BIBLE truth.org

BIBLE truth.org Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from BIBLE truth.org, Religious organisation, AGIP, Debre Berhan.

15/06/2020

የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል። የማይታየውን እንጂ የሚታየውን
ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ
ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። ድንኳን
የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት
የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና። በዚህ ውስጥ በእውነት
እንቃትታለንና፥ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን
ራቁታችንን አንገኝም። በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ
ልንገፈፍ የማንወድ ስለ ሆነ፥ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን። ነገር ግን ለዚሁ
የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን። እንግዲህ ሁልጊዜ
ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት
እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥ ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር
በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል። ስለዚህ ደግሞ ብናድር ወይም ተለይተን ብንሆን
እርሱን ደስ የምናሰኝ ልንሆን እንቀናለን። መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥
እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ
ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።
እንዴት ድንቅ ክፍል ነዉ! (ወገኖች ይህንን ክፍል እያንዳንዱን ቃል በማጤን በጥሞና
አንብቡት) ጳውሎስ ጌታን ኢየሱስን ከሙታን ያስሳዉ እግዚአብሔር እኛን አማኞችን ከእርሱ
ጋር እንደሚያስነሳን በመግለፅ የውጭዉ ሰዉነታችን ቢጠፋም (በምንም ሁኔታ ዉስጥ ቢያልፍ)
የዉስጥ ሰዉነታችን ግን እንደሚታደስ ይናገራል፡፡ ስለዚህም ይህ እንደ ድንኳን የሚሆነዉ
መኖሪያ (ሰዉነት) ቢፈርስ እንኳን ከዚህ እጅግ የሚበልጥ መኖሪያ (የማይሞት ሰዉነት)
እንዳለን እናዉቃለን ማለት ነዉ፡፡ ምንም እንኳን ይህ የሚጠፋዉ ድንኳን ከብዶን ብንቃትትም
ለዚህ የሰራን እግዚአብሔር ነዉና የማይሞተዉን እንደምንለሰብስ እርግጥ መሆኑን ለማረጋገጥ
የመንፈሱን መያዣ እንደሰጠን ያስረዳል፡፡ ይህ ማንም ሊወስድብን የማይችል ታላቅ
የእግዚአብሔር የፀጋዉ ስጦታ (ደህንነት) ነዉ፡፡ ታዲያ የአማኞችን ዝግጁነት የሚጠይቀዉ
ጉዳይ ምንድን ነዉ?
 ስሞት ገነት ይሆን የምገባዉ ወይስ ሲኦል የሚለው ጥያቄ ነዉ? አይደለም!
 ለዘላለም ህይወት ብቁ የሚያደረገኝን ሥራ አልሰራሁም የሚለው ይሆን? አይደለም!
አማኞች ተዘጋጅተዉ (ሊኖሩ የተገባቸውን ህይወት ኖረዉ) ወደ ጌታ እንዲሄዱ የሚጠይቀዉ
ጉዳይ ከላይ በተመለከትነዉ ክፍል በቁጥር10 ላይ የተገለፀዉ ነዉ፡፡(ይቀጥ...)

