ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል ሚዲያ

ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል ሚዲያ "ንሕነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ።" ፩ኛ. ቆሮ.፩፥፳፫
(1)

"ብዙ ነገር አሳልፌያለሁ፤ እግዚአብሔር የማልችለውን አልሰጠኝም። ሁሉን እንድችል አድርጎ በስኬት ያቆመኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ግቢ ጉባኤ ጸሎትን የተለማመድኩባት፣ መንፈሳዊ ሕይወትን ...
29/03/2026

"ብዙ ነገር አሳልፌያለሁ፤ እግዚአብሔር የማልችለውን አልሰጠኝም። ሁሉን እንድችል አድርጎ በስኬት ያቆመኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ግቢ ጉባኤ ጸሎትን የተለማመድኩባት፣ መንፈሳዊ ሕይወትን የጀመርኩባት የስኬቴ ምክንያት ናት"

ነቢዩ ዳዊት: የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ

መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል በጥበበ ግዮን ግቢ ጉባኤ ያስተማራቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በአባቶች ቡራኬ አስመርቋል።

ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል እኩል 3.98 ነጥብ በማምጣት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያዘጋጀውን የወርቅ ሜዳሊያ የተሸለሙት ነቢዩ ዳዊት እና ፍቅር ገብሩ የጥበበ ግዮን ግቢ ጉባኤ ፍሬዎች ናቸው።

ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል ባዘጋጀው የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ሁለቱን የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች ጨምሮ በግቢ ጉባኤው አገልግሎት በሥራ አስፈጻሚነት ያገለገሉና የከፍተኛ ማእረግ ተሸላሚዎች የሆኑትን ልዩ ስጦታ እና እውቅና ተበርክቶላቸዋል።

በመርሐ ግብር ላይ ተገኝቶ የተሰማውን ደስታ የገለጸው ተመራቂ ነቢዩ ዳዊት ብዙ ነገር አሳልፌያለሁ፤ እግዚአብሔር የማልችለውን አልሰጠኝም። ሁሉን እንድችል አድርጎ በስኬት ያቆመኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ግቢ ጉባኤ ጸሎትን የተለማመድኩባት፣ መንፈሳዊ ሕይወትን የጀመርኩባት የስኬቴ ምክንያት ናት በማለት የተሰማውን ስሜት ገልጿል።

ሌላኛዋ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ፍቅር ገብሩ የፊዚዮቴራፒ ትምህርት ክፍል ተመራቂ ስትሆን 3.98 ነጥብ በማምጣት ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀውን የወርቅ ሜዳሊያ በመጋራት ለመሸለም በቅታለች።

የግቢ ጉባኤው የሥራ አስፈጻሚ አባላት የነበሩ 3 የከፍተኛ ማእረግ ተመራቂዎችም በጉባኤው ላይ ተገኝተው ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

በመጨረሻም የወርቅ ሜዳልያ እና የከፍተኛ ማእረግ ተሸላሚ ተማሪዎቹ የህጻናት የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው የሕይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል።

👇👇👇👇👇👇
ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ማእከል ሚዲያ፦
ቴሌግራም፦👇
https://t.me/mkbdcenter
ፌስቡክ፦👇
https://m.facebook.com/mkbahirdarcenter

"ግቢ ጉባኤ ለእኔ መተኪያ የላትም።"ማስረሻው ዋለ- የከፍተኛ ማእረግ ተመራቂ ተማሪመጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ምማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል በጥበብ ግዮን ግቢ ጉባኤ ያስተማራቸውን 18...
29/03/2026

"ግቢ ጉባኤ ለእኔ መተኪያ የላትም።"

ማስረሻው ዋለ- የከፍተኛ ማእረግ ተመራቂ ተማሪ

መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል በጥበብ ግዮን ግቢ ጉባኤ ያስተማራቸውን 180 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በአባቶች ቡራኬና በአደራ መስቀል አስመርቋል።

በማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል ምክትል ሰብሰቢ አቶ ብርሃኑ አሳሳ በምረቃ በዓሉ ላይ ተገኝተው የማኅበረ ቅዱሳንን መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ማኅበረ ቅዱሳን እናንተን ሲያስተምር ከተመረቃችሁ በኋላ በግቢ ጉባኤ ያገኛችሁትን እውቀት መንፈሳዊና የአገልግሎት ልምድ አሳድጋችሁ በምትደርሱበት ምድር ሁሉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእውቀታችሁ፣ በገንዘባችሁና በጉልበታችሁ እንድታገለግሏት በማሰብ ነው ብለዋል።

