Guuta Christianawi Ministry

Guuta Christianawi Ministry Guuta Christianawi Ministry is religious organizatio founded with the purpose of equipping ministers

ከዚህ ቀደም የተዘመሩና ቆየት ያሉ ዝማሬዎች በተደጋጋሚ ስትጠይቁ የነበራችሁ ወገኖች ሁሉ በዩቲዩብ እና በቲክ ቶክ ገጼ ላይ እንደምታገኙ እየገለጽኩ አገልግሎቱ ለሌሎችም እንዲደርስ ሳብስክራይብ...
19/03/2024

ከዚህ ቀደም የተዘመሩና ቆየት ያሉ ዝማሬዎች በተደጋጋሚ ስትጠይቁ የነበራችሁ ወገኖች ሁሉ በዩቲዩብ እና በቲክ ቶክ ገጼ ላይ እንደምታገኙ እየገለጽኩ አገልግሎቱ ለሌሎችም እንዲደርስ ሳብስክራይብ፣ ላይክና ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን በጌታ ፍቅር እናሳስባለን።

የለገሠ ጂሎ የቀድሞ እና የአሁን መዝሙሮች ለማግኘት ይሄንን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

12/10/2021

ጉታ ክርስቲያናዊ ሚኒስትሪ
ሁለንተናዊ (መንፈሳዊና ማህበራዊ) አገልግሎት በመስጠት ቤተ ክርስቲያንን ማገዝና በአካባቢው ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተሐድሶ እንዲመጣ የሚሠራ ሃይማኖታዊ ድርጅት ነው።

ዓላማውም:- የክርስቶስን አርአያ የተከተለ ደቀ መዝሙርነት፣ የሥነ-መለኮት፣ የለውጥ አመራር እና የማህበረሰብ ልማት ትምህርትና ሥልጠና በመስጠት አገልጋዮችን ማብቃትና አስመርቆ ማሰማራት ነው።

የዘማሪ ለገሠ ጂሎ ቆየት ያለ ሲዳሚኛ መዝሙር“በሕይወቴ ሳለሁ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፣ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ” (መዝ. 104፡33)
17/06/2020

የዘማሪ ለገሠ ጂሎ ቆየት ያለ ሲዳሚኛ መዝሙር
“በሕይወቴ ሳለሁ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፣ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ” (መዝ. 104፡33)

የዘማሪ ለገሠ ጂሎን ቆየት ያሉና አዳዲስ የሲዳሚኛና የአማሪኛ መዝሙሮችን በዚህ ዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ በማድረግ ያገኛሉ፡፡

ያዕቆብ ዋዩና የሲዳሚኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Qullaawa Maxaafa)ያዕቆብ ዋዩ ከዚህ በታች ፎቶግራፉ የሚታየው ሲሆን የተወለደው በሲዳማ ያናሴ/አርፌ አካባቢ ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ጌታን በማገ...
17/06/2020

ያዕቆብ ዋዩና የሲዳሚኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Qullaawa Maxaafa)

ያዕቆብ ዋዩ ከዚህ በታች ፎቶግራፉ የሚታየው ሲሆን የተወለደው በሲዳማ ያናሴ/አርፌ አካባቢ ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ጌታን በማገልገልና ለትውልዱ መልካም አርአያ በመሆን የሚታወቅ ወንድም ነው፡፡ የትምህርት ዝግጅቱ ከዲፕሎማ ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ ድረስ የሥነ-መለኮት ሥልጠና በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዲላ አገልጋዮች ማሰልጠኛ፣ በአዲስ አበባ ኢቫንጀልካል ቲኦሎጂካል ኮሌጅ እና በኢትዮጵያ ድህረ-ምረቃ ሥነ-መለኮት ኮሌጅ ተከታትሏል፡፡ አብዘኛውን ጊዜ ወንጌልን በመስበክና በማስተማር አብያተ ክርስትያናትን የሚያገለግል ሲሆን አመርቂ በሚባል ሂኔታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራ ሠርቷል፤ ባሁኑ ጊዜ በአዲስ አባባ ወርድ ፎር ዘ ወርልድ በተባለ ድርጅት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራ አማካሪ ሆኖ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

