አምልኮ-worship Tube

አምልኮ-worship Tube የተለያዪ መፀሀፍ ቅዱሳዊ ቪዲዮችን የተለያዪ አስተማሪ የስብ?

12/09/2021
የትዳር ጓደኛ እንዴት እንምረጥ?የሕይወት ጓደኛ ምርጫ መስፈርቶችትዳር ምስረታ ማሰብ ሲጀመር፣ ትዳር እንዲጸና ማድረግ የሚያስችሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሰብዓዊ መስፈርቶች መኖራቸው ቸል ሊባል የሚገ...
29/07/2021

የትዳር ጓደኛ እንዴት እንምረጥ?

የሕይወት ጓደኛ ምርጫ መስፈርቶች
ትዳር ምስረታ ማሰብ ሲጀመር፣ ትዳር እንዲጸና ማድረግ የሚያስችሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሰብዓዊ መስፈርቶች መኖራቸው ቸል ሊባል የሚገባው ነጥብ አይደለም፡፡ ጋብቻ መለኮታዊም ሰብዓዊም ተቋም እንደ መሆኑ መጠን፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርኆዎችና፣ ሰብዓዊ ተሞክሮዎች፣ ቋሚና ዘላቂ መመሪያዎች እንዲሁም አላፊና ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ተገናዝበው የሚተገበሩበት ሲሆን፣ ምንጊዜም ቢሆን ለመለኮታዊው፣ ዘላቂና ቋሚ ለሆነው መስፈርት ቅድሚያ ሊሰጥ ይገባል፡፡

1. ምርጫው በውስጣዊ ማንነት እንጂ ውጫዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ብቻ እንዳይመሰረት መጠንቀቅ፣
ምንም እንኳ ውጫዊ ውበት ወይም ነገሮች በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ ያላቸው መሆኑ ባይካድም፣ ውስጣዊ ውበት፣ የአስተሳሰብ ቁንጅና፣ በእምነት የተሞላ ቅንና ሩህሩህ ልብ፣ እንዲሁም ሙያ የላቀ ትኩረት ሊሰጣቸው ወይም ተመዛዝነው ሊታዩ ይገባል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ውጫዊ ውበታቸውን መንከባከብ ላይ ብቻ ለሚያተኩሩ አማኝ እህቶች ሲመክር “…ለእናንተም ጠጕርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፣…” ካላቸው በኋላ የላቀውን ነገር ሲያመለክታቸው “…ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ …” በማለት የትኩረት አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ያሳባቸዋል (1ጴጥ.3፡3-4፤ )። ይህ ምክር ለወንዶችም ጠቃሚ ነው፡፡

2. ለጋብቻ የታሰበው ወንድ ወይም የተመረጠችው ሴት አማኝ መሆኑን/ኗን ማረጋገጥ
ክርስቲያናዊ ጋብቻ ቃል ኪዳናዊ ግንኙነት እንደ መሆኑ መጠን መከናወን ያለበት አማኝ በሆኑ ተቃራኒ ጾታ ባላቸው ሁለት ግለሰቦች መካከል ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት የሰጠ ሲሆን፣ “… ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? …” በማለት የሚያቀርበው ሙግት በተለይ ከጋብቻ አንጻር በጥልቀትና በጥሞና ሊታይ የሚገባው እውነታ ነው (2ቆሮ.6፡14-16) ፡፡

3. የወደፊት ተጣማጆች ልብ ዝንባሌ መሰረቱ እውነተኛ ፍቅር እንጂ የሌሎች ነገሮች ግፊት እንዳይሆን መጠንቀቅ፣
በተቃራኒ ጾታዎች መካከል መሳሳብ፣ መፈላለግ መኖሩ ተፈጥሯዊ ጉዳይ በመሆኑ አንዱ ሰው ሌላውን ማፍቀር ኃጢአት አይደለም፡፡ ስለዚህ ከሁሉ አስቀድሞ አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ለጋብቻ ሲታሰብ መነሳት ያለበት ጥያቄ፣ በእርግጥ ይህን/ይህቺን ሰው እወደዋሁ/እወዳታለሁ? የሚለው እንጂ፣ ምን አለው? ከማን ወገን ነው? …ወዘተ ሊሆን አይገባም፡፡