15/06/2020

ይህ ዝግጅት ምንድን ነዉ?
ዝግጅቱ ሁለት አይነት የሰዎች ህይወትን ይመለከታል
1. በጌታ ላልሆናችሁ ወገኖች፡-
ምንአልባት ጌታን ያላገኛችሁና ወደዚህ የዘላለም ህይወት መግባት እንዴት ይቻላል? የምትሉ
አንባቢዎች ብትኖሩ አንድ በረጅም እርቀት ላይ የሚገኙ ሁለት ቦታዎች ላይ መኖሪያ ያለዉ
ሰዉን ምሳሌ እንዉሰድ፤ ይህ ሰዉ ረጅም ጊዜ ለመቆየት ከአንዱ መኖሪያዉ ወደ ሌላኛው
ለመሄድ በሚያስብበት ጊዜ ለመኖር የሚያስፈልገዉን ጓዝ ሁሉ ከመነሳቱ በፊት ማሰባሰብና
ማከት ይኖርበታል፡፡ ታዲያ ይህ ሰዉ ዝግጅቱን አጠናቆ ከተጓዘ በኋላ በመኖሪያ ቤቱ ሲደርስ
የቤቱን ቁልፍ መክፈቻ እንዳልያዘ ቢያረጋግጥ ወደ ቤቱ መግባት ባለመቻሉ ሌላው ድካሙ
ሁሉ ከንቱ መሆኑ ነው፡፡ በምድራዊ ህይወት የሚደረግ ማንኛዉም ዝግጅት ቢኖር በጌታ
በኢየሱስ ክርስቶስ (በመክፈቻዉ) በኩል ካልሆነ ማንም ወደ ዘላለም ህይወት እንደማይገባ ጌታ
ራሱ በዮሐንስ 14፡6 እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም
በማለት ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም፡- ዮሐ 3፡16፣ 3፡18፣ ኤፌ 2፡8-9፣ ሮሜ 4፡4-5፣ የሐዋ 4፡
12፣ 5፡24 ተመልከቱ
2. የአማኞች ዝግጅት፡-
በእርግጥ ሁሉም ፍጡር በየተሰጠዉ የመረዳት ደረጃ በህልፈተ ህይወት (ሞት) ጊዜ ያለዉን
ህመም ወይም ስቃይ በመገንዘብ፣ አሁን የሚገኝበትን ሁነት በመዉደድና ይህንንም ላለማጣት
ከመነጨ ፍላጎት የተነሳ ሞትን አጥብቆ ሊፈራ ይችላል፡፡ ሰዉ ደግሞ በእግዚአብሔር ምሳሌ
የተፈጠረና ዘላለማዊነት ያለዉ በመሆኑ ከሞት በኋላ ስላለዉ ጉዳይ በመጨነቅ ሞትን ይፈራ
ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ ክርስቲያኖች ከላይ የተጠቀሰዉ የፍጡር ባህርይ እንዳለ ሆኖ በክርስቶስ
የዘላለም ህይወት እንዳገኘን የምናዉቅና የምናምን በመሆኑ የስጋ ሞትን ስናስብ ሊኖር
የሚችለዉ ስጋት የዝግጅት ጉዳይ ብቻ ነዉ፡፡ 2 ቆሮ 4፡13-5፡10
ነገር ግን አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ
ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤ ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛን
ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሣን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለንና።
በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ፥ ሁሉ
ስለ እናንተ ነውና። ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ ( ይቀጥ...)

