Ethiopian Orthodox Reformation Church

Ethiopian Orthodox Reformation Church Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Orthodox Reformation Church, Religious organisation, Boditi.

30/04/2025
ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ያውቃሉ?✝️የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ66 መጽሐፍት1,189 ምዕራፎች3...
11/04/2025

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ያውቃሉ?✝️

የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
66 መጽሐፍት
1,189 ምዕራፎች
31,173 አንቀፆች
810,697 ቃላት
3,566,480 ፊደላት ይገኛሉ።

በጣም ረጅሙ መጽሐፍ- መዝሙረ ዳዊት ሲሆን
በጣም አጭሩ መጽሐፍ- ሶስተኛ ዮሐንስ
በጣም ረጅሙ ምዕራፍ- መዝሙረ ዳዊት 119
አጭሩ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት 117 ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ አማካይ ስፍራ መዝሙረ ዳዊት 118:8 ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ሰዎች መጠሪያ የሆነው ስም ዘካሪያስ ነው።

ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ስም "ዳዊት" ሲሆን 1008 ጊዜ ተጠቅሷል። በመቀጠልም ኢየሱስ 973 ጊዜ፤ ሙሴ 829 ጊዜ ተጠቅሰዋል።

ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እና የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ አስደናቂ መመሳሰል አላቸው።
ይኸውም፦
መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጽሐፍ ሲኖሩት ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ምዕራፎች አሉት።

የመጀመሪያው 39 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝብ ነው። እንደዚሁም የመጀመሪያው የትንቢተ ኢሳይያስ 39 ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝቦች ነው።

የመጨረሻው 27 የመጽሐፍት ቅዱስ መጻህፍት የሚያስተምሩት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ እንደዚሁም የመጨረሻዎቹ 27 የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ ክርስቶስ መምጣት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ተፅፎ ያለቀው በ1600 ዓመታት የጊዜ ልዩነት ውስጥ ሲሆን ይህም ከ1500 ዓመተ ዓለም እስከ 100 ዓመተ ምህረት ድረስ ያለውን ዘመን ያጠቃልላል።

መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21)

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 49 የምግብ ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ በተለይ "ጨው" 30 ጊዜ ተጠቅሷል።

ከቤት እንሰሳት መካከል ስሟ ያልተጠቀሰ እንሰሳ
"ድመት" ብቻ ናት።
ውሻ 14 ጊዜ ተጠቅሷል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ ሰዎች ሰባት ሲሆኑ
እነርሱም፦ 1. አቤሜሌክ 2. ሳምሶን 3. ሳዖል 4. የሳዖል ወታደር 5. አኪጦፌል 6. ዚምራ 7. ይሁዳ ናቸው።

በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ
ስለ ፀሎት 400 ጊዜ
ስለ እምነት 500 ጊዜ
ስለ ገንዘብና ሐብት ደግሞ 2,000 ጊዜ ተፅፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው ይለዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው በ 1388 ዓ.ም ነው።

መፅሐፍ ቅዱስ የሕይወት ቃል ✝️

25/07/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mihretu Chekole, Zesamika Ye Jr., Selam Bekele Ymam, Asrat Neny

ረጅም መሄድ ካሰብክ እነዚህን አትርሳ!!አላማ ላላቸው ሰዎች አራት ምክር አለኝ!!1ኛ ፀልይ ፀሎት ለአንድ አማኝ መሰረታዊ ነገር ነው የክርስትና ፈር ቀዳጅ የሆነው መስራች ኢየሱስ የፀሎት ሰው...
14/05/2024

ረጅም መሄድ ካሰብክ እነዚህን አትርሳ!!

አላማ ላላቸው ሰዎች አራት ምክር አለኝ!!