ይህን ጉዳይ አውጥቶ አውርዶ የመወሰን ግላዊ ነጻነትን የሚጋፉ አያሌ ልምዶች ቤተ ክርስቲያን አካባቢ መኖራቸው እሙን ሲሆን፣ ውጤታቸውም አስከፊ ነው፡፡ ከነዚህም ምክንያቶች መካከል የፍቅር ግንኙነቱን ከሚፈልጉት አንዱ “እግዚአብሔር አንቺን/አንተን ሰጥቶኛል” ብሎ ጥያቄ ማቅረብ፣ አንዳንድ ነቢያት ነን ባዮች “አከሌን/እከሊትን እንድታገቢ/እንድታገባ እግዚአብሔር ተናግሮኛል” ሲሉ የሚያመጡት አሳሪ መልዕክት፣ እንዲሁም
ማንም ሰው የፍቅር ስሜት የሌለውን ሌላ ሰው አግብቶ ሰላም ያለበት፣ የተረጋጋና የእግዚአብሔር በረከቶች የሚከተሉት ኑሮ መሥርቶ መኖር ስለሚቸገር ራስን እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሥራ መጥመድ ይሆናል፡፡ እንዲህ ዓይነት ግንኙነት ውስጥ ዘሎ ከተገ

✝️ቤተክርስቲያን – ማን ናት ?ቤተክርስቲያን የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች ባስተማሩት ወንጌል ላይ መሰረትዋን የጣለች የክርስቶስ አካል ነች፡፡ክርስቶስን አምነው በጥምቀት የለበሱት፣ እርሱን በማወ...
28/07/2021

✝️ቤተክርስቲያን – ማን ናት ?

ቤተክርስቲያን የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች ባስተማሩት ወንጌል ላይ መሰረትዋን የጣለች የክርስቶስ አካል ነች፡፡ክርስቶስን አምነው በጥምቀት የለበሱት፣ እርሱን በማወቅና በማደግ እስከ ሙላቱ ድረስ በቃሉና በመንፈሱ ለመታነጽ በአንድነት ተያይዘው የሚኖሩባት ማህበር ናት፡፡ይህች ቤተክርስቲያን በዚህ ዘመን ከሚገኙት ቤተ እምነቶች በዋናነት የምትለየው ሰው ሁሉ ጌታ የሰጠውንና ሀዋርያት እንደተቀበሉት ያስተማሩትን ትምህርት ብቻ በመቀበልና በማመን መንግስተ ሰማይ እንደሚገባ ማመንዋ ነው፡፡

ኢየሱስ በገዛ ደሙ የዋጃት የእግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ለኢየሱስ ክርስቶስ የተለዩ ወገኖች ማህበር ሆና ከክርስቶስ ጋር በተሳሰረችበት ስሙ አማካይነት መልካሙን ስራ ለማድረግ የተፈጠረች ናት፡፡ዋና መለያዋም ቅዱሱና አዳኙ ስም "ኢየሱስ" መሆኑ ታላቅ ክብር ሆኖአታል፡፡

ኤፌ. 2:10 “እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።”

በትውልዳችን መሀል የምትገኝ ማህበር/ቤተክርስቲያን በሐዋርያት ስራ ምእራፍ ሁለት ላይ ከተፈጠረችው ጋር አንድ ስለመሆንዋ በሚከተለው መለያ እውነተኛነትዋ ሊረጋገጥ ይችላል፡፡ ዋና ዋናዎቹ ምክኒያቶች ፡-

ሀ.የትምህርቱን መሰረት በተመለከተ፡-

አስራ-ሁለቱ የክርስቶስ ሀዋርያት ብቻ እውነተኞች በመሆናቸው የእነርሱን ትምህርት መሰረት ማድረግ ተገቢ ነው ብላ ልታምን ይገባል፡፡ ሀዋርያቶች ስለምን ይታመናሉ?የእነርሱን መመረጥና መሾም የሚያጸድቁ ብዙ መረጃዎች በቃሉ ላይ ስላሉዋቸው ይታመናሉ፡፡ሀዋርያቶች ስለራሳቸው እግዚአብሄርን ምስክር ጠርተው እውነተኛነታቸውን አረጋግጠዋል፡-

1ዮሐ.4:6 “እኛ ከእግዚአብሔር ነን፤ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፤ ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም። የእውነትን መንፈስና የስሕተትን መንፈስ በዚህ እናውቃለን።”አሉ፡፡

የኢየሱስ ሀዋርያት በእውነት መንፈስ የተመሩ ስለነበሩ ትምህርታቸው እውነተኛውን የመዳን ወንጌል የሚገልጥ ነበር፡፡ሀዋርያት ብቻ በእግዚአብሄር ተቀባይነት ያላቸው ስለመሆናቸው ጌታ ራሱ መንፈስ ቅዱስን በማውረድ አረጋግጦአል፡፡ ከሀዋርያት ህልፈት በሁዋላ እጅግ ብዙ አስተማሪዎች ከልባቸው ያፈለቁትን ትምህርት ለክርስቲያኖች አስተዋውቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳቸውም ደፍረው “እግዚአብሄርን የሚያውቅ እኛን ይሰማል” በሚል ጽኑ ቃል ስለራሳቸው መመስከር አይችሉም፡፡መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሊመሰክርላቸው አይችልምና፡፡ስለዚህ በዚህም ዘመን ያለች እውነተኛ ቤተክርስቲያን የሀዋርያትን ዱካ ልትከተል፣ በሄዱበት መንገድ ልትሄድ፣ በጽናታቸው ልትጸና፣ወጋቸውን ልትቀበል ያስፈልጋል፡፡ምክኒያቱም በዚያ ልምምድ ውስጥ አብሮአቸው የተጉዋዘ ጌታ እንዲህ በምትለማመድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሊገኝ ፈቃዱ ነውና፡፡

