የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

  • Home
  • Ethiopia
  • Bahir Dar
  • የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በባሕርዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሚዲያ ገጽ ነው፡፡

  ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት 778 የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በብፁዕ አቡነ አብርሃም አባታዊ ቡራኬ አስመረቀ📍 ጳጕሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም. | ባሕር ዳርየባሕር ዳር ሀገረ ...
06/09/2026

ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት 778 የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በብፁዕ አቡነ አብርሃም አባታዊ ቡራኬ አስመረቀ

📍 ጳጕሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም. | ባሕር ዳር

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት፣ በሀገረ ስብከቱ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አስተባባሪነት በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሲማሩ የነበሩ 778 ተማሪዎችን በብፁዕ አቡነ አብርሃም አባታዊ ቡራኬ አስመርቋል።

የምረቃ መርሐ ግብሩ በደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመገኘት ለተመራቂዎቹ አባታዊ ቡራኬና መልዕክት ሰጥተዋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ሰብሳቢ አቶ አየለ አዱኛ ባቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ አንድነቱ በ102 አድባራትና ገዳማት የሚገኙ 83,625 አባላትን በማሳተፍ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም፣ በ59 አጥቢያዎች ለ27,542 ተማሪዎች ወጥ የሆነ ሥርዓተ ትምህርት ተግባራዊ መደረጉ ተገልጿል።

🎓 ምረቃ የመጨረሻ ሳይሆን፣ ለአዲስ የእውቀት፣ የእምነትና የአገልግሎት ምዕራፍ መነሻ ነው!

🙏 የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

ፎቶ ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሚዲያ

#ባሕርዳርሀገረስብከት #ሰንበትትምህርትቤቶችአንድነት #778ተመራቂዎች #ምረቃ #አቡነአብርሃም #ሥርዓተትምህርት #ኦርቶዶክስ

📚 የምርቃት መርሃ ግብሩ እየተካሄደ ነው! ✝️የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ በ2018 ዓ.ም. በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎችን የማስመረቂያ መርሃ ግ...
06/09/2026

📚 የምርቃት መርሃ ግብሩ እየተካሄደ ነው! ✝️

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ በ2018 ዓ.ም. በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎችን የማስመረቂያ መርሃ ግብር በደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ማርያም ሰ/ቤት እያካሄደ ይገኛል።

🙏 በመርሃ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳር እና የሰሜን ጎጃም አሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ተገኝተዋል።

🎓 ለተመራቂዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ!

#የምርቃትበዓል #ሰንበትትምህርትቤት #ኦርቶዶክስ #ባሕርዳርሀገረስብከት

📚 “ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ” — መዝ. 118፥26✝️ የምርቃት ጥሪየባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ በ2018 ዓ.ም. በአዲሱ የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ...
30/08/2026

📚 “ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ” — መዝ. 118፥26

✝️ የምርቃት ጥሪ

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ በ2018 ዓ.ም. በአዲሱ የሰንበት ት/ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ትግበራ ሲያካሂዱ የነበሩ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችን፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከትና የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ያስመርቃል።

👉 ቀን፦ የፊታችን እሑድ፣ ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም.
👉 ሰዓት፦ ከቀኑ 7፡00
👉 ቦታ፦ በደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ማርያም ሰ/ቤት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ

🙏 ሁላችሁም በመገኘት የምርቃት በዓሉን እንድታከብሩ በክርስቲያናዊ ፍቅር ጋብዘናል።

🌐 የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

📺 SUBSCRIBE:
📱 ማኅበራዊ ሚዲያ:
መረጃውን ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ያዳርሱ። 🙏✝️
#ኦርቶዶክስ #ሰንበትትምህርትቤት #የምርቃትበዓል

ሁለት ቀን ብቻ ቀረውትኬቱን 👉 በሰንበት ትምህርት ቤቱ ንዋዬ ቅድሳት መሸጫ👉 በታዬ ሞላ ስቴሽነሪ👉 በዮፍታሄ የመጽሐፍት መደብር👉በአዳነ የመጽሐፍት መደብር👉 በየአካባቢያችን መንፈሳዊ አገልግሎ...
28/08/2026