በግቢ ጉባኤው የባች ማስተባበሪያ አገልግሎት ክፍል ተጠሪ እና በፋርማሲ ትምህርት ክፍል 3.94 በማምጣት የከፍተኛ ማእረግ ተመራቂው ማስረሻው ዋለ ስለስኬቱ ሲናገር ግቢ ጉባኤ እናት፣ አባት፣ እህት፣ ወንድም ሆና ለዚህ ስኬት አብቅታኛለችና ግቢ ጉባኤ ለእኔ መተኪያ የላትም በማለት ተናግሯል።

ሃይማኖት ዝግአለ ይባላል። የግቢ ጉባኤው የሙያና በጎ አድራጎት ክፍል ተጠሪ እና በሜዲካል ላቭራቶሪ ትምህርት ክፍል 3.94 በመምጣት የከፍተኛ ማእረግ ተሸላሚ ነው። ግቢ ጉባኤ ለእኔ ያለችኝን ጥቂት ጊዜ ተጠቅሜ በትኩረት በማንበብ ውጤታማ እንድሆን አድርጋኛለች ሲል የስኬቱን ምስጢር ይናገራል።

መአዛ ሙሉዓለም የግቢ ጉባኤው ፀሐፊ በመሆን ስታገለግል ነበር። የህጻናት ነርስ ትምህርት ክፍል ተመራቂ ተማሪ ስትሆን 3.7 በማምጣት በከፍተኛ ውጤት ተመርቃለች። የአብነት ትምህርት በግቢ ጉባኤው ውስጥ በመማር መዝሙረ ዳዊትን ዘልቃለች። መአዛ ግቢ ጉባኤ ለእኔ እናቴ ናት በችግር ጊዜ የመፍትሔ ሰው መሆን እንድችል አስተምራኛለች በማለት ትገልጻለች።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሕክምና እና ጤና ሳይንስ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 255 ተመራቂዎች መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ማስመረቁ የሚታወስ ሲሆን ከእነዚህ ተመራቂዎች መካከል 180 የሚሆኑት ተመራቂዎች በግቢ ጉባኤ የሚሳተፉ የነበሩ ናቸው።

👇👇👇👇👇👇
ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ማእከል ሚዲያ፦
ቴሌግራም፦👇
https://t.me/mkbdcenter
ፌስቡክ፦👇
https://m.facebook.com/mkbahirdarcenter

ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል 20ኛው ሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አካሄደ።መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ምማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል 20ኛውን ዙር የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ወደ ...
29/03/2026

ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል 20ኛው ሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አካሄደ።

መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል 20ኛውን ዙር የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ወደ ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት መካነ ቅዱሳን አየር ኃይል አቡነ አረጋዊ ወአቡነ በትረ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካሂዷል።

የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብሩ በደብሩ ካህናት ጸሎተ ወንጌል ተጀምሮ መዝሙር በዘማርያን፣ ትምህርት እና ምክረ አበው መርሐ ግብር በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ተከናውኗል።

የመካነ ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ ወአቡነ በትረ ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት መላኩ አልልኝ ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ማእከል የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብሩ በቤተ ክርስቲያናችን እንዲዘጋጅ በመፍቀዱና በማስተባበሩ እያመሰገንን ቤተ ክርስቲያኑ ያለው ቦታ በጣም አነስተኛ ቦታ በመሆኑ የምእመናንን ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር የደም ልገሳ መርሐ ግብር የተካሄደ ሲሆን ከ100 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሕይወት መሆን የሚችል የደም ልገሳ መካሄዱን የባሕር ዳር ደም ባንክ አገልግሎት አስታውቋል።

በሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብሩ የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ሊቀ ስዩማን አያና በላይን ጨምሮ የልዩ ልዩ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች እና እስከ ከ1500 በላይ የሚደርሱ ከባሕር ዳር እና አካባቢው የተሰባሰቡ ምእመናን ተሳትፈዋል።

