ወንጌል ለዓለም Tube

ወንጌል ለዓለም Tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ወንጌል ለዓለም Tube, Religious organisation, Awassa.
(7)

በአገልጋይ ተመስገን ነጋሽ ~ ከአዉስትራሊያ
08/08/2026

በአገልጋይ ተመስገን ነጋሽ ~ ከአዉስትራሊያ

በአገልጋይ ተመስገን ነጋሽ ከአውስትራሊያ Temesgen NegashChristian teachingBible ...

"ሰው ሲሞት ጮኾ መሞት አይችልም! በታላቅ ድምጽ ለመሞት ኃይል፣ አቅም ይጠይቃል። ምክንያቱ ነፍሱን ተወስዶበት ሳይሆን በፍቃዱ ነው!!" ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን ጌታችን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ...
07/08/2026

"ሰው ሲሞት ጮኾ መሞት አይችልም! በታላቅ ድምጽ ለመሞት ኃይል፣ አቅም ይጠይቃል። ምክንያቱ ነፍሱን ተወስዶበት ሳይሆን በፍቃዱ ነው!!" ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን

ጌታችን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ለ6 ሰዓታት ቆይቷል። ሚስማር አይደለም ድንኳን የምንወጥረበት አይነት ትልቅ ችንካር በእጆቹ ላይ እግሮቹ ላይ የተመታው፣ በመስቀል ላይ ሆኖ ክብደቱን ሲለቀው እጆቹ ላይ የሚፈጠረው ህመም ከባድ ነበር።ቀና ለማለት ክብደቱን እግሩ ላይ ማድረግ አለበት ያን ጊዜ የሚፈጠረውን ህመም አስቡት ስቃዩ በጣም በጣም ዘግናኝ ነው።ይሄ ብቻ አይደለም መስቀል ላይ ያለ ሰው መናገር ከባድ ነው ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ 7 ነገሮችን ተናግሯል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱና የመጨረሻው ተፈፀመ የሚል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ከስድስት የተለያዩ ቁስለቶች ደም ይፈሰው ነበር። ጌታ ኢየሱስ የሞተው ሞት የድል ሞት ነው ምክንያቱም በሞቱ ነው ድል የነሳው። በታላቅ ድምጽ ጮኾ ነፍሱን ሰጠ፣ ሰው ሲሞት ጮኾ መሞት አይችልም፣ በታላቅ ድምጽ ለመሞት ኃይል፣ አቅም ይጠይቃል። ምክንያቱም ነፍሱን ተወስዶበት ሳይሆን በፍቃዱ ነው። ተፈፀመ አለ ምንድን ነው የተፈፀመው?
1)የኃጢያትን ችግር፣ ውስብስብነት ካልተረዳን በቀር ኢየሱስ የከፈለልን ዋጋ አናውቀውም።የኃጢያትን ችግር ከሰው ይልቅ ፣ ከሰይጣን ይልቅ እግዚአብሔር ጋር ነው።እንዴት? እግዚአብሔር አጥብቆ የሚወደውን ሰው እና እግዚአብሔር አምርሮ የሚጠላው ኃጢያት ተገጣጠሙበት፣ መለየት እስከማይቻል ድረስ...ሰረፀ...ገባ ...መለየት በማይቻል መጠን ስለዚህ እግዚአብሔር በፅድቅ ፣በእውነት ፈርዶ የሰው ልጅ የሚገባውን ቅጣት በገሃነም መስጠት ይችላል ምንም ችግር የለበትም ግን ምህረቱ አይፈቅድለትም አምረሮ የሚጠላው ኃጢያት እንዲቀጣለት ቢፈልግም አጥብቆ የሚወደው ሰው ልጅ እንዲጠፋ አይፈልግም። እውነቱ ደግሞ የሰው ልጅ ምህረት ይደረግለት ፣ ዝም ብሎ ይዳን ፣ የዘላለም ህይወት ያገኝ ቢል ደግሞ ኃጢያት የሚገባውን ቅጣት ሳገኝ ፅድቁ እሺ አይለውም።መስቀል የእግዚአብሔእር ጥበብ እውነት እና ምህረትን ያስታረቀ ያስማማ ነው።ለመለኮታዊ ተግዳሮት መለኮታዊ መፍትሔ ያገኘበት ቦታ ነው መስቀል።
አጥብቆ የሚጠላውን ኃጢያት ልጁ ላይ አደረገ። ሮሜ 8፡3-4 ኃጢያትን በልጁ አደረገ እና ኃጢያትን ኮነነው።እግዚአብሔር በሰው ሁሉ ላይ ያለውን ቁጣ በልጁ ላይ አደረገ፣ ኃጢያትን ቀጣው፣ ኮነነ ያንን ጊዜ ፅድቁ ረካ እውነቱ ረካ ምክንያቱም ፍትህ ተፈፀመ። በመስቀሉ ስራ የሰው ልጅ አምኖ የሚድንበት ስራ ተሰራ። ኢየሱስ ራሱን ያቀረበው ለአብ ነው (ኤፌሶን 5:2) ለአብ ራሱን መስዋት አድርጎ አቀረበ። ኢየሱስ ክርስቶስ በፍፁም ቅዱስ ስለሆነ ያቀረበው መስዋት እንከን የሌለበት ነው እንደዚህ አይነት መስዋት ማቅረብ የሚችል የለም። አሁንም በዚህ መድኃኒት ወደ አብ የሚመጣ ሁሉ ተፈፅሞለታል፣ ተሰርቶለታል ሰተት ብሎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ነው ፣ አማላጅ አያስፈልገው፣ አጋፋሪ አያስፈልገው፣ ሰተት ብሎ መግባት ይችላል።
ኤፌሶን 2:16-18"ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።
“መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤
በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና"
የመስቀሉ ስራ ለሚያምን ሁሉ ፃዲቅ ያደርጋል። የኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነፃል። ተፈፀመ።