ወንድማችን ያዕቆብ ዋዩ መጽሐፍ ቅዱስን (Qullaawa Maxaafa) በሲዳሚኛ ቋንቋ (Sidaama afoo) በመተርጎም ውጤታማ ከመሆኑም በላይ ለሲዳሚኛ ቋንቋ ዕድገት ያደረገው አስተዋኦ ትልቅ በመሆኑ በወንጌል አማኞች ብቻ ሳይሆን በመላው የሲዳማ ሕዝብና ልህቃን ዕውቅና ሊሰጠው የሚገባው ሰው ነው፡፡ በዚህ በሲዳሚኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ጊዜ እንደሥነ-መለኮት ምሁር የተለያዩ ጥንታዊ ቋንቋዎች (የእብራይስጥና የግሪክ ቅጂዎችን) በማጠንና በመተንተን መተርጎም ብቻ ሳይሆን ከሲዳማ ሕዝብ ባህልና ቋንቃ አውድ ጋር አዛምዶ በጽሑፍ ውስጥ እንዲቀመጥ ያደረገው ጥረት ቀላል አልነበረም፡፡ በመሆኑም ይህ ወንድም የቋንቋ ምሁር በተለይም የሲዳሚኛ ቋንቋ ሊቅ ቢባል ያንሰዋል እንጂ አይበዛበትም፡፡

ይህን የሲዳሚኛ መጽሐፍ ቅዱስ ኃላፊነት ወስዶ ያሳትመው የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር እና ዳኒሽ ሚስዮን ሲሆን በማማከር እገዛ ያደረገው ኤስ አይ ኤል (Society of Linguistic Institute) የተባለ ድርጅት ነው፡፡ ለመተርጎም ሥራ በሲዳማ አካባቢ ያሉ ሦስት ቤተ ክርስቲያናት (ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ደቡብ ሲኖዶስ፣ የቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን መሃል ደቡብ ቀጣና እና የካቶሊክ) ቤተክርስቲያናት ተርጓሚዎችን እንዲመድቡና 50% የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሲሆን ሌሎቹ 5 (የሙሉ ወንጌል፣ የሕይወት ብርሃን፣ የገነት፣ የመሠረተ ክርስቶስ እና የአድቨንትስት) ቤተክርስቲያናት ሥራውን አይተው (Review) አስተያየት እንዲሰጡ ተደርጎ ሥራው እንደተጀመረ ወንድማችን ያዕቆብ ይናገራል፡፡

ይህ የሲዳሚኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራ የፈጀው ጊዜ 16 ዓመት (ከህዳር 1991-2007 ዓ.ም) ሲሆን በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት የአንበሳውን ድርሻ ወስዶ በመሥራትና እስከ መጨረሻ ጸንቶና ብዙ ተግዳሮቶችን አልፎ ሥራውን ከዳር ያደረሰው ወንድማችን ያዕቆብ ዋዩ ነበር፡፡ በመጀመሪያ ከእርሱ ጋር የነበሩት የሁለቱ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች አንዱ በጡረታ እና ሌላው በራሱ ምክንያት ሲያቋርጡ በእነርሱ ምትክ የተመደቡትን ሥራውን ማላመድ ለወንድማችን ያዕቆብ ተጨማሪ ሸክም ከመሆኑም በተጨማሪ ከዋና ቅጂዎች የተተረጎመውን በኮምፒዩተር የመጻፍ ኃላፊነትም የእርሱ የእርሱ ብቻ ነበር፡፡

በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ያዕቆብን ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል አንዱና ዋናው ቤተክርስቲያኑ በገባችው ቃል መሠረት 50% የገንዘብ ድጋፍ ለ11/2 ብቻ ያውም እየተንጠባጠበ ካደረገች በኋላ መቋረጡ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ካቋረጠ ሥራው እንደማይቀጥል ስለገባቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበርና ዳኒሽ ሚስዮን ለሚቀጥሉት ለ141/2 ድጋፍ በማድረግ ቀጥሎ እንዲያጠናቅቅ አድርገዋል፡፡ የገንዘቡ መቋረጥ ብቻ ሳይሆን በዚያን ጊዜ የነበሩት የቤተክርስቲያን መሪዎች “ይኸን ሁሉ ጊዜ ለምን ታጠፋለህ? ለቀህ ወደ ቤተክርስቲያን አገልግሎት ብትሄድ ይሻልሃል” እያሉ ሞራል የሚነካ ንግግር ሲናገሩት እርሱ ግን እየሠራ ያለውን ሥራ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ጥርሱን ነክሶ ከዳር ሊያደርስ የቻለ የጠራውን ጌታና ቤተክርስቲያኑን ያላሳፈረ ቆራጥ አገልጋይ ነው፡፡