👇👇👇👇👇👇
ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ማእከል ሚዲያ፦
ቴሌግራም፦👇
https://t.me/mkbdcenter
ፌስቡክ፦👇
https://m.facebook.com/mkbahirdarcenter

ኒቆዲሞስመጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በግሪክ ቋንቋ ኒቆዲሞስ የሚለው ቃል ትርጓሜ ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን የሚያመለክት ነው፡፡ በዘመነ ሥጋዌ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ...
29/03/2026

ኒቆዲሞስ

መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም

በግሪክ ቋንቋ ኒቆዲሞስ የሚለው ቃል ትርጓሜ ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን የሚያመለክት ነው፡፡ በዘመነ ሥጋዌ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌልን በሚሰብክበት ጊዜ አንድ ፈሪሳዊ ከአይሁድ አለቆችና መምህራን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ ሰው እንደነበረና የጌታችንን ቃል በሌሊት ወደ እርሱ በመሄድ እንደተማረ በወንጌለ ዮሐንስ ተጠቅሷል። (ዮሐ.፩፥፪)

በአይሁድ አለቆች ፊትም ‹‹ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?›› በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እርሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር መሆን ያመኑበት ኦሪትን የማያውቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር ‹‹አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሣ መርምርና እይ›› አሉት እንጂ አልተቀበሉትም። (ዮሐ.፯፥፵፰-፶፪)

ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረው ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ›› እንዲል፤ (ዮሐ ፲፱፥፴፱) በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል።

ኒቆዲሞስ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ?

፩. ኒቆዲሞስ መምህር ስለነበር ‹‹ስማር ሰዎች ቢያዩኝ ውዳሴ ከንቱ መምህር መባል ይቀርብኛል›› ብሎ ነው፡፡ እኛስ ዛሬ የዘለዓለም ሕይወት የሚሰጠንን ቅዱስ ቃል በትሕትና መማር ሲገባን ለምድራዊ ክብር ብለን በቀን ጊዜያችን መማር ያልቻልን ስንቶቻችን ነን? ስለዚህ ቀን ጊዜያችንን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል። ‹‹ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና፡፡›› (ዮሐ ፱፥፬)

፪. ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ስለነበር እንዳያዩት ፈርቶ ሌሊት እየመጣ ይማር ነበር፤ እኛስ ዛሬ ልባችን የተረዳውን እውነት በግልጥ እንዳንፈጽም በፍራቻና በይሉኝታ የምንሠውር ስንቶቻችን ነን? ፍጹም ፍቅር ፍርሃት የለውም፤ ፍርሃት ቅጣት አለውና፡፡ (፩ኛዮሐ.፬፥፲፰) ፍርሃትን አስወግደን ለእውነት ልንቆም ይገባል።

፫. ኒቆዲሞስ በሙሉ ልቡ በማስተዋል ለመማር ስለፈለገ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የማታውን መረጠ፤ ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ከልብ ሆነን የምንማር? የሰማነው ቅዱስ ቃል በሕይወታችን ፍሬ እንዲያፈራ ቅዱስ ቃሉን ከልብ ሆነን በማስተዋል ልንሰማ ይገባናል፡፡ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ልብ መልካም መሬት ተብሏል፡፡ ‹‹በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው፡፡›› (ማቴ.፲፫፡፥፳፫)

አንዳንዶቻችን ጸሎት እያደረግን እንኳን አንደበታችን የእግዚአብሔርን ቃል ይረሳል፡፡ ልቦናችን ወደ ሌላ ቦታ ይጓዛል፤ በማኅበር ጸሎትም አብረን እየጸልይን በመካከል በተመሳሳይ ሁኔታ ሐሳቦቻችን ወደ ሌላ ነገር የሚሳቡበት አጋጣሚ ይኖራል፡፡

፬. ሌሊት ጨለማ ነው፤ ብርሃን የለም፤ ይህም የኃጢአት ምሳሌ ነው፤ ኒቆዲሞስ በሌሊት መምጣቱ ኃጢአተኛ እንደሆነና ንስሓ ፈልጎ ወደ ጌታችን እንደመጣ ያስረዳናል፡፡ ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን ስንሰማ በተአምኖ ኃጢአት በንስሓ ውስጥ ሆነን የምንሰማ? ያለንስሓ የምንሰማው ቃል በሕይወታችን ፍሬ የማፍራት ዕድሉ ጠባብ ነው፡፡ ምክንያቱም በንስሓ ከልባችን ያልጸዱት ክፉ ምኞቶች እንደ እሾህ ሆነው ያንቁታልና፡፡ ‹‹ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፤ እሾህም ወጣና አነቀው›› ተብሎ የተጻፈው ለዚህ ነው። (ማቴ.፲፫፥፰)