15/06/2020

ወደ ጌታ ለመሄድ ዝግጁ ነህ?
ባዩ ጥላሁን
ሰኔ 6 / 2012 ዓ.ም
መግቢያ
ሰላም ወገኖች! ዛሬ የምንመለከተዉ መልዕክት «ዝግጁ ነህ ወይ» በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ
ነዉ፡፡ የነገሮችን ክዋኔ ወይም ፍፃሜ የተሻለ (መልካም) ለማድረግ አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት
ማድረግ የተለመደ ጉዳይ ነዉ:: የምንዘጋጅለት ጉዳይ አንገብጋቢነት የዝግጅቱን ሁኔታ
ይወስነዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ዝግጁ ሆነን እንድንገኝ የሚያስተምረን ብዙ ጉዳዮች አሉ፡፡
በአጠቃላይ ሰዉ በምድር የሚኖረዉ ዘመን ከዘላለም ጋር ሲነፃፀር በጣም ትንሽ (Negligible)
በመሆኑ ይህን ህይወት የዝግጅት ጊዜ ነዉ ማለት እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ሰዉ በስጋዊ ሁነት
ላይ በመደገፍ እና በሚታይና በሚጨበጠዉ ላይ በማመን ይህነ ህይወት እንደ ዋና በማድረግና
እልፈተ ህይወትን እንደ ህይወት ፍፃሜ በመቁጠር «ሳልኖር እንዳልሞት» በሚል መቃተት
ውስጥ ያልፋል፡፡ በመሠረቱ ክርስቲያኖች በምድር ላይ የጌታን ምፅዓት እየተጠባበቅን በዝግጅት
እንደምንኖር ይታሰባል፡፡ ጌታም 2ጴጥ 3፡8-9 እንደተገለፀው ሁሉም ወደ ንስሃ እንዲመለስ
እንጂ እንዳይጠፋ ስለሚፈልግ ይታገሳል፡፡ ሆኖም ጌታ ስለተስፋ ቃሉ አይዘገይምና ይመጣል፡፡
ነገር ግን በዚህ መልዕክት ማተኮር የምፈልገዉ ሰዉ ወደ ጌታ የሚሄድበት (የስጋ ሞት)
ክስተት ላይ ነዉ፡፡ በወቅቱ የሰዉን ልጅ እያስጨነቀ የሚገኘዉ ብርቱ የኮቪድ-19 መቅሰፍት
እንደ ማሳሰቢያ ሊያገለግለን ይችላል፡፡ በዚህ መቅሰፍት ከ4 መቶ ሺህ በላይ ሰዎች ወደ
ማይመለሱበት እንደሄዱና በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ደግሞ በመቅሰፍቱ ተይዘዉ በሞት ፍርሃት
ዉስጥ እንደሚገኙ መረጃዎችን መመልከት ይቻላል፡፡ ሰዉ በነፃ የተሰጠዉን አየር መተንፈስ
ተስኖት ከመቃተት የበለጠ ምን የጭንቀት ቀን ይምጣ? (መክብብ 12 ተመልከቱ)፡፡ ከእነዚህ
ብዙዎቹ ባላሰቡት መንገድ በድንገት መቅሰፍትና ሞት በራቸዉን አንኳኩቶ በመግባቱ የዚህን
ምድር ጉዳይ ተሰናብተዋል፡፡ ታዲያ እነዚህ ሰዎች በዋዜማዉ የነበሩበት ሁኔታ ወይም ህይወት
ለዘላለም ህይወት የሚያበቃ ያልሆነ እንደሆነ ዛሬ ተመልሰው የሚያስተካክሉበት እድል ፋንታ
የላቸዉም፡፡ (ይቀጥ...)

12/06/2020

መ. (ቁ. 1-3)(46-50) እግዚአብሔር ለዳዊት መታመኛዉ መሆኑን የሚያዉጅበት
ቁ.1-3 “አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ፡፡ እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።”
በዚህ ክፍል ዳዊት ስለ አምላኩ ስለ እግዚአብሔር 3 ቁልፍ ነገሮችን ይናገራል፡፡
እግዚአብሔር ጉልበቴ ነዉ፡-በእርግጥም የዳዊት ጉልበት እግዚአብሔር መሆኑን ጎልያድን ድል ካደረገበት ክስተት መረዳት ቀላል ነዉ፡፡ እግዚአብሔር
መታመኛዬ
ረዳቴ
ዓለቴ
የደኅንነቴ ቀንድ በሚል ድንቅ አገላለጽ በመግለጽ የዳዊት ሙሉ ህልዉናዉ በእግዚአብሔር በአምላኩ ላይ የተመሰረተና በዚህም ታምኖ የሚኖር መሆኑን ያመለክተናል፡፡
በቁ 33 ላይ “እግሮቼን አንደ ብሆር እግሮች የሚያበረታ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነዉ” የሚለዉን ስመለከት ዳዊት አለቱ ከሆነዉ ከእግዚአብሔር ጋር በመቆራኘቱ ባገኘዉ የህይወት ሙላትና ስኬት በሀሴት ተሞልቶ የሚናገር ይመስለኛል፡፡ እኛስ በህይወታችን እግዚአብሔርን የቱ ጋር ነዉ ያስቀመጥነዉ?

