሪያ ሁሉ እየተጓዘ አስተማረ፤ ሰበከም፡፡ ኢየሱስ ይህን ያደረገው፤ ምናልባትም፤ የዝናው መግነን ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ፤ ስለእኛ ለመሞት ወደ መሥቀሉ ከመሄድ አንዳይከለክለው፤ እየፀለየ፤ ማስተማርና መስበክ ላይ እንጂ ተዓምራት ማድረግ ላይ ለማተኮር ስላልፈለገ ነው፡፡

የመጀመሪያው ትምህርት፡- ኢዮብ 7፡1-7

ጥያቄ፡- ኢዮብ ስለ ሕይወቱ የተሰማው ስሜት ምንድን ነበር?

መልስ፡- ኢዮብ በሕይወቱ ዕጣ ተሥፋ ቆርጦ ነበር፡፡ ደክሞና ከባድ ጭንቀት ተጭኖት ስለነበር፤ ኢዮብ ከዚያ በኋላ በጭራሽ ደስተኛ እንደማይሆን አስቦ ነበር፡፡ ኢዮብ ስለ አዳኙ እግዚአብሔር፤ የምሥራች ቃል የመናገር ፍላጎት ጠፍቶበት ነበር፡፡

ጥያቄ፡- ኢዮብን እንዲህ የተሰማው ለምንድን ነበር?

መልስ፡- ኢዮብ ልጆቹ ሁሉ በድንገተኛ አደጋ ሞተውበት እንዲሁም ንብረቱ እና ክብሩ ሁሉ ጠፍቶበት ነበር፡፡ ከዚያም ጤናውን አጥቶ ነበር፡፡ ጓደኞቹ በኢየብ ላይ ይህ ሁሉ የደረሰበት፤ “በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አድርጎ ነው” ብለዋል፡፡ ኢዮብ ግን እነርሱንና ወቀሳቸውን አልተቀበለም፡፡ እግዚአብሔር ሩቅ እና ተገቢ ያልሆነ ነገር እያደረገ ይመስላል፡፡ የደረሰበት ሥቃይም ፤ ኢዮብን ወደ ተስፋ መቁረጥ መራው፡፡

ጥያቄ፡- ኢዮብ በእግዚአብሔር ላይ ያለው ዕምነት እንዳልጠፋበት እንዴት ታውቃለችሁ?

መልስ፡- ኢዮብ በሕይወቱ ላይ ከደረሱበት ጥፋቶች የተነሳ፤ ተሥፋ ቢቆርጥና ቢደክምም እንዲሁም ከባድ ጭንቀት ቢጫነውም፤ “ሕይወቴ እስትንፋስ እንደ ሆነ አስብ” እያለ፤ በነበረበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ፤ እግዚአብሔርን በፀሎት ይጠይቃል፤ ወደ እግዚአብሔር ይፀልያል (7፡7)፡፡

ሁለተኛው ትምህርት፡- 1ኛ ቆሮንቶስ 9፡16-23

ጥያቄ፡- ጳውሎስ ወንጌል እንዲሰብክ፤ ምን ያህል ይከፈለው ነበር?

መልስ፡- ጳውሎስ የወንጌል አገልጋይ ሆኖ በመካከላቸው ሲሠራ፤ ሊከፈለው የሚገባ መብቱን ሳይጠቀም፤ ለቆሮንቶስ ሰዎች ወንጌልን በነፃ ሰበከላቸው (9፡15)፡፡ በተለምዶ ይህ ቅር የሚያሰኝ ሲሆን፤ ጳውሎስ ግን በዚህ ሁኔታ ይመካል፡፡ ጳውሎስ ለመስበክ የተነሳሳው በወንጌል ነበር እንጂ በገንዘብ አልነበረም፡፡

ጥያቄ፡- ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ. 9፡22 ላይ፤ “በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን አድን ዘንድ፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ” ሲል ምን ማለቱ ነው?