የሕዝበ ክርስቲያን ሕገ መንግስት ቃሉ ነዉ! በደቡብ አፍሪካ ስለህገወጥነት ካነሳን ሕገ ወጥነትን የሚቃወሙ አገልጋዮች ተቀደሱ፤ ተለወጡ፤ ተመለሱ የሚል መልክት ያዘለ ሰዉ ሆኖ ሕጋዊዉን መንገድ...
07/08/2026

የሕዝበ ክርስቲያን ሕገ መንግስት ቃሉ ነዉ!

በደቡብ አፍሪካ ስለህገወጥነት ካነሳን ሕገ ወጥነትን የሚቃወሙ አገልጋዮች ተቀደሱ፤ ተለወጡ፤ ተመለሱ የሚል መልክት ያዘለ ሰዉ ሆኖ ሕጋዊዉን መንገድ ተከትሎ መሄድ አለበት እንጂ አገልጋይ ሆኖ በሕገወጥ መንገድ መሄድ ሕገወጥ ሆኖ መግባት የለበትም። 95 በመቶ ሕገ ወጥ ነዉ! ሳዉዝ አፍሪካ ሄደዉ የራሳቸዉን ሽያጭ በሚያደርጉት እኔ ተቆጣጣሪያቸዉ አደለሁም። ፓስተር ሳሙኤል ጌታቸዉ (ዶ/ር)

ሐሰተኛ ልምምዶች አሉ አዎ አሉ። ከናይጄሪያ ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ሐሰተኛ ልምምዶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ተቃርኖ ያላቸዉ አሉ። ዘይት ቀብታችሁ እንጂ ብልቃጥ ዉስጥ አድርጋችሁ ሽጡ አይለንም። ፈዉስ ለሽያጭ መቅረብ የለበትም። የሕዝበ ክርስቲያን ሕገ መንግስት ቃሉ ነዉ!
በሳዉዝ አፍሪካ ቤተ ክርስቲያናችን የዘይት ሽያጭን አታበረታታም። ከተነሱ አገልጋዮች ረጅም ጊዜ 31 ዓመት በፀጋ አገልግሎት አገልግያለሁ ተአምራቶች በአገልግሎቴ ሆነዋል።
እግዚአብሔር በኔ አልፎ ለሰራዉ ስራ ክፍያ ጠይቄ አላዉቅም። ዘይት ሸጬ የተለያዩ ቁሳቁሶች ሸጬ አላዉቅም። በግል አቋሜን ገልጫለሁ። ይሄን ስል ግን ሳዉዝ አፍሪካ መጥተዉ የራሳቸዉን ሽያጭ ሲያደርጉ እኔ ተቆጣጣሪያቸዉ አደለሁም።