እወድሃለሁ / I will love You/
ይህ አገላለጽ ከአሁኑ ባለፍ የወደፊቱንም ቁርጠኝነት የሚያመለክት ነዉ፡፡ እግዚአብሔርን መዉደድ በክርስትና ህይወት ዉስጥ ቁለፍ ጉዳይ ሲሆን፡-
መዉደድ የሚገለጸዉ በመታዘዝ ንዉ------ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ ዮሐ 14፡15
መዉደድ ኃላፊንት መቀበልን ያስከትላል-----ዮሐ 21፡15 (…ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፤ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው።…)

እጠራዋለሁ…ያድነኛል
አምላኩን በቅርብ ከሚያዉቅ ሰዉ በስተቀር ማንም ይህንን በሙሉ መተማመን ሊናገር አይችልም፡፡
ወገኖች፡- ከላይ በዳዊት ሕይወት የምንመለከታቸዉን ሁነቶችና በዉሰጡ የተሞላዉን መተማመን ከራሳችን የግል ሕይወት ጋር እያነጻጸር ብንመለከት መልካም ነዉ፡፡ እግዚአብሔርን በነገራችን ሁሉ ላይ አምላክና ገዢ እንዲሆን ከፈቀድንለት የዚህ አይነት የመተማመንና የሙላት ሕይወት ይኖረናል፡፡
እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!
ጌታ ይባርካችሁ!

12/06/2020

ቁ.30ና31፡- የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው። ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችን በቀር አምላክ ማን ነው?...
በዳዊት ዘመን በዙሪያዉ የነበሩ አህዛብ ከአሁኑ ዘመን የሚለዩ ይመስለኛል፤ አማልክትም ልዩ ልዩ ነበሩ፡፡ በአሁኑ ዘመን ብዙ ሰዉ ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ የለም ብትሉት “እና ማን ሊኖርልህ ፈለክ! እርሱ ሰማይን ያለ ምሰሶ ምድርን ያለካሰማ ያቆመ… ”ወ.ዘ.ተ ብሎ ሊመልስ ይችላል፡፡ ገለጻዉ ደስ ቢያሰኝም ይህ አምላክ በሰዉ በግል ሕይወት ዉሰጥ ከሌለ ግን ምንም አይጠቅምም፤ ኃይሉም ለፍርድ ይሆናል፡፡
*አምላክ ማለት ሲመለክ ነዉ፤ ማምለክ ማለት ደግሞ
እግዚአብሔርን ሕይወታችን በእያንዳንዱ ጉዳይ እነዲወስን ስንፈቅድለት፣
ስንጨነቅ የምንጠራዉ እርሱ ብቻ ሲሆን፣
ሲያደርግልን ስላደረክልኝ አመሰግንሃለሁ ስንለዉ፣
በቀሪ ዘመናችን ደግሞ በእርሱ በመተማመን የምንራመድ ከሆነ፤
ያን ጊዜ በእዉነትም በሕይወታችን ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ የለም ማለት ነዉ፡፡

ቁ.35
ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸሰጠኸትናትና አለዉ)
ቀኝህም ትረዳኛለች………………..(ኃይል ይሰጠዋል)
ተግሣጽህም ታስተምረኛለች……….(ይቀጣዋል)
ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች..(በተማረዉ ይኖራል)
በነዚህ ቁጥሮች ዉስጥ የዳዊትን የተሟላ የአምልኮ ሕይወት እንመለከታለን፡፡ዛሬ በኛ ሕይወትስ?
የደህንነታችን ዋስትና ክርስቶስ፤ ኃየላችንም ከእግዚአብሔር ዘንድ ሲሆን በተግሳጹ የምንማርና በተማርነዉም ለዘላለም የምንጸና መሆን የኖርብናል፡፡

