አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Birhan
  • አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን  የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አቡቀለምሲስ ማለት ረአየ ኅቡኣት አበ ራዕይ አበ ትንቢት ማለት ሲሆን የተሰወረውን የተደበቀውን የተከደነውን የሚገልጥ ማለት ነው።

28/08/2026

በአሜሪካ ዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የጽዋ ማኅበርተኞች ለተፈናቃዮች 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ እህል ድጋፍ አደረጉ!!

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...
28/08/2026

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንኳን ለ21ኛ ዓመት በዓለ ሢመተ ጵጵስናዎ በሰላምና በጤና አደረሰዎት!!

ቅድስት ጸሎትዎ አይለየን!! በረከትዎ ይድረሰን!!

በአሜሪካ ዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የጽዋ ማኅበርተኞች ለተፈናቃዮች 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው  የምግብ እህል ድጋፍ አደረጉ!!ነሐሴ ፲፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (አቡቀለምሲስ ሚዲያ ፤ ...
27/08/2026

በአሜሪካ ዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የጽዋ ማኅበርተኞች ለተፈናቃዮች 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ እህል ድጋፍ አደረጉ!!

ነሐሴ ፲፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (አቡቀለምሲስ ሚዲያ ፤ ደብረ ብርሃን)
++++ ++++ ++++ +++++ +++++ +++++

በአሜሪካ ዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የጽዋ ማኅበር አባላት አማካኝነት በባቄሎ ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች 45 ኩንታል የዱቄትና 922 ሊትር የዘይት ድጋፍ መደረጉን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ምግባረ ሠናይ ክፍል ኃላፊ መጋቤ ሠናያት ቀሲስ ዮናስ አድማሱ ገለጹ።

​ኃላፊው እንደገለጹት፣ በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ካምፖች በርካታ በጎ አድራጊዎች ድጋፍ የሚያደርጉ ቢሆንም፤ የባቄሎ ካምፕ ግን ትኩረት ሳያገኝ እና ሳይጎበኝ የቆየ በመሆኑ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በሰጡት መመሪያ መሠረት ድጋፉ በዚህ ካምፕ ተደርጓል ብለዋል።

​በካምፑ ውስጥ በርካታ የጤና ችግር ያለባቸው፣ የስኳር ሕመምተኞች፣ በአልጋ ላይ ያሉ፣ ሕጻናትና አረጋውያን እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

ቀሲስ ዮናስ አክለውም በዳላስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቅዱስ ሚካኤል ማኅበርተኞች ከሚያገኙት ጥቂት ገቢ ላይ በመቀነስ ለተቸገሩ ወገኖቻቸው የላኩትን ድጋፍ በቦታው ተገኝተው ማስረከባቸውን ተናግረዋል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሲስ መልአከ ስብሐት ቆሞስ አባ ወልደ ማርያም ዘጎርጎርዮስ እንዳመለከቱት ማኅበሩ ቀደም ሲል ባደረገው ተመሳሳይ ድጋፍ የተፈናቃዮችና የአዛውንቶች ከፍተኛ ምስጋና ደርሶታል።

በስደት የሚኖሩት የጽዋ ማማበሩ አባላት አነስተኛ ገቢያቸውን በማካፈል ለተቸገሩ ወገኖች የላኩትን ይህንን ድጋፍ በዛሬው ዕለት ለተፈናቃዮቹ ማድረሳቸውን ገልጸው፣ ለማኅበሩ አባላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከኦሮምያ ክልል ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች "የሰው እጅ ከማየት አልፈን የዕለታዊ ምግብና የሕክምና ድጋፍ እጥረት ፈተና ሆኖብናል» አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍም ያስፈልገናል ሲሉ የካምፑ አስተባባሪ ቄስ ወንድሙ ተገኝ ጥሪ አቅርበዋል።

ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛ የመጠለያና የምግብ ፣ የአልባሳትና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ ችግር ቢኖርባቸውም በተለይም በአሁኑ ወቅት የሸራ መጠለያው በጭቃና በውኃ የተከበበ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ምክንያት በርካታ ተፈናቃዮች ለብርድና ለነርቭ በሽታ መጋለጣቸውን፣ ጤነኞችም የነበሩት አካል ጉዳተኛ እስከመሆን መድረሳቸውን የካምፑ አስተባባሪው ጠቁመዋል።

በተለይም በአልጋ ቁራኛ ላይ የሚገኙ አዛውንቶች የነርቭ ፣ የስኳር ፣ የደምና የሪህ ታማሚዎች ተገቢውን የሕክምናና የምግብ እንክብካቤ በማጣታቸው ለከፋ አደጋ መጋለጣቸውንና አልጋ ላይ መዋላቸውን አንስተዋል።