ዘይት ለሽያጭ አይቀርብም ምናልባት የምናከብራቸዉ የቃለ ሕይወትና የመካነ ኢየሱስ እንዲሁም መሪዎቻችን ስህተትና የአካሄድ ግድፈት ስላለ የነቢያት አገልግሎት የለም ብንል ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ እንችላለን ከሚል መልካም እሳቤ ያመጡት ሃሳብ ሊሆን ይችላል እንጂ ቢሆንም ልክ አደለም። የሰጠዉ ክርስቶስ ነዉ።

ስለህገወጥነት ካነሳን ቀድሞ የገቡ ሕገ ወጥነትን የሚቃወሙ አገልጋዮች ሐሰተኞችን የሚቃወሙት እነሱም ሆነ ሌላዉ የገቡበት መንገድ ሕጋዊ አደለም።

ካላጋነንኩ 95% በሳዉዝ አፍሪካ ያለዉ ኢትዮጵያዊና ኤርትራዊ ሕጋዊ ሁኔታዎችን ጠብቆ የሄደ አይደለም። ቪዛ ስለማይሰጣቸዉ የሄዱበት መንገድ ልክ አይደለም። የሄዱበት motive ግን ራሳቸዉን ለመለወጥ ቤተሰብ ለመለወጥ የሄዱ እግዚአብሔር ከረዳቸዉ በአገራቸዉ ጉዳይ እጃቸዉን ለመዘርጋት ነዉ።

በተለይ የወንጌል አገልጋይ ሆነዉ በሕገ ወጥ መንገድ መግባት አለበት ወይ ከተባለ አራት ነጥብ ሕገ ወጥ ሆኖ መግባት የለበትም። ተቀደሱ፤ ተለወጡ ተመለሱ የሚል መልክት ያዘለ ሰዉ ሕጋዊዉን መንገድ ተከትሎ መሄድ አለበት እንጂ አገልጋይ ሆኖ በሕገወጥ መሄድ ተገቢ አደለም። ሲሉ ከዲቫይን ሾዉ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ በተለያዩ ጉዳዮች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል።

“ተስፋችን በሰው ኃይል ወይም በፖለቲካ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ብቻ ነው'' ቬኔዙዌላውያን በቬኔዙዌላ ከ300 በላይ በሚሆኑ ከተሞች በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ተሰብስበው ኢየሱስ ክርስ...
05/08/2026

“ተስፋችን በሰው ኃይል ወይም በፖለቲካ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ብቻ ነው'' ቬኔዙዌላውያን

በቬኔዙዌላ ከ300 በላይ በሚሆኑ ከተሞች በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ተሰብስበው ኢየሱስ ክርስቶስ በሀገራቸው ላይ ጌታ መሆኑን በይፋ ያወጁበት ታላቅ የጸሎትና የምስጋና መርሃ ግብር አካሄዱ።

"ቬኔዙዌላ የጸጋ ምድር" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ ዝግጅት አማኞች አደባባዮችንና ጎዳናዎችን በአምልኮ፣ በምስጋናና በጸሎት በመሙላት ለሀገራቸው ሰላም፣ አንድነት፣ ተስፋና ዘላቂ ለውጥ ተመኝተዋል።

ሀገሪቱ በፈታኝና እርግጠኝነት በጎደላቸው የችግር ጊዜያት ማለፏ የሚታወስ ሲሆን ተሳታፊዎቹ የመጨረሻ ተስፋቸው በሰው ኃይል ወይም በፖለቲካ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ብቻ የተመሰረተ መሆኑን አውጀዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

02/08/2026
በአገልጋይ ተመስገን ነጋሽ ~ ከአዉስትራሊያ መንገደኞቹ መንገዳቸውን ቀየሩ!
01/08/2026

በአገልጋይ ተመስገን ነጋሽ ~ ከአዉስትራሊያ
መንገደኞቹ መንገዳቸውን ቀየሩ!

በአገልጋይ ተመስገን ነጋሽ ከአውስትራሊያ Temesgen NegashChristian teachingBible ...

