Bati Abune Teklehaymanot Church/ባቲ ጉህ ጽባህ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን/

  • Home
  • Ethiopia
  • Batia
  • Bati Abune Teklehaymanot Church/ባቲ ጉህ ጽባህ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን/

Bati Abune Teklehaymanot  Church/ባቲ ጉህ ጽባህ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን/ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bati Abune Teklehaymanot Church/ባቲ ጉህ ጽባህ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን/, Church, Batia.

15/08/2020
03/04/2020

የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ አስመልክቶ የቤተክርስቲያንዋ ምዕመን ሊኖረው የሚገባው አቋም በተመለከተ ውይይት እናድርግ። በተጨማሪም የሲኖዶሱን ውሳኔ ተከትሎ ቤተክርስቲያንዋ ዉስጥ ሆነው እራሳቸውን ከአለም ለይተዉ ቅዳሴውን ውዳሴውን ለማድረስ በቀረበው ጥሪ መሠረት አባታችንን እድሜዬ ቤተሠቤ ጤናዬ ስራዬ ሳይሉ ለዚህ አገልግሎት
እራሳቸውን ያቀረቡትን አባቶቻችንን መላከ ፀሀይ አባ ዩሀንስ ፈጠነን እና ቀሲስ በላይ ረዴን ፀጋቸውን ያብዛላቸው እድሜ ጤና ይስጥልን። በዚህ ወቅት ለነዚህ አባቶች የሚያስፈልጋቸውን ምግብ መጠጥ በማሟላትና ቤተሠባቸውም የሚያስፈልጋቸውን ለዚህ ክፉ ቀን መሻገሪያ የሚሆነዉን በማድረግ ከዚህ በረከት እንድንካፈል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

15/02/2020

ዉድ የእግዚአብሔር ቤተሠቦች ሠላም ናችሁ?
ከጥንት ጀምሮ ቤተክርስቲያናችን ተቋማዊ በሆነ እና ባልሆነ መንገድ ለብዙ ፈተናወች መዳረግዋና እነዚህ ፈተናወች ደግሞ የራሳቸውን ጠባሳ አሳርፈዉ ማለፋቸው የሚታወቅ ነው።ለማሣያ ይሆን ዘንድ ብዙ ቁጥር ያለው ምእመኗ እምነቱን እንዲቀይር ረጅም እድሜ ያላቸው እና በስነ ህንፃ ውበታቸው አለምን ሊያስደምሙ የሚችሉ ህንፃ ቤተክርስቲያኖች እንዲወድሙ የአለምን ጥያቄወች በሁሉም መስክ መልስ የሚሠጡ መፅሀፍት ተቃጥለው እንዲወድሙ ሁኗል።እነዚህ ሁሉ ፈተናወች ግን የቤተክርስቲያንዋን ምእመን በተወሠነ ደረጃ ከማንገዳገድ ባለፈ ምእመኗን ከቤተክርስቲያንዋ የመለየት አቅም ግን አልነበረዉም።እንደኔ ሀሣብ ይህ የሆነው በአባቶች ፀሎት ፈተናወችን መነሻ ለይቶ በማወቅ እና ለችግሮቹም ቁርጠኛ እና በመንፈስ ቅዱስ የተመራ ውሳኔን በማሳለፈቸው እንደሆነ አምናለዉ። ለማሣያም የቅርቡን እንኳ ብንመለከት የሠማእቱ አባታችንን የአቡነ ጴጥሮሥንነ ሰማእትነት አገርን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ከማድረግ ባለፈ ጣሊያን በቤተክርስቲያንዋ ላይ የጋረጠውን አደጋ በመገንዘብ ያስተላለፉት ዉሳኔ ነበር። ገር ግን የአሁኑ የቤተክርስቲያናችን ፈተና ከስከዛሬው ሁሉ የተለየ እና የራሡ መልክ እንዳለው አስባለዉ።የዚህ ቤተሠብ አባላት እሥኪ የወቅቱን የቤተክርስቲያናችንን ፈተና እና ይህ ፈተና እንዴት በዚህ ወቅት ሊገጥመን እንደቻለ እንድንወያይ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ

19/10/2019

ባለ ማዕተቧ ሐና ዮሐንስ !!💚💛❤️
በ2012 ዓም የለዛ አዋርድ ላይ ለሽልማት በቀረበች ጊዜ እንዲህ አለች👇👇👇👇♥
•••
የኢትዮጵያ አምላክ ልጅሽ ነውና ስለሀገራችን ስለ ቤተክርስቲያናችን ለልጅሽ አሳስቢ ሁሉ በእርሱ ነውና "
•••
ከእርሷ በፊት የነበረው የቅዳሴ ማርያም ደራሲ አባ ሕርያቆስ ደግሞ በቅዳሴ ማርያም ድርሰቱ እንዲህ አለ።
••••
“ ድንግል ሆይ ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ ዘንድ አሳስቢ። ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከእርሱ ጋራ ከሀገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ከአንቺ ጋራ መሰደዱን አሳስቢ። ድንግል ሆይ ርኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ አሳስቢ። ጥፋትን አይደለ ይቅርታን አሳስቢ። መዓትን አይደለ ምህረትን አሳስቢ። ለጻድቃን አይደለ ለኃጥአን አሳስቢ። ለንጹሐን አይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ። [ ቅዳሴ ማርያም ]

31/07/2019

የእመቤታችን ተዓምር በግብፅ
~~~~~~~°°°•••~~~~~~°°°•••~~
በካይሮ ከተማ 700 የመኖሪያ አፓርታማ በመስራት ላይ
የነበረው ኢንጅነር ሳያስበው ራሱን ስቶ ከመሬት ወደቀ ፡፡
ከቀናት ቡሀላ ከሰመመን ሲነቃ ICU ሆስፒታል ውስጥ
ተኝቶ እንዳለ እና በቲየመር ፡ በልብ እና በነርቭ በሺታ
እንደተያዘ ተነገረው፡፡
ኢንጅነሩም "እመቤቴ ይሄ እንዲሆን ፈቀድሺን ?"በማለት
በእየ እለቱ ማልቀሱን ቀጠለ ፡፡
አንድ ቀን ምሺት የብርሀን አምድ ወደ እሱ ቀረበውና
የብርሀን ፍንጣቂው ወደ ልቡ ውስጥ ሲገባ ታወቀው ፡፡
ይህን ብርሀን ያዩት የሆስፒታሉ አስታማሚወች ተገረሙ ፡፡
ከቀናት ቡላም የሆስፒታሉ ቦርድ ኢንጅነሩ ወደ አሜሪካ
ክሌቬላንድ ሆስፒታል ሄዶ እንዲታከም ወሰኑ ፡፡
አሜሪካ ክሌቬላንድ ሆስፒታል ገብቶ ከሀገሩ ከግብጽ ይዞ
የመጣውን የእመቤታችን ስዕል ላይ ጾሎቱን ጀመረ ፡፡"
እመቤቴ ምልጃሺ ካልደረሰልኝ በወጣትነቴ ሞት
እያዣቨቨብኝ ነው ፡፡የሰው ጥበብ ውስን ነው ፡፡ የልጅሺ
ምህረት ፡ማዳኑ ፍቅሩና የአንቺ ምልጃ ግን ስፍር ልኬትም
የለውምና ረደትነትሺ ያሻኛል ፡፡" እያለ በበሺተኛ ጉልበቱ
ተንበርክኮ ይለምን ፡ ያነባም ጀመር፡፡
አንድ ምሺት ላይም እየጸለየ እያለ ምኝታ ክፍሉ በብርሀን
ተሞላ ፡፡" አይዞህ ልጄ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ ፡፡" የሚል
ድምጽ ሰማ ፡፡ቀና ሲልም በስእሉ የሚያውቃት እመቤታችን
ናት ፡፡ እመቤታችንም ባረከችው ፡፡ ክፍሉ በመልካም
መዐዛ ተሞላ ፡፡
በማግስቱ በቀጠሮው መሰረት ኦፕራሲዮን ሊደረግ
የቅድመ ኦፕራሲዮን ምርመራ ቢየደርጉ ምንም በሺታ
አጡበት ፡፡ አሜሪካ አዲስ የህክምና ታሪክ ገጠማት ፡፡
እንዴት ፍጹም ጤነኛ እንደሆነ ጠየቁት ፡፡ ኢንጅነሩም
በእመቤታችን እንደተፈወሰ አስረዳቸው ፡፡ሆስፒታሉም ታሞ
የመጣ ነገር ግን በታምር ያለ ህክምና የተፈወሰ በሚል
ማስረጃ ሰጥተውት ወደ ሀገሩ ተመለሰ ፡፡ ይህ ሰው
በካይሮ ከተማ በጤና እና በበረከት ስራውን በመስራት
ላይ ይገኛል ፡፡
የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም የታምሩን እውነተኛነት
አረጋግጣ ለህዝቧ በመገናኛ ብዙሀን አስተዋወቀች ፡፡
ልመናዋ ክብሯ የልጇ የወዳጇ ቸርነት በሁላችን ላይ ይደር

31/07/2019

እሱ ያውቃል እሱ ያውቃል ▶ እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባል። ዮሐ 3፥30
††† እንኳን ለቅዱስ መርቆሬዎስ እና ለቅዱሳኑ ቴክላ: አበከረዙን: ዱማድዮስ እና ኄኖክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕተ ሮሜ †††
