መጽሐፍስ ምን አለ ? What Says The Bible ? Page

መጽሐፍስ ምን አለ ? What Says The Bible ? Page “እንደ ማያፍርና የእውነትን ቃል በትክክል እንደሚያስረዳ የተመሠከረለት ሠራተኛ፣ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ልታቀርብ ትጋ።” 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥15 (አ.መ.ት)

13/10/2025
*  #ቤዛችን ኢየሱስ * ! ይህን   ተቀላቀሉ !ቤዛ የቃሉን ትርጉም ስንመለከት  ፦ ለውጥ ፣ ምትክ : ስለሌላው የሚከፈል ዋጋ ማለት ሲሆን ፥ ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ለነፍሱ የሚመጥን  ...
24/04/2025

* #ቤዛችን ኢየሱስ * !
ይህን ተቀላቀሉ !
ቤዛ የቃሉን ትርጉም ስንመለከት ፦ ለውጥ ፣ ምትክ : ስለሌላው የሚከፈል ዋጋ ማለት ሲሆን ፥ ሰው አለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ለነፍሱ የሚመጥን ስለራሱ ቤዛ (የነፍስ ዋጋ ) ለእግዚአብሔር መክፈል አይችልም
መዝ 49፡7 / ማር 8፡36 / ማቴ 16፡26
ምክንያቱም የነፍስ ቤዛ በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም እንዲኖር እና ጥፋትን እንዳያይ ዋጋው ከብሯል ወይም እጅግ ብዙ ነው መዝ 49፡7 ፡፡

ስለዚህ ማንም ሰው የነፍስን ዋጋ ሊከፍል ስለማይችል ፥ ለሰው ሁሉ ቤዛ የሚሆን እራሱ እግዚአብሔር አንድ ልጁን እርሱም ኢየሱስን አዘጋጀ ፡፡
ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ ፦
“… የሰው ልጅ … ነፍሱንም ለብዙዎች #ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
(ማቴዎስ 20፥28 /ማር 10፡45 ) በመሆኑም

1/* ቤዛነትን #ያገኘነው በክርስቶስ ነው እንዲህ እንደተፃፈ ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእርሱ የተነሣ ነው፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ …… #ቤዛችንም ሆኖአል ። አሜን
³¹ እንግዲህ፣ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፤ “የሚመካ በጌታ ይመካ።”

2/* ቤዛነትን ያገኘነው ደም ነው ፦
“ ፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ #በደሙ የተደረገ #ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።” (ኤፌሶን 1፥7)

*•* በመሆኑም እግዚአብሔር ስለ ኃጢአተኞች የተቀበለው የቤዛነት ዋጋ የኢየሱስን ሞት ብቻ ነው ( ዕብ 9:12 ዮሐ 1፡29 ፤ ኤፌ 1፡7፤ 1ጢሞ 2፥ 5) ።

#ብቸኛ ቤዛችን የሆነው ጌታ ኢየሱስም ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ በመስጠት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ሆኖ ይህን ማንም ሊከፍል የማይችለውን ውድ የቤዛነት ዋጋ ከፍሏል ። እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ ፦

1ኛ ጢሞቴዎስ 2 :
⁵ አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው #መካከለኛው ደግሞ ፥ #እርሱም ሰው የሆነ ነው፤
⁶ #ራሱንም ለሁሉ ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ ፤ አሜን ።

ወገኖቼ የነፍሳችሁን ዋጋ የከፈለ ብቸኛ መካከለኛ ፥ ጌታ ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ አስተዋላችሁን ? ቃሉ እንዲህ ይላል ፦
ሮሜ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤
²⁴ #በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው እንዲያው #በጸጋው

Address

Bahir Dar

Telephone

+251932858434

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መጽሐፍስ ምን አለ ? What Says The Bible ? Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to መጽሐፍስ ምን አለ ? What Says The Bible ? Page:

Share

Category