Fitse Tube ፍጼ ቲዩብ

Fitse Tube  ፍጼ ቲዩብ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fitse Tube ፍጼ ቲዩብ, Church, Debre Birhan.

ይህን ድንቅ መዝሙር ጋበዝኳችሁ  በፍቅር ተጋበዙልኝ
31/01/2025

ይህን ድንቅ መዝሙር ጋበዝኳችሁ በፍቅር ተጋበዙልኝ

💚💚💚 💛💛💛 💗💗💗 ከዚህ በፊት የተለቀቁ ቪዲዮ ለማየትና እኛንም ለመደገፍ ​​ ​​ እንዲሁም የደውል መልክቷን ጫን ያድርጉ እና All ያድርጉ ይህ ቻናል የተከፈው የኢኦ....

እስኪ ይሄን ድንቅ  #ቪዲዮ ተጋበዙልኝ   https://youtu.be/BUM-XODsEcU😇
18/01/2025

እስኪ ይሄን ድንቅ #ቪዲዮ ተጋበዙልኝ https://youtu.be/BUM-XODsEcU😇

ጥምቀት በጃንሆይ ሜዳ (1963 ዓ.ም) Epiphany Celebration in Addis Ababa, Ethiopia (1971). Epiphany Celebration at the religious grounds of Jan Hoy Meda in the northern ...

እንኳን ለሰማዕቷ ለቅደስት አርሴማ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን ፡፡ ሰብስክራይብ ሼር ላይክ በማድረግ መዝሙሩን ጋበዝኳችሁ
08/10/2024

እንኳን ለሰማዕቷ ለቅደስት አርሴማ ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ
አደረሰን ፡፡ ሰብስክራይብ ሼር ላይክ በማድረግ መዝሙሩን ጋበዝኳችሁ

💚💚💚 💛💛💛 💗💗💗 ከዚህ በፊት የተለቀቁ ቪዲዮ ለማየትና እኛንም ለመደገፍ ​​ ​​ እንዲሁም የደውል መልክቷን ጫን ያድርጉ እና All ያድርጉ ይህ ቻናል የተከፈው የኢኦ....

ድንቅ መንፈሳዊ ተረካ
26/08/2022

ድንቅ መንፈሳዊ ተረካ

💚💚💚💚💚💚💛💛💛💛💛💛💛💗💗💗💗💗💗💗ከዚህ በፊት የተለቀቁ ቪዲዮ ለማየትና እኛንም ለመደገፍ ​​ ​​ እንዲሁም የደውል መልክቷን ጫን ያድርጉ እና All ያድርጉ .....

ድንቅ መንፈሳዊ ትረካ
26/08/2022

ድንቅ መንፈሳዊ ትረካ

💚💚💚💚💚💚💛💛💛💛💛💛💛💗💗💗💗💗💗💗ከዚህ በፊት የተለቀቁ ቪዲዮ ለማየትና እኛንም ለመደገፍ ​​ ​​ እንዲሁም የደውል መልክቷን ጫን ያድርጉ እና All ያድርጉ .....

+ ለምን ትቀናለህ? +   በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ ...
26/08/2022

+ ለምን ትቀናለህ? +

በዜና አበው ላይ አጋንንት አንድን መነኩሴ ለማሰናከል ሲማከሩ የሚያሳይ ታሪክ ተጽፎአል፡፡ መነኩሴው ለብዙ ዘመናት በተጋድሎ አሳልፎ ከብቃት የደረሰ መናኝ ነበር፡፡ የአጋንንቱ ጭፍራ በአለቃቸው ተመርተው ይህንን መነኩሴ ለማሳት ዘመቱ፡፡ ተራ በተራ ወደ እርሱ እየሔዱ የፈተና ወጥመዳቸውን ዘረጉበት፡፡ በዝሙት ሊፈትኑት ሞከሩ፡፡ አልተሳካም፡፡ በምግብም ሞከሩ ድል ነሣቸው፡፡ የሚያውቁትን የፈተና ስልት በተለያየ መንገድ እየተገለጹ አንዴ ሰው አንዴ መልአክ እየመሰሉ ሊጥሉት ቢሞክሩም አልቻሉም፡፡

አለቃቸው ይኼን ጊዜ በሉ እኔ የማደርገውን ተመልከቱ አላቸውና መንገደኛ መስሎ ወደ መነኩሴው ቀረበ፡፡ በጆሮው የሆነ ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ፡፡ ይህንን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፍፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት፡፡ በዚህም ተደንቀው ምን ብለህ ነው ያሸነፍከው? ብለው አለቃቸውን ጠየቁት፡፡ እርሱም እንዲህ አላቸው፦ ‘ከአንተ ጋር ያደገውና ከአንተ ጋር የተማረው ጓደኛህ እኮ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ’ ብዬ ነገርኩትና ወጣሁ፡፡ አሁን ልቡ በቅናት እየነደደ ነው አላቸው፡፡ አጋንንቱ በደስታ ጨፈሩ፡፡

