Boditi Full Gospel Believers' Church የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ቦዲቲ አጥብያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Boditi
  • Boditi Full Gospel Believers' Church የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ቦዲቲ አጥብያ

Boditi Full Gospel Believers' Church የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ቦዲቲ አጥብያ Welcome to the official page of
The Ethiopian Full Gospel Believers' Church Boditi Local Ch

ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የቦዲቲ ከተማ ወጣቶች እና ምዕመናን በወላይታና አከባቢ አልፎ በአለም ዙሪያ ያላችሁ ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንምከኢየሱስ ክርስቶስ ጸ...
17/04/2024

ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የቦዲቲ ከተማ ወጣቶች እና ምዕመናን በወላይታና አከባቢ አልፎ በአለም ዙሪያ ያላችሁ ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም
ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን ። የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ቦዲቲ አጥብያ አዲሱን የቤተክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ ስራ ከጀመረች ወራቶችን አስቆጥራለች።
አሁን ላይ የመጀመሪያ ዙር ግንባታ አጠናቃ ሁለተኛ ዙር ግንባታ ስራ ነገ ማለትም በቀን 10/08/2016 ትጀምራለች ....
ቅዱሳን በዚህ መልካም ስራ የድርሻችሁን እንድታበረክቱ እንደ ሁሉ ጊዚያችን በእግዚአብሔር ፍቅር እንጠይቃለን።
ከነገ ጀምሮ በሚሰራው ስራ ከቦዲቲ እናት ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ወጣቶች ጋር በመሆን መታችሁ በመሥራት የበረከቱ ተቋዳሽ እንድትሆኑ በጌታ ፍቅር እናሳስባችኋለን!!
በገንዘባችሁ ለመደገፍ ለምትፈልጉ የባንክ አካውንት ቁጥራችን...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000564308114

ብርሃን ባንክ
1011218251350

ኦሮሚያ ባንክ
1055200074664

አዋሽ ባንክ
013521194882600

አቢሲኒያ ባንክ
1351447889

ለበለጠ መረጃ ፦
ፖስተር ተፈሪ ሁኩሞ
የቤ/ያኒቱ ሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ስልክ-09-13-83-65-88
ኮማንደር ታደሰ ተፈራ
የቤ/ያኒቱ ሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ
ስልክ-09-16-83-29_09
ከዚ ቀጥሎም በምናከናውናቸው ተግባራት ትጋታችሁ አብሮነታችሁ ቀድሞ ከነበረው ይበልጥ እንዲሆን በእግዚአብሔር ፍቅር እናሳስባችኋለሁ።
እግዚአብሔር አምላክ እንደ ባለጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል ያትረፈርፍላችኋል።
አሜን!

05/03/2024

የቦዲቲ ከተማ እናት ሙሉ ወንጌል ህንፃ ግንባታ እንዲህ ባለ መልኩ ተጠናክሮ እየተሰራ ይገኛል::

ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የቦዲቲ ከተማ ወጣቶች እና ምዕመናን በወላይታና አከባቢ አልፎ በአለም ዙሪያ ያላችሁ ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንምከኢየሱስ ክርስቶስ ጸ...
28/02/2024

ሰላም የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የቦዲቲ ከተማ ወጣቶች እና ምዕመናን በወላይታና አከባቢ አልፎ በአለም ዙሪያ ያላችሁ ቅዱሳን ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም
ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን ። የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ቦዲቲ አጥብያ አዲሱን የቤተክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ ስራ ከጀመረች ወራቶችን አስቆጥራለች።
አሁን ላይ የግራደ ቢም አርማታ ሙለት (grade beam concrete work) ስራ ነገ ማለትም በቀን 21/06/2016 ትጀምራለች ....
ቅዱሳን በዚህ መልካም ስራ የድርሻችሁን እንድታበረክቱ እንደ ሁሉ ጊዚያችን በእግዚአብሔር ፍቅር እንጠይቃለን።
ከነገ ጀምሮ በሚሰራው ስራ ከቦዲቲ እናት ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ወጣቶች ጋር በመሆን መታችሁ በመሥራት የበረከቱ ተቋዳሽ እንድትሆኑ በጌታ ፍቅር እናሳስባችኋለን!!
በገንዘባችሁ ለመደገፍ ለምትፈልጉ የባንክ አካውንት ቁጥራችን...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000564308114