ሐ. (ቁ. 20-29) በጽድቅ የሚገኝ በረከትና የዘሩትን ማጨድ ወይም እንደ ስራ መከፈል
ቁ. 20-26 “እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል። የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁም።…”
*ዳዊት ይህንን የሚናገረዉ በትእቢት ሳይሆን እዉነታዉን ከመግለጽ አንጻር ነዉ፤ እግዚአብሔርም “እንዳልቤ የሆነ” በማለት መስክሮለታል፡፡
*እግዚአብሔር ፍረዱ ሚዛናዊና ለሁሉም እንደ እጁ ስራ የሚከፍል መሆኑንም ይናገራል፤
ቁ. 27 …የትዕቢተኛ ዓይን …“አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ።”
ሰዉ ሌሎችን ተመልክቶ በሚታዩ፣ አካላዊ ወይም ቁሳዊ በሆኑ ነገሮች የመመዘን ዝንባሌ አለዉ፤ ከመመዘኛ መስፈርቶቹ ጀምሮ ለትእቢት የተጋለጠ ሊሆን ይችላል፡፡እግዚአብሔር ግን ሳሙኤል ንጉስ ለመቀባት በእሴይ ቤት በነበረበት ጊዜ በ1ሳሙ.16: 7 ላይ “… ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው።” በማለት እግዚአብሔር የሳሙልን እይታ ያስተካከለ ሲሆን ከዚህ በተቃራኒም ሰዉ በተሳሳተ መስፈርት ሰዎችን በመመዘን አሳንሶ ወይም ራሱን አብልጦ በትቢት ሊመለከት ይችላል (ሆኖም በማንኛዉም መስፈርት ሰዉ ሌላዉን አሳንሶ በትዕቢት ሊመለከት አይገባዉም)፡፡ ስለዚህ ዳዊት (የትዕቢት ጀማሪ ከሆነዉ ከሰይጣን ፍጻሜም እንደምናየዉ) የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ በማለት ይናገራል፡፡
( ይቀጥላል...)

12/06/2020

ወገኖች የጌታ ሰላም ይብዛላችሁ!
የሚከተለዉን ክፍል እስከመጨረሻዉ እንድታነቡት በጌታ ፍቅር እጋብዛችኋለሁ

ባዩ ጥላሁን

ኃይልና ምህረቱን ያየ ሰዉ ይተማመን
(መዝሙር 18)
ዳዊት አቤቱ ጉልበቴ ሆይ እወድሃለሁ ብሎ የሚጀምረዉ በህይወቱ ያለፈባቸዉን የመከራ ጊዜያትና የእግዚኣብሔርን ማዳን በማስታወስ ነዉ፡፡ ሁሉ ካለፈ በኋላ ዳዊተ በተረጋጋ ሁኔታ ቁጭ ብሎ በገጠመዉ መከራ ላይ የእግዚብሔርን ደራሽነትና ምህረቱን ይዘምራል፡፡
መዝሙር 18ን በ5 ዋና ዋና ክፍሎች ከፍለን እንመለከተዋለን (ለዚህ ምልከታ)
ሀ. (ቁ. 4-6) ዳዊት መከራ በገጠመዉ ጊዜ ወደ እግዚኣብሔር የጮኸበትን የሚያሳይ ክፍል ነዉ፣