​ተፈናቃዮቹ ቀደም ሲል ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፣ ካምፑ ከትራንስፖርት መስመር ርቆ የሚገኝ በመሆኑ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት በየጊዜው እንደሚያቋርጥ አብራርተዋል።

ተፈናቃዮቹ ለዕለታዊ ኑሯቸው የቀን ሥራ ለመሥራት እንኳን የትራንስፖርት ወጪ ከፍለው ወጥተው ያለማግኘታቸው ችግሩን የበለጠ አባብሶታል።

በመሆኑም መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በመላው ዓለም የሚገኙ በጎ አድራጊ ግለሰቦችና ረጂ ድርጅቶች አስቸኳይ የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የልብስ፣ የኩሽና ዕቃዎችና የመጠለያ ዘላቂና አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ከምስራቅ ወለጋ እና ከምዕራብ ሸዋ ፣ ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ከምዕራብ ወለጋ የተፈናቀሉ በሌሎች የተፈናቃይ ጣቢያዎች ያሉትን ሳይጨምር 5 ሺህ 418 ዜጎች ከ5 ዓመታት በላይ በባቄሎ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ በችግርና በስቃይ ውስጥ የመከራ ሕይወት እየገፉ ይገኛሉ።

በአሜሪካ ዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የጽዋ ማኅበርተኞች ለተፈናቃዮች 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው  የምግብ እህል ድጋፍ አደረጉ!!ነሐሴ ፳፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (አቡቀለምሲስ ሚዲያ ፤ ...
27/08/2026

በአሜሪካ ዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የጽዋ ማኅበርተኞች ለተፈናቃዮች 1 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው የምግብ እህል ድጋፍ አደረጉ!!

ነሐሴ ፳፩ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (አቡቀለምሲስ ሚዲያ ፤ ደብረ ብርሃን)
++++ ++++ ++++ +++++ +++++ +++++

በአሜሪካ ዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የጽዋ ማኅበር አባላት አማካኝነት በባቄሎ ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች 45 ኩንታል የዱቄትና 922 ሊትር የዘይት ድጋፍ መደረጉን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ምግባረ ሠናይ ክፍል ኃላፊ መጋቤ ሠናያት ቀሲስ ዮናስ አድማሱ ገለጹ።

​ኃላፊው እንደገለጹት፣ በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ካምፖች በርካታ በጎ አድራጊዎች ድጋፍ የሚያደርጉ ቢሆንም፤ የባቄሎ ካምፕ ግን ትኩረት ሳያገኝ እና ሳይጎበኝ የቆየ በመሆኑ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በሰጡት መመሪያ መሠረት ድጋፉ በዚህ ካምፕ ተደርጓል ብለዋል።

​በካምፑ ውስጥ በርካታ የጤና ችግር ያለባቸው፣ የስኳር ሕመምተኞች፣ በአልጋ ላይ ያሉ፣ ሕጻናትና አረጋውያን እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

ቀሲስ ዮናስ አክለውም በዳላስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቅዱስ ሚካኤል ማኅበርተኞች ከሚያገኙት ጥቂት ገቢ ላይ በመቀነስ ለተቸገሩ ወገኖቻቸው የላኩትን ድጋፍ በቦታው ተገኝተው ማስረከባቸውን ተናግረዋል።

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሲስ መልአከ ስብሐት ቆሞስ አባ ወልደ ማርያም ዘጎርጎርዮስ እንዳመለከቱት ማኅበሩ ቀደም ሲል ባደረገው ተመሳሳይ ድጋፍ የተፈናቃዮችና የአዛውንቶች ከፍተኛ ምስጋና ደርሶታል።

በስደት የሚኖሩት የጽዋ ማማበሩ አባላት አነስተኛ ገቢያቸውን በማካፈል ለተቸገሩ ወገኖች የላኩትን ይህንን ድጋፍ በዛሬው ዕለት ለተፈናቃዮቹ ማድረሳቸውን ገልጸው፣ ለማኅበሩ አባላትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከኦሮምያ ክልል ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች "የሰው እጅ ከማየት አልፈን የዕለታዊ ምግብና የሕክምና ድጋፍ እጥረት ፈተና ሆኖብናል» አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍም ያስፈልገናል ሲሉ የካምፑ አስተባባሪ ቄስ ወንድሙ ተገኝ ጥሪ አቅርበዋል።

ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛ የመጠለያና የምግብ ፣ የአልባሳትና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ ችግር ቢኖርባቸውም በተለይም በአሁኑ ወቅት የሸራ መጠለያው በጭቃና በውኃ የተከበበ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ምክንያት በርካታ ተፈናቃዮች ለብርድና ለነርቭ በሽታ መጋለጣቸውን፣ ጤነኞችም የነበሩት አካል ጉዳተኛ እስከመሆን መድረሳቸውን የካምፑ አስተባባሪው ጠቁመዋል።

