Mar Zeneb " ማርዘነብ "

Mar Zeneb " ማርዘነብ " ዲንህን ጠብቅ

23/08/2022

አሰላሙአለይኩም

23/08/2022
23/08/2022
17/08/2022

በየትኛው መመዘኛ??
**********************
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን አሁን እየመራሁ ነኝ የሚለው አካል እራሱን ለቦታው የተገባ አድርጎ የሚያይበት ምንም አይነት ህጋዊ ሰውነት እንደሌለው እራሱን ጨምሮ ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ሆኖ ሳለ ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ ሹም ሽር ሲያካሄድ ውሏል:: እስኪ ህሊና ያለውን ሁሉ እንጠይቅ:- ይህ ህገ ወጥ ቡድን መጅሊስ የገባው በትክክለኛ ምርጫ ነውን? በየትኛው መመዘኛ ነው ምርጫው የተካሄደው? ርክክቡስ እንዴት እንደነበረ መግለጫ የሚሰጡበት አንደበት አላቸውን? ምርጫ ከታች ወደላይ ሲሉ የነበሩ አፈቀላጤዎች ልሳናቸውን ምን ዘጋው? ምርጫው ፍትሃዊ እንዲሆን እንዲህ እንዲህ መደረግ አለበት ያሉትስ ምን ዋጣቸው? አህሉሱናን ያላሳተፈ የድራማ ምርጫ እውነት ህሊና ተቀብሎት "ምርጫ" እያሉ ይደሰኩሩለታልን?
****************************
ሁሉም ሙስሊም ማወቅ ያለበት ነገር የኛ መሪዎች አሁንም እነሙፍቲ ናቸው:: ምንም ቢፈጠር በዐቂዳ የማይገጥመን ሰው የዲናችን መሪ ሊሆን አይችልም:: ማንም ምንም ቢል ከወሃብያ ጋር ያለንን ልዩነት ማጥበብ አይችልም:: ምክኒያቱም መሰረታዊ የእምነት ልዩነት ስላለን:: ሰውን ለማሞኘት "የፈለገ ቢስሚላህን ድምፁን ጮክ አድርጎ ይቅራ ያልፈለገ ድምፁን ዝቅ ያድርግ" ስለተባለ ልዩነታችን ጥቃቅን ፊቅሃዊ ነጥቦች ናቸው ብለን አንደለልም:: ውስጠ ሚስጥራቸውን በማስረጃ አጋልጠናል:: የአይኤስ አይኤስ እና የአልሸባብ አሸባሪ ቡድኖች ከወሃብያ መድረሳ የተፈለፈሉ እንደሆኑ ኪታቦቻቸውን አጣቅሰን አብራርተናል::
****************************
የመንግስት ባለስልጣናት ለሰላምና ለደህንነት ለልማት መስራት ሃገራዊ ሃላፊነታቸው ቢሆንም አንድ ያልሆኑ ሰዎችን "አንድ ነን በሉ አለዚያ እናስራችሗለን እናፍናችሗለን" የማለት መብቱም ስልጣኑም የላቸውም:: ይህንን ደግሞ እነሱም ያውቁታል:: በፍፁም ህግን የተላለፈ ሳይሆን ህገ-መንግስታዊ መብትን መጠቀም ነው:: ስለዚህ ማንም ድምፃችንን የማፈን ሰላማዊ ትግላችንን የማስቆም መብት የለውም:: መጅሊሳችንን ትክክለኛ መሪዎች እስኪረከቡት ድረስ ትግላችን ይቀጥላል::
ድል ለአህሉ ሱና ወልጀማዓህ

04/08/2022

ነባሩ ሙስሊም ማህበረሰብ በሚከተለው እስልምና እና መጤው በሚያራምደው አስተምህሮ ያለው ሰፊ ልዩነት «ንፅፅር»!
♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦

1) - ትክክለኛ «ሙስሊሞች» የአስምህሯቸው መሪ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ሲሆኑ!
~
❌ በእስልምና ሽፋን የሚንቀሳቀሰው «ወሃቢያ» ደግሞ መሪው የአይሁዳዊያን ሰለባ የሆነው ነው።

2)- ሙስሊሞች እምነታዊም ይሁን፣ ንግግራዊ፣ ወይም ተግባራዊ ሸሪዓዊ መንገዳቸው.. ከነብዩ ሙሐመድ ﷺ ሲወርድ ሲዋረድ በመጣ የሰነድ ሰንሰለት ሲሆን!
~
❌ «ወሃቢያ» ግን የአስተምህሯቸው ሰንሰለት የዛሬ 300 አመት ገደማ የነበረው ላይ ይቋረጣል። ሰነዳቸውም የሙስሊሞች አይደለም።