፭. ሌሊት የቆየው ኪዳን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው፤ ኒቆዲሞስም ‹‹እኔ ምሁረ ኦሪት እንጂ ምሁረ ወንጌል አይደለሁም፡፡ ወንጌልን ካንተ እማር ዘንድ ያስፈልገኛል›› ሲል በሌሊት ለመማር ወደ ጌታችን ይመጣ ነበር፡፡ የብሉያትን ከሐዲሳት መጻሕፍት ጋር ተዋሕደው ሲተረጎሙ ሰሙና ወርቁ ተጣምሮ የሕይወት ትምህርት ያስገኛል፡፡ አንዳንዶች ዛሬ ‹‹ብሉያት ጭራሽ አያስፈልጉም›› ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ነገር ግን እንደ ኒቆዲሞስ ሁለቱን ኪዳናት አዋሕዶ መጓዝ ትክክለኛው መንገድ ነው፡፡ ጌታ ሲያስተምር ‹‹እውነት እላችኋለሁ! ሰማይና ምድረ እስኪያልፍ ድረስ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አታልፍም›› በማለት አበክሮ የተናገረው ለዚህም ነው፡፡ (ማቴ.፭፥፲፰)

ኒቆዲሞስ ምንም እንኳን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ባይመቸውም በሌሊቱ ሰዓት ለመማር ችሏል፡፡ እኛም ከእርሱ ተምረን ከልብ ካለቀሱ እንባ አይጠፋምና ምንም ሥራ ቢበዛብን ለቅዱስ ቃሉ ጊዜ አይጠፋም፡፡ ቅዱስ ወንጌል ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያሻግር የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ዘወትር ልንማር ያስፈልጋል፡፡

በተለይም በአዘቦት ቀንም ሆነ በሰንበታት ወደ ቤተ ክርስቲያን በማዘውተር በሰርክ፣ በወርኃዊ እና በዓመታዊ በዓላት ላይ በሚደረጉ የዐውደ ምሕረት ጉባኤዎች ላያ በመሳተፍ ቅዱስ ቃሉን መማር ይገባል፡፡ የድኅነት መንገድን ዐውቀንና ተረድተን በጽድቅ ጎዳና ካልተጓዝን መዳን አይቻለንም፡፡ ለኃጢአትም ተጋልጠን ፈጣሪያችንን እናስከፋዋለን፡፡ የእግዚአብሔርንም መንግሥት ከመውረስ ይልቅ ለዘለዓለማዊ ቅጣት እንዳረጋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላችን ቅዱስ ቃሉን እንድንረዳ አስተዋይ ልቡና ይስጠን፤ አሜን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

©ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

የኦርቶዶክሳዊያን ሙያተኞች ማኅበር ተመሠረተ።መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ምማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል የኦርቶዶክሳዊያን ሙያተኞች ማኅበር መመስረቱን አስታውቋል።  የሙያተኞች ማኅበር የ...
28/03/2026

የኦርቶዶክሳዊያን ሙያተኞች ማኅበር ተመሠረተ።

መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል የኦርቶዶክሳዊያን ሙያተኞች ማኅበር መመስረቱን አስታውቋል።

የሙያተኞች ማኅበር የተመሠረተው ማእከሉ ባዘጋጀው የኦርቶዶክሳዊያን ሙያተኞች ጉባኤ መካሄዱን ተከትሎ መሆኑን የማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል ሙያ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ አቶ ታጠቅ የኔሁን ገልጸዋል።

የሙያተኞች ማኅበሩ መመስረት ባለሙያዎች ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን የሙያ አገልግሎት በተደራጀ መልኩ በጥራት፣ በጊዜ እና በሰፊ ተደራሽነት ለማከናወን እንደሚያግዝ አቶ ታጠቅ ገልጸዋል።