1ኛ ፀልይ

ፀሎት ለአንድ አማኝ መሰረታዊ ነገር ነው የክርስትና ፈር ቀዳጅ የሆነው መስራች ኢየሱስ የፀሎት ሰውም ጭምር ነበር ። ያልፀለየበት ቀን ያለ አይመስለኝም ደቀመዛሙርት ሲደክሙ እሱ ግን ከፀሎት አይለይም ሲለው አዳር ይፀልያል ። ጳውሎስ የፀሎት ሰው ነበር የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በፀሎት የታሸ ሕይወት ነበራቸው ። በምስጋና እና በሚፈጠሩ አሁናዊ ጉዳዮች ላይ ሁሉ ይፀልያሉ ። ፀሎት የማታያቸውን የጥላት ስራዎች ያመክናል !! ስለዚህ መፀለይ መሰረታዊ ነገር መሆኑን አውቀህ ፀልይ !!

2ኛ ቃሉን አንብብ

መፅሐፍ ቅዱስ እንድናነበው እና የእግዚአብሔር ዘላለማዊ አጀንዳ እና ፍቃድ ተረድተን ለእዚህ አጀንዳ ምላሽ ሰጥተን እንድንኖርበት የተሰጠ ሰነድ ነው ። ይህንን ካላነበብን ከእግዚአብሔር አጀንዳ ጋር ፍቃዱን ከመረዳት ጋር እንተላለፋለን ። ኢየሱስ በእዚህ ምድር እያለ እጅግ የሚያነብና በእዚህም የእውነት ተቃዋሚዎችን ፀጥ የሚያደርግ ብርቱ ነበር ጳውሎስ በሽምግልና ወራቱ እንኳ መፅሐፍ አምጣልኝ ብሎ ጢሞቲዮስን የሚጠይቅ አስገራሚ ሰው ነበር ።

"ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖስ፣ ጥቅልል መጻሕፍቱን በተለይም የብራና መጻሕፍቱን አምጣልኝ።"
2 ጢሞቴዎስ 4:13

3ኛ ተጠንቀቅ

በአገልግሎት በክርስትና ሕይወት ውስጥ ብዙ ሰዎች በታላቅ ክብር ጀምረዋል በትልቅ ተነሳሽነት ተስፈንጥረዋል ነገር ግን ሁሉም አልቀጠሉም የተወሰኑ ሰዎች ሩጫውን አቋርጠው ተመልሰዋል የቱ መሆን ትፈልጋለህ ? ከሚቀጥሉት ወይስ ከሚያቋርጡት ? ከሚቀጥሉት ካልከኝ ይሄንን አስብ!! ራስህን ከተንኮለኞች ጠብቅ በፀሎትህ ይሄንን አትርሳ ጌታ ከተኮለኞች እንዲጠብቅህ ፀልይ የዋህ እንጂ አጉል የዋህ አትሁን ከቻልክ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የመከረውን አንብብ !!

4ኛ ልብህ አይውረድ

በክርስትና አገልግሎትህ ውስጥ ብዙ ያልጠበካቸው ነገሮች ሊገጥሙህ ይችላሉ ። የከበረ ያልከው ወርዶ ጥሩ ያልከው ተቀይሮ ልታገኝ ትችላለህ ። ለመልካም ያደረከው ለክፉ ይተረጎማል ።ያቃኑልኛል ያልካቸው የሚያጣምሙ ሊሆኑ ይችላሉ ። ይሄ አዲስ አይደለም ጴጥሮስ ስለ ጳውሎስ ሲመሰክር እንዲህ ብሏል ።

"እርሱ ስለ እነዚህ ነገሮች በመልእክቶቹ ሁሉ ጽፎአል፤ በመልእክቶቹም ውስጥ በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግቱ ነገሮች አሉ። ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ፣ እነዚህንም ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።"
2 ጴጥሮስ 3:16

ስለዚህ በሰዎች ምክንያት ለአገልግሎት ልብህ አይውረድ መቀጠል ምትፈልግ ከሆነ ወደ ጎን ማየቱን ቀንስ እያደረክ ወደ እላይ እየተመለከትክ ቀጥል ...

ፀልይ አንበብ ተጠንቀቅ ልብህ አይውረድ ....

✍️ Girum Difek

Address

Boditi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Orthodox Reformation Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share