12/08/2025
መዝሙር 23
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
² በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
³ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
⁴ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
⁵ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ፤ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
⁶ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።