ደብረ ታቦር ፬ቱ ጉባኤያት ምስክር ጉባኤ ቤት

ደብረ ታቦር ፬ቱ ጉባኤያት ምስክር ጉባኤ ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ደብረ ታቦር ፬ቱ ጉባኤያት ምስክር ጉባኤ ቤት, Religious organisation, Debre Tabor.

ይህ ጉባኤ ቤት በደ/ጎ ሀ/ስብከት በደ/ ታቦር ከተማ መንበረ ጵጵስናው ደ/ታቦር ደ/ል መድኃኔዓለም ቤ/ክ ይገኛል
https://t.me/joinchat/v3Qs80gi1co4Yzlk
https://www.youtube.com/channel/UCMN-okaBXejqn6OmwW9ixlw

06/06/2026
https://youtu.be/COiFbQzmXhg
05/06/2026

https://youtu.be/COiFbQzmXhg

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

04/06/2026

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ታቦር ቅርንጫፍ ሰራተኞች የደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ4ቱ ጉባኤ ቤትን በመጎብኘት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደብረ ታቦር ቅርንጫፍ ሰራተኞ...
03/06/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ታቦር ቅርንጫፍ ሰራተኞች የደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ4ቱ ጉባኤ ቤትን በመጎብኘት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደብረ ታቦር ቅርንጫፍ ሰራተኞች፣ ለደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የ4ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት የ37,373 (ሰላሳ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሰባ ሦስት) ብር የገንዘብ ድጋፍ አበረከቱ። ሰራተኞቹ ድጋፉን ያበረከቱት በጉባኤ ቤቱ ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ሂደት በአካል ተገኝተው ከጎበኙ በኋላ የቅርንጫፉን ሰራተኞች ወክለው የመጡት ጎብኚዎች በቦታው የተከናወኑ አስደናቂ የልማትና የትምህርት ሥራዎችን የተመለከቱ ሲሆን፣ ጉባኤ ቤቱ አሁን ላይ ለደረሰበት አበረታች ደረጃ መብቃት የብዙ ምእመናን መስዋዕትነት እና የከፍተኛ ትጋት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም ለሀገርና ለትውልድ የሚበጁ ይበልጥ ታላላቅ ሥራዎችን ለማከናወን የተያዙት ቀጣይ እቅዶችም ከግብ መድረስ እንዳለባቸው አሳስበዋል። ሰራተኞቹ በሰጡት አስተያየት ጉባኤ ቤቱ አሁን ለደረሰበት የላቀ ደረጃ በመብቃቱ ታላቅ ደስታ እንደተሰማቸውና በቦታው ላይ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች በማድነቅ በተለይም የጠፋው ታሪክ ዳግም ህያው ሆኖ በመታየቱ ከፍተኛ እርካታ እንዳገኙና ወደፊትም ቢሆን በሚቻላቸው አቅም ሁሉ ከጉባኤ ቤቱ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል።
በሌላ በኩል የጉባኤ ቤቱ መምህር መምህረ መምህራን በጽሐ ዓለሙ እና የጉባኤው አስተባባሪ ኮሚቴዎች በበኩላቸው፤ ጉባኤ ቤቱን ለታለመለት ታላቅ ዓላማ ለማብቃትና ሂደቱን ለማስቀጠል በተለያዩ የልማት ሥራዎች ላይ የሚደረገው የሕዝብ ድጋፍና ተሳትፎ ትልቅ ብርታት መሆኑን ገልጸው በእለቱ ለተደረገው የገንዘብ ድጋፍ እና ይበልጥ ለመደገፍ ለተነሳው የባለቤትነት ስሜት የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከሚዲያ ክፍል

03/06/2026

የተገለጠው እውነታ በ ወንድማችን #ዲያቆን #ብርሃኑ #አድማስ እንደተፃፈ

በምሥራቃዊው ኢትዮጵያ ይልቁንም በሐረር፣ አርሲና ባሌ አካባቢዎች ላይ ትኩረት አድርጎና አቅዶ ክርስቲያኖችን የሚገድል፣ የሚያፈናቅል እና የሚያሳድድ የአክራሪ ክንፍ መኖሩ ተደጋግሞ ሲነገር ኖሯል። ይህ አካል ደርግ ወድቆ ኢህአዴግ ከተተካበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛዋንም የለውጥ፣ የምርጫ እና የመሳሰሉትን የጫና ወቅቶች ጠብቆ አደጋ ያላደረሰበት ጊዜ የለም።
ከተቻለ የመንግሥት መዋቅርን በመጠቀምና በየዘመኑ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም እና ለሚገድላቸው አካላት ከወቅቱ ፖለቲካ አንጻር የሚስማማ ታርጋ በመስጠት የሚቻለውን ያህል ይገድላል፣ ያፈናቅላል፣ ያሳድዳል።

ይህ የተገለጠ እውነት ነው። ተደጋግሞም ተነግሯል፣ ተገልጿል። ሆኖም እንደዚህ ዘመን እንደ ልቡ ክርስቲያኖችን የሚያጸዳበት ስለመኖሩ ግን አላውቅም። በእኔ እምነት ኢህአዴግ ከመጣበት ጀምሮ የተፈጸሙት ተደምረው በዚህ ዓመት ብቻ የፈጸመውን የመግደልና የማሳደድ ተግባር የሚያክሉ አይመስለኝም። ይህ ሁሉ ሲሆን አንድም መንግሥታዊ ተቋም ሐዘኔታ ሲያሳዩ፣ አንድም አካል ተጠያቂ ሲደረግ ዓይተንም ሰምተንም አናውቅም።
ይህም የተገለጠ እውነት ነው።

ምንም ቢሆን፣ ማንም ቢሆኑ ይህ ሁሉ መከራ የሚደርስባቸው ሰዎች ደግሞም ዜጎች ነበሩ። በደቡብ አፍሪካ ላለው ከሀገራችን ውጡ የሚል ዐመጽ ዜጎቹን ለመከላከል መንግሥት በኢንባሲው በኩል እየሠራ እንደሆነ የሚገልጽ ዜና ከሰማንና ለዚህኛው መንግሥት በዝምታ የሚያልፍ ከሆነ ድርጊቱን የሚፈጽመው እርሱም ጭምር ነው የሚለውን ወቀሳ እውነት ነው ብሎ በአዎንታ እንደተቀበለው ለመረዳት ግዴታችን ጭምር ይሆናል። ይህ በእውነት ከልብ ያሳዝናል።

አንድ የተረጋገጠና የትገለጠ እውነት ደግሞ አለ። የሰው ደም በከንቱ ፈስሶ አይቀርም። እግዚአብሔር የሚባል ተበቃይ አምላክ አለና። ለንስሐ ጊዜ ቢሰጥም "በቀል የእኔ ነው" ያለውና "ከኦሪትና ከነቢያት አንዲት ቃል ከምታልፍ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል" ያለው አምላክ ቃሉ የታመነ ነውና አይቀርም። እርሱ ሁላችንንም ይቅር ይበለን፣ የመከራውንም ወቅት አሳልፎ ለሰላምና ለፍቅር ያብቃን።

Address

Debre Tabor
6300

Telephone

+251919187972

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደብረ ታቦር ፬ቱ ጉባኤያት ምስክር ጉባኤ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ደብረ ታቦር ፬ቱ ጉባኤያት ምስክር ጉባኤ ቤት:

Share