3)- ሙስሊሞች "إنما بعثت لأتمم مكارم الأخلاق" የሚለውን ሐዲስ መሰረት በማድረግ ሰላምን፣ መቻቻልን እና መልካም ስነ ምግባርን በማንገስ የአንበሳውን ድርሻ ሲወስዱ!
~
❌ «ወሃቢያ» ግን "እኛን ያልተከተለ ከሃዲ ነው" በሚል የመሪያቸው ፈሊጥ በተመቻቸላቸው ቁጥር ሃገራትን ሲያወድሙ፣ ማህበረሰቡን ሲረሽኑ፣ ሽብርን ሲያነግሱ ይታያሉ። የሶሪያ፣ አፍጋኒስታን፣ ሊቢያ፣ ግብፅ፣ ዒራቅና የመን ጉዳይም ለዚህ ምስክር ነው። በሃገራችን የሚታየው የመጅሊስ መመሰቃቀልም አንዱ የአስተምህሯቸው ገፅታ ነው።

4)- ሙስሊሞች አላህን በፍጥረት በምንም አይነት መልኩ ሳይመስሉ እና ወደ ፍጥረቱ ከመከጀል የተጥራራ ጌታ እንደሆነ.. እንደዚሁም በሰው ልጅ አዕምሮ እርሱነቱን ሊደርሱበት የማይቻለውን ሃያሉን ን ሲያመልኩ!
~
❌ «ወሃቢያ» ግን ቁርአንን አጣሞ በመተርጎም በአዕምሯቸው ስለው ከዓርሽ በላይ ያስቀመጡትን የውሸት ጣኦት ያመልካሉ። ይወጣል ይወርዳል ብለው በሃዲስ እቃቃ ይጫወታሉ። ይህ መንገዳቸውም የአይሁ*ድ መንገድ ነው።

5)- ሙስሊሞች የነብዩ ሙሐመድ ﷺ ትውስታ በሙስሊማኑ ቀልብ ያይል ዘንድ መውሊድን ሸሪዓዊ ባስቀመጠው ህግጋት መሰረት ሲያከብሩ!
~
❌ «ወሃቢያ» ግን ቢድዓ በሚል ስግጥና የታላቁን ነብይ ﷺ ትውስታ ይከስም ዘንድ መውሊድን ይከለክላሉ። መውሊድን ከልክለውም የራሳቸውን አመራሮች [አል ሱዑድ] ትውስታ ከፍ ለማድረግ ሲጥሩ ይታያሉ።

6) ሙስሊሞች ዓሊሞቻቸው፣ መሪዎቻቸው፣ መሻይኾቻቸው፣ መንገድ ቀያሻቸው «ወረሰቱል አንቢያእ» ተብሎ የነብያት አስተምህሮ ወራሽ መሆናቸው ሲመሰከርላቸው!
~
❌ «ወሃቢያ» ግን መሪያቸው በነብያችን ﷺ አንደበት "هناك يطلع قرن الشيطان" ከሳኡድ አረቢያዋ ነጅድ የሰይጣን ቀንድ ይወጣል ተብሎ ተወግዟል። ይህ ቀንድም የይሁድ ሰለባ የሆነው የወሃቢያዎች መሪ ። ሐዲሱም በቡኻሪ ዘገባ አለ።

7)- ሙስሊሞች በረከትን በመሻት የነብዩ ﷺ ቅርሶችን በጥንቃቄ ሲጠብቁ ኑረዋል። ይህም በቡኻሪ ዘገባ የመጣውን ነብዩ ﷺ ጸጉራቸውን እና ጥፍራቸውን ማከፋፈላቸውን መሰረት በማድረግ ሲሆን!
~
❌ «ወሃቢያ» ግን ሽርክ በሚል ፍልስፍና 90% በመቶ የሚሆነውን በሒጃዝ የነበረውን ነብያዊ ቅርስ አውድመዋል። አቃጥለዋል። ትውስታቸው ከሙስሊሙ ቀልብ እንዲጠፋ ነብዩ ﷺ የተወለዱበትን ቦታ ሳይቀር ከብት በረት አድርገውታል። በመጨረሻም ውግዘቱ ሲበዛ ወደ ቤተ-መፅሃፍት ቀይረውታል። ይባስ ብሎም ከፊሉን መፀዳጃ ቤት አድርገውታል። በአንፃሩ የመሪዎቻቸውን ቅርስ ጫማዎቻቸው ሳይቀሩ በቅርስነት አስቀምጠዋል።