መልስ፡- ጳውሎስ በእነዚህ ቃላት የሚያመለክተው፤ ለሰሚዎቹ ያለውን የአገልጋይነት አመለካከት ነው፡፡ እንደ ክርስቲያን ጳውሎስ፤ ሕሊናን በሚመለከቱ ጉዳዮች፤ በክርስቶስ ሙሉ ነፃነት ያለው ቢሆንም፤ በ1ኛ ቆሮ. 10፡33 ላይ እንደተናገረው፤ “ሁሉንም ሰው፤ በሁሉም መንገድ ለማስደሰት” ክርስቲያናዊ ነፃነቱን አልተጠቀመም ነበር፡፡ ይህንንም ያደረገው፤ ወንጌልን ለመስበክ ዕድል ያገኝ ዘንድ ነበር፡፡

ጥያቄ፡- ጳውሎስ ወንጌልን እንዲሰብክ ያነሳሳው ምንድነው?

መልስ፡- ጳውሎስ ወንጌልን እንዲሰብክ ያነሳሳው፤ የኃጢአት ይቅርታን በሚያስገኘው ወንጌል በኩል፤ ኢየሱስ የሰጠው ነፃነት ነው፡፡ ይህን የኃጢአት ይቅርታ የሚያስገኝ ወንጌል፤ ለሌሎች ይሰብካል እንጂ ዝም ማለት አይችልም፡፡ ጳውሎስ ደከመኝ፤ ሰለቸኝ የማይባልበት፤ በታላቅ ፍላጎት የሚሰብከው የወንጌል ሥራ ነበረው፡፡

የሁለተኛው ትምህርት ደጋፊ፡- ሮሜ 8፡28-30

ጥያቄ፡- በዚህ ምዕራፍ፤ ቀደም ባሉት ክፍሎች፤ ለምሳሌ በቁጥር 22 ላይ፤ “ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና” እያለ ጳውሎስ ይናገራል፡፡ ከዚህ ሌላ የምናውቀው ምንድን ነው?

መልስ፡- “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።” (8፡28)

ጥያቄ፡- የእግዚአብሔር ዓላማ፤ እኛን አሁን የግድ ደሥተኞች ማድረግ አይደለም፡፡ ታዲያ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዓላማ ምንድን ነው?

መልስ፡- አሁንም፤ ለዘላለምም፤ የእግዚአብሔር ዓላማ፤ የልጁን የኢየሱስ ክርስቶስን መልክ እንድንመስል ነው፡፡ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት፤ አማኞች እንድንሆን የመረጠንም ለዚሁ ዓላማ ነው፡፡ (ምን ዓይነት አስደናቂ ፀጋ ነው!)

ጥያቄ፡- ጳውሎስ፤ ምን ዓይነት የማይጠስ ሰንሠለት እንድንስል ይፈልጋል?

መልስ፡- ጳውሎስ እንድንስል የፈለገው የማይበጠስ ሰንሠለት፤ የእግዚአብሔር ፀጋ ሰንሠለት ሲሆን ይህም፤ ልጆቹ እንዲሆኑ ከዘላለም ዘመናት በፊት እግዚአብሔር ሰዎችን ወሰናቸው፡፡ በዚህ ዓለም ሲኖሩም፤ በኢየሱስ እንዲያምኑ ጠራቸው፡፡ የጠራቸውንም በእርሱ ፍርድ ቤት፤ ስለ ኢየሱስ ብሎ፤ “ጥፋት የላባችሁም” አላቸው፣ አፀደቃቸው፣ አከበራቸውም፡፡ እንደ ፀሐይ ልናበራ፤ ገና በአዲሲቱ ምድር ላይ አይደለንም፡፡ ነገር ግን፤ ከእግዚአብሔር ፀጋ የተነሳ፤ ልክ በአዲሲቱ ምድር ላይ የሆነንን ያህል መልካም ሆኖልናል፡፡ (ምን ዓይነት አስገራሚ ፀጋ ነው!)