1ሳሙ. 30 ፡ 1-8
አማሌቃዊያን በጺቅላግ ላይ አደጋ ጥለዉ ወንዶችና ሴቶችን በማረኩ ጊዜ ምርኮ የተማረከባቸዉ የጺቅላግ ሰዎች ዳዊትን ሊወግሩት ተማከሩ፡፡
ዳዊት ተጨነቀ!
ሚስቶቹ ተማረኩበት
ህዝቡ ተማረከበት
ከተማዋ ተቃጠለች
የገዛ ህይወቱም ላይ አደጋ ተጋረጠበት (የጺቅላግ ሰዎችሊወግሩት ተማከሩ)
መፍትሔ፡ ዳዊት አብያታርን ኤፉዱን አቅርብልኝ አለ እግዚብሔርንም ጠየቀ፡፡
በክርስትና ህይወት ዉስጥ 3 አይነት ገጽታ አናያለን፣
በክርስቶስ የሚያምን ነገር ግን የማይተማመን (ክርስቶስ ያድናል ከማለት ያልዘለለ) በእያንዳነዱ የህይወቴ ክፍል እግዚብሔር ጣልቃ ገብቶ ይስራል ብሎ መተማመን የተሳነዉ ህይወት
መከራ ሲመጣ አቤቱ የሚል ሌላ ጊዜ ከእግዚብሔር ጋር ያልተጣበቀ ህይወት
የዳዊት አይነት ሕይወት፣ በሰላም ጊዜ የሚያመሰግን በመከራ ጊዜ ደግሞ አምላኩን በመተማመን የሚጠራ
ዳዊት ሦስተኛዉ አይነት ሰዉ ነበረና በመከራዉ ጊዜ በእምነት ወደ እግዚብሔር እንደጮኸ እንዲህ ብሎ ይናገራል፡-
(ቁ. 4-6) የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፤ የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ። በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።
*ዳዊት በተጨነቀ ጊዜ በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አበረታ፣ ኤፉዱን አምጡልኝ አለ፣ አምላኩን እግዚአብሔርን ጠራ እርሱም ዘንበል አለለት፡፡
ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን ባይመልስም እንኳን ሊመለክ የተገባዉ አምላክ ነዉ! እግዚአብሔር ግን ይህንንም ይሰጣል፤ ይመልሳልም፤ ከሚያስፈልገን ነገር አነዳች አያጎድልም፡፡
ለ. (ቁ. 7-19) እና (ቁ.30-45) እግዚአብሔር እንደ ዳዊት እምነት ምላሽ ሲሰጠዉ፤ ጠላቶቹን ሲያሳፍር የምንመለከትበት ነዉ
በ ቁ.30-45
ዳዊት በድንቅ የስንኝ ችሎታዉ የእግዚኣብሔርን ክብርና፣ ግርማ፣ ኃይሉንና አስፈሪነቱን ቁጭ ብሎ የተቀኘበትን እንመለከታለን፤
*እግዚኣብሔር ምህረቱ ላልተገለጠባቸዉ ሰዎች ምንኛ አስፈሪ ነዉ?!
*በልጁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዉስጥ ለማያያቸዉ ሰዎች ምን ያህል ቁጣዉ አስፈሪ ነዉ?!
*በኃጢአተኞች ላይ ቁጣዉ ይነድዳል፤ እኛ ግን ቁጣዉ በልጁ ላይ አልፎልን፤ በከበረ ደም ዋጋ ተገዝተን በምህረት አይን ይመለከተናልና ክብር ለወደደነን ለእግዚአብህር ይሁን!
ቁ.19 ወዶኛልና አዳነኝ …
ለተደረገልን ነገር ሁሉ መሰረቱ ምንድን ነዉ? የእግዚኣብሔር ፍቅር ነዉ!
ለፍቅሩ መሰረቱ ምንድን ነዉ? የሰዉ መልካምነት አይደለም፤ መጀመሪያዉ ከባሐህርዩ የሆነ የእግዚኣብሔር ፍቅር ሲሆን ቀጥሎም እግዚኣብሔር ለዚህ ፍቅር ምላሽ መስጠትን (በልጁ ማመንን) ከሰዎች ይፈልጋል፡፡
ሰዉ ይህንን ፍቅር በሚገፋበት ጊዜ ቁጣዉ መመለሻ አይኖረዉም፤ አማላጅም የለም፤ መሸ ማገልም የለም፤ መጨረሻዉ የዘላለም ጥፋት የሆናል!
( ይቀጥላል...)