''መጽሐፍ ቅዱስ በተገኘበት ይነበብ” — ፕሬዚዳንት ናይብ ቡኬሌየኤል ሳልቫዶር ፕሬዚዳንት ናይብ ቡኬሌ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ሙሉ ነፃነት ሊኖራቸው እንደሚ...
30/07/2026

''መጽሐፍ ቅዱስ በተገኘበት ይነበብ” — ፕሬዚዳንት ናይብ ቡኬሌ

የኤል ሳልቫዶር ፕሬዚዳንት ናይብ ቡኬሌ ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ሙሉ ነፃነት ሊኖራቸው እንደሚገባ ያላቸውን ጽኑ ድጋፍ ገለጹ።

ተማሪዎች በትምህርት ቤት ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲያነቡ ይፈቀድላቸው እንደሆነ በአንድ ህፃን የቀረበላቸውን ጥያቄ መሠረት በማድረግ ምላሽ የሰጡት ፕሬዚዳንቱ፣ እያንዳንዱ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል በነፃነት የማንበብና የመረዳት መብት እንዳለው ገልጸዋል።

​አክለውም የመጽሐፍ ቅዱስ ተዳራሽነት በትምህርት ቤቶች ብቻ መወሰን እንደሌለበት የጠቆሙት ቡኬሌ፣ ማረሚያ ቤቶች በርካታ ሰዎች ተስፋን፣ ይቅርታንና የሕይወት ለውጥን የሚሹበት ስፍራ በመሆናቸው በዚያም ቢሆን የእምነት መሪዎችና መጋቢዎች የእግዚአብሔርን ቃል የማድረስ አገልግሎታቸው ሊጠበቅለት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

መፅሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ታነባላችሁ? አንድ ሰዉ ለሁለት ጌቶች መገዛትና ማገልገል አይችልም ያለዉ ሁለት ጌቶች ማንና ማናቸዉ!? ሀ) ለእግዚአብሔርና ለተቀረጹ ምስሎች አትችሉምለ) ለእግዚአብሔ...
30/07/2026

መፅሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ታነባላችሁ?

አንድ ሰዉ ለሁለት ጌቶች መገዛትና ማገልገል አይችልም ያለዉ ሁለት ጌቶች ማንና ማናቸዉ!?

ሀ) ለእግዚአብሔርና ለተቀረጹ ምስሎች አትችሉም
ለ) ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም
ሐ) ለእግዚአብሔርና ለባለሥልጣናት አትችሉም
መ) ለእግዚአብሔርና ለሠይጣን መገዛት አትችሉም
ሠ) ሁሉም መልስ ነዉ።
ረ) መልሱ አልተሰጠም።

የሐና ተክሌ መልክት ነዉ፦ መከሩ ብዙ ነው! አዋጥተን የምንደርሰው እንጂ ብቻችንን የምንሞላው አለም የለም! የተሰጠንንና የተመደብንበትን እርሻ በደንብ እንረስ! የምንጠየቀው በተሰጠን ድርሻ ነ...
30/07/2026

የሐና ተክሌ መልክት ነዉ፦

መከሩ ብዙ ነው! አዋጥተን የምንደርሰው እንጂ ብቻችንን የምንሞላው አለም የለም! የተሰጠንንና የተመደብንበትን እርሻ በደንብ እንረስ! የምንጠየቀው በተሰጠን ድርሻ ነው!

የጳዉሎስ ልመና ፀሎት ምን ይሁን?https://youtu.be/hO8GwJ5WN9Y?si=auWn-bMU816xxJzd♦️ዛዶግ ፐርዝ የመጽሃፍ  #ቅዱስ ትምህርት ጊዜበZadok Perth Internat...
25/07/2026

የጳዉሎስ ልመና ፀሎት ምን ይሁን?
https://youtu.be/hO8GwJ5WN9Y?si=auWn-bMU816xxJzd
♦️ዛዶግ ፐርዝ የመጽሃፍ #ቅዱስ ትምህርት ጊዜ
በZadok Perth International Ministry እየተዘጋጀ❗️🙌በወንድም ተመስገን ነጋሽ
👉👉በZadok Perth Youtube የሚቀርብ መልእክት

ሙሉ ትምህርቱን ኮሜንት ስር ያገኙታል።

በአገልጋይ ተመስገን ነጋሽ ከአውስትራሊያ Temesgen NegashChristian teachingBible ...

Address

Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወንጌል ለዓለም Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share