Hawassa Tabor Mekane Eyesus Church

Hawassa Tabor Mekane Eyesus Church This page is official page of hawassa tabor mekane eyesus church

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ነሐሴ 24፣ 2018 ዓ.ምከሥላሴ በኋላ 10ኛ እሑድእውነተኛና ሐሰተኛ ጽድቅ👉ኤር. 31፥7-9👉ሮሜ 5፥12-21👉ማቴ. 23፥1-12ፕሮግራም መሪ፦ ወ/ም ገዛኸኝመዝሙር አ...
30/08/2026

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ነሐሴ 24፣ 2018 ዓ.ም

ከሥላሴ በኋላ 10ኛ እሑድ
እውነተኛና ሐሰተኛ ጽድቅ

👉ኤር. 31፥7-9
👉ሮሜ 5፥12-21
👉ማቴ. 23፥1-12

ፕሮግራም መሪ፦ ወ/ም ገዛኸኝ
መዝሙር አገልግሎት፦ የጉባዔ አምልኮ መሪዎች
ቃል አቅራቢ፦ ቄስ ሃብተወልድ አሸናፊ

የቀጠለ (ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ)
ርዕስ፦ የእግዚአብሔር ቃልና ቅዱሳት ሚስጥራት (የጸጋ መቀበያ መሣሪያዎች)
ሉቃ. 6፥46-49

የሚጠመቁት ልጆች የትኞቹ ናቸው?

አማኝ የሆነ፣ ሊንከባከባቸውና ቃሉን ማስተማር የሚችል ወላጅ ያላቸው። የክርስትና እናት ወይም አባት አላማው ወላጆች በሞት ቢለዩ እነርሱን ተክተው ለመንከባከብ እንዲመች ነው።

ማጥመቅ የሚችለው ማን ነው?

ለአገልግሎቱ የተመደበ አገልጋይ ወይንም ደግሞ አስቸኳይ ጥምቀት ከሆነ(ተጠማቂው የሞት አፋፍ ላይ ከሆነ) ማንኛውም ምእመን

ቅዱስ ጥምቀት የት መካሄድ አለበት?

የቦታ ወሰን የለውም። ቤትም፣ ከቤት ውጪም ሊካሄድ ይችላል።

እምነት ወይስ ጥምቀት ይቅደም?

እምነትና ጥምቀት የተነጣጠሉ ሳይሆን አብረው መሄድ የሚችሉ ነገሮች ናቸው። ግን ቤተክርስቲያናችን ልጆችን አጥምቃ ታስተምራለች። አዋቂዎችን ደግሞ አስተምህራ ታጠምቃለች።

ጥምቀት በማን ስም ይደረግ?

በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም። በሐዋርያት ሥራ ላይ ሐዋርያት በኢየሱስ ስም ብቻ ያጠመቁት አይሁዶች በእግዚአብሔር አብና በመንፈስ ቅዱስ ስለሚያምኑ የማያምኑት በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ስለሆነ በዚያ ምክንያት ነው።

3. የጌታ እራት(ቅዱስ ቁርባን)

የጌታ እራት ሌላኛው የጸጋ መቀበያ መንገድ ሲሆን ጌታችን በማቴ. 26፥26-29 ያቋቋመው ሥርዓት ነው።

ቤተክርስቲያናችን ጌታ ይህ "...እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። . . . ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።" ስላለ የምንወስደው ኅብስትና ወይን እውነተኛ የጌታ ሥጋና ደም ነው ብለን አምነን ነው የምንቀበለው።

26/08/2026
መደበኛ የእሑድ አምልኮ ነሐሴ 17፣ 2018 ዓ.ምከሥላሴ በኋላ 9ኛ እሑድጊዜን በከንቱ አለማሳለፍ👉1 ነገ. 17፥8-16👉ኤፌ. 2፥1-10👉ሉቃ. 4፥23-30ፕሮግራም መሪ፦ መዝሙር አገልግሎት፦...
23/08/2026

