ንሴብሆ ለእግዚአብሔር ቲዩብ

ንሴብሆ ለእግዚአብሔር ቲዩብ Subscribe to our channel:- www.youtube.com/ ንሴብሆ ለእግዚአብሔር ዩቲዩብ
Te

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በቢሾፍቱና አካባቢው ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የቃጅማ ደብረ  ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅ...
01/06/2025

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በቢሾፍቱና አካባቢው ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የቃጅማ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ክብረ በዓል ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ : ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በታላቅ መንፈሣዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሮ ዋለ።

መርሓ-ግብሩን የመሩት ክቡር የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ በቅደም ተከተል በተቀመጠው ሰዓት እና ደቂቃ መሠረት በሊቃውንት እና በሰንበት ትምህርት ዘማርያን ያሬዳዊ ዜማ እና ከተለያዩ ማኅበራት በተወጣጡ ወጣት ዘማርያን በኅብረት በአንድነት ዜማ
ምሥጋና ቀርቦአል።

በብፁዕ አባታችን መልካም ፈቃድ የህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የሆኑህ አቶ መለሰ ግርማ ከመሠረት ጀምሮ እስከ ፍጻሜው የሒሳብ እና የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅረበዋል ። በተያያዘም የሕንፃ ቤተክርስቲያኑ ግንባታ ከተመሠረተ ጀምሮ የቃለ ዐዋዲውን ሕግ እና ሥርዓት ጠበቀው ለአሠሩ የወረዳው የአብያተ ክርስቲያናቱ ሰበካ ጉባኤ እና ህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ለካህናት ለአረጋውያን አባቶች እና እናቶች እንዲሁም በእውቀታቸው በገንዘባቸውና በጉልበታቸው ለረዱና ለተባበሩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በብፁዓን አባቶች የሽልማትና የእወቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶአል።

በብፁዕ አባታችንን አቡነ ጎርጎርዮስ ግብዣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ "
ወይእዜኒ ኀረይክዎ ወቀደስክዎ ለዝንቱ ቤት ከመ ይሰመይ ስምየ እስከ ለዓለም ወህየኒ ይከውና አዕይንትየ ወልብየኒ በኵሉ መዋዕል። (ትርጉም ) አሁንም ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዓይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ። 2ኛ ዜና 7፥16 በሚል መነሻ ቃል የራቀውን አቅርበው የቀረበውን አጉልተው ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ጎርጎዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ታሪክ ወደ ኃላ በማንሳት መሠረት ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ የነበሩ ለሕንፃ ግንባታው ሥራ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በመሥራት እራሳቸውን በማደራጀት ይህንን ህንጻ ቤተ መቅደስ ሠርታችሁ ለዚህ ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ለዚህ ታሪካዊ እና የበረከት ቀን አደረሳችሁ በማለት በቃለ ምዕዳንና ጸሎት በዓሉ። ተጠናቋል።

በበዓሉ ላይም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ክቡር መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ : የሀገረ ስብከቱ እና የወረዳው ቤተ ክህነት የክፍል ኃላፊዎች :የካቴድራል ገዳማት አድባራት አስተዳዳሪዎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ ካህናት ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተገኝተዋል።

 ⛪️⛪️በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት በበደሌ ከተማ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን የተዘጋጀው ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ የጠዋት መርሃ ግብር ተከናውኗል። በዚህ መርሃ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቡ...
01/06/2025

⛪️⛪️
በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት በበደሌ ከተማ ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን የተዘጋጀው ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ የጠዋት መርሃ ግብር ተከናውኗል። በዚህ መርሃ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሥርዓተ ቅዳሴውን የመሩ ሲሆን፣ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ብሉይ ሣህለ ማርያምም ተገኝተዋል። የወንጌል፣ የዝማሬ እና የገቢ ማሰባሰቢያ የተካኸደ ሲሆን በመጨረሻም የአዲሱ ሕንፃ ቤተክርስቲያን መሠረተ ድንጋይ በብፁዕ አባታችን ተቀምጧል።

የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ አቢነ ታዋድሮስ አንብሮተ ዕድ 8 አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች !ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)የግብፅ ኮፕ...
01/06/2025

የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ አቢነ ታዋድሮስ አንብሮተ ዕድ 8 አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመች !

ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
የግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በዜሬው ዕለት ከበዓተ ግብፅ በዓል ጎን ለጎን በብፁዕ ወቅዱስ አቢነ ታዋድሮስ አንብሮተ ዕድ 8 አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን በመቀባት በዓለ ሢመታቸውን አክብራለች። አዳዲሶቹ ኤጲስ ቆጶሳት በተለያዩ አህጉረ ስብከት እና በታላላቅ ገዳማት ኃላፊነት የተሾሙ ናቸው።በዛሬው ዕለት በፓትርያርክ ታዋድሮስ አንብሮተ ዕድ የተሾሙ መነኮሳት

1. አባ ጎብሬያል ኤል-ማህራቂ ብፁዕ አቡነ ፓክሆሚየስ ተብለው በአሌክሳንድሪያ ተራራ አልቃሊሊ፣ ቤሄራ ጠቅላይ ግዛት የቅዱስ መቃርዮስ ገዳም ጳጳስ
2. አባ አንድራዌስ ኤል-ሶሪያኒ - ብፁዕ አቡነ ካራስ ተብለው የማትሮው ሀገረ ስብከት እና የአምስቱ ምዕራባዊ ከተሞች ጳጳስ
3. አባ ቴዎፋን አቫ ሚና - ብፁዕ አቡነ ሚና ተብለው የቦርግ ኤል አረብ ሀገረ ስብከት ጳጳስ
4. አባ ዳንኤል ኤል-ጊዮርጊስ - ብፁዕ አቡነ ቦክተር ተብለው የዲርምዋስ እና ዴልጋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ
5. አባ ዲስኮረስ ኤል-አንቱኒ - ብፁዕ አቡነ ዲስኮረስ ተብለው የደቡባዊ ጀርመን እና በክሮፍልባች የቅዱስ አንቶኒ ገዳም አቡነ ጳጳስ
6. አባ ኦሎጊዩስ ኤል-ባራሞሲ - ብፁዕ አቡነ ኦሎጊዩስ ተብለው በአይን ሻምስ፣ ማታሪያ እና ሄልሚት ኤል-ዘይቱን ላሉት አብያተ ክርስቲያናት ጳጳስ
7. አባ ያኮቦስ አንባ ቢሾይ - ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ተብለው በሃዳቅ ኤል-ቁባ፣ ኤል-ዋይሊ፣ አባሲያ እና ማንሺየት ኤል-ሳድር ላሉት አብያተ ክርስቲያናት ጳጳስ።
8. አባ ኢግናቲየስ ኤል-ሶሪያኒ - ብፁዕ አቡነ ኢግናቲየስ ተብለው የቄና ሀገረ ስብከት ጳጳስ እና የሜትሮፖሊታን ሻሮቢም ረዳት ጳጳስ ሲሆኑ

በበዓለ ሢመቱ ላይ 102 ሊቃነ ጳጳሳት እና ጳጳሳት፣ የካይሮ እና የአሌክሳንድሪያ የሃይማኖት አባቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።
ቅዱስነታቸው ባስተላለፉቶ መልእክት ላይ፡- “ይህ ቀን 8 መነኮሳት አባቶች ጳጳስ ሆነው የተሾሙበት አስደሳች ቀን ነው፤ በቅርቡ ብፁዓን ጳጳሳትን ሜትሮፖሊታን ጳክሆሚየስን፣ ኤጲስ ቆጶስ አግቢዮስን እና ኤጲስ ቆጶስ ሚሳኤልን አጥተናል። ሹመቱም ይህንኑ ክፍተትና ሌሎች ክፍተቶችን ለመሙላት የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ቃጅማ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ክደብረ ዘይት ቢሾፍቱ
01/06/2025

ቃጅማ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ደብረ ዘይት ቢሾፍቱ

አባቶቻችን በዘመናቸው የተናገሩት፣የተመኙት የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ከ37 ዓመታት የፈተናና የትዕግስት ቦኃላ ዛሬ ግንቦት 24/201...
01/06/2025

አባቶቻችን በዘመናቸው የተናገሩት፣የተመኙት የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ከ37 ዓመታት የፈተናና የትዕግስት ቦኃላ ዛሬ ግንቦት 24/2017 ዓ/ም ተፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

በወላይታ ሀገረ ስብከት የርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ መንክራት  አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም  ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ፣ ብፁዓን አበ...
31/05/2025

በወላይታ ሀገረ ስብከት የርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ መንክራት አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ሥርዓተ ቡራኬው ተፈጽሟል።

15/05/2023

እንደ መላእክቱ በምስጋና 🙏🙏

ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዛሬዉ እለት መግለጫ ሰጥተዋል።ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው በሀገራ...
07/12/2022

ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በዛሬዉ እለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው በሀገራችን ኢትዮጵያ ጦርነቱ በመቆሙ ሰላሙን ለፍጻሜ እንዲደርስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መልእክት አስተላልፋ እንደነበር አስታውሰዋል።

ነገር ግን ከዛ በኋላ በአርባ ምንጭ አባያ እስር ቤት የደረሰው ሞት ፣ በትግራይ ሽሬ አዲ ዳዕሮ ከተማ የደረሰው እልቂት እንዲሁም በምሥራቅ ወለጋ እየተሰማ ያለው የንጹሐን ግድያ የብዙዎችን ልብ የሚሰብር ቤተ ክርስቲያንንም የሚያሳዝን ነው ብለዋል ሲል የተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።

አክለውም ለሀገራችን መኖር የሚያስፈልገው ፍቅርና ሰላም መሆኑን ገልጸው ይህንን የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም መንግሥትም ሕግ የማስከበር ተግባሩን እንዲያከናውን ቅዱስነታቸው አሳስበዋል።

በመጨረሻም በ5ተኛው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ቀዳማይ ዕረፍት የተሰማቸዉን ሐዘን ገልጸዋል። ለመላው ሕዝበ ክርስቲያንም መጽናናትን እመኛለሁ ብለዋል።

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ( ክቡር ዶ/ር) አስኬማ፣ ልብሰ ተክህኖ፣ የእጅ መስቀልና በትረ ሙሴ ሽልማት አበረክተዋል። አቀበቱን ወጥቶ፥...
11/10/2022

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ( ክቡር ዶ/ር) አስኬማ፣ ልብሰ ተክህኖ፣ የእጅ መስቀልና በትረ ሙሴ ሽልማት አበረክተዋል።

አቀበቱን ወጥቶ፥ ቁልቁለቱን ወርዶ የሚሠራ ሰው እንዲሰጠኝ እግዚአብሔርን እጠይቅ ነበር የፍቅር አባት የሆኑትን አቡነ ኤርምያስን የመሰሉ አባት ሰጥቶኛል፤ እግዚአብሔርንም አመስግኛለሁ ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ለሚሰጡት ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት የፍቅር መግለጫ ይሆን ዘንድ ስጦታ መስጠታቸውን ብፁዕነታቸው ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚሰጡ የማይታክቱ ሐዋርያ በማግኘታችን ዕድለኞች ነንና ልናግዛቸው እንደሚገባ አሳስበዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ (ዶ/ር) በበኩላቸው ከእግዚአብሔር በታች የብፁዕነትዎ ጸሎት ሞገስ ሆኖኝ የቤተ ክህነቱ አገልጋዮችና ማኅበረሰቡ እያደረገ ያለው ቀና ትብብር ለአገልግሎቱ መቃናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራቸው ብለዋል። ለተሰጣቸው እውቅናም አመስግነዋል። ዘገባው የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ነው።

በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከ400 በላይ አርብቶ አደሮች የሥላሴን ልጅነት አገኙ !ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳን...
10/10/2022

በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ከ400 በላይ አርብቶ አደሮች የሥላሴን ልጅነት አገኙ !

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ፕሬዘዳንት በተገኙበት በትላንትናው ዕለት 409 አርብቶ አደሮች አዲስ በታነጸው ቅድስት ማርያም ወአርሴማ ቤተ ክርስቲያን ተጠምቀው ሀብተ ወልድ ስመ ክርስትናን ተቀብለዋል።

ትላንት መስከረም 29 ቀን 2015 ዓ.ም የቅድስት ማርያም ወአርሴማ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ምርቃት እንዲሁም ለኢ-አማንያን የጥምቀት ሥርዓት በተከናወነበት ዕለት ብፁዕነታቸውን ጨምሮ በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል ። መረጃውን ያገኘነው ከማኅበረ ቅዱሳን ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ነው ።

የመስቀል ደመራ በዓል በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሀገረ ስብከት በዱባይ እየተከበረ ይገኛል።
01/10/2022

የመስቀል ደመራ በዓል በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሀገረ ስብከት በዱባይ እየተከበረ ይገኛል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የእመቤታችን የቅድስት...
01/10/2022

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግስ በዓል በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተገኝተው ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ተሰጥቷል።

Address

Debre Zeyit

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ንሴብሆ ለእግዚአብሔር ቲዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share