8)- ሙስሊሞች የታላቁን ነብይ ﷺ ታላቅነት በህይወት ዘመን እያሉም፣ ሙተውም በልባቸው በማየሉ እና በሐዲስ «ቀብሬን የዘየረ ምልጃዬን ያገኛል/ ነብያት ከሞት በኃላ አካላቸው አይበስብስም/ በቀብራቸው ይሰግዳሉ» በሚሉ አበራታታች ሐዲሶች መቃብራቸውን በፍቅርና በናፍቆት ሲዘይሩ!
~
❌ «ወሃቢያ» ግን ይህን ተግባር የሚያደርግን በመግደል ያበረታታሉ። መሪዎቻቸውም የነብዩን ﷺ የተከበረውን መካነ መቃብር የማፍረስ ፍላጎት እንዳላቸው በግልፅ ተናግረዋል። የተከበረውን የነብዩ ቀብርም ጣኦት ሲል አንዱ መሃይምና ቂል መሪያቸው ተናግሯል።

9)- ሙስሊሞች የእስልምና አስተምህሮ መመሪያ የሆኑትን ቁርአንን እና ሐዲስን እስከነ አተረጓጉማቸው በጥንቃቄ፣ በብስለትና መረጃን ከመረጃ እያስማሙ ለአማኙ ማህበረሰብ ሲያደርሱ!
~
❌ «ወሃቢያ» ግን ከአይ*ሁድ እውቅና በተሰጣቸው ማስተንተን በማይችሉ ዳዒዎቻቸው ቁርአንን እርስ በርስ እያጋጩ፣ ታእዊል አናደርግም በማለት ሸሪዓዊ መሰረቶችን ሲነዱ ይታያሉ። በዚህ ምክንያትም ነው ምናባዊ ጣኦት አምላኪ የሆኑት። ይህ ጉዳይም እራሱ «ወሃቢያ» ሰነፊ፣ ሃዳዲ፣ ኢኽዋን ተብሎ እርስ በርስ እንዲሰነጣጠቅ አድርጎታል።

10)- ሙስሊሞች ታላቆቻቸውን በማክበር፣ ገድላቸውን በመዝከር፣ በመንዙማ መልኩ ዳዕዋን በማስፋፋት፣ በሰለዋትና ዚክር የእስልምና ፍቅር በማስረፅ፣ በመተናነስና በመዋደድ፣ በመታዛዘንና በመተሳሰብ፣ በጀግንነትና በአዛኝነት ልጆቻቸውን በተዋበ አስተዳደግ አሳድገው ደጋጎችን ያስተላለፉትን ትክክለኛ እስልምና በማስፋፋት ሲጠመዱ!
~
❌ «ወሃቢያ» ግን በመድረሳቸው ለልጆች ሳይቀር ሽርክ, ቢድዓ, ኩፍር, ካፊር በሚል አስተምህሮ ተብትበው.. መካፋፍልን፣ መበታተንን፣ የሙስሊሙ መዳከምን፣ የወጣት አስተሳሰብ መላሸቅን፣ ምቀኝነትን፣ ክፋትን፣ በየ መስጂዱ መፈነካከትን፣ በዲን ስም የዋዠቀ አስተምህሮ ማስፋፋትን፣ ከነርሱ ውጭ ያለው እንስሳ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ አድርጎ በመሳል.. ጭካኔን፣ አረመኔነትን፣ እናት አባት ሳይቀር ቢድዓ ከሰሩ ብለው መግደልን አስተምረው ደም አፍሳሽነትን አነግሱ። የእስልምና ስምንም አጠለሹ!

♣♣♣♣♣
ይህ በአጭሩ ለቅምሻ ያህል ያስቀመጥነው እንጂ በእስልምና እና በ«ወሃቢያ» መካከል ያለው ልዩነት እጅግ በጣም ሰፊ ነው። ወሃቢያ መጤ ነው። ወሃቢያ ቢድዓ ነው። ወሃቢያ የሽብር ቡድን ነው። ለሃገራችን አይበጃትም። በነሱ እጅ የገቡ ሃገራት ወድመዋል። መጅሊሳቸው አይወክለንም። አላህ ኡማውን ከሸራቸው ይገላግለው። ከመላው ዓለምም እንደ ሙዕተዚላዎች ይንቀልልን አሚን!

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2690533334412457&id=736333116499165

https://t.me/factofwahhabism

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mar Zeneb " ማርዘነብ " posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to Mar Zeneb " ማርዘነብ ":

Share