ሁለት ቀን ብቻ ቀረው
ትኬቱን
👉 በሰንበት ትምህርት ቤቱ ንዋዬ ቅድሳት መሸጫ
👉 በታዬ ሞላ ስቴሽነሪ
👉 በዮፍታሄ የመጽሐፍት መደብር
👉በአዳነ የመጽሐፍት መደብር
👉 በየአካባቢያችን መንፈሳዊ አገልግሎት በቅንነት በሚደግፉ የከታማችን ወጣቶች እጅ ያገኙታ።

 #ብፁዕ አባታችን ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንኳን ለ፳፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመት አምላከ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ጠብቆ...
28/08/2026

#ብፁዕ አባታችን ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንኳን ለ፳፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመት አምላከ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ጠብቆ አደረሰዎት።

🎭 ፪ኛው ክብረ ተዋህዶ የኪነ ጥበብ መርሐ ግብር"እግዚአብሔርን በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት፤ በከበሮ አመስግኑት።" — መዝሙር 150፥3-4የተዋህዶ እምነትን፣ መንፈሳዊ ባህልን እና የኦርቶዶ...
14/08/2026

🎭 ፪ኛው ክብረ ተዋህዶ የኪነ ጥበብ መርሐ ግብር

"እግዚአብሔርን በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት፤ በከበሮ አመስግኑት።" — መዝሙር 150፥3-4

የተዋህዶ እምነትን፣ መንፈሳዊ ባህልን እና የኦርቶዶክስ ኪነ ጥበብን በሚያጎላ ልዩና ድንቅ መርሐ ግብር ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም ቀን ይቀርባል።
🎼 መንፈሳዊ ዝማሬዎች
🎭 ትምህርት
📝 ግጥምና ወግ
🎤 ቅኔ
🎤 የተለያዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች
ይህን ታላቅ መንፈሳዊ የኪነ ጥበብ መርሐ ግብር እንዳያመልጥዎ።

ትኬቱን
👉 በሰንበት ትምህርት ቤቱ ንዋዬ ቅድሳት መሸጫ
👉 በታዬ ሞላ ስቴሽነሪ
👉 በየአካባቢያችን መንፈሳዊ አገልግሎት በቅንነት በሚደግፉ የከተማችን ወጣቶች እጅ ያገኙታል።

"ክብረ ተዋህዶ" — እምነትን፣ ባህልን እና ኪነ ጥበብን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ ልዩ ዝግጅት!

አዘጋጅ :- የፈ/ገ/ቅ/ጊዮርጊስ ካቴድራል ሰ/ት/ቤት

12/08/2026

የ2019 ዓ/ም ትምህርት ዘመን ለነባር እና አዲስ ተማሪዎች
#ለሕጻናት እና ታዳጊዎች ከ7ዓመት እስከ 17 ዓመት
#ምዝገባ ጀምረናል።

የሀዘን መግለጫየባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በወንድማችን ዜና እረፍት ጥልቅ ሀዘናችንን እንገልጻለን።በተለያዩ የሙያ ክፍሎችና ምድቦች በአንድነት በማገልገል፣ በመ...
11/08/2026

የሀዘን መግለጫ

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በወንድማችን ዜና እረፍት ጥልቅ ሀዘናችንን እንገልጻለን።

በተለያዩ የሙያ ክፍሎችና ምድቦች በአንድነት በማገልገል፣ በመካነ ሰላም ድባንቄ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት እንዲሁም በአቡነ አረጋዊ ሰንበት ትምህርት ሰብሳቢነት በትጋትና በቅንነት ሲያገለግል የነበረው ወንድማችን በማረፋ ሀዘናችን እንገልጻለን።

ወንድማችን በአገልግሎታቸው ዘመን ለቤተክርስቲያን፣ ለሰንበት ትምህርት ቤት እና ለወጣቶች ያበረከቱት አስተዋፅኦ ሁሌም በክብር ይታወሳል።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመዶቻቸው፣ ለጓደኞቻቸው እና ለመላው የአገልግሎት ቤተሰብ ከልብ የመጣ መጽናናትን እንመኛለን።

"እግዚአብሔር ለነፍሳቸው ዘላለማዊ ዕረፍትን ይስጥ፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸውም መጽናናትን ያድል።"

✝የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

ነሐሴ 2018 ዓ.ም.