ማቴ.10:40 “እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።”

ለ.የወንጌልን ምስጥር በተመለከተ፡-

ለእነዚህ ሃዋርያቶች ብቻ የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ እንደተሰጠ ማወቅ አለባት፡፡ ጌታ ኢየሱስ የመረጣቸውን ደቀመዛሙርት የመንግስቱን እውቀት ከማንም ይልቅ ገልጦላቸዋል፡፡ሀዋርያው ጳውሎስ ይህን መስክሮአል፡-

ኤፌ. 3:3-6 “አስቀድሜ በአጭሩ እንደ ጻፍሁ፥ ይህን ምሥጢር በመግለጥ አስታወቀኝ፤ይህንም ስታነቡ የክርስቶስን ምሥጢር እንዴት እንደማስተውል ልትመለከቱ ትችላላችሁ፤ይህም፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም መስበክ በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነ የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ፥ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለነቢያት በመንፈስ አሁን እ

 ❓በአብርሃም ( )         እና ቤተል ( )🔋  #ድንግልና( Virginity) ማለት ድንግልና /ክብረ-ንፅህና/ የሚለዉ ቃል ቀጥታ ትርጉም አገልግሎት ያልጀመረን ወይም ያለመነካትን የሚያ...
24/07/2021



በአብርሃም ( )
እና
ቤተል ( )

🔋 #ድንግልና( Virginity) ማለት ድንግልና /ክብረ-ንፅህና/ የሚለዉ ቃል ቀጥታ ትርጉም አገልግሎት ያልጀመረን ወይም ያለመነካትን የሚያመለክት ሲሆን በተለይ ከተነሳንበት የጋብቻ ወይም ጾታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምንም እንኳን በኅብረተሰባችን በነበረዉ ልማዳዊ አጠራር ቃሉ የግብረ ስጋ ግንኙነት ከወንድ ጋር ፈጽመው የማያውቁ ሴቶች መጠሪያ ሆኖ ቢያገለግልም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ከሴት ጋር አድርገው የማያውቁ ወንዶችም ድንግል የሚባሉበት ሁኔታ አለ::

💞የሴት ድንግልና የሚለይበት በብልቷ ግብረ ሥጋ
ግንኙነት ማከናወኛ በግቢያ በር ላይ የሥጋ ልፋጭ መሰል ሽፋን ሲሆን ይህም ሽፋን በእንግሊዝኛው / h***n /ተብሎ ይጠራል።

💎የድንግልና መለያ ወይም ስስ የክብረ ንጽህና ሽፋን
ዓይነታቸዉ አራት ሲሆኑ በሁሉም ሴቶች ላይ የሚኖረዉ
ዓይነት ምንም እንኳን በተፈጥሮ ተወስኖ የተፈጠረ ቢሆንም ሆኖም ግን ከግብረ ስጋ ግንኙነት ዉጭ ድንግልናየሚጠፋባቸዉ ወይም የሚወገድበት የጥንቃቄ ጉድለቶች በመኖራቸዉ ተገቢዉ ጥንቃቄ ማድረግ ድንግልናን ከመጠበቅ አንጻር በጣም ጠቃሚነቱ የጎላ ነዉ፡፡

👉ከላይ ለመፃፍ እንደሞከርነው የሴትም የወንድም ድንግል እንዳለ ገልፀናል። ስለዚህ እነዚህ #ድንግል የሆኑ ሰዎች ድንግልናቸውን ለማን መስጠት አለባቸው የሚለውን ሃሳብ ልንዳስስ ወደናል።
…………………………………………………………………………

ሃሳብ 1. ነገ ስለምንጋባ ዛሬ ድንግልናሽን ስጪኝ!
❌ ስለነገ እርግጠኛ መሆን የሚችለው ጌታ ብቻ ነው። ነገ ምናልባት የሆነ አደጋ ደርሶብህ ልትለያዩ ትችላላችሁ። ያን ጊዜ ደግሞ ዛሬ ድንግልናዋን በነገ ተስፋ ያጣች ሴት ለቀጣዩ እጮኛዋ ለማስረዳት ጭንቅ ውስጥ ትገባለች። ይህም ሰው የሰውን ሰርቋል!

❌ ስለዚህ ይህ ንግግር ውሸትና ከትክክለኛነት የራቀ ነው!