ሰይጣን የቅናትን ኃይል ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ መጽሐፈ ቅዳሴ ሞትን ሲገልጸው ‘በሰይጣን ቅናት ወደ ዓለም የገባ’ ይለዋል፡፡ ሰይጣን በሰው ልጅ ጸጋ ቀንቶ አዳምና ሔዋንን በፈጣሪያቸው እንዲቀኑና አምላክ መሆን እንዲመኙ አድርጎ ዓለምን ያመሰቃቀለ ነውና ይህንን መነኩሴ ለመጣል ለሺህ ዓመታት ብዙዎችን ወግቶ የጣለባትን ሰይፉን መዘዘበት፡፡ መነኩሴው የእኩያውን መሾም ሲሰማ ቅናቱን መቋቋም አቃተው::

ቅናት እጅግ ክፉ ኃጢአት ነው፡፡ ሰው ቢዘሙት ቢሰክር በሥጋው ነው:: ቅናት ግን በምታስተውል ነፍሱ ውስጥ የሚበቅል መርዝ ነው፡፡ ቃየልን በየዋህ ወንድሙ ላይ ያስጨከነው ቅናት ነበር፡፡ የአቤል ስኬት ለቃየል ውድቀት መስሎ ስለተሰማው በግፍ ሊገድለው በቃ፡፡

ዮሴፍ የለበሳት ቀለምዋ ብዙ የሆነ ጌጠኛ ቀሚስ በወንድሞቹ ዘንድ የመረረ ጥላቻን አትርፋለት ነበር፡፡ አንዱ አጊጦ አምሮ ሲታይ ቢሞትና ቢገላገሉት ደስ የሚላቸው የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡

ዮሴፍም አርፎ አልተቀመጠም፡፡ እየሔደ ሕልሙን ይነግራቸው ነበር፡፡ ስለ ሕልሙም የበለጠ ጠሉት ይላል፡፡ ወዳጄ ሕልምህን ዝም ብለህ ለሰዎች አትዝራ፡፡ ሕልም ስልህ ተኝተህ የምታየውን ብቻ ማለቴ አይደለም፡፡ ራእይህን ፣ ተስፋህን ዕቅድህን ሲያውቁ የሚንገበገቡ የዮሴፍ ወንድሞች በየዘመኑ አሉ፡፡ ፍቺው ባይገባቸውም ባልተፈታ ሕልም ይጠሉሃል፡፡ ምንም ነገር ሳታደርግ እንኳን "ለምን አለምከው?" ብለው ጥርስ ይነክሱብሃል፡፡ ዮሴፍ ግን ይኼ ስላልገባው ነገራቸው፡፡ ወዳጄ አንተም ሕልምህን እንደ ዮሴፍ በየዋህነት የምትዘራ ከሆንህ እንግዲህ የዮሴፍ አምላክ ይጠብቅህ፡፡

ቅናት እጅግ ከባድ ነው፡፡ እረኛው ዳዊት ጎልያድን የገደለ ዕለት የተዘፈነለት መዘዘኛ ዘፈንም ነበረ፡፡ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ ዳዊት እልፍ ገደለ’ ብለው ዘፈኑለት፡፡ ይህች ዘፈን በሳኦል ጆሮ ስትደርስ ዳዊት ላይ ብዙ ጦር አስወረወረች፡፡ ሳኦሎች ሌላ ሰው ከእነርሱ በላይ ሲመሰገን የሰሙ ዕለት በቅናት ታውረው ገበታ ላይ ሳይቀር ሰይፍ ይመዛሉ፡፡

የጠፋው ልጅ ወንድምን አስበው፡፡ (ሉቃ 15:20) ወንድሙ ከጠፋበት ተመልሶ ደስታ ሲደረግ እርሱ ግን ከፍቶት ውጪ ቁጭ አለ፡፡ ወዳጄ ቅናት ከቤተ ክርስቲያንና ከእግዚአብሔር መንግሥት ያስወጣል፡፡ የሌላው ስኬት ካበሳጨህ እንደጠፋው ልጅ ወንድም ውጪ ቁጭ ብለህ አፈር እየጫርክ ‘እምቢየው አልገባም’ እያልክ እያልጎመጎምክ ትቀራለህ፡፡