††† ቅዱሱ ከቀደምት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በ200 ዓ/ም አካባቢ እንደ ተወለደ ይታመናል:: ወላጆቹ ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና የመጡት በተአምር ነው:: ስማቸውም # ታቦትና_ኖኅ ይባላሉ:: ቅዱሱ መጀመሪያ " # ፒሉፓዴር " ይባል ነበር:: ትርጉሙ "የአብ ወዳጅ" እንደ ማለት ነው::
ቀጥሎም " # መርቆሬዎስ" ተብሏል:: ይኸውም "
# የኢየሱስ_ክርስቶስ_አገል ጋይ" እንደ ማለት ነው:: በጦርነት ኃይለኛ: በመልኩ ደመ ግቡና ተወዳጅ የነበረው ቅዱስ መርቆሬዎስ ስለ ክርስትናው መከራን የተቀበለው በ20 ዓመቱ ነው:: ዘመኑም በዳኬዎስ ቀዳማዊ ነው::
ስለ ሃይማኖቱም ለ5 ዓመታት መከራን ታግሦ በ25 ዓመቱ (ማለትም በ225 ዓ/ም) ሕዳር 25 ቀን አንገቱን ተከልሏል:: በዓለማቀፍ ደረጃም ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብሩ ከሊቀ ሰማዕታት ቀጥሎ የሚገኝ ነው::
በተለይ ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን ቅዳሴ ቤቱ ሲሆን ቤቱ በታነጸበት ሁሉ ተአምራትን ያደርጋል:: ስለዚህ ነገር ታሪክ ብቻ ሳይሆን እኛ ኃጥአንም ምስክሮች ነን:: ጋሹ አምባን ጨምሮ ዛሬም ቅዱሱ ድንቆችን ይሠራል::
††† ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ †††
††† ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኄኖክ ከአባታችን አዳም 7ኛው ደግ ሰው ሲሆን አባቱ # ያሬድ ይባላል:: በእርግጥ ቅዱሱ ሚስት አግብቶ # ማቱሳላና ሌሎች ልጆችን ወልዷል:: አካሔዱ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ነበርና ሞትን አላየም::
# ነቢዩ_ኄኖክ በ1486 ዓ/ዓ የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ( ) ጽፏል:: የዚሕ መጽሐፍ ባለቤት ደግሞ ሃገራችን ናት:: ቅዱሱ ብዙ ሰማያዊ ምሥጢሮችን ተመልክቷል::
የእርሱ ሞትን አለመቅመስ # በአቤል ሞት የፈሩትን
# ውሉደ_አዳም በተስፋ አነቃቅቷቸዋል::
"በአቤል አፍርሆሙ:
ወበኄኖክ አንቅሆሙ" እንዳለው ሊቁ:: (ዘፍ. 5:24, ኄኖክ. 4:1)
††† ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት †††
††† እናታችን ቅድስት ቴክላ በኒቆምድያ ተወልዳ ያደገች: ከአሕዛባዊ እምነት ወደ ክርስትና በሐዋርያው
# ቅዱስ_ዻውሎስ አማካኝነት የመጣች እናት ናት:: እርሷ ክርስትናን ከልብ ለሚሹ ሴቶች ሁሉ መሪና ትልቅ ት/ቤት ናት:: ወንጌልን ከሐዋርያው ስትማር ምሥጢሩ እየመሰጣት አንዳንዴ ለ3 ቀናት ምግብ አትቀምስም ነበር::
እጅግ ቆንጆ ወጣትና የሃብታሞች ልጅ ብትሆንም ስለ ክርስቶስ ሁሉን ለመናቅና መስቀሉን ለመሸከም አልተቸገረችም:: ከኒቆምድያ እስከ አንጾኪያ ወንጌልን ሰብካለች:: ወላጆቿን ጨምሮ ብዙ ነፍሳትን አድናለች:: በፈንታውም ብዙ መከራን ተቀብላ በዚህ ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስትያን " # ሐዋርያዊት " ብላ ታከብራታለች::
††† ቅዱስ አበከረዙን ጻድቅ ወሰማዕት †††
††† ስም አጠራሩ የከበረ ታላቁ # አባ_አበከረዙን ወደ ክርስትና የተጠራው ከሽፍታነት (ስርቆት) ሕይወት ነው:: ከአጋሮቹ ጋር ገዳም ለመዝረፍ ሒደው አንድ ባሕታዊ ከማታ 12:00 እስከ ጧት 12:00 ሲጸልይ አይተው ተጸጽተው ንስሃ ገብተዋል::
አበከረዙን ግን ዓለምን ንቆ በምናኔ ለ7 ዓመታት ተጋድሏል:: ነገር ግን ሰማዕት ለመሆን ከነበረው ፍቅር የተነሳ ከገዳም ወደ ከሃድያን ነገሥታት ሃገር ሔዶ ስመ ክርስቶስን ሰብኩዋል:: በእርሱ ላይ ከደረሱ ስቃዮች ብዛት የተነሳ ከሥጋው: ከአጥንቱና ከደሙ የተረፈለት የለም::