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ነሐሴ 17፣ 2018 ዓ.ም

ከሥላሴ በኋላ 9ኛ እሑድ
ጊዜን በከንቱ አለማሳለፍ

👉1 ነገ. 17፥8-16
👉ኤፌ. 2፥1-10
👉ሉቃ. 4፥23-30

ፕሮግራም መሪ፦
መዝሙር አገልግሎት፦ እ/ት ፀሐይ አድማሱ
ቃል አቅራቢ፦ ቄስ ሃብተወልድ አሸናፊ

ርዕስ፦ የእግዚአብሔር ቃልና ቅዱሳት ሚስጥራት (የጸጋ መቀበያ መሣሪያዎች)
ሉቃ. 6፥46-49

የእግዚአብሔር ቃልና ቅዱሳት ሚስጥራት የጸጋ መቀበያ መንገዶች በመባል ይታወቃሉ። ቅዱሳት ሚስጥራቱ ሁለት ናቸው። ቅዱስ ጥምቀትና የጌታ እራት። ቅዱሳት ሚስጥራት "ቅዱስ" የተባሉት የማይታየው የእግዚአብሔር ቃል በሚታዩ ነገሮች (ውሃ፣ ኅብስት እና ወይን) ላይ ሲያርፍና ሲዋሃድ ጸጋን ስለሚሰጥ ነው። ይህም ከጌታችን ትእዛዝ፣ ትምህርትና የተስፋ ቃል ላይ የተመሠረተ ነው።

1. የእግዚአብሔር ቃል
የእግዚአብሔር ቃል የሁሉም ነገር ባለስልጣን ነው (ዘፍ. 21፥21፤ ዕብ 4፥12፤ ኢሳ. 40፥8፣ ኢሳ. 55፥10-11፤ኤር. 1፥12፤ 2ኛ ጢሞ. 3፥15-17)።

2. ቅዱስ ጥምቀት
ቅዱስ ጥምቀት በጌታ የታዘዘና ጾታና እድሜን የማይለይ የጸጋ መቀበያ መንገድ ነው(ማቴ. 28፥19-20)።
ጥምቀትን የውሃ ብዛትና የአጠማምቅ ሁኔታ፣ አጥማቂው ማንነት እና የጥምቀት ቦታ ላይ ያልተመሠረተ ይልቁኑ በእግዚአብሔር ቃልና ተስፋዎቹ ላይ መሠረት ያደረገ ቅዱስ ሥርዓት ነው።

የጥምቀት አይነቶች
1. የአይሁድ ጥምቀት፦ አይሁዶች ወደእነርሱ እምነት ወይም ሥርዓት የሚገባን ሰው አንጽተው የሚቀበሉበት ጥምቀት።
2. የመጥምቁ ዮሐንስ ጥምቀት፦ የጌታን መንገድ ለመጥረግ የተደረገ የንስሐ ጥምቀት።
3. ጌታ የመሠረተው ጥምቀት፦ በጌታ ማቴ. 28፥19-20 ትእዛዝ የተመሠረተ ጥምቀት

ጌታ የመሠረተው ጥምቀት፦
👉ያድናል(1ኛ ጴጥ. 3፥21)።
👉የኃጢአት ስርየትን ያስገኛል(ሐዋ 2፥38)።
👉የጸጋ ስጦታዎችን እንቀበላለን(ሐዋ 2፥38)።
👉የጌታ ደቀመዝሙር መሆኛ የመጀመሪያው መንገድ ነው(ማቴ. 28፥19-20)።
👉ክርስቶስን ያለብሰናል(ገላ. 3፥27)።
👉ይቀድሰናል
👉የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ተካፋዮች ያደርገናል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥምቀት ስለሚደረግበት ሥርዓት ወጥ መመሪያ የለም። ነገር ግን በአንክሮ ስናጠና የሚከተሉትን ነገሮች እናገኛለን፦
1. መርጨት (ሐዋ. 2፥41)
2. ማፍሰስ (ሐዋ. 9፥18)
3. ማጥለቅ (ሐዋ. 8፥33-38)

ቅዱስ ጥምቀት ሕጻናትን ያገለለ አይደለም። ምክንያቱም፦
👉ጌታችን ስለጥምቀት ሲያዝ ሕጻናትንም ስላካተተ("አሕዛብን ሁሉ" በእንግልዝኛው "all nations' ማቴ. 28፥19-20)
👉ሕጻናት ማመን ስለሚችሉ(መዝ. 22፥9)
👉ሕጻናት የውርስ ኃጢአት ስላለባቸው(መዝ. 51፥5)

