28/08/2026
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
እንኳን ለ21ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ጵጵስናዎ በሰላምና በጤና አደረሰዎት!!
በእነዚህ ባለፉት 21 የታላቁ ሐዋርያዊ አገልግሎት ዓመታት፦
• ቅዱሳት መጻሕፍትንና የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በጥልቀት በመረዳት፣ በቃልም በጽሑፍም በመግለጥ፣ ምእመናንን በርትዕት ሃይማኖት የመገቡ፣ ሕግንና ሥርዓትን በበሰለ እውቀት ያጸኑ እውነተኛ መሪ ፤ ምንም ዓይነት ድካም ሳይበግርዎት፣ በሌሊትና በቀን ፣ በቅርብና በሩቅ ተዘዋውረው የጌታን መንጋ በመጠበቅ፣ የጌታ ታማኝ አገልጋይ ፤ ለአዘኑት መጽናናት፣ ለተቸገሩት ደጋፊ፣ ለጠፉት መላሽ፣ ሁልጊዜም በፊታቸው በሚበራው የፍቅርና የትሕትና ፈገግታ በሩን ሳይዘጉ ሰውን ሁሉ በክርስቶስ ፍቅር የሚቀበሉ የይቅርታና የእሩኅሩኅ ልብ ባለቤት
• ብፁዕ አባታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ከእርስዎ ብዙ አትርፋለች ትውልዱ ኃይማኖቱን እንዲጠብቅ በጽናት እንዲኖር በፍቅር እና በመተሳሰብ እንዲዋሀድ ያደረጉ የዘመናችን ታላቅ ሐዋርያ በመሆንዎ ሁላችንም በአባትነት ጸጋዎ ስር የተጠለልን ልጆችዎ እግዚአብሔርን አብዝተን እናመሰግናለን።
አምላካችን እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜን፣ ሙሉ ጤናንና ሰማያዊ ጥበብን አብዝቶ እንዲያድልዎት፤
አገልግሎትዎን፣ ጸሎትዎንና ቡራኬዎን አጽንቶ ለብዙ ዓመታት በታላቁ መንበርዎ ላይ እንዲያቆይልን የዘወትር ጸሎታችን ነው።
ከፍጹም አክብሮትና ፍቅር ጋር፣
የደብረ ምጥማቅ ፃድቃኔ ማርያም ገዳም ሚዲያ