እንዲያውም አንዴ በዓየር ላይ ዘቅዝቀው ሰቅለው ደሙ በአፍና በአፍንጫው እየጐረፈ ለ10 ቀናት ቆይቷል:: በወቅቱ የመኮንኑ ሴት ልጅ እየመጣች ያለ ርሕሪሔ ታሰቃየው ነበርና እርሷን መልአክ ወርዶ ቀሥፎ ገደላት::
እርሱ በተሰቀለ በ22ኛው ቀን: እርሷ በተቀበረች በደግሞ በ12ኛው ቀን ከተሰቀለበት አውርደውት ከሞት አስነስቷታል:: ታላቁ አበከረዙንን በዚህች ቀን ብዙ አሰቃይተው: ወገቡን ሰብረው: አንገቱንም ሰይፈው ገድለውታል::
††† ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ †††
††† ለቤተ ክርስቲያን በንጹሕ ሕይወታቸው ካበሩላት ዐበይት ቅዱሳን አንዱ # ቅዱስ_ዱማድዮስ ነው:: እርሱ ወደ ክርስትና የመጣው ከባዕድ አምልኮ ሲሆን መሪው ነው:: ጣዕመ ሕይወቱን ሲሰሙት ዕዝነ ልቡናን ደስ ያሰኛል::
ገና በወጣትነቱ እንደ # ሐዋርያት ሰብኮ አሕዛብን አሳምኗል:: እንደ # ጻድቃን አካሉ አልቆ አጥንቶቹ እስኪታዩ ተጋድሏል:: እርሱ
# ድንግል : # ንጹሕ : # መነኮስ : # ባሕታዊና # ካህን ነው:: ግን ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላል:: በዚህ ምክንያት ካደረበት አይውልም: ከዋለበትም አያድርም::
እርሱ በጸሎቱ የተዘጉ ማሕጸኖችን ከፍቷል:: ዕውራንን አብርቷል:: ለምጻሞችን አንጽቷል:: አንካሶችን አርትቷል:: በፈጣሪው ኃይል ፈሳሽ ወንዝን አቁሟል:: እንደ ገናም እንደ ነበረው መልሶታል::
የቅዱስ ዱማድዮስ መጨረሻው ደግሞ # ሰማዕትነት ነው:: በበዓቱ ውስጥ ሳለ ከደቀ መዝሙሩ ጋር ክፉዎች በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: ድንጋዩም የኮረብታ ያህል ነበር:: ልክ በዓመቱ በዚህች ዕለት ምዕመናን ሥጋውን አፍልሠዋል::
††† ቸር አምላክ ከነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃንና ሰማዕታት ክብርን ያሳትፈን::
††† ሐምሌ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ዕርገቱ)
3.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
4.ቅዱስ አበከረዙን ታላቁ (ጻድቅና ሰማዕት)
5.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ (ጻድቅና ሰማዕት)
6.ቅድስት ኢላርያ ሰማዕት
7.ቅዱሳት ቴክላ ወሙጊ ሰማዕታት
8.ቅዱስ እንዲኒና ሰማዕት
9.አባ ይስሐቅ ሰማዕት
10.አባ ሕጻን ሞዐ ዘደብረ ሊባኖስ
11."25,000" ሰማዕታት (የአትሪብ /ግብፅ/ ሰዎች)
††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
3.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
††† "እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::" †††
(ዕብ. 6:10-13)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

29/07/2019

እጃቹህን ከመምህራችን እና ከቅድስት ቤተክርስትያን አንሱ
6 hrs · Public
50 · Like · React · 5 Comments · Share ·

29/03/2019
26/03/2019

ቤተ ክርስቲያናችን ፡ከመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ለግንባታው ስራ የሚውል ገቢ እንድናሰባስብ ፈቃድ ተሰጠ፡፡ ከእንግዲህ ጎበዝ እንበርታ...

26/03/2019

Ymiyastesasren siga ena atit adelem yegeta siga ena Dem eji

Address

Batia

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bati Abune Teklehaymanot Church/ባቲ ጉህ ጽባህ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category