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ነሐሴ 10፣ 2018 ዓ.ምከሥላሴ በኋላ 8ኛ እሑድታማኝና ብልሃተኛ መጋቢ👉ሶፎ. 1፥14-18👉1 ተሰ. 4፥3-12👉ማር. 13፥32-37ፕሮግራም መሪ፦ ሳምሶን አለማየሁ መ...
16/08/2026

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ነሐሴ 10፣ 2018 ዓ.ም

ከሥላሴ በኋላ 8ኛ እሑድ
ታማኝና ብልሃተኛ መጋቢ

👉ሶፎ. 1፥14-18
👉1 ተሰ. 4፥3-12
👉ማር. 13፥32-37

ፕሮግራም መሪ፦ ሳምሶን አለማየሁ
መዝሙር አገልግሎት፦ ናታኒም የመዘመራን ኅብረት
ቃል አቅራቢ፦ ቄስ በፍቃዱ ቦረና

ርዕስ፦ ለተገለጠልን መለኮታዊ እውነት መታዘዝ
ዘፍ. 22

እግዚአብሔር አብርሃምን በዑር ምድር በአባቶች ዘንድ ከነበረበት ከሀገሩ፣ ከዘመዱና ከአባቱ ቤት እንዲወጣ አዘዘው። ሲያዘውም ሦስት የተስፋ ቃሎችን ሰጥቶት ነበር።

1. የብዙዎች አባት አደርግሃለሁ
2. ለበረከት አድርግሃለሁ
3. ስምህ እባርካለሁ/ አከብራለሁ

👉አብርሃምም በእምነት እግዚአብሔርን ታዝዞ ወጣ። እግዚአብሔር እንደተናረውም ባረከው።

👉በዘፍጥረት ምዕራፍ 22 ላይ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ በረከትና መልካም ነገር ካደረገለት በኋላ አብርሃምን ሊፈትነው መጣ። አብርሃምም ያለውን አንድ ልጁን ለእግዚአብሔር ሊሰዋው ስላልሰሰተ እና እግዚአብሔር የልቡን ቁርጠኝነት ስላየ ባረከው።

👉አብርሃም ዓይኑን ከፍ አድርጎ የዱር በግ በይስሐቅ ቦታ እንዲሰዋው እግዚአብሔር አመለከተው። አብርሃም በእድሜው ገፍቶ ስለነበር በጉ ሮጦ እንዳያመልጠው ቀንዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዘው ነበር።

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ነሐሴ 3፣ 2018 ዓ.ምከሥላሴ በኋላ 7ኛ እሑድለኃጢአት አለመገዛት👉ኤር. 23፥21-32👉1 ዮሐ. 1፥5-10👉ማቴ. 19፥16-22ፕሮግራም መሪ፦ ሀብታሙ ጋቾመዝሙር አገ...
09/08/2026

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ነሐሴ 3፣ 2018 ዓ.ም

ከሥላሴ በኋላ 7ኛ እሑድ
ለኃጢአት አለመገዛት

👉ኤር. 23፥21-32
👉1 ዮሐ. 1፥5-10
👉ማቴ. 19፥16-22

ፕሮግራም መሪ፦ ሀብታሙ ጋቾ
መዝሙር አገልግሎት፦ ሩሐማ የሥነ ጹሑፍ ኅብረት
ቃል አቅራቢ፦ እ/ት ቤቴል ስጦታ

ርዕስ፦ እግዚአብሔር ታማኝነት ነው
ሰቆ. ኤር. 3፥21-26

ኤርምያስ ኢየሩሳሌም በተዋረደችበት ጊዜ ሕዝቡም በባቢሎን ከደረሰባቸው አስጨናቂ ምርኮና ውርደት ውስጥ የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስታውሳል። የኢየሩሳሌም ሁኔታ ባይለወጥም ኤርምያስ የእግዚአብሔርን የማይለወጠውን ታማኝነት ልብ በማለት ፊቱን ወደ እርሱ ያዞራል።

እግዚአብሔር ታማኝ ነው ስንል፦

👉ቃሉን የሚፈጽም ወይም የሚጠብቅ ነው።
👉ቃል አባይ ያልሆነ ነው።
👉ሊደገፉበት የሚችል ነው።
👉ለኪዳኑ ቆራጥ ነው።
👉እግዚአብሔር እራሱን አይክድም (2ኛ ጢሞ. 2፥13)።
👉እግዚአብሔር አይለወጥም(ሚል. 3፥6)።

ለእግዚአብሔር ታማኝነት የእኛ ምላሽ ምን ሊሆን ይገባል?

