በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤ/ያን የቡርሳ ከተማ አጥብያ ሕይወት ብርሃን ቤ/ያን

  • Home
  • Ethiopia
  • Bursa
  • በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤ/ያን የቡርሳ ከተማ አጥብያ ሕይወት ብርሃን ቤ/ያን

በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤ/ያን የቡርሳ ከተማ አጥብያ ሕይወት ብርሃን ቤ/ያን ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።
ሐዋርያት ሥራ 4:12
የፀሎት መስመር +251913819672

✨ ልዩ የአምልኮ እና የምስጋና ምሽት ✨"ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን፤ ለምድኃኔዓለማችን አምላክ እልል እንበል፤ በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ፤ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል!"— መዝሙረ ዳ...
12/08/2026

✨ ልዩ የአምልኮ እና የምስጋና ምሽት ✨

"ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን፤ ለምድኃኔዓለማችን አምላክ እልል እንበል፤ በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ፤ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል!"

— መዝሙረ ዳዊት 95:1-2 📖
የጌታን ታላቅነት በህብረት የምናከብርበት፣ በዝማሬና በምስጋና በፊቱ የምንፈነጥዝበት ልዩ የአምልኮ ምሽት ተዘጋጅቶልዎታል! እርሱን ለማመስገንና መንፈሳዊ እድሳትን ለመቀበል ።
📅 ቀን፦ ነሐሴ 7
⏰ ሰዓት፦ ሐሙስ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ ቡርሳ ከተማ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን (ከአስተዳደር ፊት ለፊት)
👥 ወዳጅ፣ ዘመድ እና ጓደኞችዎን ይዘው ይምጡ — በበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ!
#ምስጋና #አምልኮ

2 ቀን ብቻ ቀረው ልዩ የአምልኮ ምሽት አይቀርም ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም ልዩ የአምልኮ ምሽት አዘጋጅተናል አድራሻ :- በቡርሳ ከተማ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ሀሙስ 10:30 ጀምሮ
11/08/2026

2 ቀን ብቻ ቀረው ልዩ የአምልኮ ምሽት አይቀርም

ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም ልዩ የአምልኮ ምሽት አዘጋጅተናል አድራሻ :-
በቡርሳ ከተማ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ሀሙስ 10:30 ጀምሮ

5 ቀን ብቻ ቀረው ልዩ የአምልኮ ምሽት አይቀርም
08/08/2026

5 ቀን ብቻ ቀረው ልዩ የአምልኮ ምሽት አይቀርም

ልዩ የአምልኮ ምሽትነሐሴ 7/2018 ዓ.ም ልዩ የአምልኮ ምሽት አዘጋጅተናል አድራሻ :- በቡርሳ ከተማ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ሀሙስ 10:30 ጀምሮ
07/08/2026

ልዩ የአምልኮ ምሽት
ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም ልዩ የአምልኮ ምሽት አዘጋጅተናል አድራሻ :-
በቡርሳ ከተማ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ሀሙስ 10:30 ጀምሮ

የኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን 81ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ በሐዋሳ ማካሄድ ጀመረችየኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን 81ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ የምክር ቤቱ አ...
31/07/2026

የኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን 81ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ በሐዋሳ ማካሄድ ጀመረች
የኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን 81ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ከመላው አገሪቱ የተወጣጡ የምክር ቤቱ አባላት በተገኙበት በሐዋሳ ከተማ በደመቀ ሁኔታ መካሄድ ጀመረ።
በጉባኤው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ምክትል ፕሬዝዳንት ፓስተር ታሪኩ ብርሀኑ ፣የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ፖሰተር ዶክተር ጌትነት ለማ ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የተጋበዙ ከፍተኛ የቤተክርስቲያን መሪዎች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
በመቀጠል የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት እና የካውንስሉ ምክትል ፕሬዝዳንት ፓስተር ታሪኩ ብርሀኑ ለጉባኤው ሰላምታ ሰጥተዋል፡፡ ሀዋሪያት ስራ 1፡8 የጉባኤው መሪ ጥቅስ መሆኑን ተናግረው በእግዚአብሔር መንፈስ እየተመራን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
ፓስተር ዶክተር ጌትነት ለማ በንግግራቸው ቤተክርስቲያኒቱ እያደረገች ስላለችው ትላልቅ የወንጌል ስራ ምስጋና አቅርበው፣ በተለይ አብያተክርስቲናት አንድ መሆን እና በአንድነት ለወንጌል መቆም ይገባል፡፡ በማለት አጽንዎት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በመቀጠልም ቤተክርስቲያን ዋናው ተልእኮዋ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ መስበክ ስለሆነ ልዩ ትኩረት በወንጌል ስርጭት ላይ ማድረግ እና ደቀ መዛሙርት ማድረግ ላይ ማተኮር አለብን ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል
የወንጌል አማኞች ድምፅ

• Website: bursa01hbc.com
የቤተሰባችን አባል ለመሆን Follow, Subscribe, Like እና Share በማድረግ አብረውን ይሁኑ!