የ2019 ዓ.ም የሥርዓተ ትምህርት ማስተግበሪያ የጊዜ ሰሌዳ በተመለከተበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መም...
08/08/2026

የ2019 ዓ.ም የሥርዓተ ትምህርት ማስተግበሪያ የጊዜ ሰሌዳ በተመለከተ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው ተልዕኮ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ ሕፃናት፣ ወጣቶች እና ጎልማሶችን በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖት የጸኑ፣ ሥነ ምግባራቸው ያማረ፣ ቀደምት አባቶቻቸውን በመምሰል ቤተ ክርስቲያንን የሚረከቡ እና ሀገርን የሚጠብቁ ትውልድን የማፍራት ሥራውን በመሥራት ላይ ይገኛል።

ይህንንም ከተዥጎረጎረ እና ወጥነት ከጎደለው፣ ለአንድ ዓላማና ግብ የተናጠል ሩጫ ከበዛበት አሠራር ሰንበት ትምህርት ቤቶቻችን ተላቀው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በአንድ ሐሳብና በአንድ ቃል እንዲጓዙ የሚያስችል ሥራን በመሥራት ላይ ይገኛል።

ከነዚህም አንዱና ዋነኛው የሰንበት ትምህርት ቤቶች ሥርዓተ ትምህርት ነው። ይህም ሥርዓተ ትምህርት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከት በትግበራ ላይ ይገኛል። ሰንበት ትምህርት ቤቶችም ለአተገባበር ያመቻቸው ዘንድ ዓመታዊ የትምህርት መርሐ ግብር የሚያስፈልግ በመሆኑ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ይህን ማስተገበሪያ ሰነድ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል። ይህም ዓመታዊ የትምህርት ማስተግበርያ ሰነድ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል።

በዚህ ማስተግበርያ ሰነድ ውስጥ የዓመቱን የትምህርት መርሐ ግብር መጀመርያ እና መጨረሻ ጊዜ፣ የፈተና መርሐ ግብራት፣ የሴሚስተር የሪፖርት ጊዜያትን፣ የመርጃ መሣርያ ዝግጅትን ወዘተ በዝርዝር የያዘ ነው። ለዚህም የትምህርት መርሐ ግብር የየአህጉረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እንዲሁም አጥቢያ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ሓላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ሰፊውን ድርሻ መያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ የትግበራ ሰነድ ወይም የትምህርት መርሐ ግብር በተቀመጠለት ጊዜና ሰዓት ተፈጻሚ መደረግ ይኖርበታል።

ሰነዱንም በአንድነቱ የዌብሳይት ገጽ ላይ ከስር ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።

https://eotc-gssu.org/a/የ2019-ዓ-ም-የሥርዓተ-ትምህርት-ማስተግበሪያ/

መንበረ ፓትርያርክ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሀገር አቀፍ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
ሐምሌ 2018 ዓ.ም (አንድነት ሚዲያ)

ዘገበው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ነው።

 #በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ከሐምሌ ፩ ጀምሮ ሲሰጥ የሰነበተው የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ሥልጠና በብፁዕነታቸው መመሪያ ሰጭነት ተጠናቀቀ።            +++++++++++++(ሐ...
31/07/2026

#በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ከሐምሌ ፩ ጀምሮ ሲሰጥ የሰነበተው የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ሥልጠና በብፁዕነታቸው መመሪያ ሰጭነት ተጠናቀቀ።

+++++++++++++
(ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ባሕር አንድነት ሚዲያ)
+++++++++++++