ብርሃን ባንክ
1011218251350

ኦሮሚያ ባንክ
1055200074664

አዋሽ ባንክ
013521194882600

አቢሲኒያ ባንክ
1351447889

ለበለጠ መረጃ ፦
ፖስተር ሻምበል አየለ
የቤ/ያኒቱ መሪ እረኛ እና ሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ
ስልክ-09-13-25-17-14
ኮማንደር ታደሰ ተፈራ
የቤ/ያኒቱ ሕንፃ አሰሪ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ
ስልክ-09-16-83-29-07
ከዚ ቀጥሎም በምናከናውናቸው ተግባራት ትጋታችሁ አብሮነታችሁ ቀድሞ ከነበረው ይበልጥ እንዲሆን በእግዚአብሔር ፍቅር እናሳስባችኋለሁ።
እግዚአብሔር አምላክ እንደ ባለጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል ያትረፈርፍላችኋል።
አሜን!

በማድረግ መልዕክቱን ለሁሉም እድታደርሱ ይሁን 🙏

02/02/2024

በወንድማችን በመጋቢ ተሾመ በቀለ( Teshome Bekele )

17 የብሉይ ኪዳን የነቢያት መጽሐፍት አጭር ጥቅልል ዳሰሳ። ከእነዚህም የነቢያት መጽሐፍት መካከል

5ቱ ታላቅ ነቢያት ተብሎ ልመደቡ የምችሉ ሲሆን...፤
ታላላቅ የተባሉት በጹሑፋቸው ይዘት ነው።

1. ትንቢተ ኢሳይያስ፡- የኢሳይያስ ትንቢቶች በእስራኤልና በሌሎች ብሔራት ላይ የሚነገሩ የፍርድ መልእክቶችን ያጠቃላል ፤ ነገር ግን ስለሚመጣው መሲሕና ስለ ወደፊቱ ተሃድሶ የሚናገሩትን ተስፋዎችም ይዘዋል።

2. ትንቢተ ኤርምያስ፡ የኤርምያስ ትንቢታዊ አገልግሎት የይሁዳን ሕዝብ ወደ ንስሐ በመጥራትና ስለሚመጣው የባቢሎን ወረራ በማስጠንቀቅ ላይ ያተኮረ ነበር። በተጨማሪም አምላክ ከሕዝቡ ጋር ስለሚገባው አዲስ ቃል ኪዳን ተናግሯል።

3. ሰቆቃው ኤርምያስ፡ ሰቆቃው ሰቆቃው ኤርምያስ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በኢየሩሳሌም መጥፋት ምክንያት የሐዘንና የሐዘን መግለጫዎችን ይዟል።

4. ትንቢተ ሕዝቅኤል፡- የሕዝቅኤል ትንቢቶች ስለ አምላክ ክብር የተመለከቱ ራእይዎች፣ በእስራኤልና በሌሎች ብሔራት ላይ የተነገሩት የፍርድ መልእክቶች፣ የመልሶ ማቋቋምና አዲስ ቃል ኪዳን የሚገቡበት ተስፋዎች ይገኙበታል።

5. ትንቢተ ዳንኤል፡- የዳንኤል መጽሐፍ ስለወደፊቱ ግዛቶች እና ስለ "የሰው ልጅ" መምጣት የተነገሩትን ትንቢቶች ጨምሮ ታሪካዊ ትረካዎችን እና የምጽዓት ራእዮችን ቅልቅል ይዟል።



ታናናሽ የተባሉት በጹሑፋቸው ይዘት ነው።

1. ትንቢተ ሆሴዕ፡- የሆሴዕ የትንቢት አገልግሎት አምላክ ከእስራኤል ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሳየት የጋብቻ ዝምድና ዘይቤን በመጠቀም አምላክ ታማኝ ላልሆኑት ሕዝቦቹ ባለው አካሄድ በፍቅር ጭብጥ ላይ ያተኮረ ነበር።

2. ትንቢተ ኢዩኤል፡- ኢዩኤል ስለ አውዳሚ የአንበጣ ቸነፈር የእግዚአብሔርን ፍርድ ለማስጠንቀቅ ተንብዮአል፣ነገር ግን የተሃድሶ እና የመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ ተስፋን ሰጥቷል።

