አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

አቡቀለምሲስ  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ This is the Official page of Abukelemsis Media.

አቡቀለምሲስ ማለት “ረአየ ኅቡኣት አበ ራዕይ አበ ትንቢት” ማለት ሲሆን የተሰወረውን የተደበቀውን ፣የተከደነውን፣ የሚገልጥ/የሚያወጣ ማለት ነው ።

መሠራታዊ ዓለማው ፦በሀገረ ስብከታችን ብሎም በመላ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የተሰወሩ ገዳማትን ፣የተደበቁ ሊቃውንትን፣ የተከደኑ ታሪኮችን ፣የተሸሸጉ ቅርሶችን ማውጣት እና የጎበጠውን አዲሱን ትውልድ በሥነ ምግባር በመቅረፅ ለቤተ ክርስቲያን ልሳን በመሆን የጥንታዊቷ እና የታሪካዊቷ ቤተ ክርስቲያናችን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ይመለስ ዘንድ አይነተኛ ድምፅ መሆን ነው ።


ስለሆነም መረጃዎችን ከትክክለኛው ከቅድስት ቤተክርስቲያን ልሳን ለማግኘት ተከታዮን የዩቲዩብ፣ የፌስ ቡክ ፣ቴሌግራም እና ኢንስታግራም አካውንታችን ሰብስክራይብ እና ላይክ በማድረግ የሚዲያችን ቤተሰብ ይሁኑ!! ሌሎችም ሰብስክራይብ እንዲያደርጉ መንፈሳዊ ሓላፊነትዎን ይወጡ፡፡

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ...
23/08/2026

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለ272 አገልጋዮች ሥልጣነ ክህነት ሰጡ።

ነሐሴ ፲፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (አቡቀለምሲስ ሚዲያ ፤ ደብረ ብርሃን)

++++ ++++ ++++ +++++ +++++ +++++

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የምስካየ ኅዙናን ገዳም የበላይ ጠባቂ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በዓለምገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተገኝተው ለ272 የአብነት ተማሪዎችና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ሥልጣነ ክህነት ሰጥተዋል።

ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ እና ብፁዕ ዋና ፀሐፊው በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ተምረው ፈተና ላለፉ ለ238 የዲቁና፣ ለ 33 የቅስና ሥልጣነ ክህነት ለ1 አባት ደግሞ የቁምስና ማዕርገ ክህነት ሰጥተዋል።

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አባቶቻችን በጊዜያቸውን ቤተክርስቲያንን አገልግለው ለእኛ እንዳስረከቡን ሁሉ እኛ ደግሞ በጊዜያችን የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የተሳካና የተቃና ይሆን ዘንድ ያለ ዕረፍት ለ24 ሰዓት እያገለገልን ነው ብለዋል።

ብፁዕነታቸው ቤተ ክርስቲያን ተተኪ ምትክ አገልጋይ እንደሚያስፈልጋት በመግለጽ ትምህርታቸውን ሲከታቱሉ ቆይተው ትምርታቸውን ላጠናቀቁ ሥልጣነ ክህነት እንደሰጡ ተናግረዋል።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዛሬ ዕለት ሥልጣነ ክህነት ለተቀበሉ ሁሉ ሃይማኖታቸውን ጠንክረው በመጠበቅ በትጋት ሊያገለግሉ እንደሚገባ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስም ክህነት መጠራት መሆኑን በመግለጽ ቅዱሳን ሐዋርያት ከልዩ ልዩ የሥራ መስክ ተጠርተው ቤተ ክርስቲያንን እንዳስፋፉ ሁሉ በዛሬው ዕለት ሥልጣነ ክህነት ለተቀበሉ አገልጋዮች ሰው ካልተማረ ማገልገል ኣይችልምና የቀረባቸውን ትምህርት በደምብ በመማርና የጎደላቸውን ትምህርት በማሟላት ምእመናንን በማስተማር የቤተ ክርስቲያን ተከታዮችን ማብዛትና መጠበቅና እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