ወንድማችን ያዕቆብ ይህንና የመሳሰሉትን ተግዳሮቶች አልፎ የሲዳሚኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Qullaawa Maxaafa) በ2007 ዓ.ም ተጠናቅቆ በህዳር 2008 ዓ.ም እንዲመረቅ አድርጓል፡፡ ባሁኑ ጊዜ አዲስ ኪዳን በሲዳሚኛ መቅረጸ-ድምጽ (Sidama Bible Audio Recording) በአሜሪካ (Faith Comes by Hearing) በሚባል ድርጅት ተዘጋጅቶ እንዲመጣ የተላከ ሲሆን በሂደቱ በኮሮና በሽታ ተፅዕኖ ምክንያት የዘገየ ቢሆንም እንኳ ተጠናቅቆ እንደሚመጣ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ሥራ ላይ ወንድማችን ያዕቆብ 1 ወር ሙሉ አስተባባሪ ሆኖ፣ ከዚህ ቀደም አብረውት ይሠሩ የነበሩትን አቶ ቀጸላ ቃንቁራ ከመካነ ኢየሱስ እና አቶ ተፈራ ጃና ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን በማሳተፍ ሥራው በጥራትና በቅልጥፍና እንዲሠራ ከማድረጉም በላይ እርሱ በአራቱ ወንጌላትና በራዕይ ላይ የኢየሱስ ገጸ-ባሕሪይ ሆኖ በመቀረጽና ሌሎችንም ቀልጣፋ አንባቢያን በመመልመል ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ይህን ፕሮግራም ሲያካሂዱ የነበሩት የድርጅቱ ተወካዮች ኬንያውያን ሲሆኑ ሥራው ከታሰበው ጊዜ በላይ በፍጥነት በመጠናቀቁ ተደስተው “እስካሁን በሌሎች ሀገሮች ከተሠሩት ሁሉ በጥራትም ሆነ በጊዜ ፍጥነት ተወዳዳሪ የለውም” በማለት አድናቆታቸውን ገልጸውለተጋል፡፡
ከዚህ ሁሉ የ16 ዓመታት የያዕቆብ ብዙ ድካምና ልፋት በኋላ ተጠናቅቆ ከ6-7 ሚሊየን ለሚሆነው ሕዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ የቀረበው የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ቁጥር 3,000 /ሦስት ሺህ/ ብቻ መሆኑ ደስታው ሙሉ እንዳይሆን ከማድረጉ በተጨማሪ በምረቃው ዝግጅት ላይ ታሳትፎ እንዳይኖረው ተደርጎ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደማንኛውም ተጋባዥ እንግዳ ሆኖ እንዲገኝ ጥቂት ቀናት ሲቀሩ ተነግሮት ስሜቱን ዋጥ አድርጎ ፕሮግራሙን በመሳተፍ አለፈ፡፡

ከምንም በላይ ያዕቆብን ብቻ ሳይሆን የዚህን አካባቢ ሕዝበ-ክርስቲያንና አገልጋዮች ልብ እጅግ ያሳዘነውና ያስከፋው ክስተት በመጽሐፍ ቅዱሱ ዳግም ህትመትና ሥርጭቱ ላይ የታየው ቅጥፈትና ተንኮል የተሞላ ድርጊት ነው፡፡ ይኸውም የሲዳሚኛ መጽሐፍ ቅዱስ ፍላጎት በማህበረሰቡ በተለይም በወጣቱ ዘንድ እጅግ በጣም ከፍተኛ ስለነበር በብዙ ጉትጎታና ግፍት ለዳግም ህትመት በቅቶ ወደ 16,000 /አሥራ ስድስት ሺህ/ ቅጂ መጥቷል የተባለው የውኃ ሽታ ሆኖ መቅረቱ ነበር፡፡ ዳግም ታትሞ የመምጣቱ ወሬ የደረሳቸው ሰዎች የት እንደሚያገኙ ስላልገባቸው በተደጋጋሚ ያዕቆብ ጋር እየደወሉ ይጠይቃሉ፡፡ እርሱም የዚህን አካባቢ አስተባባሪዎች ሲጠይቅ በቂ መረጃ ማግኘት አልቻለም ነበር፡፡ ነገር ግን ከላይ ተገለጸው የአዲስ ኪዳን መቅረጸ-ድምጽ ለመሥራት የሲዳሚኛ መጽሐፍ ቅዱስ ሲፈለግ በዲላ ከተማ እንደሚገኝ ተነግሯቸው ከዚያ አስመጥተው እንደተጠቀሙ ተሰማ፡፡ የባሰ አታምጣ በሉኝና የሚፈልጉ ሰዎች ከዚያ ሄደው ለመግዛት አስተባባሪውን በስልክ በሚጠይቁበት ጊዜ አልቋል ይባላል፡፡ 16,000 /አሥራ ስድስት ሺህ/ እንዴት ሆኖ፣ ማንስ ገዝቶት፣ ከመቼውስ አለቀ የሚለው ጥያቄ የሁላችንም ይሆናል፡፡