ክርስቶስ ላይ አይሁድ ያቀረቡት ትችት ሁሉ ለሕግ ከመቆርቆር ሳይሆን ከቅናት ነበር፡፡ ጲላጦስ እንኳን ‘በቅናት አሳልፈው እንደሠጡት ያውቅ ነበር’ ይላል፡፡ አንዳንዴ ሰዎች ቅናታቸውን በሌላ ነገር እንደ አይሁድ ሸፍነው ትችት ያቀርባሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንደተቆረቆሩ ፣ ለሥርዓቱ እንዳዘኑ መስለው ውስጣቸው ያለውን ቅናትና ጥላቻ ያንጸባርቃሉ፡፡

የሰንበት መሻር ፣ ለቄሣር ግብር መከፈል ፣ የመቅደሱ በሦስት ቀን ፈርሶ መሠራት እንዳንገበገባቸው እርር እያሉ ቢናገሩም እውነታው ግን ቅናት ነው፡፡ ‘የቤትህ ቅናት በላኝ’ እንዳለው ጌታ በየዘመኑ የሰዎች ቅናት ብዙ ንጹሐንን ትበላለች፡፡

ወዳጄ በሌላው ትቀና እንደሆን አሁኑኑ ከዚህ ውስጥን በልቶ ከሚጨርስ ካንሰር ራስህን አድን፡፡

ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ በምድር ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው አንተን የሚመስል ሌላ ሰው የለም፡፡ ካንተ ቀድሞም በትክክል አንተን የሆነ ሰው አልተፈጠረም ለወደፊትም አይፈጠርም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ ያልሠራው ደግሞም የማይሠራው ምርጥ ዕቃው ነህና ራስህን ከሌላ ጋር አታወዳድር፡፡

ለአንተ ብቻ የሠጠው ጸጋ አለና ሌሎችን መመልከት ትተህ ውስጥህ ያለውን ውድ ማንነት ቆፍረህ አውጣ፡፡ ያንተ ሕይወት ቁልፍ የተቀበረው አንተው ውስጥ ነው፡፡ ሌሎችን ረስተህ ወደ ራስህ ጠልቀህ ግባ፡፡ መብለጥ ከፈለግህም አሁን ያለውን ራስህን ብለጠውና ሌላ ትልቅ አንተን ሁን፡፡

በቅናት እንዳትቃጠል ሌሎችን ሰዎችንም ውደዳቸው፡፡ ከወደድሃቸው ‘ፍቅር አይቀናም’ና የእነርሱ ስኬት የደስታህ ምንጭ ይሆናል፡፡ የቅናት ስሜት ሲሰማህም ‘ቀናተኛ ልቤን ፈውስልኝ’ ብለህ ለምነው፡፡

‘በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን’ ሮሜ 13፡13

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

እንኳን አደረሳችሁ አደርሰን
22/08/2022

እንኳን አደረሳችሁ አደርሰን

የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንፁህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ከአንቺ በነሳው ሥጋ ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ ቢያየው እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመፅሐፍ ነገረን። የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተፃፈ። የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ሥጋ ሆነ ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ ተባለ። ይደንቃል።

መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ስብሐት ለእግዚአብሔር አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ስብሐት ነው እንጂ። ሰማይ ከክብሩ የተነሳ የምትጠበውን በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ፀሐፊ ከፍቅሩ የተነሳ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና እቅም በማጣት ሠአሊ ለነ ብሎ ጽሑፉን ይዘጋዋል። አይችልምና።

የአንቺ ሥጋ ከአቤል ይልቅ ተወደደ፤ ከደገኛው አብርሐም ይልቅ ከፍ አለ፤ ከንጉሱ ከዳዊት ይልቅ ሥጋሽ የተለየና የተመረጠ ሆነ ...ዳዊትም፦ ንጉስ ደም ግባትሽን ወደደ ብሎ ፃፈልሽ። ከእስራኤላውያን አባት ከያዕቆብ ድንኳን ይልቅ የአንቺ ሥጋ ተመረጠ። ሎጥ፦ መላእክትን ወደ ቤቴ ግቡ ቢላቸው በአደባባይህ እንሆናለን እንጂ አንገባም አሉት። ድንግል ሆይ የአንቺ ሥጋ ግን መላእክትን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆነ። ለዚህ ቃል የለም ዝምታና አንክሮ እንጂ።

