06/07/2026
ሰዎች የስህተት ትምህርትን ሲሞሉ ወደ ክርስቶስ ማደግ ያቆሙና ወደ ተቀባ ሰው ማደግ ይጀምራሉ ተቀብቷል ብለው ወደሰየሙት ሰው ያድጋሉ ክርስቶስን ከመምስል ይልቅ ሰውዬው ይመስላሉ ሰዎቹ የተጠሩት ክርስቶስን እንዲመስ ነበረ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው። ሮሜ 8፥29-30
አብ የጠራን እገሌን እና እገሌን እንድንመስል ሳይሆን ክርስቶስን እንድንመስል ነው ክርስቶስን ስለ መምሰል አስቡ
የጌታችን የኢየሱስ ፀጋ እና ሠላም በእናተ ጋር ይሁን
ወንድም ተስፋዬ ጋቢሶ