በተለይም በአልጋ ቁራኛ ላይ የሚገኙ አዛውንቶች የስኳር ፣ የደምና የሪህ ታማሚዎች ተገቢውን የሕክምናና የምግብ እንክብካቤ በማጣታቸው ለከፋ አደጋ መጋለጣቸውንና አልጋ ላይ መዋላቸውን አንስተዋል።

​ተፈናቃዮቹ ቀደም ሲል ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፣ ካምፑ ከትራንስፖርት መስመር ርቆ የሚገኝ በመሆኑ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት በየጊዜው እንደሚያቋርጥ አብራርተዋል።

ተፈናቃዮቹ ለዕለታዊ ኑሯቸው የቀን ሥራ ለመሥራት እንኳን የትራንስፖርት ወጪ ከፍለው ወጥተው ያለማግኘታቸው ችግሩን የበለጠ አባብሶታል።

በመሆኑም መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በመላው ዓለም የሚገኙ በጎ አድራጊ ግለሰቦችና ረጂ ድርጅቶች አስቸኳይ የምግብ፣ የመድኃኒት፣ የልብስ፣ የኩሽና ዕቃዎችና የመጠለያ ዘላቂና አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ከምስራቅ ወለጋ እና ከምዕራብ ሸዋ ፣ ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ከምዕራብ ወለጋ የተፈናቀሉ በሌሎች የተፈናቃይ ጣቢያዎች ያሉትን ሳይጨምር 5 ሺህ 418 ዜጎች ከ5 ዓመታት በላይ በባቄሎ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ በችግርና በስቃይ ውስጥ የመከራ ሕይወት እየገፉ ይገኛሉ።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተከበረ።ነሐሴ  ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አቡቀለምሲስ ሚዲያ(ደብረ ብርሃን)++...
22/08/2026

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነምሕረት ቤተ ክርስቲያን ተከበረ።

ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም አቡቀለምሲስ ሚዲያ(ደብረ ብርሃን)
++++++ +++++ ++++ +++++ +++ +++ ++++++

በየዓመቱ ነሐሴ ፲፮ የሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በአንጎለላ ጽርሐ አርያም ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ የሰሜን ሽዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በክብረ በዓሉ ላይ ክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ "ቃልኪዳኔን እንዳላጎድል በራሴ ማልሑልሽ" በሚል ኃይለ ቃል መነሻነት ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።

ክቡር ሥራ አስኪያጁ በትምህርታቸው ቅዱስ ያሬድ "ቃልኪዳኔን እንዳላጎድል በራሴ ማልሑልሽ" በማለት ለእናቱ ድንግል ማርያም የገባላትን የምሕረት ቃልኪዳን የማይሻር የማይለወጥ ስለመሆኑ ከቅዱሳት መጻሕፍት ከቅዱሳኑ ቃል አስረጂ እያጣቀሱ በስፋት አብራርተዋል።

ዛሬ የምናከብረው ከድንግል ማርያም ፴፫ቱ በዓላቶቿ መካከል አንዱ እና ታላቅ በዓሏን ነው በማለት የበዓሉን ምስጢር አስፍተው ገልጠዋል።

ድንግል ማርያም ፷፬ ዓመት ሲሞላት ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህ ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ጠራት በዚህ የከበረ ጥሪ ነፍሷ ከስጋዋ ተለየች፤ ሐዋርያት በአይሁድ ልማድ መሠረት አክብረው ገንዘው ሊቀብሯት ወደጌቴሴማኒ በሚሔዱ ጊዜም አይሁድ በምቀኝነት ተነሱ።

ቀድሞ ልጇ ተነሣ ዐረገ እያሉ ቤተ አይሁድን ሲያውኩ ኖረዋል፣ አሁን ደግሞ እርሷን ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና ኑ የማርያምን ሥጋ በድንጋይ ወግረን በእሳት አቃጠለን እናጥፋ በማለት ክፋት መክረው መጡ፦

ታውፋንያ የተባለ ከመካከላቸው አንዱ የእመቤታችንን ስጋ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ የአልጋውን ሸንኮር ጨበጠ። ያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ የታውፋንያን እጆች በሰይፍ ቀጣቸው ያሉት ክቡር ሥራ አስኪያጁ ፦

እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው እንደቀሩ ገልጠው የምሕረት እናት ድንግል ማርያም በምልጃዋ እጆቹ እንደነበሩ እንዲሆኑለት እንዳደረገች አንስተዋል።