3. ትንቢተ አሞጽ፡- አሞጽ የእስራኤልን ማኅበራዊ ኢፍትሐዊነትና የሥነ ምግባር ውድቀት አውግዟል፤ ንስሐ እንዲገባ ጥሪ አቅርቧል እንዲሁም የፍትህና የጽድቅን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥቷል።

4. ትንቢተ አብድዩ፡ የአብድዩ አጭር መጽሐፍ በኤዶምያስ ሕዝብ ላይ በእስራኤል ላይ በፈጸመው በደል ፍርዱን ያውጃል፣ነገር ግን የእግዚአብሔርን ሕዝብ የመጨረሻውን ተሃድሶ ይናገራል።

5. ትንቢተ ዮናስ፡- ዮናስ ወደ ነነዌ ከተማ የተላከው እግዚአብሔር ለአሕዛብ ሁሉ ያለውን ርኅራኄና ለፈቃዱ መታዘዝ አስፈላጊ መሆኑን በማሳየት ሕዝቡን ወደ ንስሐ እንዲጠራ ነው።

6. ትንቢተ ሚክያስ፡ ሚክያስ ስለ ማሕበራዊ ኢፍትሃዊነት እና የጣዖት አምልኮ ጉዳዮች ተናግሯል፣ በተጨማሪም ስለ መሲሑ በቤተልሔም መወለድን ጨምሮ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ተስፋ ተናግሯል።

7. ትንቢተ ናሆም፡ ናሆም በአሦራውያን ከተማ በነነዌ ላይ ትንቢት ተናገረ፤ ጥፋቷንም በክፋትዋና በዓመፅዋ ምክንያት እየመጣች መሆኑን ተናግሯል።

8. ትንቢተ ዕንባቆም፡ ዕንባቆም ስለ ክፋትና የፍትሕ መጓደል ችግር እግዚአብሔርን ጠየቀ፣ በመጨረሻም በእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና ፍትሐዊ ተስፋ ላይ።

9. ትንቢተ ሶፎንያስ፡- ሶፎንያስ ስለ መጪው “የእግዚአብሔር ቀን” የፍርድ ጊዜ እንደሆነ አስጠንቅቋል፣ ነገር ግን ለቀሩት የእስራኤል ቀሪዎች ወደፊት ስለሚታደስ እና በረከት ተናግሯል።

10. ትንቢተ ሐጌ፡- ሐጌ ከግዞት በኋላ የነበሩትን ማኅበረሰቦች በኢየሩሳሌም የሚገኘውን ቤተ መቅደስ እንደገና እንዲገነቡ አበረታቷቸዋል፤ ይህም እግዚአብሔርን ማስቀደምና መንግሥቱን መፈለግ አስፈላጊ መሆኑን በማጉላት ነበር።

11. ትንቢተ ዘካርያስ፡- የዘካርያስ ትንቢቶች የኢየሩሳሌምን መልሶ መቋቋም በተመለከተ የሚያበረታቱ መልእክቶች እንዲሁም ስለሚመጣው ንጉሥና እረኛ የሚናገሩትን መሲሐዊ ትንቢቶችን ያካትታሉ።

12. ትንቢተ ሚልክያስ፡- ሚልክያስ በሕዝቡ መካከል ያለውን መንፈሳዊ ግዴለሽነትና ታማኝነት የጎደለው ድርጊት በመግለጽ ለአምላክ እውነተኛ አምልኮና ታማኝነት እንዲኖራቸው ጠራቸው።

ኢየሱስ ያድናል። ተባረኩ።

19/01/2024

ኢየሱስ ጌታ ነው!!
1 ቆሮ 12:3

በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የቦዲቲ እናት አጥቢ አዘጋጅነት ከጥር 3 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ኮንፈረንስ በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ ቦዲቲ ፤ ጥር ፤...
15/01/2024

በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የቦዲቲ እናት አጥቢ አዘጋጅነት ከጥር 3 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ኮንፈረንስ በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ

ቦዲቲ ፤ ጥር ፤ 5/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የቦዲቲ እናት አጥቢ አዘጋጅነት ከጥር 3 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ኮንፈረንስ በሰላም መጠናቀቁን ቤተክርስቲያኒቷ አስታውቃለች።

አቶ በረከት በላይነህ የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እንዲሁም የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ በማጠቃለያው ፕሮግራም ላይ በእንግድነት ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ቤተክርስቲያኗ በዚህ በታላቅ ኮንፈረንስ ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የከተማው መንግስት አካል ተገኝቶ ንግግር እንዲያደርግ በመጋበዙ መደሰታቸውን ገልጸዋል ።

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የቦዲቲ እናት አጥቢ እስከዛሬ በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች ህብረተሰቡን እየደገፈች እንዳለች በመጥቀስ በቀጣይም ይህንን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል እምነታቸውን ተናግረዋል።

የከተማው አስተዳደርም በቀጣይ ግዜያት አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በማቀራረብና ብርቱ የሆነ ቅንጅት በመፍጠር በጋራ እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

Credit : Asres Petros 😍❤

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የቦዲቲ እናት አጥቢያ አዘጋጅነት ከጥር 3 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ኮንፈረንስ በሰላም ተጠናቀቀ።
14/01/2024

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የቦዲቲ እናት አጥቢያ አዘጋጅነት ከጥር 3 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው መንፈሳዊ ኮንፈረንስ በሰላም ተጠናቀቀ።

ታገኙ ዘንድ ሩጡበሚል ርዕስ የተዘጋጀ ታላቅ መንፈሳዊ ሩጫ በሰላም ተጠናቋል ቦዲቲ ፤ ጥር ፤ 03/2016 ዓ.ም  በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር  ከጥር 3 እሰከ 5  በኢትዮጵያ ሙሉ...
12/01/2024

ታገኙ ዘንድ ሩጡ
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ታላቅ መንፈሳዊ ሩጫ በሰላም ተጠናቋል

ቦዲቲ ፤ ጥር ፤ 03/2016 ዓ.ም በወላይታ ዞን በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ከጥር 3 እሰከ 5 በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን በቦዲቲ እናት አጥቢያ የሚካሄደውን መንፈሳዊ ኮንፍራንስ ምከንያት በማድረግ "ታገኙ ዘንድ ሩጡ" በሚል መሪ ቃል ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ መርሀግብር ተደርጓል።

በሩጫ መርሃግብሩ የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪ አካላት እንዲሁም ከተለያዩ የአለማችን አከባቢዎች የመጡ እንግዶችና የቤተክርስቲያኗ ምዕመናን ተሳትፈዋል።

የዛሬው ታላቁ ሩጫ ዋና አላማ በቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በሚሰሩ በመልካም አስተዳደር እና በልማት ጉዳዮች ላይ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን የቦዲቲ አጥቢያ በአጋርነት እንደምትሰራ ማሳያ እንዲሆን ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል ።

ታገኙ ዘንድ ሩጡበሚል ርዕስ የተዘጋጀ ታላቅ መንፈሳዊ ሩጫ በሰላም ተጠናቋል እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏
12/01/2024

ታገኙ ዘንድ ሩጡ
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ታላቅ መንፈሳዊ ሩጫ በሰላም ተጠናቋል
እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏

እንግዶቻችን በሰላም ገብተዋል 🙏እግዚአብሔር ይመስገን
10/01/2024

እንግዶቻችን በሰላም ገብተዋል 🙏እግዚአብሔር ይመስገን

09/01/2024
 የሩጫውን ትሸርት የምትፈልጉ በቦዲቲ እናት ሙሉ ወንጌል ቸርች ግቢ ማግኘት ትችላላችሁ!!! #ወይም -0922489015-0936664741-0913360343-0916405511-0903742134-0...
06/01/2024


የሩጫውን ትሸርት የምትፈልጉ በቦዲቲ እናት ሙሉ ወንጌል ቸርች ግቢ ማግኘት ትችላላችሁ!!!
#ወይም
-0922489015
-0936664741
-0913360343
-0916405511
-0903742134
-0938981963

በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ይደዉል ☎️

Address

Boditi

Telephone

+251465590161

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Boditi Full Gospel Believers' Church የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ቦዲቲ አጥብያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share