አቶ ታጠቅ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በሙያ መደገፍ ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን እንድትወጣ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ በመጠቆም፣ የሙያ አገልግሎቱንም የሙያ ሥነ-ምግባርን፣ ኦርቶዶክሳዊ እሴትን እና ዘመኑን የዋጀ አተገባበርን በመጠቀም መፈጸም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

መምህር አስተርአየ ገላው በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የፈለገ ሰላም ቅድስት አርሴማ ፈለገ አእምሮ የዐራቱ ጉባኤያት ጉባኤ ቤት መምህር የሙያተኞች በማኅበሩ ምስረታ ተገኝተው ስለሙያና አገልግሎት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ክርስቲያናዊ ትውፊቶችን መሰረት በማድረግ ለባለሙያዎች ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።

በምስረታው ላይ የተገኙ ከተለያየ የሙያ ክፍሎች የመጡ ባለሙያዎችም፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በሙያ ለማገልገል በዚህ መልኩ ማኅበሩ መመስረቱ ለማገልገል ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑ የገለጹ ሲሆን፣ በትኩረትና በንቃት አገልግሎት ለመፈጸም እንደሚተጉም ቃል ገብተዋል።

በመጨረሻም 7 አባላት ያለው ማኅበሩን የሚያስተባብር አስተባባሪ ኮሚቴ የተመረጠ ሲሆን፣ ኮሚቴውም በየሙያው ዘርፍ የተደራጁ ባለሙያዎችን አገልግሎት እየተከታተለ የሚያበረታታ፣ የልምድ ልውውጥ በማድረግ አገልግሎትን የሚያጠናክርና የማኅበሩ ጉባኤ በየጊዜው እንዲካሄድ የሚደግፍ ሆኖ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።

👇👇👇👇👇👇
ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ማእከል ሚዲያ፦
ቴሌግራም፦👇
https://t.me/mkbdcenter
ፌስቡክ፦👇
https://m.facebook.com/mkbahirdarcenter

“ግቢ ጉባኤን እንደ እናት አድርጎ የሰጠንን አምላክ እናመሰግናለን።”የዋንጫ ተሸላሚ ተመራቂዎች መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ብርሃን ማእከል በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ...
28/03/2026

“ግቢ ጉባኤን እንደ እናት አድርጎ የሰጠንን አምላክ እናመሰግናለን።”

የዋንጫ ተሸላሚ ተመራቂዎች

መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ብርሃን ማእከል በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ካምፓስ ያስተማራቸውን 98 የግቢ ጉባኤ አባላት አስመረቀ።

ከግቢው የተሰጠውን ሁለት ዋንጫ የግቢ ጉባኤ ልጆች ወስደውታል።

ከጠቅላላ ተመራቂ ተማሪዎች በከፍተኛ ማእረግ የተመረቀው ተመራቂ ቢተውልኝ ደባስ ሲሆን 3.95 በማምጣት የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት ተቀብሏል። በግቢ ጉባኤ አገልግሎት በኦዲት እና ኢንስፔክሽን የንዑስ ክፍል ተጠሪ ሆኖ ያገለገለ ነው።

ሁለተኛውን ዋንጫ የተቀበለችው ተመራቂ ውዴ መላኩ ስትሆን ውጤቷም 3.92 ነው። የግቢ ጉባኤ አገልግሎት የመምህራን ምደባ ንዑስ ክፍል ጸሐፊ ሆና ስታገለግል ነበር።

በምረቃ መርሐግብሩም ላይ የማእከሉ ምክትል ሰብሳቢ ዲ/ን ዶ/ር አለማየሁ በመገኘት የማኅበሩን መልእክት ያስተላፉ ሲሆን በዓላማችሁ ፀንታችሁ ለዚህ ስለበቃችሁ ቤተክርስቲያን ተደስታለች ብለዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ በዚህች ግቢ ጉባኤ ተከታትላችሁ ከሁሉም ተማሪዎች ለከፍተኛ ማእረግ ስለበቃችሁ ማኅበረ ቅዱሳንን አኩርታችኋል ብለዋል።