የአንቺን ሥጋ በመቃብር የለም በአብ ቀኝ እንጂ። አንዳንዶች ተነስታለች ለማለት ከበዳቸው። ለመሆኑ ልጅሽ አልዓዛርን ከመቃብር ያስነሳ መሆኑን አላነበቡ ይሆንን? የኢያዒሮስ ልጅን ታሪክ አልተመለከቱ ይሆን አንቺ ግን ወደ ሰማያት ከተነጠቁት ከሄኖክና ከኤልያስ ትበልጫለሽ። #ትንሣኤሽን #የሚያምን ሁሉ #አሜን ይበል።

#ምልጃሽ #ኢትዮጵያን #ይታደግ። ለአለም ምህረት ይሁን ።

12/07/2022
☞ጌታ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የሰጠው ቃልኪዳን፡፡☞ሰው ሁሉ ወደ ሥጋዊ ተግባርም ሆነ ወደ መንፈሳዊ ተግባርም ቢሆን ሲሄድይህ የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ነው ብሎ ቅጽሩን፤...
07/07/2022

☞ጌታ ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የሰጠው ቃልኪዳን፡፡
☞ሰው ሁሉ ወደ ሥጋዊ ተግባርም ሆነ ወደ መንፈሳዊ ተግባርም ቢሆን ሲሄድ
ይህ የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ነው ብሎ ቅጽሩን፤ ገራገሩን
ቢሳለም የተሳለመውን ሰው ቢኖር እኔ መንበረ መንግሥቴን አሳልመዋለሁ፡፡
☞የገድልህንም መጽሐፍ የተሳለመ ቢኖር እኔ መንበረ መንግሥቴን
አሳልመዋለሁ፡፡
☞የገድልህ የተአምርህ መጽሐፍ የተነበበትን ውኃ እኔ እንደተጠመቅሁበት እንደ
ማዮርዳኖስ አደርገዋለሁ፡፡ የገድልህ መጽሐፍ በተነበበት ውኃ የተጠመቀበት
ሰው ቢኖር የሰማንያ ዓመት ኃጢአቱን አስተሠርይለታሁ፡፡
☞ወንድን የአርባ ቀን ሴቷን የሰማንያ ቀን ሕፃን አደርጋቸዋለሁ፤እኔ
በተጠመቅሁበት ማየ ዮርዳኖስ እንደተጠመቀ ሆኖለት ከኃጢአቱ ይነጻል፡፡
☞ሰውም ሆነ እንስሳ ቢታመም በጹኑ እምነት ይደረግልኛ ብሎ አምኖ ያለ
ጥርጥር ውኃ አቅርቦ የገድልህን መጽሐፍ በላዩ ላይ አንብቦ የተነበበትን ውኃ
ቢታጠብበት ወይንም ቢጠጣ ያለ ጥፋት ፈጥኖ ከደዌው ይፈወሳል፡፡
☞የገድልህን መጽሐፍ የተነበበትን ማየ ጸሎት በቤቱ ውስጥ ቢረጭ ከዚያ ቤት
በረከቴን እመላበታለሁ፤ ተድላን፤ ደስታን፤ ጥጋብን በዚያ ቤት አሳድራለሁ፤ እሰከ
ዘላለሙ ድረስ በቤቱ ውስጥ የእህል መታጣትና ርሃብ፤ የውኃ ጥማት፤ተላላፊ
በሽታ አይገባበትም፤ፈጽሜም አላመጣበትም፡፡
☞ሥጋዬን ደሜን መቀበል ያልተቻለሁ ሰው ቢኖር ለመታሰቢያህ ዝክር
ከተደረገው ፍርፋሪ ይቅመስ፤ ሥጋዬን ደሜን እንደተቀበለ እኔ አደርግለታለሁ፡፡
☞ፍርፋሪ ባያገኝ እንጀራውና ዳቦውን የተበላበትን ገበታ፤ ጠላው የተጠጣበትን
ጽዋ በምላሱ ይላስ፤ እኔ ኢየሱስ ቃል የሚያብለው ሥጋዬን ደሜን እንደተቀበለ
አደርገለታለሀ፤ ሰለ እምነቱ ሥጋዬን ደሜን ለመቀበል የሚያበቃውና
እውነተኛውን ምግባር የጽድቅ ሥራ እንዲሠራ አደርገዋለሁ ቡሎጌታ
ለመጥምቀ መለኮት ቃል ኪዳን ስጥቷል፡፡
☞(ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ)
☞እኛም የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የቃልኪዳኑ ተከፋይ ያድርገን
በጸሎቱ ይማረን፡፡

Address

Debre Birhan
106

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fitse Tube ፍጼ ቲዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Fitse Tube ፍጼ ቲዩብ:

Share

Category