የወንጌል ትምህርት፡- ማርቆስ 1፡29-39

ጥያቄ፡- ከረጅም የሙሉ ቀን አገልግሎቱ በኋላ፤ ኢየሱስ ምን ተሰምቶት ነበር?

መልስ፡- ኢየሱስ ከረጅም፤ የሙሉ ቀን አገልግሎቱ በኋላ፤ ደክሞት ስለነበር፤ ለብቻው የሚሆንበትን ጊዜና ቦታ ፈልጎ ነበር፡፡ ሕዝቡ ደግሞ የሚሰማቸውን ይፈልጉ ነበር፡፡ ነገር ግን እጅግ በጣም የሚያሳዝነው፤ ኢየሱስን ሲከተልና ሲሰማ የነበረው ሕዝብ፤ የበለጠ የተደሰተው፤ የሥጋ ፈውስ፣ ብዙዎችን መመገብና አጋንንትን የማውጣት ተዓምራት በመሳሰሉት፤ ምድራዊ፣ ጊዜያዊና ቁሳዊ በረከቶች እንጂ፤ ኢየሱስ ሊሰጠን በመጣው፤ የኃጢአት ይቅርታና የዘላለም ሕይወት በመሳሰሉት፤ ሰማያዊ፣ ዘላለማዊና መንፈሳዊ በረከቶች አልነበረም፡፡

ጥያቄ፡- ኢየሱስ፤ ሕዝቡ የበለጠ ለፈለጉትና ለተደሰቱበት ነገር፤ ምላሽ የሰጠው እንዴት ነበር?

መልስ፡- አብ ለኢየሱስ የሰጠው ዋና ተልዕኮ፤ ወንጌልን መስበክና ለነፍሳት የዘላለም ፈውስን ማምጣት መሆኑን፤ ለሕዝቡ በሚገባ ነግሯቸው፤ እነርሱ የነበሩበትን ቦታ በመተው፤ ወንጌልን ሊሰብክ ወደ ሌሎች መንደሮች ሄደ፡፡ ኢየሱስ ደከመኝ፤ ስለቸኝ ሳይል፤ ወንጌል የመስበክ ታላቅ ፍጎት ነበረው፤ ሰበከም፡፡

እነዚህን የተነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዋና ሃሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ስለተካፈሉ እናመሰግናለን! ለቤተሰብዎና ለጓደኞችዎ በማካፈል ወይም share በማድረግ፤ እንዲሁም ማየት የተሳናቸው የድምፁን ፋይል እንዲሰሙና መስማት የተሳናቸው ደግሞ ፅሁፉን እንዲያነቡ በማመቻቸት፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲታነፅ ይርዱ!
ለተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል አገልግሎት፡- 0930-107598 ወይም 0941-057792 ላይ ይደውሉ፡፡ [email protected] ላይ ይፃፉልን፡፡
ቢሾፍቱ (ደብረ ዘይት)፣ ኢያሱ ሜዳ፣ የባቡር ሐዲድ ተሻግሮ፣
ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ኦሮምያ ክልል፣ ኢትዮጵያ፡፡
የእንግሊዘኛውን ቅጂ ለማግኘት https://wels.net/worship-help/
የሚለውን ሊንክ ይጎብኙ፡፡
To access the English version, check out this link https://wels.net/worship-help/

ከጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ክብር መገለጥ በኋላ፤ 5ኛ ዕሁድ - የሚነበቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፤ ዋና ሐሳብ፣ ጥያቄዎችና መልሶች፡፡ ዕሁድ፣ የካቲት 07/2013 ዓ.ም.ኢየሱስ፤ ...

Address

Eyasu Meda
Debre Zeyit

Opening Hours

Monday 06:00 - 18:00
Tuesday 09:00 - 18:00
Wednesday 06:00 - 18:00
Thursday 06:00 - 18:00
Friday 06:00 - 18:00
Saturday 06:00 - 18:00
Sunday 06:00 - 18:00

Telephone

+251930107598

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Lutheran Church of Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to The Lutheran Church of Ethiopia:

Share