ክህነት ሰማያዊ እና ሰማያዊ ንጉሥ ለማገልገል መሆኑን የገለጹት ብፁዕነታቸው ፣ በዛሬው ዕለት በክህነት እንድታገለግሉ ተጠርታቹኋል፤ የሰው አገልጋዮች ሳትሆኑ የሰማያዊ ንጉሥ አገልጋዮች ናችሁ፤ አሁን ተቀብታቹኋል ተቀድሳቹኋል እና በትሕትና በቅድስና ሁናችሁ ማገልገል አለባችሁ ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኅን ሥርጭት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር አካለወልድ ተሰማ፣ የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሰላም ዓለማዮ ተፈራ፣ ሊቀ ሥዩማን ተስፋዬ ለሜቻ የሸር ከተመ ሀገረ ስብከት ዋና ፀሐፊ፣ የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች፣ የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ምሐረት ፀጋዬ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተከበረ።ነሐሴ  ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አቡቀለምሲስ ሚዲያ(ደብረ ብርሃን)++...
22/08/2026

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተከበረ።

ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አቡቀለምሲስ ሚዲያ(ደብረ ብርሃን)
++++++ +++++ ++++ +++++ +++ +++ ++++++

በየዓመቱ ነሐሴ ፲፮ የሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ የሰሜን ሽዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በክብረ በዓሉ ላይ ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ "ቃልኪዳኔን እንዳላጎድል በራሴ ማልሑልሽ" በሚል ኃይለ ቃል መነሻነት ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።

ክቡር ሥራ አስኪያጁ በትምህርታቸው ቅዱስ ያሬድ "ቃልኪዳኔን እንዳላጎድል በራሴ ማልሑልሽ" በማለት የገለጠው ጌታ ለእናቱ ድንግል ማርያም የገባላትን የምሕረት ቃልኪዳን የማይሻር የማይለወጥ ስለመሆኑ ከቅዱሳት መጻሕፍት ከቅዱሳኑ ቃል አስረጂ እያጣቀሱ በስፋት አብራርተዋል።

ዛሬ የምናከብረው ከድንግል ማርያም ፴፫ቱ በዓላቶቿ መካከል አንዱ እና ታላቅ በዓሏን ነው በማለት የበዓሉን ምስጢር አስፍተው ገልጠዋል።

ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት ሲሞላት ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህ ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ጠራት በዚህ የከበረ ጥሪ ነፍሷ ከስጋዋ ተለየች፤ ሐዋርያት በአይሁድ ልማድ መሠረት አክብረው ገንዘው ሊቀብሯት ወደጌቴሴማኒ በሚሔዱ ጊዜም አይሁድ በምቀኝነት ተነሱ።

ቀድሞ ልጇ ተነሣ ዐረገ እያሉ ቤተ አይሁድን ሲያውኩ ኖረዋል፣ አሁን ደግሞ እርሷን ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና ኑ የማርያምን ሥጋ በድንጋይ ወግረን በእሳት አቃጠለን እናጥፋ በማለት ክፋት መክረው መጡ፦

ታውፋንያ የተባለ ከመካከላቸው አንዱ የእመቤታችንን ስጋ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ የአልጋውን ሸንኮር ጨበጠ። ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ የታውፋንያን እጆች በሰይፍ ቀጣቸው ያሉት ክቡር ሥራ አስኪያጁ ፦

እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው እንደቀሩ ገልጠው የምሕረት እናት ድንግል ማርያም በምልጃዋ እጆቹ እንደነበሩ እንዲሆኑለት እንዳደረገች አንስተዋል።

ክቡር ሥራ አስኪናጁ አክለውም የእመቤታችን ስጋዋን መላእክት በገነት አኖሩት የምስጢር ሐዋርያ የተባለ ቅዱስ ዮሐንስ ይህን አየ፤ ሐዋርያት ቅዱስ ዮሐንስ ያየውን ምስጢር እነርሱም ያዩ ዘንድ ሽተው ከነሐሴ ፩ ጀምረው በጾምና በጸሎት ሱባኤ ያዙ በሁለተኛው ሱባኤ ማብቂያ ጌታችን የድንግል ማርያም ስጋዋን አምጥቶ ሰጣቸው። እነርሱም በጌቴሴማኒ መቃብር አክብረው ቀበሩት፦