ከፍተኛ ማእረግ ላመጡ የግቢ ጉባኤው ተማሪዎች ማእከሉ ሥጦታ አበርክቶላቸዋል።

ከፍተኛ ማእረግ ላገኙ ተማሪዎች የማእከሉ ሰብሳቢ ዲ/ን አድማሱ አበራ እናንተ የቤተ ክርስቲያን ብርቅየዎች ስለሆናችሁ በሄዳችሁበት ሁሉ በሞያችሁ እና በሁሉ ነገራችሁ ቤተ ክርስቲያንን እና ሕዝባችንን በቅንነት እና በታማኝነት እንድታገለግሉ በማለት አደራ አስተላልፈዋል።

© ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

👇👇👇👇👇👇
ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ማእከል ሚዲያ፦
ቴሌግራም፦👇
https://t.me/mkbdcenter
ፌማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል ሚዲያarcenter

ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል 108 ሺህ 751 አዳዲስ አማንያን አስተምሮ ማስጠመቁን ማኅበረ ቅዱሳን አስታወቀ።መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ምበዛሬው ዕለት እየተከናወነ በሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን...
28/03/2026

ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል 108 ሺህ 751 አዳዲስ አማንያን አስተምሮ ማስጠመቁን ማኅበረ ቅዱሳን አስታወቀ።

መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

በዛሬው ዕለት እየተከናወነ በሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር ጉባኤ ላይ የሥራ አመራር ጉባኤ ጽ/ቤት ሪፓርት በማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ አቶ ካሳሁን ኃይለ ማርያም የቀረበ ሲሆን የማኅበሩ የስልታዊ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መ/ር ዋሲሁን በላይ ቀርቧል።

በዚህም ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት ከአከናወናቸው አገልግሎቶች መካከል ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል 108 ሺህ 751 አዳዲስ አማንያንና 14ሺ 372 ጠፍተው የተመለሱ ምእመናን መጠመቃቸውንና 17 አብያተ ክርስቲያናት መሠራታቸውን የተገለጸ ሲሆን የውዳሴ ማርያም፣የጸሎት መጽሐፍና የነገረ ድህነት ቡክሌት በአማርኛ ቋንቋ በብሬል ተዘጋጅቶ መስማት ለማይችሉ ምእመናን ተደራሽ መደረጉ እንዲሁም በተለያዩ ቋንቋዎች መጻሕፍት፣ ድምጽ ወምስልና ቡክሌት መዘጋጀቱ ተጠቅሷል።

በተያያዘ ዘገባ በሚዲያ አገልግሎት ተቋም በየሳምንቱ ከ40 በላይ በሚሆኑ መደበኛ መርሐ ግብራት በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በትግረኛ፣ በሲዳመኛ፣ በወላይተኛ፣ በእንግሊዘኛና መስማት በተሳናቸው ቋንቋዎች የተላለፈ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ሌሎች አገልግሎቶች እንደተከናወኑም ነው የተነገረው።

በተጨማሪም በዜማና ኪነ ጥበባት ማእከል ፣ በግቢ ጉባኤያት አገልግሎት፣ በሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት፣ በቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገትና መንፈሳዊ ት/ቤቶች፣ በልማት ተቋማትና በሌሎች አገልግሎቶች የተከናወኑ ተግባራትን በሪፖርቱ ቀርቧል።

የኤዲቶሪያል አገልግሎት ፣ የኦዲት አገልግሎት ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛሉ።

©ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

👇👇👇👇👇👇
ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ማእከል ሚዲያ፦
ቴሌግራም፦👇
https://t.me/mkbdcenter
ፌስቡክ፦👇
https://m.facebook.com/mkbahirdarcenter

የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር የ6ወር ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ምበየዓመቱ በ6 ወር የሚካሄደው የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ...
28/03/2026

የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር የ6ወር ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።

መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም

በየዓመቱ በ6 ወር የሚካሄደው የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም በማኅበሩ ሕንፃ 3ኛ ወለል ላይ በሚገኘው ንቡረ ዕድ ድሜጥሮስ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

በጠቅላላ ጉባኤው ላይ መጋቤ ሃይማኖት አባ አብርሃም ገረመው የቅዱስ ሲኖዶስ ም/ጸሐፊ እና የሰሜን አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት፣የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት፣ የማእከላት ሰብሳቢዎች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ መዝሙር፣ ትምህርተ ወንጌል የቀረበ ሲሆን የ6 ወር የሥራ አመራር ቃለ ጉባኤ ላይ ውይይት እየተከናወነ ይገኛል።

©ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

👇👇👇👇👇👇
ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ማእከል ሚዲያ፦
ቴሌግራም፦👇
https://t.me/mkbdcenter
ፌስቡክ፦👇
https://m.facebook.com/mkbahirdarcenter

26/03/2026

"ልሳነ ግእዝ ትምህርት ክፍል ፲፫ ነባር አናቅጽ" ZwT||ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን (Official Video) #ዜማወጥበብዘማኅበረቅዱሳን Subscribe: https://www.youtube.com/channel/UC2...