30/09/2018

በኑሮ ትግልዎ ዉስጥ በየመሃሉ እነዚህን የተፈጥሮ ስርዓቶች አስተዉለዉ ያዉቃሉ? ጊዜንስ እንዴት ይረዱታል? የሳምንቱ ቀናት እየተመለሱ ይመጣሉ፤ ወራት በየአመቱ እየተመለሱ ይመጣሉ፡፡ ታዲያ ጊዜ እንደነዚህ ቀናትና ወራት እየተመለሰ ይመጣል? ወይስ ወደፊት ይገሰግሳል? ተመልሶ የሚመጣ ቢሆንማ ትላንት ብይ ሲጫወቱ እንደነበረ ወደፊትም በተጫወቱ ነበር፡፡ ምን ያህል ትዝታዎች አሉዎት? አያት ቅድመ አያትዎን ወይም እናት አባትዎን ያስታዉሳሉ? እጆችዎን ይዘዉ ወደ ትምህርት ቤት ሲወስዱዎት የነበሩትን ዛሬ በተራዎ ደግፈዉ በአልጋቸዉ ላይ ሲያስተኟቸዉ አይገርምዎትም? ለሁሉም ጊዜ አለዉ፤ የነሱ ተራ አልፎ የእርስዎ ተራ መጥቷል፤ ከዚያስ……?
ይህ ማንም ሊቀይረዉ የማይችል የተፈጥሮ ስርዓት ነዉና ሁላችንም ወደድንም ጠላንም በዚህ ዉስጥ እናልፋለን፡፡ ሰዉ ዘላለማዊ ፍጡር መሆኑንስ ያዉቃሉ? ያለ ጥርጥር! ታዲያ እነዚያ ተራቸዉን የጨረሱት በምን ሁኔታ ዉስጥ ይገኙ ይሆን ብለዉ ሳያስቡት አይቀሩም፤ እርስዎም ወደፊት እንደ አባቶችዎ መሆንዎ የማይካድ ሀቅ ነዉ፡፡ ዋናዉ ነገር ግን አጭሩን ይህንን የህይዎትዎን ክፍል ሲጨርሱ የሚጀምሩት ዘላለማዊ አኗኗር ሁኔታ የሚወሰነዉ በዚህ በአጭሩ ዘመንዎ በሚወስኑት ዉሳኔ መሆኑ ነዉ፡፡
ፈጣሪ ሰዉን በአምሳሉ የፈጠረዉ መሆኑን በቃሉ ለሰዉ ልጆች ገልጧል (ዘፍጥረት 1፡27)፡፡ ይሁን እንጂ ሰዉ የፈጣሪዉን ትዕዛዝ ባለመጠበቁ ሞትን በራሱ ላይ አመጣ (ዘፍጥረት 3፡19)፡፡ ፈጣሪዉ ግን በመልኩ የፈጠረዉን ሰዉ እጅግ ከመዉደዱ የተነሳ ከሞት በኋላ ካለዉ ዘላለማዊ ቅጣት የሚድንበትን መንገድ ራሱ በማዘጋጀት ተስፋ የሌለዉን ሰዉ እንደገና ተስፋ አዘጋጀለት፡፡ ነገር ግን ፈጣሪ ማንንም የማያስገድድ በመሆኑ ከዚህ ዘላለማዊ ቅጣት ለማምለጥ በዚች አጭር የስጋ ዘመንዎ የርስዎን ምርጫ የሚጠይቅ ይሆናል፡፡
ይህ የመዳን ተስፋ ምንድን ነዉ?
እንዴትስ መዳን ይቻላል?
ከኔ የሚጠበቀዉስ ምንድን ነዉ?
ብለዉ ከጠየቁ ፡- ሰዉ ሁሉ ከአባቱ ከአዳም በወረሰዉ ኃጢአትና ሁልጊዜም ኃጢአትን ለመስራት የሚፈልግ ተፈጥሮዉ የዘላለም ሞት ወይም የገሃነም ቅጣት እንደሚገባዉ እግዚአብሔር በቃሉ ተናግሯል (ሮሜ 3፡23 ፣ 6፡23)፡፡
ታዲያ የአዳም ልጅ ያልሆነ ማን ነዉ? በሁላችንም ዉስጥ ደካማና ኃጢአትን የሚወድ ተፈጥሮ አለ፡፡ በዚህም ሁል ጊዜ ተስፋ ልንቆርጥና ልንተክዝ እንችል ይሆናል፡፡
እግዚአብሔር ያዘጋጀልን የመዳን መንገድና ተስፋ
የፍቅር አምላክ የሆነዉ እግዚአብሔር ግን ይህ ቅጣት በሰዉ ላይ እንደይደርስ ልጁን ኢይሱስ ክርስቶስን ላከልን፡፡ ይህም በዮሐንስ ወንጌል 3፡16-17 እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡-
"በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረዉ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡፡ አለም በልጁ አንዲድን ነዉ እንጂ በአለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ አለም አልላከዉምና፡፡ "
ሰዉ በኃጢአት ምክንያት ከሚመጣበት ኩነኔ ለመዳን ብዙ ሊጨነቅ፣ የተለያዩ መንገዶችን ሊፈልግ ይችላል፡፡ እግዚአብሄር ግን በነጻ በጸጋዉ የሰጠዉ ከዚህ ኩነኔ የመዳኛ ብቸኛና አስተማማኝ መንገድ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በዮሐንስ ወንጌል 3፡18 እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡-
"በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል፡፡" በማለት ሰዉን ሁሉ በሁለት ክፍል መድቦታል፡-
• በክርስቶስ የሚያምን የዘላለም ቅጣት(ፍርድ) የማያገኘዉ ሲሆን
• በክርስቶስ የማያምን ሁሉ አሁኑኑ የተፈረደበት መሆኑን የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል፡፡
ይህም መዳን (ጽድቅ) በመልካም ስራችን ወይም በጥረታችን የምናገኘዉ ሳይሆን እግዚአብሔር ስለወደደን እንዳንጠፋ በጸጋዉ በነጻ የሰጠን ስጦታ ነዉ፡፡ ይህም በኤፌሶን 2፡8-9 እንደዚህ ተብሎ ተጽፏል፡-
"ፀጋዉ በእምነት አድኗችኋልና ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነዉ እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም፡፡" ይላል፡፡ በሮሜ 4፡4-5 ላይ ደግሞ፡-