በመጨረሻም የወንድማችን የያዕቆብ ልፋትና ጥረት ሕዝቡ የእግዚአብሔር ቃል በራሱ ቋንቋና አውድ አግኝቶ እርሱን ደስ የሚያሰኝ ሕይወት እንዲኖርና በሁለንተናዊ ማንነቱ እንዲለወጥ በመመኘት እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በተጨማሪም ይህ የሲዳሚኛ መጽሐፍ ቅዱስ በሕዝቡ ቋንቋ ተተርጉሞ እንዲዳረስ በሚያደርግበት ጊዜ ለቋንቋው ዕድገትና ለሥነ-ጽሑፉ ያደረገው አስተዋፅኦ ቀላል የሚባል ስላይደለ በአካባቢው ሕዝብ፣ ምሁራንና መንግስት ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል የሚል አስተያየት አለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ይህ በወንድማችን ያዕቆብ ልፋትና ጥረት እውን የሆነው የሲዳሚኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Qullaawa Maxaafa) የሕዝብ ሀብትና ንብረት ስለሆነ በሥርጭቱ ላይ የሚታየው ችግርና ቅጥፈት የተሞላበት አካሄድ ተገቢ ክትትልና እርምት ተደርጎ ለሕዝቡ ተዳረሽ እንዲደረግ በአጽንኦት ያሳሰብን ላሁኑ በዚሁ ላይ እናበቃለን፡፡

“በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ እግዚአብሔር ልጆች ናቸውና”ታላቅ የጸሎት ጥሪ!የእግዚአብሔር መንፈስ ሁላችንም በያለንበት ነእንዲህ እንድንጸልይ ያሳስበኛል፡-ዛሬ በዓም ሁሉ እየሠራ...
05/01/2019

“በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ እግዚአብሔር ልጆች ናቸውና”