👉እግዚአብሔርን ማመን(ምሳ. 3፥5)
👉እርሱን መጠበቅ ተስፋ ማድረግ
👉አማራጭ አለማስቀመጥ
👉የእግዚአብሔር ታማኝነት ማሰብ
👉እግዚአብሔርን ማመስገን

እሁድ መደበኛ አምልኮበቃል፧ቄስ  ዋኘውኘሮግራም በምራት ፧ወ/ም ዮሃንስ ዱለቻበዝማረ፧ ሻሎም መዘምራንርዕስ፡ የታደሰ ቁመና ኢያሱ 14 ፥6
02/08/2026

እሁድ መደበኛ አምልኮ
በቃል፧ቄስ ዋኘው
ኘሮግራም በምራት ፧ወ/ም ዮሃንስ ዱለቻ
በዝማረ፧ ሻሎም መዘምራን

ርዕስ፡ የታደሰ ቁመና
ኢያሱ 14 ፥6

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ሐምሌ 19፣ 2018 ዓ.ምከሥላሴ በኋላ 5ኛ እሑድደቀ መዝሙር ሆኖ እስከ መጨረሻ መኖር 👉ዘፍ. 12፥1-9👉1 ቆሮ. 3፥10-14👉ማቴ. 16፥13-20ፕሮግራም መሪ፦ ዶ/...
26/07/2026

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ሐምሌ 19፣ 2018 ዓ.ም

ከሥላሴ በኋላ 5ኛ እሑድ
ደቀ መዝሙር ሆኖ እስከ መጨረሻ መኖር

👉ዘፍ. 12፥1-9
👉1 ቆሮ. 3፥10-14
👉ማቴ. 16፥13-20

ፕሮግራም መሪ፦ ዶ/ር ሳምራዊት እሸቱ
መዝሙር አገልግሎት፦ ርኆቦት የመዘመራን ኅብረት
ቃል አቅራቢ፦ ወ/ም አያናው ብርሃኑ

ርዕስ፦ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ታማኝነት የመጨረሻው መገለጫ


ታማኝነት የሚለካው ከተነገረው ተስፋ አንጻር ነው። ተስፋ ከሌለ ታማኝነት መኖሩን ወይም አለመኖሩን መመዘን አይቻልም።

ስለኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር የገባቸው የተስፋ ቃሎችና በታማኝነት የፈጸማቸው ነገሮች

1. በዘፍጥረት የተገባው ተስፋ
👉የተስፋው ቃል፦ የሴቲቱ ዘር (ዘፍ. 3፥15)፤ የአብርሃም ዘር (ዘፍ. 12፥6)።
👉የተስፋ ቃሉ ፍጻሜ፦ ሮሜ 1፥1፤ ገላ. 3፥16።

2. በመዝሙር
👉የተስፋው ቃል፦ መዝ. 22፥16-18
👉የተስፋ ቃሉ ፍጻሜ፦ ማቴ. 27፥35-37፣ 46።

3. በነቢያት እግዚአብሔር ያብራራው
👉 ኢሳ. 53፥1-8።

4. የእምነት አባቶች ስለተስፋው ቃል
👉 1ጴጥ. 1፥10-12፤ ዕብ. 11፥13።

መደምደሚያ፦ ገላ. 3፥26፣29፤ ዕብ. 11፥11

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ሐምሌ 12፣ 2018 ዓ.ምከሥላሴ በኋላ 4ኛ እሑድጽድቅና ርኅራኄ👉ሆሴ. 14፥1-9👉ሮሜ 2፥1-13👉ማር. 9፥42-50ፕሮግራም መሪ፦ ታረቀኝ አበበመዝሙር አገልግሎት፦ ባ...
19/07/2026

