ደ/ታቦር/አ/አ/ቅ/ዑራኤል ካቴድራል ገፅ D/T Saint Urael Cathedral

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Tabor
  • ደ/ታቦር/አ/አ/ቅ/ዑራኤል ካቴድራል ገፅ D/T Saint Urael Cathedral

ደ/ታቦር/አ/አ/ቅ/ዑራኤል ካቴድራል ገፅ D/T Saint Urael Cathedral Debere Tabor Urael

ይህ ማስታወቂያ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ይደረግ።
11/03/2026

ይህ ማስታወቂያ ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን ይደረግ።

በቅዱስ ዑራኤል መግቢያ በቀኝ በኩል Basment Plus 1 የሆነ የሰንበት ት/ቤት አዳራሽ የዲዛይን ሥራ ተጠናቅቆአል።መራኄ ፍኖት የሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ርዝመቱ(H) 53 ሜትር ሲሆን ወር...
28/12/2025

በቅዱስ ዑራኤል መግቢያ በቀኝ በኩል Basment Plus 1 የሆነ የሰንበት ት/ቤት አዳራሽ የዲዛይን ሥራ ተጠናቅቆአል።

መራኄ ፍኖት የሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ርዝመቱ(H) 53 ሜትር ሲሆን ወርዱ 19 ሜትር የሆነ ከ1000 በላይ ምዕመናን እንዲያስተናግድ ታስቦ የሚገነባ ሲሆን ለሰ/ት/ቤቱ መገልገያ የሚሆኑ ከ5በላይ ጽ/ቤቶችን የያዘ ነዉ።

ግራዉንዱ ለመካነ መቃብር አገልግሎት የሚዉል ሲሆን ለ30 አባዉራ ለእያንዳንዳቸዉ 5*4.3 ስፋት ያለዉና ከምዕራብ ወደ ምስራቅ (በሥርዓቱ መሰረት) የሚሰጥ ነዉ።

ስለዚህ በዚህ የሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ግንባታ ግራዉንድ ግንባታዉን እስከ እስላቭና ኮለን ድረስ እነዚሁ 30 ምዕመናን የግንባታ ዋጋዉን በመጋራት እንዲገነባ ከተደረገ በኋላ ግንባታዉ ሲጠናቀቅ በእጣ የሚከፋፈሉት ይሆናል።

ከእስላቭ በላይ የሚገኘዉን የአዳራሽና የጽ/ቤት ክፍሎች ግንባታ ደግሞ የካቴደራሉ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤትና የልማት ክፍሉ ምዕመናንን በማስተባበር የሚያጠናቅቁት ይሆናል።

በዚህም መሰረት እስከ አሁን ድረስ በዚህ የግራዉንድ ግንባታ ለመሳተፍ 10 ሰዎች የተመዘገቡ ሲሆን ተጨማሪ 20 ሰዎች ከከተማዉ ከየትኛዉም አቅጣጫ እንዲሳተፋና የዚህ የግንባታ አካል ይሆኑ ዘንድ ሰበካ ጉባኤዉ ጥሪዉን ያቀርባል።

ለተጨማሪ ለአስተዳዳሪዉ በ0918140590
ለልማት ክፍል ኃላፊ
ለሕዝብ ግንኙነት 0905242222 በመደዎል የዚህ እድል ተሳታፊ ይሁኑ።

17/11/2025

አንዳንድ የቤተ ክርስቲያኑአ ወሣኝ ጉዳዮች በቅዱስ ሲኖዶስ ሣይመከርባቸው በማን አለብኝነት በግለሰቦች መረዳት ብቻ ሊወሰኑ አይገባም።ቤተ ክርስቲያን የሥርዓት ሁሉ ምንጭ ናት!!!በእርሱአ የሚኖሩ ጠንቅቀው ያውቁአታል።

01/05/2025

ሚያዚያ 24/2017

"የፃድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.111፥6"

👉በስመ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን በትንሣኤው ክብር ለምናመሰግንበት ፃድቁ አባታችንን በምልጃ ፀሎታቸዉ እንዲራዱን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉የስማቸው ትርጉም የሆነው አባታችን ከእናታቸው እግዚሐርያ ከ አባታቸው ፀጋዘአብ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታህሳስ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ

👉አባታችን ናቸው ጻድቁ አባታችን ገና እንደተወለዱ በሶስተኛው ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ እያሉ በመስገድ የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል

👉እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ አድርጎ መርጧቸዋል ጻድቁ አባታችን ክብረ በዓላቸው እንደሚከተለው ነው

✝️ህዳር 24 ቀን ሃያ አምስተኛ ካህናተ ሰማይ ሆነው በሰማይ #የሥላሴን መንበር ያጠኑበት እለት ነው

✝️ታህሳስ 24 ቀን የአባታችን ልደት ነው

✝️ጥር 24 ቀን የአባታችን ሰባረ አፅሙ ነው

✝️መጋቢት 24 ቀን የአባታችን ፅንሰታቸው ነው

✝️ግንቦት 12 ቀን የአባታችን ፍልሰተ አፅሙ ነው

✝️ ነሐሴ 24 ቀን የአባታችን እረፍታቸው ነው

👉የፃድቁ አባታችን ቡራኬ ይድረሰን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ከኛ ጋር ይሁን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

22/04/2025
ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦችየበረከት ስራ ይዘን መጥተናል እና እነሆ የደ/ታቦር አ/አ/ቅ/ዑራኤል ወአቡነ ተክለ ሐይማኖት ካቴድራል1. ከደ/ታቦር ከተማ የውሀ አቅር...
24/06/2023

ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች
የበረከት ስራ ይዘን መጥተናል እና እነሆ
የደ/ታቦር አ/አ/ቅ/ዑራኤል ወአቡነ ተክለ ሐይማኖት ካቴድራል
1. ከደ/ታቦር ከተማ የውሀ አቅርቦት ችግር ጋር ተያይዞ ካቴድራሉ በውሀ ችግር ምክንያት የተለያዪ አገልግሎቶችን ለመፈጸም እየተቸገረ ይገኛል። ይህንን የውሀ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የውሀ ማጠራቀሚያ ታንከር መግዛት እንደሚገባ ታምኖበታል
2. ከቤተክርስቲያኑ ወደ ቤተልሔሙ የሚወስደው ድልድይ ለፀሀይ እና ለዝናብ የተጋለጠ በመሆኑ አገልጋይ ካህናት ለአገልግሎት ሲመላለሱ እየተቸገሩ ስለሆነ ድልድዩን ጣራ የማልበስ ስራ መሰራት አስፈላጊ ሆኗል
ስለሆነም እነዚህ ችግሮች ለመፍታት በመንቀሳቀስ ላይ ስለሆን የመላኩ ቅዱስ ዑራኤል የአባታችን የአቡነ ተክለ ሐይማኖት ወዳጆች የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና የካቴድራሉን ችግሮች እንድንፈታ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

15/04/2023

🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም፡፡
🌿🌿🌿🌼🌼🌼🌿🌿🌿🌼🌼🌼
"ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም። 'የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው።' እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደተናገረ አስቡ።"
(ሉቃ ፳፬፥፭-፯)

"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።"
(፩ቆሮ ፲፭፥፳-፳፪)
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

አባቶቻችን
12/02/2023

አባቶቻችን

እናስተውል!“እኛ ሙቀቱ ሳይጠፋ ብለን የምንጣደፍበት ውሳኔ የለንም። የቤተክርስቲያን ሙቀት መንፈስ ቅዱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ አንዴ ሞቅ አንዴ ደብዘዝ የሚያደርገን አይደለም። ሁሌም በሙቀቱ እ...
12/02/2023

እናስተውል!
“እኛ ሙቀቱ ሳይጠፋ ብለን የምንጣደፍበት ውሳኔ የለንም። የቤተክርስቲያን ሙቀት መንፈስ ቅዱስ ነው። መንፈስ ቅዱስ አንዴ ሞቅ አንዴ ደብዘዝ የሚያደርገን አይደለም። ሁሌም በሙቀቱ እቅፍ ውስጥ ነን። እኛ እና መንፈስ ቅዱስ ስንወስን እንጂ እኛና የወቅቱ ሞቅታ ወስነን አንነግራችሁም። መንፈስ ቅዱስ የሚመራት ቤተክርስቲያን ልኬቷ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው።”

(ብፁዕ አቡነ አብርሃም)

Address

Debre Tabor
Debre Tabor

Telephone

+251941674341

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደ/ታቦር/አ/አ/ቅ/ዑራኤል ካቴድራል ገፅ D/T Saint Urael Cathedral posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ደ/ታቦር/አ/አ/ቅ/ዑራኤል ካቴድራል ገፅ D/T Saint Urael Cathedral:

Share