25/03/2026
''አንዱን ዋንጫ ለእናቴ ሁለተኛውን ዋንጫ ለማኅበረ ቅዱሳን'' የሁለት ዋንጫ ባለቤት የሆነችው የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተመራቂዋ  ተማሪ አባይነሽ ታምርመጋቢት ፲፬/፳፻፲፰ ዓ.ም           ...
23/03/2026

''አንዱን ዋንጫ ለእናቴ ሁለተኛውን ዋንጫ ለማኅበረ ቅዱሳን'' የሁለት ዋንጫ ባለቤት የሆነችው የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተመራቂዋ ተማሪ አባይነሽ ታምር

መጋቢት ፲፬/፳፻፲፰ ዓ.ም



በማኅበረ ቅዱሳን ደባርቅ ማእከል የግቢ ጉባኤ ኮርስ ሲከታተሉ የቆዩ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መጋቢት 13 ቀን 2018ዓ.ም ምቃራ ኢየሱስና ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በሚገኘው የግቢ ጉባኤው አዳራሽ አስመርቋል፡፡



በመርሐ ግብሩ ታማኝና ቸር አገልጋይ በሚል ርእስ ትምህርተ ወንጌል የሰጡት የቅኔ፣ የሐዲሳት እና የብሉያት መምህር ይሔይስ ጀጃው ተመራቂ ተማሪዎች ለሀገራቸው እና ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን የደባርቅ ማእከል ሰብሳቢ መ/ር ጸጋየ ደምሌ ለተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት “ተማሪዎች ይህ የመጀመሪያ እንጅ የመጨረሻችሁ እንዳልሆነ በመረዳት ሁል ጊዜም ጠንክራችሁ መሥራት ያስፈልጋል፤” በማለት ግቢ ጉባኤውን የሚረከቡ ተማሪዎችም የተመራቂዎችን የስኬት ፈለግ ተረክበው በትምህርታቸውና በግቢ ጉባኤ አገልግሎታቸው ጠንካራ ይሆኑ ዘንድ መልእክት አስተላልፈዋል ።

ከአጠቃላይ ተመራቂዎች 3.97ውጤት በማስመዝገብ በሁለቱም ጾታ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀውን ሁለት ዋንጫዎች እና 2 ሜዳልያ ተሸላሚ ለመሆን የበቃችው የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባኤ ሒሳብና ንብረት ክፍልን ሥራ አስፈጻሚ በመሆን 2 ዓመት ያገለገለችው ተማሪ አባይነሽ ታምር የመርሐ ግብሩ ድምቀት ሆናለች።

ተማሪ አባይነሽ የስኬቴ ምንጭ ማኅበረ ቅዱሳን እና ቤተሰቦቼ ናቸው ያለች ሲሆን ለዚህም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ አንዱን ዋንጫ ለእናቴ ሁለተኛውን ዋንጫ ለማኅበረ ቅዱሳን አበርክቻለሁ ብላለች።

በዚህ የምረቃ መርሐ ግብር ትምህርተ ወንጌል :በተመራቂ ተማሪዎች መዝሙር እና ሥነ ጽሑፍ የቀረበ ሲሆን በመጨረሻም የአደራ መስቀል በመልአከ ጽባሕ ቄስ ዘመን አታሌ የምቃራ ኢየሱስ እና ቅድስት ሥላሴ አብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ ተሰጥቷል፡፡

ዘገባው : የደባርቅ ማእከል ሚዲያ ክፍል ነው።

👇👇👇👇👇👇
ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ማእከል ሚዲያ፦
ቴሌግራም፦👇
https://t.me/mkbdcenter
ፌስቡክ፦👇
https://m.facebook.com/mkbahirdarcenter

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል ሚዲያ:

Share