ሃሳብ 2. ድንግልናሽን የማትስጪኝ ከሆነ እንደማይወትጂኝ አውቃለሁ!

💔 ብዙ እህቶች በዚህ ነገር እንደተጎዱ ይነግሩናል። ይህን ካላደረገች እንደሚለያት እሷም ያንን ፍራቻ ድንግልናዋን ትሰጣለች። ይህ ደግሞ ከምንም በላይ እግዚአብሔርን መበደል ነው። ሥለዚህ እንዲህ ብሎ ለሚጠይቃው ሳው መልሱ "እውድሃለሁ ነገር ግን ድንግልናዬን ለአንተ መስጠቴ ለአንተ ያለኝን ፍቅር ለመግለጥ አልጠቀምበትም። የምትታገስ ከሆነ ከተጋባን በኋላ እንደርስበታለን" ብሎ መመለስ ነው።

ሃሳብ 3. S*x ካላደረግን እለይሻለሁ!

🖤 እንደዚህ አይነት አፍቃሪ ቢቀርብሽም ችግር የለውም። እያስፈራራ የሚቆይ...አብሮ ለመሆን S*x ማድረግን የሚፈልግ። S*x የማታደርጊው እግዚአብሔርን ለማክበር ነው። በዛ ደግሞ ጌታ ይደሰታል። ስለዚህ S*x ካላደረግን እለይሻለው ለሚለው አትጨናቂ አንቺ ብቻ ለጌታ ታማኝ ሁኚ!

ሃሳብ 4. ድንግልናሽን ሳላረጋግጥ አላገባሽም

🎁 በቅድሚያ ለምድነው የማገባው የሚለው ጥያቄ ሊመለስ ይገባል። አንዳንድ ሰው S*x ለማድረግ ብቻ አስቦ ያገባል። ጋብቻ ከዛም ያለፈ ነው። ድንግል ነኝ ካለችህና የእውነት ድንግል ከሆነች እመናት። ምናልባት በተለያየ አደጋ ምክንያት( ተደፍራ,በጥንቃቄ ጉድለት) ድንግልናዋን አጥታም ከሆነ ከምር ካፈቀርካት እመናት!

💌 ስለዚህ ድንግልናን ለማሳመን ተብሎ #ዝሙት ማድረግ አይጠበቅም!

ምክር!

💎ድንግልና ክብር ነው። በአንድ ነገሽን ማበላሸት የለብሽም። ድንግልናሽን ጠብቂው።

ድንልናቸውን በአደጋ ምክንያት ሊያጡ ይችላሉ?
ካጡስ ምን ማድረግ አለባቸው?

#ድንግልናዬ

Share ♻️ Share

🛑 Protestant mezmur | ልብ የሚነኩ የፀሎት መዝሙሮች | Ethiopian new mezmur protestant  #2https://bit.ly/2N4D7y5Protestant mezmur,ne...
10/03/2021

🛑 Protestant mezmur | ልብ የሚነኩ የፀሎት መዝሙሮች | Ethiopian new mezmur protestant #2
https://bit.ly/2N4D7y5

Protestant mezmur,new protestant mezmur,new ethiopian protestant mezmur 2020 worship,ethiopian protestant mezmur,mezmur protestant,mezmur,new protestant mezmur 2021,protestant mezmur,new protestant mezmur worship,misgana mezmur,mezmur protestant 2020 ethiopia,amharic mezmur,protestant mezmur 2021,new protetstant mezmur this week,mezmur protestant 2020,Amazing Worship songs new 2020 Ethiopia,New Ethiopian Gospel Song 2020

14/01/2021

ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው ነብይ እኔነኝ የእስራኤል ዳንሳ አሳፋሪ ንግግር

14/01/2021

ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው ነብይ እኔነኝ የእስራኤል ዳንሳ አሳፋሪ ንግግር

https://youtu.be/UlJzlTmqNrw
06/01/2021

https://youtu.be/UlJzlTmqNrw

ወንጌል ይለዉጣል አምልኮ-worship tube officialሰላም ሰላም ዉድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ነፍስን እና ሕይወትን የሚያድሱ ቀደምት የሆኑና አዳዲስ ዝማሬዎችን ለእናንተ እናቀርባለን፡፡ሀሳብ እና...

https://youtu.be/RXm9oTkqxRs
06/01/2021

https://youtu.be/RXm9oTkqxRs

ወንጌል ይለዉጣል አምልኮ-worship tube officialሰላም ሰላም ዉድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ነፍስን እና ሕይወትን የሚያድሱ ቀደምት የሆኑና አዳዲስ ዝማሬዎችን ለእናንተ እናቀርባለን፡፡ሀሳብ እና...

Address

Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አምልኮ-worship Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Place Of Worship

Send a message to አምልኮ-worship Tube:

Share