ድንግል ማርያም ሞት ይዟት አልቀረችም በ፫ኛው ቀን በልጇ ጥሪ በክብር ተነሳች እንደ ልጇ ትንሣኤ ተነሥታም ዐረገች እንጂ ብለዋል።

ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ በመንገድ የድንግል ዕርገቷን እንዳየ አንስተው ቀድሞ ከልጅሽ ትንሣኤ ተለየሁ ተጠራጣሪም ተባልሁ አንቺስ ከበረከተ ትንሣኤሽ ለምን ከለከልሽ ባላት ጊዜ አንተ ያየኸውን ያየ የለም ሒድ ወደ ሐዋርያት ትንሣኤና ዕርገቴን ንገራቸው አለችው ሰበኗንም ምስክር ይሆነው ዘንድ ሰጠችው ሲሉም ገልጠዋል።

ሐዋርያው ቶማስ ወደ ሐዋርያቱ ሔዶ እንደጠየቃቸው ሰበኗንም እንዳሳያቸው በዓመቱ ሐዋርያት ቶማስ ያየውን የእመቤታችንን ዕርገት ለማየት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ እንደጀመሩ በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ልጇ እንደተቀበለ ቀድሶ እንዳቆረባቸው ገልጠዋል፤ በሐዋርያቱ ሱባኤ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ቸርነት አብራርተዋል።

የእመቤታችን ትንሣኤ እና ዕርገት ሲነገር ግራ ሊገባን አይገባም ያሉት ክቡር መጋቤ ሐዲስ በእግዚአብሔር ፊት ያረጉ ሄኖክና ኤልያስን አውስተው በሰፊው አስረድተዋል።

እኛም የሐዋርቱን ጾም ጾመን፦ ቅዱስ ዮሐንስ ያየውን ክብሯን፣ ቅዱስ ቶማስ ያየውን ትንሣኤዋን እንድናይ ናፍቀን በዚህ ቅዱስ ስፍራ ተሰብሰበናልና ከዚህ የቅድስና አምባ ያገኘነውን ሰላምና በረከት ተመልሰን ስንሔድ መጠበቅ ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ የደብሩ ሊቃውንት እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን በዓሉን በገለጠ ወረብ አመስግነዋል።

ላእከ ኄራን በቀለ ደመረ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅ እና የቁጥጥር ክፍል ሓላፊን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ልኡካን፣ መልአከ አርያም ኃይለማርያም ማለደ የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ምእመናን በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተዋል።

ፎቶ፦ ሚክያስ ዐቢይ

የእመቤታችን ትንሣኤ እና ዕርገት በዓል አከባበር  በደብረ ብርሃን ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በፎቶ:-በቴዎድሮስ አየለ
22/08/2026

የእመቤታችን ትንሣኤ እና ዕርገት በዓል አከባበር በደብረ ብርሃን ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በፎቶ:-

በቴዎድሮስ አየለ

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት በደብረ ብርሃን ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ አባታዊ ቡራኬ ተከበረ።ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ...
22/08/2026

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት በደብረ ብርሃን ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ አባታዊ ቡራኬ ተከበረ።

ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም(አቡቀለምሲስ:ደብረ ብርሃን)
⛪️⛪️⛪️ ⛪️ ⛪️⛪️ ⛪️⛪️ ⛪️⛪️ ⛪️⛪️⛪️

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት በደብረ ብርሃን ከተማ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ አባታዊ ቡራኬ በድምቀት ተከብሯል!!

በክብረ በዓሉ ላይ መራሔ ሊቃውንት ያዕቆብ ተክለ አረጋዊ የጠባሴ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት መምህር «ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ፈለሰች” በሚል መነሻ ኃይለ ቃል ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተከበረ።ነሐሴ  ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አቡቀለምሲስ ሚዲያ(ደብረ ብርሃን)++...
22/08/2026

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተከበረ።

ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አቡቀለምሲስ ሚዲያ(ደብረ ብርሃን)
++++++ +++++ ++++ +++++ +++ +++