 🙏በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ፔንተኮስታል ቲዎሎጅካል ኮለጅ ለሦስት ዓመት ተኩል በድግር መርሐ ግብር በበንሳ ዳዬና በቡርሳ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዳዬ ከተማ በሰላም አስመር...
03/07/2026

🙏
በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ፔንተኮስታል ቲዎሎጅካል ኮለጅ ለሦስት ዓመት ተኩል በድግር መርሐ ግብር በበንሳ ዳዬና በቡርሳ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዳዬ ከተማ በሰላም አስመርቆል።
አስጀምሮ ላስጨረሰን ለፈጣርያችን ክብር ምስጋና ይድረሰው ።

29/04/2026
 #የቤተክርስትያን  #መሪዎችና  #አገልጋዮች  #ኮንፎረንስ:በቡርሳ ከተማ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያን ህብረት ከፐርፐዝፉል ጎስፕል ሚኒስትር ጋር በመተባበር በተዘጋጀ የመሪዎች ስልጠና ጌታ ...
29/04/2026

#የቤተክርስትያን #መሪዎችና #አገልጋዮች #ኮንፎረንስ:
በቡርሳ ከተማ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያን ህብረት ከፐርፐዝፉል ጎስፕል ሚኒስትር ጋር በመተባበር በተዘጋጀ የመሪዎች ስልጠና ጌታ ድንቅ ሥራ ሰርቶአል።
ክብር ለእርሱ ይሁን!!!
#ለጌታ ለዘላለም ክብር ይሁን!
#ጌታን አመስግኑልን:

ርዕስ:- እርሱ ለምን ቈሰለ? 👉   የመልዕክት አቅራቢ   #መጋቢ ዘዉደ ደመሳ04/08/2018ዓ.ም‎   የቃሉ ክፍል ‎➣ ኢሳ  53:5  ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላ...
12/04/2026

ርዕስ:- እርሱ ለምን ቈሰለ?
👉 የመልዕክት አቅራቢ #መጋቢ ዘዉደ ደመሳ
04/08/2018ዓ.ም
‎ የቃሉ ክፍል
‎➣ ኢሳ 53:5 ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
‎➣ ሮሜ 4:24-25 ነገር ግን እግዚአብሔር ጽድቅ አድርጎ ለሚቈጥርልን፣ ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው በእርሱ ለምናምን ለእኛም ጭምር ነው። እርሱ ስለ ኀጢአታችን እንዲሞት ዐልፎ ተሰጠ፤ እኛን ጻድቅ አድርጎ ለማቅረብም ከሞት ተነሣ።
‎➣ ኤፈ 1:7በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገ ቤዛነት፣ የኀጢአትን ይቅርታ አገኘን፤
‎ 👉ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የቆሰለው
‎1.መተላለፋችንን ይቅር ልለን
‎2.በእርሱ ቊስል እኛ እንድንፈወስ
‎3.እኛን ለማስጽደቅ ነው
‎4.ለእኛ ህይወትን ልሰጠን

የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች የ1.5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ​አርባ ምንጭ፦ መጋቢት 29 / 2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ...
07/04/2026

የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች የ1.5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
​አርባ ምንጭ፦ መጋቢት 29 / 2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሙኒኬሽን)
​በጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ይውል ዘንድ የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ከልማት ድርጅቷ ጋር በመተባበር የ1.5 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደርጓል ።
​ድጋፉን ያስረከቡት የኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች ካውንስል ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ታሪኩ ብርሃኑ ና የቤተክርስቲያኗ የልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ተመስገን ግዛው ናቸው። መጋቢዎቹ በአደጋው የበርካታ ዜጎች ሕይወት በመጥፋቱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል።
​አክለውም ቤተክርስቲያኗ ያደረገችው ይህ ድጋፍ የመጀመሪያው እንጂ የመጨረሻው እንዳልሆነ ገልጸው፣ በቀጣይም የዞኑ መንግስት ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚያደርገው ጥረት ቤተክርስቲያኗ ሁልጊዜም ከጎናቸው መሆኗን አረጋግጠዋል።
​ድጋፉን የተረከቡት የጋሞ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ የአደጋው መጠን ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፣ መንግስት ተጎጂዎችን ለመርዳት በሚያደርገው ሰፊ ጥረት የሃይማኖት ተቋማትና አጋር ድርጅቶች እያሳዩት ያለው አጋርነት እጅግ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።
​አቶ ገዛኸኝ በአሁኑ ወቅት ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ​ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ማቋቋም፤​ጊዜያዊ መጠለያዎችን መገንባት፣​ወላጆቻቸውን ያጡ ሕፃናትን መርዳት፣ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ መሆኑን ተናግረዋ።
​እነዚህን ተግባራት በስኬት ለማጠናቀቅ የሁሉም አካላት ድጋፍና ትብብር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም ቤተክርስቲያኗ ላበረከተችው ወገናዊ ድጋፍ በዞኑ አስተዳደርና በተጎጂዎች ስም ምስጋና አቅርበዋል።

Address

Bursa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤ/ያን የቡርሳ ከተማ አጥብያ ሕይወት ብርሃን ቤ/ያን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share