ክቡር ሥራ አስኪናጁ አክለውም የእመቤታችን ስጋዋን መላእክት በገነት አኖሩት የምስጢር ሐዋርያ የተባለ ቅዱስ ዮሐንስ ይህን አየ፤ ሐዋርያት ቅዱስ ዮሐንስ ያየውን ምስጢር እነርሱም ያዩ ዘንድ ሽተው ከነሐሴ ፩ ጀምረው በጾምና በጸሎት ሱባኤ ያዙ በሁለተኛው ሱባኤ ማብቂያ ጌታችን የድንግል ማርያም ስጋዋን አምጥቶ ሰጣቸው። እነርሱም በጌቴሴማኒ መቃብር አክብረው ቀበሩት፦

ድንግል ማርያም ሞት ይዟት አልቀረም በ፫ኛው ቀን በልጇ ጥሪ በክብር ተነሳች እንደ ልጇ ትንሣኤ ተነሥታም ዐረገች እንጂ ብለዋል።

ሐዋርያው ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሰ በመንገድ የድንግል ዕርገቷን እንዳየ አንስተው ቀድሞ ከልጅሽ ትንሣኤ ተለየሁ ተጠራጣሪም ተባልሁ አንቺስ ከበረከተ ትንሣኤሽ ለምን ከለከልሽ ባላት ጊዜ አንተ ያየኸውን ያየ የለም ሒድ ወደ ሐዋርያት ትንሣኤና ዕርገቴን ንገራቸው አለችው ሰበኗንም ምስክር ይሆነው ዘንድ ሰጠችው ሲሉም ገልጠዋል።

ሐዋርያው ቶማስ ወደ ሐዋርያቱ ሔዶ እንደጠየቃቸው ሰበኗንም እንዳሳያቸው በዓመቱ ሐዋርያት ቶማስ ያየውን የእመቤታችንን ዕርገት ለማየት ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ እንደጀመሩ በ፲፮ኛው ቀን የሐዋርያትን ሱባኤ ልጇ እንደተቀበለ ቀድሶ እንዳቆረባቸው ገልጠዋል፤ በሐዋርያቱ ሱባኤ የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ቸርነት አብራርተዋል።

የእመቤታችን ትንሣኤ እና ዕርገት ሲነገር ግራ ሊገባን አይገባም ያሉት ክቡር መጋቤ ሐዲስ በእግዚአብሔር ፊት ያረጉ ሄኖክና ኤልያስን አውስተው በሰፊው አስረድተዋል።

እኛም የሐዋርቱን ጾም ጾመን፦ ቅዱስ ዮሐንስ ያየውን ክብሯን፣ ቅዱስ ቶማስ ያየውን ትንሣኤዋን እንድናይ ናፍቀን በዚህ ቅዱስ ስፍራ ተሰብሰበናልና ከዚህ የቅድስና አምባ ያገኘነውን ሰላምና በረከት ተመልሰን ስንሔድ መጠበቅ ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል።

በክብረ በዓሉ ላይ የደብሩ ሊቃውንት እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን በዓሉን በገለጠ ወረብ አመስግነዋል።

ላእከ ኄራን በቀለ ደመረ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ልኡካን፣ መልአከ አርያም ኃይለማርያም ማለደ የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ምእመናን በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተዋል።

ፎቶ፦ ሚክያስ ዐቢይ

22/08/2026
22/08/2026

የእመቤታችን በዓለ ዕርገት በደብረ ብርሃን ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን !!

22/08/2026

በብፁዕ አባታችን አቡነ ቀሌምንጦስ በደብረ ብርሃን ደብረ ምሕረት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የሰጡት አባታዊ ቃለ ምዕዳን ቡራኬ!!

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት በደብረ ብርሃን ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ አባታዊ ቡራኬ ተከበረ።ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ...
22/08/2026

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት በደብረ ብርሃን ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ አባታዊ ቡራኬ ተከበረ።

ነሐሴ ፲፮ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም(አቡቀለምሲስ ሚዲያ:ደብረ ብርሃን)
⛪️⛪️⛪️ ⛪️ ⛪️⛪️ ⛪️⛪️ ⛪️⛪️ ⛪️⛪️⛪️

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት በደብረ ብርሃን ከተማ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ አባታዊ ቡራኬ በድምቀት ተከብሯል።

በክብረ በዓሉ ላይ መራሔ ሊቃውንት ያዕቆብ ተክለ አረጋዊ የጠባሴ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤያት መምህር "ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ፈለሰች” በሚል መነሻ ኃይለ ቃል ሰፊ ትምህርት ሰጥተዋል።

22/08/2026

#ዕርገታለማርያም #ፍልሰታለማርያም #ፍልሰታ #ክብረበዓል #ነሐሴ 16 ...

Address

Debre Birhan
0000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to አቡቀለምሲስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሚዲያ:

Shortcuts

Share