በየዓመቱ ነሐሴ ፲፮ የሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ የሰሜን ሽዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ልኡካን፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ምእመናን በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በክብረ በዓሉ ላይ ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ "ቃልኪዳኔን እንዳላጎድል በራሴ ማልሑልሽ" በሚል ኃይለ ቃል መነሻነት በዓሉን የተመለከተ ትምህርት ሰጥተዋል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት ጸሎተ ቅዳሴ በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በፎቶ፦ነሐሴ  ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አቡቀለምሲስ ሚዲያ(ደብረ ብ...
22/08/2026

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት ጸሎተ ቅዳሴ በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን በፎቶ፦

ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አቡቀለምሲስ ሚዲያ(ደብረ ብርሃን)
++++++ +++++ ++++ +++++ +++ +++

22/08/2026

#ዕርገታለማርያም #ፍልሰታለማርያም #ፍልሰታ #ክብረበዓል #ነሐሴ 16 ...

"በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" መዝ.፵፬÷፱እንኳን ለእመቤታችን የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!++++++++++++++በነገረ ማርያም ላይ ተጽፎ እንደምናገ...
21/08/2026

"በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" መዝ.፵፬÷፱

እንኳን ለእመቤታችን የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

++++++++++++++

በነገረ ማርያም ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው እመቤታችን ፷፬ ዓመት በሞላት ጊዜ ልጇ ወዳጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኃላፊው ዓለም ወደማያልፈው ሰማያዊውና ዘለዓለማዊው ዓለም እንደሚወስዳት ነገራት፤ በጥር ፳፩ ቀንም በልጇ ፈቃድ በይባቤ መላእክት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየች።

ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "የሕይወት ደም ግባት የአምላክ እናት ከሊባኖስ ውጪ፤ ፍቅርሽ የቀና ነው፤ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ፤ የመለኮት ማደሪያ ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ የአምላክ እናት ማርያም ሆይ ልጅሽ ወደ ዘላለማዊ ሕይወትና ወደ ክብር መንግሥት ይጠራሻል" በማለት ስለ ዕረፍቷ በምሥጢር ይናገራል።

ቅዱሳን ሐዋርያትም በአምላክ እናት ሥጋ ፊት ምስጋናን እያሰሙ እየዘመሩ በክብር ገንዘው በጌቴሴማኔ በመቃብር ሥፍራ ቅዱስ ሥጋዋን አሳርፈዋል። ጌታችንም ቅዱስ ሥጋዋን ከዮሐንስ ጋር በደመና ነጥቆ በገነት በሕይወት ዛፍ ሥር አኑሯታል።

ቅዱስ ዮሐንም ለቅዱሳን ሐዋርያቱ በዕፀ ሕይወት ሥር ማረፏን በነገራቸው ጊዜ እኛ ይህን ምሥጢር ሳናይ ብለው በነሐሴ ፩ ሱባኤ እንደጀመሩ በ፲፬ኛው ቀንም ጌታችን የእናቱን ሥጋ አምጥቶ ሰጥቷቸው በጌቴሴማኔ እንደቀበሯት መጽሐፍት ይነግሩናል።

ኋላም በልጇ ሥልጣን የቅድስት ድንግል ማርያም ነፍሷና ሥጋዋ ተዋሕደው በተወደደች እለት ነሐሴ 16 ከሞት ተነስታለች በክብር አርጋለች።

ነሐሴ ፲፮ ቀን አስደናቂውን የእመቤታችንን የዕርገቷን በዓል ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በማኅሌት፣ በቅዳሴ አንዲሁም በዝማሬ በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች።

ከእናቷ ማሕፀን ጀምራ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀች አዳማዊ ኀጢአት ያላገኛት፤ ኀጢአት አልባ የኾነች እንዲያውም አዳምና ሔዋን ይኽነን መርገም ከመስማታቸው በፊት ከነበራቸው ንጽሕና የበለጠ ንጽሕናን ገንዘብ ያደረገች ናትና በመቃብር አልቀረችም ልጇ ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሣ የመቅደሱ ታቦት ቅድስት ድንግልም በልጇ ሥልጣን ከሞት ተነሥታ በሰማይ አለች፡፡

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ በረከት የእናትነት ፍቅሯ ከሁላችን አይለየን ከትንሣኤዋ ከዕርገቷ በረከት ታሳትፈን!!!

መልካም በዓል!

20/08/2026

Address

Debre Birhan
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ:

Shortcuts

Share