ታላቅ የጸሎት ጥሪ!
የእግዚአብሔር መንፈስ ሁላችንም በያለንበት ነእንዲህ እንድንጸልይ ያሳስበኛል፡-
ዛሬ በዓም ሁሉ እየሠራ ያለው የዓመፅ ምስጢር ወይም የ“ምስጢር ማህበርና የኢሚናቲዎች” አሠራር በአገራችን በኢትዮጵያ በተለይም በጠቅላይ ሚኒስተራችን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ላይ ያነጣጠረው ዒላማ እንዳይሳካ አጥብቀን እንጸልይ፡፡ ይህ አሠራር በአገራችን በኢትዮጵያ ከአፀዎቹ ዘመን ጀምሮ እስከ ህወሓት መራሽ ኢህአዴግ መንግስት ድረስ በምስጢር ሲሠራ የቆየና አሁን ግን በእግዚአብሔር ኃይልና በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን እየፈረሰ ያለ ስለሆነ እየመጣ ያለውን ለውጥ ለመቀልበስ ባለና በሌለ ኃይሉ ተግቶ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ከእኛ ጋር ያለው ከእነርሱ ጋር ካለው በብዙ እጥፍ ስለሚበልጥና ምሽግን ለመስበር ብርቱ በሆነ መሣሪያችን በጸሎት ሥራቸውን እናፍርስ፡፡ “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” (2ቆሮ. 10፡3-6፣ ሮሜ 8፡37)፡፡
ባሁኑ ጊዜ አገሪቱን እንደተምችና ደጎቢያ እየበላና እየጎጠጎጠ ያለው የሐሰተኛ መንፈስና ነቢያት ሥራ እንዲፈርስ እንጸልይ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር አስከፊ ጭቆና በፀናቸው ክንዱና በተዘረጋቸው እጁ ለማውጣት ሙሴንና አሮንን በላከ ጊዜ በእጃቸው ባለችው በትር ተአምራት ሲሠሩ የግብፅ አስማተኞች ደግሞ በበትራቸው ያን ለማድረግ ሲሞከሩ እንደነበረ ሁሉ ዛሬ በአገራችን በኢትዮጵያ በሕዝባችን ላይ ለዘመናት ተጭኖበት የነበረውን የግፍና የመከራን ቀንበር በመስበርና ከድህነት አረንቋ አውጥቶ ወደ ዕድገት ከፍታ ሊያወጣ እግዚአብሔር በተነሳበት ጊዜ በአንጻሩ በሰይጣን መንፈስ የተሞሉና ጣጠቁ ሐሰተኛ ነቢያት ይህን ደሀውንና ጭቁኑን ሕዝብ ዘርፈው እነርሱ እየበለጸጉ ሕዝቡ ግን ከሁለንተናዊ ሕይወት ጉስቁልና እንዳይወጣ እያደረጉት ነው፡፡ ስለሆነም ይህን ክፉ አሠራር ለማፍረስ በጸሎትና በቃሉ ዕውቀት እንደሙሴ፣ እንደኤልያስና ኤልሳዕ በነፍሳችንም ቢሆን ተወራርደን ሕዝባችንንና አገራችንን ለመናጠቅበት የምንጋደልበት ጊዜ በመሆኑ አሁን እንነሳ፡፡ (ዘጸ. 8፡16-19፣ 1ነገ. 18፡36-40፣ 2ነገ. 2፡14)
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ የ”ዓመፅ ምስጢር” እና የ”ሐሰተኛ ነቢያት” አሠራር በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ዘመን የእግዚአብሔር እና የሕዝቡ ጠላት የሆነው የሰይጣን ዲያብሎስ ዋና መሣሪያዎች ናቸው፡፡ እነዚህን የክፋት አሠራሮች የእግዚአብሔር ሕዝብ በቅድስ ሕይወት በመኖርና በቃሉ አውነት ላይ ተመሥርቶ በሚጸልይበት ጊዜ በክፉ ኃይላት ላይ ድልን ሲቀዳጅና ነፃ ሲወጣ ኖሯል፡፡
ስለሆነም አሁን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት በእምነት ሆነን እንዲህ እንጸልይ፡-
 አሁን በዚህ ጊዜ በዓለም ሁሉ ላይ እየሠራ ያለውን የዓመፅ ምስጢር ወይም የምስጢር ማህበርና የኢሉሚናቲዎች አሠራር በአገራችን መንግስት መሪዎች ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ እንዳይኖራችሁ ሥራችሁን እናፈርሳለን፣ በጌታ በኢሱስ ስም ሥራችሁን እንቃወማለን፣ በጠቅላይ ሚኒስተራችን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ በአቶ ለማ መገርሳ፣ በአቶ ደመቀ መኮንን፣ በዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና በሌሎችም የመንግስት ባለሥልጣናት ላይ ምንም እንዳትሠሩ በኢየሱስ ስም ሥራችሁን አፈረስን!!!
 አሁን በዚህ ጊዜ በአገራችን በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ እየሠራ ያለውን የሐሰት አሠራርና የሐሠተኛ ነቢያት እንቅስቃሴና ክፉ ለልምምድ፣ የገንዘብ ዘረፋ፣ የርኩሰት ሥራ፣ ቃሉን የሚያጣምም፣ መንፈስ ቅዱስን የሚያሳዝን የክፉ መንፈስ አሠራር በጌታ ኢየሱስ ስም የታሰረ ይሁን፤ ሥራችሁን እናፈርሳለን፣ የፈረሰ ይሁን!!!
 ባሁኑ ጊዜ በአገራችን በኢትየዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ እያደረገ ያለውን መንፈስ፣ የኦነግ ጦር ሠራዊት እንቅስቃሴ፣ የወደቀው የቀድሞ መንግስት ስግብግብ ባለሥልጣናት የዝርፊያና ሕዝብን የሚከፋፍል መንፈስ የተገታና የቆመ ይሁን፤ የእስራአል አምላክ በኤርትራ ባሕር ውስጥ የፈርዖንን ሠራዊት ሰረገላና መንኮራኩ እንዳሰረ (ዘጸ. 14፡24) የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች እግር በጌታ በኢየሱስ ስም የታሰረ ይሁን!!!
 በአጠቃለይ በአገራችን በኢትዮጵያ ያለው ጥልቅ ድህነት፣ ሁለንተናዊ (መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ) ችግሮች፣ የአየር መዛባት፣ የሕዝባችንን ተስፋ የሚያጨልም መንፈስ የሚያመጣው ማንኛውም ተፅዕኖ እና የክፉ አሠራር በሙሉ በሰማይና በምድር ሥልጣን ባለው በጌታችን በኢየሱስ ስምና ሥልጣን የተሰበረ ይሁን!!! አሜን፣ አሜን፣ አሜን፡፡

19/09/2018

Address

Awassa
1000

Telephone

+251960373673

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guuta Christianawi Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share