ከሐምሌ ፩ ጀምሮ በብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መመሪያ ሰጭነት ሲሰጥ የቆየው የገዳማትና አድባራት ሥልጠና በዛሬው ዕለት ልዩ ልዩ መልእክቶች ተላልፈውና ለወደፊት ሀገረ ስብከቱ፣ አድባራቱና ገዳማቱ እንደ ግብዓት ወስደው ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ሐሳቦችን ያካተተ የአቋም መግለጫ ቀርቦ ተጠናቀቀ፡፡
ይህ ሥልጠና፡-
· አስተዳደራዊ ጉዳዮች፣
· የአኅት አብያተ ክርስቲያናት አንድነትና ልዩነት፣
· ክብረ ክህነት፣
·የቴክኖሎጂ አጠቃቀም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያለው ተጽዕኖ፣
· የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በአበው ታሪካዊ ሕይወት፤
በሚሉ ዐበይት ጉዳዮች ላይ በልዩ ልዩ አሠልጣኝ መምህራን ሲሰጥ ሰንብቷል፡፡ በሥልጠናው ሂደት ላይ ሐሳባቸውን የገለጹት ሠልጣኝ አባቶች «ብፁዕነታቸው ብፁዕ አቡነ አብርሃም በእያንዳንዱ ሥልጠና ላይ አብረው በመገኘትና ከሠልጣኞች ለሚነሡ ጥያቄዎች ከአሠልጣኞች በተጨማሪ ተግባራዊ መልሶችን በመስጠት ሥልጠናው የተሳካና ሙሉ እንዲሆን አድርገውታል» ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በሥልጠናው ላይ የተሳተፉ አስተዳዳሪዎች ሥልጠናው ብዙ ክፍተቶቻቸውን የሞሉበትና ራሳቸውን የገመገሙበት እንደሆነ ጠቅሰው፣ ይህ ሥልጠና በመዘጋጀቱ ብፁዕነታቸውንና ሀገረ ስብከቱን ደጋግመው አመስግነዋል፡፡ በመቀጠልም በሥልጠናው ካገኙት ግብዓት በመነሣት በቀጣይ አገልግሎታቸው እንደ መመሪያ የሚጠቀሙባቸውና በአጥቢያቸው በግልም በጋራም የሚፈጽሟቸውንና የሚያስፈጽሟቸውን ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ ጠንከር ያለ የአቋም መግለጫ አቅርበዋል፡፡
በሥልጠናው ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ሰላም ኤፍሬም ሙሉ ዓለምም ሥልጠናው እጅግ አስፈላጊና ወቅቱን ያገናዘበ መሆኑን አንሥተው፤ ይልቁንም በዚህ ዘመን የቤተ ክርስቲያንን ክብር በሚገባ ባለመረዳት ቤተ ክርስቲያን ችግር እንደፈጠረች የሚናገሩ ሰዎች እንዳሉ ገልጸው «ቤተ ክርስቲያናችን ግን ችግር ሆናም፣ ችግር ፈጥራም አታውቅም፤ ግለሰቦች የፈጠሩትን ችግር ቅድስት፣ ንጽሕትና ምልዕተ ጸጋ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን እየሰጡ በአገኙት መንገድ ሁሉ የሚናገሩ በዝተዋል» ብለዋል፡፡
ክቡር ሥራ አስኪያጁ አክለውም «የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች የሆናችሁ አባቶች ይህንን ተረድታችሁ በእኛ ድክመት ቤተ ክርስቲያናችንን እንዳናስነቅፍ በርትተን በቅንነትና ያለ ነውር ልናገልግል ይገባል» በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው «አንድን እንኳን በአድልዎ ሳታደርግ እነዚህን ያለማዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ» (፩ኛ ጢሞ ፭፥፳፩) የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስን መልእክት መነሻ በማድረግ አባቶች ያለ አድልዎ በሚገባ እንዲያገለግሉ ሰፊ አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ጸሎተ ቡራኬ ሰጥተው የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት ክፍል

Address

Bahir Dar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት:

Shortcuts

Share