"ለሚሰራ ደመወዝ እንደ እዳ ነዉ እንጂ እንደ ጸጋ አይቆጠርለትም፣ ነገር ግን ለማይሰራ ኃጢአተኛዉንም በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰዉ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል፡፡"
በማለት ጽድቅ በክርስቶስ በማመን ብቻ የሚገኝ መሆኑን ይነግረናል፡፡
ስለዚህ መዳን በኃጢአት ምክነያት ከመጣብን አስፈሪ ዘላለማዊ የገሀነም ቅጣት ሊያድነን ከድንግል ማርያም ተወልዶ ሰዉ ሆኖ በመጣዉ፣ እኛ በኃጢአታችን ምክነያት መሞት ሲገባን እርሱ ግን በእኛ ፈንታ በመስቀል ተሰቅሎ በሞተልንና ሞትን ድል አድርጎ በተነሳዉ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ እንጂ በሌላ እንደሌለ በሐዋርያት ሥራ 4፡12 ላይ እንደዚህ ተብሎ ተጽፏል፡-
"መዳንም በሌላ በማንም የለም፣ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና፡፡"
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዮሐንስ ወንጌል 14፡6 እንደዚህ ብሎ ተናግሯል፡-
"እኔ መንገድና እዉነት ሕይወትም ነኝ፣ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም፡፡" በማለት ብቸኛዉ የጽድቅ መንገድ እርሱ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ኃጢአታችን በዝቶብን ተስፋ ለቆረጥን ደግሞ፡-
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡"
በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ 11፡28 ለኃጢአተኞች ሁሉ ጥሪ አድርጓል፡፡
ታዲያ እርስዎስ የህንን ታላቅ ግብዣ ይቀበላሉ? ከኃጢአት ሸክምና ከዘላለም ሞት እንዲድኑ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶልዎታል፡፡
ጥሪዉን ከተቀበሉ ይህንን ጸሎት ይጸልዩ ፡-
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ ስለኔ ኃጢአትም በመስቀል ላይ እንደ ሞትክልኝ አምናለሁ! ጌታ ሆይ ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ! ቀሪ ዘመኔን ሁሉ ልከተልህ ወስኛለሁ!
አሜን!

እግዚአብሔር ይባርካችሁ
ባዩ ጥላሁን

16/09/2018

9 If you declare with your mouth, “Jesus is Lord,” and believe in your heart that God raised him from the dead, you will be saved. 10 For it is with your heart that you believe and are justified, and it is with your mouth that you profess your faith and are saved.

Romans 10: 9 -10

17/02/2016

the bible says, all man is sinner...and the result of sin is death...means eternal death.....so how dare man can ignore it ?......finding a way ........but God himself find away since man can't do it ..he condemn his only begotten son "'JESUS" to pay it all...shed his perfect blood for the siner to be set free.....ohhhh!!!....but how the sinner man escape from eternal condemination ignoring this perfect blood shade for him?................the bible is the word of God ..the truth.......oh Lord save man you created in Your own image

05/12/2015
26/11/2015

a must watch

Address

AGIP
Debre Berhan
CHRIST

Telephone

0921137323

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BIBLE truth.org posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share