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ሐምሌ 12፣ 2018 ዓ.ም

ከሥላሴ በኋላ 4ኛ እሑድ
ጽድቅና ርኅራኄ

👉ሆሴ. 14፥1-9
👉ሮሜ 2፥1-13
👉ማር. 9፥42-50

ፕሮግራም መሪ፦ ታረቀኝ አበበ
መዝሙር አገልግሎት፦ ባስልኤል የመዘመራን ኅብረት
ቃል አቅራቢ፦ ቄስ ከፍያለሁ ሙሉጌታ

ርዕስ፦ በአስቸጋሪው ዘመን መካከል ሁሉ በድል የሚያራምድ ሕይወት መያዝ
ዳን. 6፥10-28

የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ትንቢተ ዳንኤልን በሁለት ይከፍሉታል። ከምዕራፍ 1-6 ታሪክ እና ከምዕራፍ 7-12 ትንቢታዊ ወይም መገለጥ።
ይህ ዘመን ከተለያየ ተግዳሮት የተነሳ ክፉና አስቸጋሪነው። ስለዚህ በድል መመላስ የግድና አስፈላጊ ነው።

በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በድል ለመጓዝ ከዳንኤል ሕይወት ምን እንማር?
1. በቅድስናና እግዚአብሔርን በመፍራት መመላለስ
2. የጸሎት ሕይወት
3. በቅንነትና በበደል አልባ ሕይወት መመላለስ
4. ሁልጊዜ በመሰጠት የማምለክ ሕይወት

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ሐምሌ 5፣ 2018 ዓ.ምከሥላሴ በኋላ 3ኛ እሑድስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት👉መሳ. 21፥1-3፣ 15👉1 ቆሮ. 12፥4-6፣ 12-27👉ማር. 3፥31-35ፕሮግራም መሪ፦ ...
12/07/2026

መደበኛ የእሑድ አምልኮ ሐምሌ 5፣ 2018 ዓ.ም

ከሥላሴ በኋላ 3ኛ እሑድ
ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት

👉መሳ. 21፥1-3፣ 15
👉1 ቆሮ. 12፥4-6፣ 12-27
👉ማር. 3፥31-35

ፕሮግራም መሪ፦ ኤልሳቤጥ እንግዳየሁ
መዝሙር አገልግሎት፦ የእሁድ ትምህርት ቤት መዘመራን (Sunday School Choir)
ቃል አቅራቢ፦ መጋቢ ዘሩባቤል ሙሉጌታ

ርዕስ፦ የአይነተኛ ወላጅ ባህሪያት
ማቴ. 18፥6፤ ቲቶ 2፥7

👉ወላጆች በልጆችና በእግዚአብሔር መካከል ያሉ ናቸው። ስለዚህ ወላጆች ለልጆች ቃል እና ከንግግር በዘለለ በተግባር እግዚአብሔርን ሊያሳዩአቸው ይገባል።
👉ልጆች እግዚአብሔርን በመፍራት ካላደጉ በአመጽ ይወረሳሉ።
👉 ወላጆች በልጆቻቸው ፊት ክብር የጎደለው ንግግር ሊያደርጉ አይገባም። በተጨማሪም ሥራን እንዴት መሥራት እንዴት እንዳለባቸው እያጠፉም ቢሆን ሊያስተምሯቸው ይገባል።

ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወላጅ ልንማራቸው የምንችላቸው ነገሮች

👉የጠፋው ልጅ አባት ልጁን በፍቅሩ ከጥፋት ታደገው።
👉ኢዮብ እርሱ በማይደርስበት ስፍራ ልጆቹን በጸሎት ይሸፍን ነበ።
👉የዳዊት ቤት ፍትሐዊነት የጎደለው ቤት ነበር።
👉የኤሊ ቤት ተገቢ ያልሆነ ርህራሄ የሚንጸባረቅበት ቤት ነበር።
👉ሐና ደግሞ የጸሎትና የቃል ኪዳን እናት ምሳሌ ናት።
👉የጢሞቴዎስ እናት ልጇን የእግዚአብሔርን ቃል መግባው አሳደገች።

የወላጅነት ምሰሶዎች

1. ግልጽነት፦ ንግግራችንና ተግባራችን አብረው ሊሄዱ ይገባል።
2. መገኘት፦ ለልጆቻችን ተገቢውን ጊዜ ልንሰጥ ይገባል።
3. ፍቅርና ሥነ ሥርዓት፦ ፍቅርና ሥነ ሥርዓትን በሚዛናዊነት ልንጠቀም ይገባል።
4. አዳማጭነት፦ ልጁን የሚሰማ ወላጅ እርሱን የሚሰማውን ልጅ ያገኛል።
5. ታማኝነት

Address

Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa Tabor Mekane Eyesus Church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share